Major Prophets Daniel

Daniel 11-12

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Stone Daniel 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 652 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ዳንኤልን እና አጠቃላይ የታላላቅ ነቢያትን ጥናታችንን እንጨርሳለን ፡፡ ነገ ወደ አዲስ ኪዳን ወደ ዕብራዊያን መፅኀፍት እንመለሳለን ፡፡ እንዳለዉ ለማጥናት በዚህ በዳንኤል ዉስጥ ብዙ እንቆያለን ብዬ አልጠበኩም ፤ ዳንኤል በምርኮ 70 አመታትን አሳለፈ ባገለገላቸዉ በእያንዳንዶቹ መንግስትም ስር ሞገስን አገኘ ፡፡ ምዕራፍ 12 ለማጥናት እንዲያዘጋጀን መጀመሪያ ምዕራፍ 11 እንመለከታለን ፡፡

ትምህርት

ዳንኤል 11፡ የምዕራፍ 11 ቁጥሮች ከሁለት መቶ የሚበልጡ የጦርነት አመታትን ይሸፍናሉ ፡፡ በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ ስታነቡ በእያንዳንዳቸዉ ዉስጥ ያለዉ ታሪካዊ መግለጫ ይህን ግለፅ ለማድረግ የተሰጠ ነው ፡፡

ዳንኤል (11፡ 1-4)፡ በቁጥር 2 መልዓኩ ለዳንኤል በመናገር ምን ይመጣ እንደ ነበር ነገረው ፡፡ ከቂሮስ በኋ በፋርስ ሰዎስት ተጨማሪ ሌሎች ነገስታቶች ይነሳሉ ( ካምብይስ፣ ሲዶስመርዴ እና ዳርዮስ ሀይስታስፔ) እና አራተኛዉ ንጉስ (አርጤክስ የመጀመሪያው) ባለፀጋ ስለሚሆን ሁሉንም በግብፅ ላይ ያነሳሳል/ያሳምፃል ፡፡ አስተዉሉ፡ ይህ እንደ አስተዳዳሪ ሕዝብ በሌሎች ሕዝቦች በመሸነፍ እንደሚወድቅ ቀድሞ ስለ ናቡከደነፆር የምስሉ ሕልም ከምናዉቀዉ የመጣ የሚያስገርም ነገር አይደለም ፤ ምስሉ በድንጋዩ በኢየሱስ ክርስቶስ ድል አድራጊነት ይሰባበራል ፡፡ ኃያሉ ንጉስ (ታላቁ አሌክሳንደር የሜቅዶኒያው) በሁሉም ሕዝብ ላይ ይነሳል (ቁጥር 3) ፡፡ ታላቅ አሌክሳንደር በሞተ ጊዜ (ቁጥር 4) መንግስቱ ወደ አራት ክፍል ይከፋፈላል ፤ አንዱ ክፍል በደቡቡ መንግስት በግብፁ ፍጠሎሚስ ይመራ ነበር፣ ሌለኛዉ ክፍል ደግሞ በሰሜኑ መንግስት በአሶሩ ሰሉሲድስ ያመራ ነበር (ቁጥር 5-6) ፡፡

ዳንኤል (11፡ 5-19)፡ ቀጥሎም የደቡቡ መንግስት (ግብፅ) ልክ እንደ አንዱ አዛዥ ወይም አለቃ ጠንካራ ይሆናል (ቁጥር 5) ፡፡ በቁጥር 6 በግብፃዊዉ ፍጠሎሚ ሁለተኛ ሴት ልጅ እና በአሶራዊዉ አንቲኮስ ሰዎስተኛ መካከል በጋብቻ ጥምረት መስረተዉ ነበር ፤ ይሁን እንጂ ጥምረታቸዉ ተስፋ እንዳደረጉት ዉጤታማ አልነበረም አንቲኮስ ፈትቷት በነበረችዉ ሚስት በርኒስ እና ልጅ ተገደሉ ፡፡ የበርኒስ ወንድም በመነሳትም በሰሜኑ መንግስት ላይ መጣ (ቁጥር 7) ፤ የአሶርን ሰራዊትም በማሸነፍ በጦርነቱ ያገኛቸዉን እቃዎች እና ጣዖቶቹን መልሶ ወደ ግብፅ ወሰደ (ቁጥር 8) ፡፡ በቁጥር (9-10) አሶራዊያን መልሰዉ ለመዋጋት ሞከሩ ነገር ግን አልተሳካላቸዉም ነበር ፤ በቁጥር 11 ፍጠሎሚ አራተኛ እንደ ገና አሶርን አሸነፈው ፡፡ በቁጥር (13-17) የሰሜኑ ንጉስ (የአሶር) አንቲኮስ በግብፅ ላይ ዘመተ ፤ ድል አድራጊነቱም ፍልስጤምን እንዲቆጣጠር ሰጠው ፡፡ ግብፅን ካሸነፈ በኋላ አንቲኮስ ወደ ግሪክ ዞረ ነገር ግን በሮማን ሉሲየስ ሲፖ ኤሲያስቲክ ተሸነፈ (ቁጥር 18) ፡፡ አንቲኮስ ትኩረቱን ወደ ራሱ ምድር አዞረ ነገር ግን በዚያ ተገደለ (ቁጥር 19) ፡፡

ዳንኤል (11፡ 20-35)፡ በቁጥር 20 ተመርዞ የነበርና ወዲያዉኑ ሞቶ በነበረዉ በሮም የተጠየቀዉን ግብር ለመክፈል ግብርን የሚልክ ሌላ መሪ (ሴልዩከስ አራተኛ ፊሎፓተር ) ይነሳል ፤ በመቀጠልም በአሶር ለሰሜኑ በጣም የተናቀ መሪ (አንቲኮስ አራተኛ ኤፋኒስ) ይነሳል አስተዳደሩም በቁጥር 35 ዉስጥ የተቀመጠ ነው ፡፡

ዳንኤል (11፡ 36-45)፡ ቁጥር (36-39) የዳንኤልን ሰባኛዉን ሳምንንት እና የኃሰተኛዉ ክርስቶስን መነሳት ይዘረዝራል ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ከሁሉም አማልዕክት በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል የቁጣዉም ቀን እስኪያበቃ ድረስ ስኬታማ ይሆናል (ቁጥር 36-37) ፡፡ ካይል የሐሰተኛዉ ክርስቶስ መንፈስ በሰዎች እና በግለሰቦች ዉስጥ የሚሰራባቸዉ ወቅቶች እናዳሉ ያምናል ፡፡ ሰይጣን አለምን መቆጣጠር በቻለበት ጊዜ በሚያደርጋቸዉ ክስተቶች በነዚያ ጊዜ ሰዎችን እንደ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ሊሰራባቸዉ ይችላል ፡፡ ይሁን እንጂ በቁጥር 36 ትንቢቱ በመከራዉ ጊዜ ወደ ሚመጣው ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ይሄዳል ፤ በኃይል የተከበረ ይሆናል ገዢዎችን እንዲሰግዱለት ያደርጋቸዋል (ቁጥር 38-39) ፡፡ ቀጥር (40-45) የመጀመረሱን ዘመን መጀመሪያ ይገልፃል ፤ የሰሜን ንጉስ በሰረገላ፣ በፈረሶች እና በብዙ መርከቦች በመዉረር ስልጣኑንበአገራት ላይ ይዘረጋል ፡፡ ኤዶምያስ፣ ሞዓብ እና የታወቁት የአሞናዊያን ሰዎች ያመልጣሉ ፤ በክልሉም ዉስጥ ጦርነት ይሆናል ፤ ቁጥር (44-45) መጨረሻዉን ከክርስቶስ ጋር የሚገናኝበትን የአርማጌድዮን ጦርነት ይገልፃል ፡፡

ዳንኤል (12፡ 1-4)፡ “ በዚያን ጊዜ “ (ቁጥር 1) የመለዓክት አለቃ ሚካኤል በሚገለጥበት ጊዜ ወደ ዳንኤል (11፡ 36-45) ያመለክታል ፡፡ ሚካኤል በዳን (10፡ 13, 21, 12፡ 1, በይሁዳ 9 እና በራዕይ 12፡ 7) ላይ የተጠቀሰ ነው ፤ ሁልጊዜ ሚካኤል ከፍ ያለ ዉጊያ በሚከናወንበት ጊዜ ይገለጣል ፡፡ በዚያን ጊዜ በመፅኀፉ ላይ ተፅፈዉ የተገኙት ሁሉም ሰዎች ያመልጣሉ (ቁጥር 1) ፤ ከዚያም የሙታን ትንሳኤ ይሆናል አንዳንዶች ለዘላለማዊ ህይወት አንዳንዶቹ ደግሞ ለዘላለማዊ ፍርድ (ቁጥር 2-3) ፡፡

ማክአርቱር በመፅኀፍ ቅዱስ ላይ የትንሳኤን ጊዜ ያስቀምጣል፡

  • “ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ (ማቴ 28፡ 1-7, ማር 16፡ 1-7, ሉቃ 24፡ 1-8, ዮሐ 20፡ 1-10, ሐዋ 2፡ 24, 3፡ 15, 10፡ 40, 17፡ 3, ሮሜ 1፡ 4, 4፡ 25, 10፡ 9, 1ቆሮ 15፡ 4, ኤፌ 1፡ 20, 1ተሰ 4፡ 14, 1ጴጥ 3፡ 18)
  • በክርስቶስ ትንሳኤ ጊዜ የጥቂት ቅዱሳን ትንሳኤ (ማቴ 27፡ 50-53)
  • በዳግም ምፅዓት ላይ ስለሚሆን ትንሳኤ (1ቆሮ 15፡ 51-58, 1ተሰ 4፡ 14-17)
  • የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ (ኢሳ 26፡ 19-21, ሕዝ 37፡ 12-14, ዳን 12፡ 1-3)
  • የመከራዉ ቅዱሳን ትንሳኤ (ራዕ 20፡ 4-6)
  • ያላመኑት ሙታን በታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ፊት ለመቆም የሚሆን ትንሳኤ (ራዕ 20፡ 11-15) “ ፡፡

ቁጥር 3 የከበረዉን መንግስት ይገልፃል ፡፡ ዳንኤል ይህን መረጃ በመፅኀፍ ላይ እስከ መጨረሻዉ ቀን እስከ መከራዉ ጊዜ እንዲያትመዉ ተነገረው (ቁጥር 4) ፡፡ ማክአርቱር “ በመከራዉ ዉስጥ ሰዎች ለጥፋቱ መልስ እንደሚፈልጉ እና በተቀመጠዉ በዳንኤል መፅኀፍ በኩል የሚበልጥን እወቀት እንደሚያገኙ “ ይገልፃል ፡፡

ዳንኤል (12፡ 5-13)፡ በዚያ ዳንኤል ሌሎች ሁለት በወንዙ በእያንዳንዱ ዳርቻ ሲመለከት ቆመዉ አዬ (ቁጥር 5) ፡፡ ከእነርሱ ዉስጥ አንዱ ከዳንኤል ጋር ያለዉን ሰዉዬ እነዚህ የተለዩ ነገሮች እስከሚሆኑ ድረስ ምን ያክል ጊዜ እንደሚጠብቁ ጠየቀው (ቁጥር 6) ፡፡ “ ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኩሌታ “ የመከራዉን ሰዎስት አመት ከግማሽን ያመለክታል (ቁጥር 7) ፤ ዳንኤል ያ ሁሉ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠየቀ (ቁጥር 8) ፤ ሰዉዬዉ ለዳንኤል ምንማ ማብራሪያን አልሰጠዉም ነገር ግን እስከ መጨረሻዉ ጊዜ የታተመ/የተዘጋ እንደ ነበር አሳሰበው (ቁጥር 9) ፡፡ ይሁን እንጂ ሰዉዬው የዘወትር መስዋዕት ከጠፋ እና የክፋት ጥፋት ከተቀመጠ በኋላ 1,290 ቀናትን ይወስዳል አለ (ቁጥር 11) ፤ ይህ ማለት ኃሰተኛዉ ክርስቶስ በመምጣት የዘወትር መስዋዕትን ያጠፋል የቁጣም/የመዓትም ቀን ይጀምራል (ሁለተኛዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ የመከራ ጊዜ) ማለት ነው ፡፡ 1,290 ቀን ሰዎስት አመት ከግማሽ ሲደመር 30 ቀን ነው ፡፡ ማክአርቱር ተጨማሪዉን ሰላሳ ቀን “ የሺዉ መንግስት በረከት ከመጀመሩ በፊት ለክርስቶስ መመለስ ምናልባትም በተከታታይ በህያዋን ላይ ለፍርድ የሚፈቅድ (ማቴ 24፡ 29-31, 25፡ 31-46) እንደሆነ “ ይናገራል ፤ ከዚያም የሚጠብቁና 1,335 ቀናት (ተጨማሪ 45 ቀናት) የሚደርሱት የተባረኩ ናቸው (ቁጥር 12) ፡፡

መፅኃፉ ለዳንኤል ምድራዊ ህይወቱ እስኪያበቃ ድረስ በመንገዱ እንዲጓዝ በማዘዝ ያጠቃልላል ፤ በመጨረሻዉ ዘመንም እንደሚነሳ ተነግሮት ነበር (ቁጥር 13) ፡፡

መደምደሚያ

በፍፁም የዳንኤል መፅኀፍት በዚህ ጥልቀት የመጨረሻዉ ዘመንን የመንገድ ካርታን ይሰጠላ ብዬ በፍፁም አላዉቅም ነገር ግን ይሰጣል ! ዳንኤል ስለ ህልም እና ስለ ራዕይ ነበር ይሁን እንጂ መሲሁን እንደ ድንጋይ እንደ አለት የእግዚአብሄር መንግስት በቋሚነት የተመሰረተ እንደሚሆን እናያለን ፡፡

  1. Names included in parentheses are from John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 964–967.

  2. MacArthur, p. 968.

    MacArthur, p. 969.

  3. MacArthur, p. 968.

ጥያቄዎች

  1. ዳን (11፡ 27) “ ነገር ግን ፍፃሜው እስከ ተወሰነውጊዜ ነዉና አይከናወንላቸውም “ በሚለዉ ያበቃል ፤ ይህ ምድርን በእዉነት ስለሚቆጣጠረዉ ምን ይነግራችኋል (ዳን 11፡ 36) ? በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ተመሳሳይ ንግግር ታያላችሁ ? (ዳን 11፡ 35, ዮሐ 2፡ 4, 7፡ 30, 8፡ 20)
  2. በሚመጣዉ ዘመን ስለሚሆነዉ ነገር ለዳንኤል ተገልጦለት የነበረዉን ነገር በዳን (11፡ 32) ስታነቡ “ ነገር ግን አምላካቸዉን የሚያዉቁ ሕዝብ ይበረታሉ ያድጋሉም “ ፤ ይህ ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  3. ዳን (12፡ 1) አንብቡ ፤ ሚካኤል ማን ነበር ከሌሎች መፅኀፍትስ ስለ እርሱ ምን እናዉቃለን ? (ዳን 10፡ 13, 21, ይሁዳ 1፡ 9, ራዕ 12፡ 7)
  4. ዳን (12፡ 2) ምንን እያመለከተ ነበር ? ይህ በዮሐ (5፡ 28-29) እና በሐዋ (24፡ 15) ላይ እንደተጠቀሰው ተመሳሳይ ክስተት ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይመሳሰልም ?
  5. በዳንኤል 12 ቁጥር 3 እና 10 ሁለቱም ጥበበኛ የሆኑትን ሰዎች ይጠቅሳሉ (የሚያስተዉሉትን) ፤ ቅጥር 3 “ ጥበበኞችም እንደ ሰማይ ጸዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብትም ለዘላለም ይደምቃሉ “ ይላል ፤ እነዚህ ጥቅሶች ምን አይነት ምልከታን/እይታን እንደሚጠቅሱ ምን ታስባላችሁ ? ይህ ብዙዎችን ወደ ፅድቅ መምራታችሁን እንድትቀጥሉ ያበረታችኋል ?
  6. በዳንኤል 12 በመጨረሻው ጥቅስ ዳንኤል እንደሚሞት እና እንደ ገና ለድርሱ እንደሚነሳ ወይም በመጨረሻው ዘመን ርስቱን ለመቀበል እንደሚነሳ ተነገረው ፤ ይህ የዕጣ ክፍል ምንድን ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ጌታችን ኢየሱስ ያዘጋጀልን ለእያንዳንዳችን የእጣ ክፍል አለ ? (ሐዋ 20፡ 32, 26፡ 18, ቆላ 1፡ 12, ዕብ 9፡ 15, 1ጴጥ 1፡ 4)
  7. በዳንኤል (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Daniel 12:2–3

“Many of those who sleep in the dust of the earth will awake, some to eternal life, and some to shame and eternal contempt. Those who are wise will shine like the bright expanse of the heavens, and those who lead many to righteousness, like the stars forever and ever.”

ዳንኤል የመጨረሻዎቹን ቀናት ራዕይ ማየቱን ቀጠለ ፡፡ በዘመን መጨረሻ ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል ፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ይደምቃሉ ። ብዙዎች እስከ መጨረሻው ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል ፡፡ ሆኖም ግን ክፉዎች ክፋትን ያደርጋሉ ፣ አያስተውሉምም ፡፡ ጥበበኞች ብቻ ያስተውላሉ ፡፡ ዳንኤል ከእግዚአብሔር ያየው ራዕይ እስከ መጨረሻው ዘመን የታተመ ነበር ፡፡

አንተም እንደ ዳንኤል “ የመጨረሻው ዘምን ሊደርስ ምን ያህል ጊዜ ቀርቶት ይሆን ? ብለህ ትጠይቅ ይሆናል ፡፡ ራዕዮችን ታነባለህ ፣ የመጨረሻዎቹን ቀናት ታስባቸዋለህ እና ግን ቀኑ እስከሚደርስ ምን ታደርጋለህ ? ፈጥነህ ወደ ኢየሱስ ቅረብ ፡፡ አንተ ይህን ስታደርግ ፣ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል ፡፡ ዲያብሎስን ተቃወም ከክፉም ሽሽ ፡፡ ፍቅሩን በመቀበል በክርስቶስ ጽድቅ ተመላለስ ፡፡ በእምነት ልብህን አጥራ ፣ እጆችህንም አንጻ ፤ በህይወትህ እግዚአብሔር ማጥራትን ስለሚያደርግ ወደ እርሱ አብልጠህ ተጠጋ ፡፡ ነገ ስለሚሆነው ነገር አትፍራ ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ተጣበቅ ፤ እርሱም ሰላምና ማስተዋልን ይሰጥሃል ፡፡

“በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና ።ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ ። “

  • ዳንኤል 12፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

ዳንኤል 12:9–10 – “ እርሱም እንዲህ አለኝ ፦ ዳንኤል ሆይ ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ ፤ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል ፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም ፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ ። “

ፊልጵስዩስ 2:14–16 — “ በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ ፥ ስለዚህም በከንቱ እንዳልሮጥሁ በከንቱም እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ይሆንልኛል ። “

ያዕቆብ 4:7–8 – “ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል ፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል ። እናንተ ኃጢአተኞች ፥ እጆቻችሁን አንጹ ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ፥ ልባችሁን አጥሩ ። “