Major Prophets Daniel

Daniel's Prayer, Daniel's Vision

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Stone Daniel 8-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 651 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዳንኤል 8 በጣም ከዳንኤል 2 እና 7 ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ዳንኤል 2 እና 7 ስለ ምድራዊ ነገስታት እና ስለ አዉሬዉ ናቸው ፡፡ ትንሷ ቀንድ በምዕራፍ 7 ላይ ሐሰተኛዉን ክርስቶስን ትወክላለች ፤ ከዚያም የሰዉ ልጅ በመምጣት በእግዚአብሄር መንግስት ያበቃል ፡፡

ዳንኤል 8 ስለ አንድ አዉራ በግና ስለ አንድ ፍየል የታዬ ራዕይን አካትቷል ፤ ዳንኤል ከሌለኛዉ ቀንድ አንዱ ቀንዱ የሚበልጥ ሁለት ቀንድ ያሉትን የአዉራ በግ ምስል አዬ ፤ የአዉራዉ በግ ምስል ሜዶንንና ፋርስን ይወክላል ፡፡ ፍየሉ የግሪክ ምሳሌ እና አንድ ቀንድ ነበረው ፡፡ ፍየሉ የበጉን አዉራ አጠቃው ፤ የአዉራዉን በግ ቀንዶች በመሰባበር ረጋገጠው ፡፡ በቁጥር 9 ትንሹ ቀንድ ተሰበረ ነገር ግን በስፍራዉ ላይ አራት ቀንዶች በቀሉ ፤ ይህ የሐሰተኛዉ ክርስቶስ ጥላ ነበር ፡፡

በቁጥር (15-18) የሰዉ ምስያ ድምፅ - የገብርኤል ድምፅ - ለዳንኤል ተናገረው ፤ ገብርኤል ዳንኤልን እያየዉ የነበረዉ ራዕይ የመጨረሻዉን ዘመን እንደሚወክል/እንደሚያመለክት ነገረው ፡፡ ከዚያም የመከረዋ መጨረሻ ለዳንኤል ተገለፀለት ፤ በመጨረሻም ገብርኤል የዳንኤል ራዕይ የሚወክለዉን ነገር ማብራሪያን አቀረበለት ፡፡

የራዕዩ ዉጤት ለቀናት ዳንኤል የታመመ መሆኑ ነበር ፤ ዳንኤል ራዕዩን እንዲያትመዉ ተነገረው ፤ ራዕዩም የታላቅ መንግስታት እና የታላላቅ መሪዎች መዉደቅ ነበር ፡፡

ትምህርት

ዳንኤል (9፡ 1-23)፡ በዚህ ጊዜ የሚገዛዉ ንጉስ ንጉስ ዳርዮስ ነበር የዘመኑም የመጀመሪያዉ አመት ነበር ፡፡ ባቢሎን ተይዛና ጠፍታ ስለ ነበር አሁን ሜዶን እና ፋርስ ዋናዎቹ የሚያስተዳድሩ ኃይላት ነበሩ ፤ ዳርዮስ በከለዳዉያን (ባቢሎናዊያን ተብለዉ በሚጠሩት ላይ) ላይ አስተዳደረ/ገዛ ፡፡ ዳንኤል የነቢዩ ኤርምያስን ቃል የኢየሩሳሌም የምድረበዳነት አመታት በተመለከተ ለሰባ አመታት እንደሚቆይ ጠቀሰ ፤ ከዚህም የተነሳ ዳንኤል ቢያንስ ለሰባ አመታት በምርኮ እንደሚኖር አሰበ ፡፡ ዳንኤል ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት ተያዘ በሚፅፍበት ጊዜም እና በዳርዮስ ዘመን ጊዜ ከክርስቶስ ልደት 538 በፊት አካባቢ ይሆናል ፡፡

ዳንኤል ጌታ እግዚአብሄር ተመለከተ ፤ ፀለዬ፣ ለመነእንዲሁም ድሞ ፆመ ፡፡ ዳንኤል በምርኮ ስለ ነበር ትዕዛዙን እንዲያከብር እግዚአብሄርን ልብ በሚነካ ሁኔታ ጠየቀው ፡፡ በቁጥር 5 ዳንኤል የህዝቡን ኃጢዓት ዕዉቅና በመስጠት ያለፉትን ኃጢዓቶች ወሰደ ፤ በሕዝቡ አለመታዘዝ በማዘን ስለእነዚህ ኃጢዓቶች በፀሎቱ ተናዘዘ ፡፡

በ 2ዜና (36፡ 21) ሰባዉ አመት ለምድሪቱ እንደ እረፍት የተጠቀሰ እና የታሰበ ጊዜ ነበር ፤ ከዳንኤል የምርኮ ጊዜ ከስልሳ ሰባት አመት በኋላ ዳንኤል አሁንምሕዝቡ እግዚአብሄርን እየለመኑ እንዳልነበር አመነ ፡፡ ዳንኤል ሕዝቡ እግዚአብሄርን የታዘዙ እንዳልነበሩ ተናገረ ፤ ከዚያም እግዚአብሄርን በሰዎስት ስፍራ ለተሀድሶ ጠየቀው፡ በኢየሩሳሌም ከተማ፣ በቅዱሱ ተራራ ላይ እና በመቅደሱ ፡፡ ማክአርቱር “ ዳንኤል ለመታደስ በሰዎስት አቅጣጫዎች ፀለዬ ፤ በዉጤቱም እግዚአብሄርን 1) ከተማዉን (ቁጥር 16, 18)፣ 2) መቅደሱን (ቁጥር 17) እና ሕዝቡን (ቁጥር 19) መልሶ እንዲያመጣ ጠየቀው ፤ የእግዚአብሄር መልስ ሰዎስቱንም ዕንደሚይዝ (ቁጥር 24-27) “ ተናግሯል ፡፡ ዳንኤል ያለማቋረጥ ምህረትን እየጠየቀ ነበር ፡፡

ዳንኤል (9፡ 24-27)፡ እግዚአብሄር የዳንኤልን ፀሎት በመስማት መልሱን ለመስጠት መለዓኩ ገብርኤልን ላከው ፡፡ ገብርኤል ዳንኤልን ማብራሪያ ሊሰጠው እና የራዕዩን የጊዜ ሁኔታን መረደታን በመስጠት ለመርዳት እና የዳንኤልን ፀሎት ለመመለስ መጣ ፡፡ በቁጥር (24-27) ገብርኤል የእግዚአብሄርን ተስፋ ለመፈፀም ሰባ ሳምንታት ታዉጆ እንደ ነበር ገለፀ ፤ እነዚህ ተስፋዎች በሁለት ዙር በሰዎስቴ የሚፈፀሙ ነበሩ ፡፡ ማክአርቱር “ መጀመሪያ ከኃጢዓት ጋር የሚገኛኙት፡ መተላለፍን መጨረስ፣ ኃጢዓትን በመጨረስ እርቅን ማድረግ ናቸው ፤ ሁለተኛ ስራዎቹ ከቅድስና ጋር የተገናኙ ናቸው፡ ቅድስናን ማምጣት፣ ራዕይን በማተም ቅዱስ ቅዱሳንንም ይቀባል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ለዳንኤል በዚህ መልስ የአንድ ሳምንንት የጊዜ መዋቅር ሰባት አመታትን ይወክላል ፡፡ ኮንስታብል ከዳን (9፡ 27) የሳምንታትን እና የአመታትን ክፍፍል፡ አንድ ሳምንንት አንድ አመትን ስለሚወክል እያንዳንዱ የአንድ ሳምንንት ግማሽ ሰዎስት አመት ከግማሽ ጋር እኩል ሲሆን የሰባቱ አመት ጊዜም መከራዉን ይወክላል በማለት ይገልፃል ፡፡ ስልሳ ዘጠኝ ሳምንት ከክርስቶስ ልደት 444 በፊት ከሚጀምረዉ 483 አመት ጋር እኩል ነው ፡፡ ኢየሩሳሌምን ለማደስ የታዘዘዉ ትዕዛዝ እስከ መሲሁ ጊዜ ድረስ በ69 ሳምንታቱ የሚወከል ይሆናል ፤ የ69 ሳምንታት ክፍፍል 49 አመታት ጋር እኩል የሆነዉን ሰባት ሳምንታት እና ከ434 አመታት ጋር እኩል የሆነዉን 62 ሳምንታትን ያካትታል ፡፡ ከ62 በኋላ የክርስቶስ ሞት ተብሎ ተተርጉሞ የነበረው መሲሁ ይቆማል ፤ ይህ ስለ መሲሁ መሞት በአርጤክስስ ትዕዛዝ ጊዜ ከነበረ ከክርስቶስ ሞት 33 አመት በኋላ ካለዉ ጊዜ ጋር ይገናኛል ፡፡

70 ሳምንታት ግንኙነት የሌለዉ እና ከ70 የምርኮ አመታት ጋር የማይገናኝ ነው ፡፡ የአሁኑ እድሜ እንደ “ ቤተ ክርስቲያን እድሜ “ የታዬ ነው ፤ ይህ የቤተ ክርስቲያን እድሜ የመጠበቅ/የትበቃ ጊዜ ነው ፡፡

ማክአርቱር “ ከክርስቶስ ልደት 445 በፊት አርጤክስስ ኢየሩሳሌምን መልሶ ለመገንባት ነህምያን ስልጣን በመስጠት ካዘዘበት(ነህ 2፡ 1-8) “ ከክርስቶስ ልደት 445 በፊት እስከ ከክርስቶስ ሞት 33 አመት እስከ መሲሁ መንግስት ድረስ የሚሆነዉን የጊዜዉን ቆይታ ማብራሪያን ይሰጣል ፤ ይህ ክርስቶስ በአሕያ ወደ ኢየሩሳሌም እስከ ገባበት ጊዜ ድረስ ይቀጥላል/ይሄዳል ፡፡

ይህ የ69 ሳምንንት ጊዜ የመጠበቂያ ጊዜ የሚኖረዉን “ በቤተ ክርስቲያን እድሜ “ የሚከተል ይሆናል ፤ ያየጊዜ መዋቅር የሐሰተኛዉ ክርስቶስ ዘመንን በአንድ ሳምንቱ ወይም በሰባት አመቱ የሚከተል ይሆናል ፤ ይህ በክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ያበቃል ፡፡ ዋይርስቤ “ አሁን የመከራ ቀን ወይም የእግዚአብሄር ቀን ብለን በምናዉቀው ጊዜ ገብርኤል ለዳንኤል በሰጠዉ በትንቢታዊ አቆጣጠር በመጨረሻው ሰባት አመት ዉስጥ ነን ፤ ሁልጊዜ አለም ጦርነትን እና ጥፋትን ቢያዉቁም (ማቴ 24፡ 3-24) የዘመኑ መጨረሻ በኢየሱስ ክርስቶስ መመለስ ከፍ የሚለዉን የኃይለኛ መከራ ችግር ጊዜን እንደሚያስተዋዉቅ (ራዕይ 6-19, ማቴ 24፡ 15-35) “ ይገልፃል ፡፡ ይህ የጊዜዉ ቅደም ተከተል ትርጓሜ ነበር በተጨማሪም ዳንኤል የእግዚአብሄርን እቅድ ለመናገር የተጠቀመበት መረጃ ነበር ፡፡

ዳንኤል 10፡ በምዕራፍ 10 ዳንኤል ተቀብሎት ስለ ነበረዉ ራዕይ ከእግዚአብሄር ማብራሪያን ለመቀበል ብቁ ለመሆን ለመዘጋጀት ለሳምንታት አዘነ ፡፡ ሌለኛዉ መለዓክ ሚካኤል ራዕዩን እንዲተረጉም ለመርዳት መጥቶ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ዳንኤል ያለማቋረጥ ራዕይን ለመቀበል ራሱን ያዘጋጅ ነበር ፡፡ ለመረዳት ስንታገል ይህን ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት በመዉሰድ ለመጨረሻዉ ዘመን እንዴት መዘጋጀት እንዳለብን ለሚለዉ ጥያቄ ለመልሱ መፀለይ ያስፈልገናል ፡፡

.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 962.

  2. MacArthur, p. 962.

  3. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Daniel, pp. 179-180; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/daniel.pdf.

  4. Constable, p. 185.

  5. MacArthur, p. 962.

  6. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 295.

ጥያቄዎች

  1. ዳንኤል “ የምታምረዉን ምድር “ በጠቀሰ ጊዜ ስለ የት እያወራ ነበር ? (ዳን 11፡ 16, 41)
  2. በዳንኤል 8 የምን ጊዜ እና በታሪኩ ዉስጥ የዳንኤል ራዕይ እየጠቀሰዉ የነበረው ማነው ? (ራዕ 6፡ 10, 7፡ 12-17, 11፡ 2, 12፡ 4, 13፡ 3-9)
  3. በዳንኤል 8 የዳንኤልን ራዕይ ማን ተረጎመዉ/ፈታው ? መጀመሪያ ሲታይ/ሲገለጥ የዳንኤል ምላሽ ምን ነበር ? የእናንተ ምላሽ ምን ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. በዳን (8፡ 13) “ ኃጢዓት ጥፋትን ያደርጋል “ (የክፋት ጥፋት) ምን ማለት ነው ? (ዳን 9፡ 27, 11፡ 31, 12፡ 11, ማቴ 24፡ 15, ራዕ 6፡ 10, 11፡ 2)
  5. በዳንኤል 9 ለሕዝቡ በዳንኤል ፀሎት ምላሽ ለስጠት ወደ እግዚአብሄር በምትጮኹ ጊዜ ራሳችሁን በማዋረድ ምላሽ ትሰጣላችሁ ወይስ ያለማቋረጥ ችግሮችን በማግኘት በአለም ላይ ለሁሉም ስህተት ትወቅሷቸዋላችሁ ? ክርስቲያን ለክስተቱ በመነሳት ዳንኤል እንዳደረገው ከፀለየ አለምን እንዴት እንደሚለይ ምን ታስባላችሁ ? (2ዜና 7፡ 14)
  6. ዳን (10፡ 12-13) አንብቡ ፤ ይህ ስለ ፀሎት፣ ስለ መለዓክት እና ስለ መንፈሳዊ አለም ምን ይነግራችኋል ? (ዳን 10፡ 20-21, 12፡ 1, ይሁ 1፡ 9, ራዕ 12፡ 7)
  7. በዳንኤል (8-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Daniel 9:17–19

“Therefore, our God, hear the prayer and the petitions of Your servant. Show Your favor to Your desolate sanctuary for the Lord’s sake. Listen, my God, and hear. Open Your eyes and see our desolations and the city called by Your name. For we are not presenting our petitions before You based on our righteous acts, but based on Your abundant compassion. Lord, hear! Lord, forgive Lord, listen and act! My God, for Your own sake, do not delay, because Your city and Your people are called by Your name.”

ዳንኤል እግዚአብሔርን መከተሉን ቀጠለ ፤ እግዚአብሔርም ዳንኤልን ነጻ አወጣው ከባባድ ከሆኑ አጋጣሚዎችም ውስጥ ህይወቱን ታደገ ፡፡ እግዚአብሔርም ስለመጨረሻው ዘመን እና ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት የሚናገር ራዕይን አሳየው ፡፡ ራዕዩም ዳንኤልን አስደነገጠው ከዚህም አልፎ ለቀናት በህመም እንድተኛ አደረገው ፡፡ አሁንም ግን ዳንኤል በጭንቀት ውስጥ ሳለ በጸሎትና በልመና እግዚአብሔርን ፈለገ ፡፡ እርሱም ሞገስን እንድያደርግ ፣ እንድሰማ ፣ እንድምር ፣ እንድያደምጥና እንድያደርግ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፡፡ እግዚአብሔርም ዳንኤልን አየው ጸሎቱንም ሰማ ፡፡ መልአክም እግዚአብሔር የዳንኤልን ጸሎት እንደሰማና በፊቱም እንደከበረ ለዳንኤል ነገረው ፡፡ ዳንኤልም ስለ ጸለየ ፣ ራዕዩን ይረዳ ዘንድ መልአኩ ረዳው ፡፡ መልአኩም ዳንኤልን እንዳይፈራ ይልቁንም እንድረጋጋና እንድበረታ ነገረው ፡፡

በዚህ አለም እየኖርክ በጭንቀት ውስጥ ስትሆን ፣ እግዚአብሔርን ስለ ራስህ ፣ ስለ ቤተሰብህ እና ስለ አገርህ ከመፈለግ እንዳትዘነጋ ፡፡ እግዚአብሔር ሞገስን እንድያደርግ ፣ እንድሰማ ፣ ይቅር እንድል ፣ እንድያደምጥና እንድያደርግ ለምነው ፡፡ እግዚአብሔር ጸሎትህን ይሰማል ፡፡ አንተ የተወደድክ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ፡፡ እርሱ የእርሱ ሰላም በአንተ ውስጥ እንደሚኖር እንድታውቅ ይፈልጋል ፡፡ በርታ ፡፡ የመጨረሻዎቹን ቀናት እንዳትፈራ ፡፡ ይልቁንም ጸንተህ ቁም ፡፡ በእግዚአብሔር ታመን ፡፡ በጸሎት እግዚአብሔርን ፈልግ እርሱም ሰምቶ ይመልስልሃል ፡፡ ዛሬ እርሱን ተደገፍ ፡፡

“ አሁንም፥ አምላካችን ሆይ፥ የባሪያህን ጸሎትና ልመናውን ስማ፤ ጌታ ሆይ፥ በፈረሰው በመቅደስህ ላይ ስለ አንተ ስትል ፊትህን አብራ። አምላኬ ሆይ፥ በፊትህ የምንለምን ስለ ብዙ ምሕረትህ ነው እንጂ ስለ ጽድቃችን አይደለምና ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዓይንህን ገልጠህ ጥፋታችንና ስምህ የተጠራባትን ከተማ ተመልከት።አቤቱ፥ ስማ፤ አቤቱ፥ ይቅር በል፤ አቤቱ፥ አድምጥና አድርግ፤ አምላኬ ሆይ፥ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና ስለ ራስህ አትዘግይ ። “

  • ዳንኤል 9፡17-19

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘዳግም 7:6 — “ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና ፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ ። “

ዳንኤል 10:12 – “ እርሱም እንዲህ አለኝ ፦ ዳንኤል ሆይ ፥ አትፍራ ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል ፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ ። “

ዳንኤል 10:19 – “ እርሱም ፦ እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ ፥ አትፍራ ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን ፤ በርታ ፥ ጽና አለኝ ። በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና ፦ አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር አልሁ ። “