Major Prophets Daniel

Interpretation of Daniel's Vision

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Stone Daniel 5-7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 650 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የዚህ ክፍል ማብራሪያ በምዕራፍ 7 ላይ ይገኛል ፡፡ ዳንኤል ወደ ባቢሎን በመጀመሪያው ዙሪ ከተወሰዱት ስደተኞች ጋር በከለዳዉያን ከምድሩ ተወስዶ የነበር ወጣት ልጅ ነበር ፡፡ ከሰዎስት አመታት በላይ ሰልጥኖ የነበርና አሁንም በምዕራፍ 7 ወጣት ልጅ ነበር ፡፡ ዳንኤል በምርኮ 70 አመታትን ኖሯል ፤ ምንም እንኳን ዳንኤል አብዛኛዉን ሕይወቱን በምርኮ ቢያሳልፍም አብዛኛዉን ነገር አድርጓል ፤ ዳንኤል በአብዛኛዉ ሕዝብ ሞገስን አገኘ ፡፡ ሕልሞችን መተርጎም ይችላል ምክንያቱም እግዚአብሄር በእርሱ በኩል በመናገር ምን እንደሚል ስለ ሚነግረው ፡፡ ጓደኞቹም ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ በእሳት ዉስጥ የተጣሉ ከሆኑ በኋላ በእግዚአብሄር ተጠበቅ ፤ እነዚህ አራት ሰዎች በምርኮ ዉስጥ እያሉም እንኳን በማሕበረሰቡ ዉስጥ ታላቅ ተፅዕኖ እያደረጉ ነበር ፡፡

በምዕራፍ 4 መጨረሻ ላይ ንጉስ ናቡከደነፆር እግዚአብሄር እያመሰገነ እና ከፍ ከፍ እያደረገ ነበር ፤ የሰማይን ንጉስ እያከበረ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ በምዕራፍ 5 አዲስ ንጉስ በስዕሉ ዉስጥ ገባ - በእግዚአብሄር ይደረግ ስለ ነበረው ነገር ዋጋ ሊሰጥ የማይችለዉ ንጉስ ብልጣሶር ፡፡ ኮንስታብል “ ብልጣሶር በያህዌ በቅዱሱ እግዚአብሄር የተቀደሱ እቃዎች በመጠጣት እንዳደረገው የናቡከደነፆር ትዕቢት/ኩራት ትክክል ወደ ላሆነ ነገር መርቶት እንደ ነበር “ አመለከተ ፡፡ ብልጣሶር በመዉሰድ በኢየሩሳሌም የቤተ መቅደስ የወርቅ እቃዎችን ተጠቀመባቸው (ዳን 5፡ 2-4) ፤ ከዚያም አንድ ከሰማይ የሆነ እጅ በመምጣት በግድግዳዉ ላይ ፃፈ ፤ ብልጣሶርም በፍርኃት ተንቀጠቀጠ ፡፡ ከጥበበኛ አማካሪዎቹ ዉስጥ ማንም ፅኁፉን ሊተረጉመዉ አልቻለም ፡፡ ንጉሱም የተፃፈዉን መተርጎም ለሚችል በመንግስቱ ዉስጥ ሰዎስተኛ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደሚያደርግ አቀረበ በተጨማሪም ሐምራዊ ልብስ እና በአንገቱ ዙሪያ እንዲለብሰዉ የወርቅ ሰንሰለት እንደሚሰጥ አቀረበ (ዳን 5፡ 5-7) ፡፡

በዳን (5፡ 10-12) ንግስቷ ብልጣሶርን በናቡከደነፆር የአስማተኞች፣ የህልም ተርጓሚዎች፣ የአስተዋዮች እና የጥበበኞች አለቃ ተደርጎ ስለ ነበረዉ እና ስሙ ብልጣሶር ተብሎ የነበረዉ ዳንኤል ፅኁፉን ሊተረጉመዉ እንደሚችል ነገረችዉ ፤ ንግስቷ ብልጣሶርን ዳንኤልን እንዲጠራዉ ነገረችዉ ፡፡ የዳንኤል ምላሽ ፅኁፉን እንደሚተረጉመዉ ነገር ግን ንጉሱን ስጦታዉን እዛዉ እንዳረገ እንዲያደርግ ማድረግ እንደሚችል ነበር ፡፡ ዳንኤል ለብልጣሶር እንደ ልዑል እግዚአብሄርን እንደ አምላክ እዉቅና ለመስጠት እምቢ ባለጊዜ በናቡከደነፆር ላይ ሆኖ የነበረዉን ነገር ቢያዉቅም እንኳን ብልጣሶር እግዚአብሄርን እንዳላከበረ መንገሩን ቀጠለ ፤ ከቤተ መቅደሱ ዋንጫዎችን በመዉሰድ ጠጥቶባቸዉ ነበር (ዳን 5፡ 13-23) ፡፡

ማኔ፣ ቴቄል እና ፋሬስ በግድግዳዉ ላይ ተፅፈዉ የነበሩት ቃላቶች ነበሩ ፡፡ ማኔ የዘመንህን ቀናት ተቆጥሯል ማለት ነበር፣ ቴቄል ተመዝነህ ቀለህ ተገኝህ ማለት ሲሆን ፋሬስ ማለት ደግሞ መንግስት ይከፈላል ለሜዶና እና ለፋርስ ይሰጣል ማለት ነበር (ዳን 5፡ 24-28) ፡፡ ንጉሱም ዳንኤልን ሐምራዊ ልብስን አለበሰው በአንገቱም ዙሪያ የወርቅ ሰንሰለትን አስቀመጠ ፤ በመንግስቱም እንደ ሰዎስተኛ ከፍተኛ አስተዳደር ተነገረ/ታወጀ ፡፡ በዚያን ምሽት ብልጣሶር ተገደለ ፤ ሜዶናዊዉ ዳርዮስ ቀጣዩ ንጉስ ሆነ (ዳን 5፡ 29-31) ፡፡

ትምህርት

ዳንኤል (6፡ 1-9)፡ ዳንኤል እንደ ገና በዳርዮስ ዘመን አሁንም ከሰዎስቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች አንዱ በመሆን የተዋወቀ/የተሾመ ነበር ፡፡ ዳንኤል ለብልጣሶር ሰዎስተኛዉ ከፍተኛ አስተዳዳሪ ነበር ሜዶን ተቆጣጥሮበት በነበረበት ጊዜ አሁንም ዳንኤል ራሱን ለሜዶን እና ለፋርስ እንደ አንድ አስተዳዳሪ አገኘው ፡፡ ይህ ምዕራፍ በአንበሶች ጉድጓድ ስለ ዳንኤል በጣም የታወቀ ነው ፡፡ ሹማምቶቹ/አለቆቹ እና መሳፍንቶቹ ሁሉም ሰዉ ለንጉሱ እንዲሰግድ የሚያዝዝ ማህተም እንዲፈርም በማድረግ ንጉሱን አሳሳቱት ፤ ከንጉሱ ዉጪ ወደሌላ ወይም ወደ አማልዕክት የሚፀልይ እና የሚሰግድ በአንበሶች ጉድጓድ ይወረወራል (ቁጥር 1-9) ፡፡

ዳንኤል (6፡ 11-18)፡ ዳንኤል በቀን ሰዎስት ጊዜ ወደ እግዚአብሄር መፀለዩን ቀጠለ (ቁጥር 10) ፡፡ ከዚያም እነዚህ ሰዎች ስለ ዳንኤል ፀሎት ለንጉሱ በመናገር ስለ ትዕዛዙ/አዋጁ አስታወሱት ፤ ንጉሱን ዳንኤል ትዕዛዙን እየተላለፈ እንደ ነበር ነገሩት ፡፡ ምንም እንኳን ንጉሱ ስለ ዳንኤል ቢያስብ እና ታዉጆ ስለ ነበረዉ ቢጨነቅም ዳንኤልን ወደ አንበሶች ጉድጓድ በመወርወር ጉድጓዱን በድንጋይ ተዘጋ (ቁጥር 11-17) ፡፡

ዳንኤል (6፡ 19-28)፡ በማግስቱም በጥዋት ንጉሱ ወደ አንበሶች ጉድጓድ በመሮጥ ወደ ዳንኤል “ ….አምላክ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን ? “ ብሎ በመጠየቅ ተጣራ ፤ ዳንኤልም “ በአንተ ፊት ቅንነት ተገኝቶብኛልና አልጎዱኝም “ በማለት መለሰለት ፡፡

ዳንኤልም ከጉድጓዱ ዉስጥ ወጣ ፡፡ በቁጥር 24 ይህን ክስ አዘጋጅተዉ የነበሩት ሰዎች እና እና ቤተሰቦቻቸው ይገደሉበት ወደ ነበረዉ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣሉ/ተወረወሩ ፡፡ በቁጥር (25-28) ሁሉም ሰዉ ያህዌን እንዲያመሰግን አዋጅ አደረገ ፤ ይህ አንድ ምድራዊ ንጉስ መንግስቱ በፍፁም የማይጠፋዉ ህያዉ እግዚአብሄር በማለት እዉቅና የሰጠበት መግለጫ ነው ፡፡

ዳንኤል (7፡ 1-12)፡ ዳንኤል የአራት አዉሬ ራዕይ ህልም ነበረው ፤ የመጀመሪያይቱ አዉሬ የንስር ክንፍ የነበራት አንበሳ ትመስል ነበር ፤ ክንፎቿም ተወገዱ የሰዉም ሀሳብ የተሰጣት ነበረች ፤ ይህ ምስል ባቢሎንን ይወክላል ፡፡ ሁለተኛይቱ አዉሬ በአፏ ዉስጥ ሰዎስት የጉድን አጥንት የያዘች ድብ ነበረች ሜዶን እና ፋርስን ትወክላለች ፡፡ ሰዎስተኛይቱ አዉሬ አራት ክንፍ እና አራት ራስ ያላት ነብር ነበረች ፤ ይህም ግሪክን ይወክላል ፡፡

አራተኛይቱ አዉሬ በአስር ቀንዶች እና በማስፈራት የተገለጠች ነበረች ፤ ይህን አዉሬ የሚወክል የእንስሳት መግለጫ አልነበረም ፤ ይህቺ አዉሬ የሮማዉያንን አገዛዝ ትወክላለች ፡፡ በቁጥር 8 ለትንሽ ቀን ማጣቀሻ/ማሳያ አለ ፤ በመፅኀፍ ላይ ይህ ትንሽ ቀንድ ሁልጊዜ የሚጠቀሰው ሀሰተኛዉን ክርስቶስ ለማሳየት እንደ ምልክት ነበር ፤ ይህ ጥቅስ የሰይጣንን መንግስት ይወክላል ፡፡ ነገር ግን ቁጥር 9 እና 10 ስለሚቋቋመዉ የእግዚአብሄር መንግስት ናቸው ፡፡

በቁጥር 11 ላይ አዉሬይቱ በመገደል ሰዉነቷ በእሳቱ ዉስጥ ተወርዉሮ ነበር ፤ በክርስቶስ በሁለተኛ መምጣት አጥፍቶታል ፤ ሌሎቹ ሰዎስቱ አዉሬዎች እስከ ጊዜ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸዉ ነበሩ ፡፡ ማክአርቱር “ ከክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት በኋላ ለመጨረሻ እና ለታደሰ/ለተነቃቃዉ አራተኛዉ አገዛዝ በመጨረሻም መኖር የሚቻል አይደለም ምክንያቱም አስፈሪዉ ጥፋት በመጨረሻም ስለሚያጠፋዉ እና የክርስቶስ መንግስት ስለሚተካው “ ብሏል ፡፡

ዳንኤል (7፡ 13-14)፡ እነዚህ ጥቅሶች የአባትን እና የልጅን በአንድ ላይ የመስራት አንድ የሚያምር ስዕልን አላቸው ልጁ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር ፤ የእግዚአብሄር መንግስት ልክ እንደ ባቢናዊያን መንግስት፣ ልክ እንደ ሜዶንና ፋርስ መንግስት፣ ልክ እንደ ግሪክ መንግስት እና እንደ ሮማዉያን መንግስት በፍፁም አይጠፋም ፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት ለዘላለም ቅዱሳን ይቀበሉታል ፡፡

ዳንኤል (7፡ 21-28)፡ አዉሬዉ/ሐሰተኛዉ ክርስቶስ የቀድመዉ ቀን እስኪደርስ ድረስ በቅዱሳን ላይ የጦር ዘመቻን ያደርጋል (ቁጥር 22) ፤ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ለሰዎስት አመት ከግማሽ ያስተዳድራል ነገር ግን እግዚአብሄር ሀሰተኛዉን ክርስቶስ በማስወገድ እርሱን እና ግዛቱን/አገዛዙን ያጠፋዋል ፡፡

መደምደሚያ

በእዉነት ቅዱሳን በእግዚአብሄር መንግስት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሳተፋሉ ፡፡

  1. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Daniel, p. 104; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/daniel.pdf.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 957.

ጥያቄዎች

  1. ራሳችሁን እንደ ንጉስ ብልጣሶር አስቡ ፤ በዳን (5፡ 5-6) በግድግዳዉ ላይ የእጅ ፁሁፍ አይቶ በነበር ጊዜ እንዳደረገዉ በተመሳሳይ መንገድ ታደርጋላችሁ ? “ የእጅ ፅሁፍ በግድግዳ ላይ እንደ ነበረው “ ተመሳሳይ ልምምድ ኖሯችሁ ያውቃል ? አዎ ከሆነ አክብራችሁታል ? ለምን ወይም ለምን አልሰማችሁትም ?
  2. የእጅ ፅኁፉን እንዲተረጉሙለት መጀመሪያ ንጉሱ ማንን ጠራ ? በግል አስተያየታችሁ ይህ መልካም ነበር ? አስማተኞች/ህልም ፈቺዎች ኃይላቸዉን ከማን እንዳገኙት ምን ታስባላችሁ ? ለፅሁፉ ትርጉሙን መስጠት ባልቻሉ ጊዜ ንጉሱ ማንን ጠራ ?
  3. በግድግዳዉ ላይ የተፃፈዉ ምን ነበር ትርጉሙስ ? ንጉስ ብልጣሶር ይህን ማስጠንቀቂያ እና የጨለማ መልዕክትን እየሰማ ለምን ዳንኤልን ሐምራዊ ልብስ እና የወርቅ ሰንሰለት በማልበስ በመንግሰቱ ላይ ሰዎስተኛ አስተዳዳሪ እንዳደረገዉ ምን ታስባላችሁ ? በንጉስ ብልጣሶር ላይ በዚያኑ ምሽት ምን ሆነ ?
  4. ንጉስ ዳርዮስ ንጉስ ከተደረገ በኋላ ሌሎቹ ሰራተኞች በዳንኤል ላይ ስህተትን ለማግኘት ለምን ፈለጉ ? ማንኛዉንም ስህተት ለማግኘት ምን አደረጉ ?
  5. ንጉሱ በፈረመዉ ህግ መሰረት በዳንኤል ላይ ምን ተፈጠረ ? ንጉሱ ይህን በዳንኤል ላይ ይህን በማድረጉ ደስተኛ ነበር ? በማለዳ ንጉሱ በአንበሶች ጉድጓድ ምን አገኘ ? ከዚያስ የተነሳ ምን ሆነ ? (ዳን 6፡ 26-27)
  6. በዳንኤል 7 ዳንኤል በነበሩት ሁለት ራዕዮች ላይ አንፀባርቁ ፤ ዳንኤልን አስቸግረዉታል ? ምና ማለት ነበሩ ? የዳንኤልን ራዕይ ማን መተርጎም እንደሚችል ምን ታስባላችሁ ?
  7. በዳንኤል (5-7) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Daniel 6:10

“When Daniel learned that the document had been signed, he went into his house. The windows in its upper room opened toward Jerusalem, and three times a day he got down on his knees, prayed, and gave thanks to his God, just as he had done before.”

ንጉሥ ዳርዮስ ከንጉሡ በቀር ሌላ አምላክን የሚያመልክ ማንኛውም ሰው ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንድጣል የሚያዝ አዋጅን አጸደቀ ፡፡ ዳንኤልም ይህን ከሰማ በኋላ እንደ ሁልጊዜው መስኮቱን ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ከፍቶ በየዕለቱ ሦስት ጊዜ በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ይጸልይና ያመሰግን ነበር ። ዳንኤልም እግዚአብሔርን ሲያመሰግን በመገኘቱ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ ፡፡ በለሊትም እግዚአብሔር ዳንኤልን ያድን ዘንድ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ ! በእውነት ስለተራመደ ደግሞም አንዱን ብቸኛውንና እውነተኛውን አምላክ ስላመለከ ፣ እግዚአብሔር ዳንኤልን አዳነው ፡፡

ምንም እንኳን በዙሪያችሁ ያለው ዓለም ባህል ምቾት እንድሰማህ ይህን መንገድ ተከተል ወይም ግራ እንዳይገባህ ይህን መንገድ ወይም ደግሞ ከጭንቀት የጸዳ ህይወት እንዲኖርህ ይሄንን ቢልም ፣ እግዚአብሔር ግን ፡- “ የምትወደኝ ከሆነ ተከተለኝ “ ይልሃል ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ ፣ እንደሚመራህ ፣ እንደሚያድንህ ፣ እንደሚያጽናናህ እናም ደግሞ ዓለትህና መሸሸጊያህ እንደሚሆን ይናገራል ፡፡ ያለምንም ማመቻመች እግዚአብሔርን እመነው ፡፡ ምናልባት ብዙዎች በማይጓዙበት መንገድ መሄድ አደጋ ያለው ሊመስል ይችላል ፣ ሆኖም ግን አታመቻምች ፡፡ በቃ ሀላፊነትን ውሰድና ኢየሱስን ተከተል ፡፡ እርሱ ለአንተ ሊገልጠው የሚፈልገው አሳብና ተስፋ አለው ፡፡ ሆኖም ግን መጀመሪያ አንተ ልትወስደው የሚገባ የእምነት እና እርሱን የመከተል እርምጃ አለ ፡፡ እግዚአብሔርን እመነው ደግሞም ከምንም ነገር በላይ እርሱን አምልከው ፡፡

“ ዳንኤልም ጽሕፈቱ እንደ ተጻፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ ፤ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር ፤ ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ በየዕለቱ ሦስት ጊዜ በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም ። “

  • ዳንኤል 6፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

ዳንኤል 6:16 — “የዚያን ጊዜም ንጉሡ አዘዘ፥ ዳንኤልንም አምጥተው በአንበሶች ጕድጓድ ጣሉት፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም፦ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ እርሱ ያድንህ አለው።

ዳንኤል 6:21–23 — “ዳንኤልም ንጉሡን፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፥ ንጉሥ ሆይ፥ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።የዚያን ጊዜም ንጉሡ እጅግ ደስ አለው፥ ዳንኤልንም ከጕድጓዱ ያወጡት ዘንድ አዘዘ፤ ዳንኤልም ከጕድጓድ ወጣ፥ በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም።

ሐዋርያት ሥራ 5:29 — “ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ ፦ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል ። “