Major Prophets Daniel

Nebuchadnezzar's Golden Statue

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Stone Daniel 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 649 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና በዳንኤል 2 መጨረሻ ላይ በንጉስ ናቡከደነፆር ህልም ላይ በፍጥነት ጨርሰናል ፡፡ ንጉሱ በህልሙ ዳንኤል ንጉሱ ከሰማይ አምላክ ኃይል እና ስልጣን ተሰጥቶት እንደ ነበር በመግለፅ የተረጎመዉን ምስል አይቶ ነበር ፡፡ የምስሉ አካላት የአለምን ኃይል ይወክላሉ ፤ ባቢሎን የምስሉ የራሱ ወርቅ ነበረች ጠላቶቿንም አሸንፋ ነበር ፡፡ ሌሎቹ የሚያንሱት መንግስታት በባቢሎን ስፍራ ላይ በማደግ እያንዳንዱን ሌላዉን እቃ ይወክላሉ፡ ሜዶ-ፋሪስ -ብር፣ ግሪክ - ነሐስ፣ እና ሮማን ኢምፓየር - ብረትን ይወክላሉ ፡፡ የሸክላ/የብረቱ እግር እና አዉራ ጣት በዉስጡ ጥቂት ብረትን በመያዝ የተከፋፈለ መንግስት ይሆናሉ የሮማን ኢምፓየርንም ይወክላል ፤ የተከፈለዉ መንግስት አንዱ አካል ጠንካራ ሲሆን ሌለኛዉ አካል ደግሞ ደካማ/የሚሰበር ይሆናል ፡፡ ህልሙ የመንግስቱ መዉደቅ ነበር ፤ በዚህ ህልም ዳንኤል ኢየሱስን የሚወክል ቃል አዬ፡ ድንጋዩ (ዳን 2፡ 45) ፡፡

ትርጓሜዉንም በሰማ ጊዜ ንቡከደነፆር በዳንኤል ፊት በመደፋት በመንግስቱ ሰዎስተኛዉን ስልጣን ላይ በማስቀመጥ አከበረው ፡፡ በተጨማሪም ንጉሱ ዳንኤልን የንጉሳዊ ልብስን እና እንዲለብሰዉም የወርቅ ሰንሰለትን ሰጠው ፤ ዳንኤል ጓደኞቹ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎም ሹመት እንዲሰጣቸዉ ጠየቀ በታመኑም ጓደኞች የተከበበ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 2 መጨረሻ ላይ ናቡከደነፆር በእግዚአብሄር አምላክ በመደነቅ ዉስጥ ነበር ነገር ግን ያ በምዕራፍ 3 የተቀየረ ይመስላል ፡፡ ዋይርስቤ “ ናቡከደነፆር ስለ ብረታ ብረት ስለሆነዉ ምስል ህልም ባየበት ምሽት (ዳንኤል 2) እና አሰርቶት በነበረዉ የወርቅ ምስል ፊት ሕዝቡ እንዲሰግዱ ባዘዘበት ቀን መካከል ያለዉ ጊዜ ምን ያክል እንደሆነ አናዉቅም ፤ አንዳንድ ተማሪዎች በምዕራፍ 3 የተገለፀዉ ክስተት ከዳንኤል እና ከጓደኞቹ ትዉዉቅ ኢየሩሳሌም ሙሉ ለሙሉ ጠፍታ ከነበረበት ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ከኃያ አመታት በኋላ እንደተከሰተ ያምናሉ “ ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ዳንኤል (3፡ 1-7)፡ ናቡከደነፆር ትልቅ ምስልን በመገንባት በዱራ ሜዳ ላይ አስቀመጠ ፤ ምናልባትም ከላይ ወደ ታች ሙሉ በወርቅ የተሸፈነ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ዋይርስቤ” ዘጠና ጫማ ከፍታ እና ዘጠኝ ጫማ ስፋት የሚታይ ምስል ለመስራት በመላዉ መንግስቱ ዉስጥ የሚበቃ ወርቅ ስላልነበር ምናልባትም በወርቅ በተሸፈነ እንጨት የተሰራ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ ንጉሱ የተሸሙትን ሁሉንም ሰራተኞቹን (ስምንን የተለያዩ አይነቶቹን) በስዕሉ ምርቃት ላይ እንዲገኙ ፈለገ (ቁጥር 2) ፤ አዛዦቹ/አለቆቹ በምስሉ ፊት በመሰብሰብ (ቁጥር 3) የሙዚቃ መሳሪያ ድምፅም በሰሙ ጊዜ በምስሉ ፊት እንዲሰግዱ ታዘዙ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ዋይርስቤ “ ይህ ፓለቲካል ከሆነ ስብስብ የሚበልጥ ነበር፣ በሙዚቃ የተሟላ እና በአምልኮዉ ላይ ድርሻቸዉን እንዲፈፅሙ የተጣራ የኃይማኖት አገልግሎት እንደ ነበር “ ተናግሯል ፡፡ ይሁን እንጂ በዚያ ያሉት መሪዎች ምርጫ አልነበራቸዉም - ማክበርን/መታዘዝን የማይመርጡ ከሆነ ይሞታሉ (ቁጥር 6) ፤ ስለሆነም ሙዚቃዉ/ድምፁ በተነፋ ጊዜ ሁሉም ለመስገድ በምስሉ ፊት ተደፉ (ቁጥር 7) ፡፡

ዳንኤል (3፡ 8-18)፡ ነገር ግን አንዳንድ ከለዳዉያን ትዕዛዙን ባለመታዘዝ እና ለምስሉ ለመስገድ እምቢ በማለት

አይሁዶችን ከሰሷቸው (ቁጥር 8-12) ፤ አይሁዶቹም ስማቸዉ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ነበሩ (ቁጥር 12) ናቡከደነፆር ስለ ሰዎስቱ አይሁዶች ወደ እርሱ እንዲያመጧቸዉ ትዕዛዝ ሰጠ (ቁጥር 13) ፡፡ ንጉሱም ተነግሮት የነበረዉ እዉነት እንደ ነበር በመጠየቅ (ቁጥር 14) ለምስሉም እንዲሰግዱ ሁለተኛ እድል ለመስጠት ዝግጁ ነበር ፤ ንጉሱም “ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማነው ? “ በማለት ጠየቃቸው (ቁጥር 15) ፡፡ ሰዎስቱ አይዶች ለንጉሱ መልስ መስጠት እንደማያስፈልጋቸዉ መለሱለት ምክንያቱም አምላካቸው ከእቶን እሳት እና ከንጉሱ ቅጣት ሊያድናቸዉ ስሊችል (ቁጥር 16-17) ፤ በተጨማሪም ንጉሱን አምላካቸዉ ባያድናቸዉም እንኳን የንጉሱን የወርቅ ምስል እንደማያገለግሉ ነገሩት (ቁጥር 18) ፡፡

ዳንኤል (3፡ 19-30)፡ ናቡከደነፆር ባለመታዘዛቸዉ በጣም ስለተበሳጨ የእሳቱን ግለት አስጨምሮት ነበር ፤ ማክአርቱር “ ንጉሱ ቃል በቃል እንደ አንድ መለኪያ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲሞቅ ሳይሆን የፈለገው ሰባት እጥፍ እሳቱ ሞቆ እንዲቆይ ወይም ሰባት እጥፍ የነዳጅ መጠን እንዲጨመርበት መፈለጉን ያመለክታል ፤ የተበሳጨ ንጉስ ማለት በኃይለኛዉ በመቆጣት ሙሉ ብስጭቱን ለመወከል ሰባትን በስዕላዊነት የተጠቀመ ማለት እንደሆነ “ ይገልፃል፡፡ በፍሙ ላይ ለማስቀመጥ በሚነድደዉ እሳት ከታች በኩል በር ነበር እንዲሁም አቅላጮች/አንጥረኞች ገብተዉ ወርቅ የሚያቀልጡበት በግቡ ላይ አንድ በር ነበረው ፡፡ ንጉሱ ሰዎቹን በማሰር በራሳቸዉ ልብስ በመሸፈን እቶኑ አናት/ጫፍ ድረስ እንዲያመጧቸው ከሰራዊቱ ዉስጥ ያሉትን ሰዎች አዘዛቸው (ቁጥር 22) ፤ ያ ማለትም ሰዎስቱ አይሁዶች ወደ እቶኑ ዉስጥ ወደ ታች ተወረወሩ ፡፡ እቶኑ/እሳቱ በጣም የጋለ/የሞቀ ስለ ነበር ሰዎስቱን አይሁዶች በአናቱ ላይ አምጥተዋቸዉ የነበሩት ወታደሮች በሙቀቱና በግለቱ ተገደሉ (ቁጥር 20-22) ፡፡

ንጉሱም ከአማካሪዎቹ ጋር በሚነድደዉ እሳት ዉስጥ የተጣሉትን ሰዎች ተመለከቱ ፤ ንጉሱም በእሳቱ ዉስጥ ከሰዎስት ሰዉ ይልቅ አራት ሰዎችን በተመለከተ ጊዜ ዘሎ ተጠጋ (ቁጥር 23-25) ፡፡ ንቡከደነፆር አራተኛዉን ሰዉዬ “ እንደ አማልዕክትን ልጅ “ ገለፀው ፡፡ ንጉሱም ሰዎቹን በእሳት ዉስጥ እንዳልቆሰሉና ያለ ጉዳትም በእሳቱ ዉስጥ እየተመላለሱ እንደ ነበሩ ማየት ቻለ ፡፡

ይህ ከመገለጡ በፊት የክርስቶስ መልክ ነው - ማለትም በምድር ላይ ከመወለዱ በፊት በመፅኀፍ ቅዱስ በጊዜው የታየበት ነው (መሳ 6፡ 11) ፡፡

ንጉሱም ሰዎስቱን አይሁዶች ከእቶኑ ዉስጥ እንዲወጡ ጠራቸው ፤ ሕዝቡም በልብሳቸዉ እና በአካላቸዉ ላይ በእሳቱ የደረሰ ምንም የጉዳት ማስረጃ ሳይኖር ባገኟቸዉ ጊዜ ተደነቁ (ቁጥር 26-27) ፡፡ ናቡከደነፆርም እነርሱን ለማዳን መልዓኩን ልኮ ለነበረዉ ለሲድራቅ፣ ለሚሳቅ እና ለአብድናጎ አምላክ ምስጋና ሰጠ (ቁጥር 28) ፡፡ ንጉሱም አድስ አዋጅን/ትዕዛዝን ሰጠ በአምላካቸዉ ላይ ምንም ነገር የሚናገር የተቆራረጠ በመሆን ቤቱም በጉድፍ መጣያ ዉስጥ እንደሚሆን አዘዘ (ቁጥር 29) ፡፡ ንጉሱም ሰዎስቱን አይሁዶች ሸለማቸው (ቁጥር 30) ፡፡

መደምደሚያ

ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ እዉነተኛ እምነትን አሳዩ ፡፡ ለእምነታቸዉ በምላሹ ዋይርስቤ “ እዉነተኛ እምነት በሚገባ ፈተናዎችን ያሸንፋል “፣ “ እዉነተኛ እምነት ጌታን ያዉጃል “ ፣ “ እዉነተኛ እምነት ጠላትን ያሸንፋል “ በተጨማሪም “ እዉነተኛ እምነት ተስፋን ያረጋግጣል “ እንደሆነ ያብራራል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 262.

  2. Wiersbe, p. 263.

  3. Wiersbe, p. 263.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 953.

  5. Wiersbe, pp. 262–266.

ጥያቄዎች

  1. ናቡከደነፆር እግዚአብሄር የጌቶች ጌታ እና የነገስታት ጌታ እንደሚሆን ቢያዉጅም እንኳን (ዳን 2፡ 47) አዘጋጅቶት ለነበረዉ የወርቅ ምስል አሁንም ሁሉም “ ሰዉ “ እንዲሰግዱ እና እንዲደፉ ለምን እንደፈለገ ምን ታስባላችሁ ? (ዳን 3፡ 4-6)
  2. በዳን (3፡ 12) ጥቂት ከለዳዉያን በሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ላይ ምን አይነት ክሶችን አደረጉ ? እነዚህ የኃሰት ክሶች ነበሩ ?
  3. በባቢሎን አድገው ሳለ ከንጉሱ እጅ እግዚአብሄር ሊያድናቸዉ እንደሚችል በእግዚአብሄር ላይ ያላቸዉን የሲድራቅ፣ የሚሳቅ እና የአብድናጎን እምነት እንዴት ትገልፁታላችሁ ? በኢሳይያስ ፅሁፍ ወይም በሌላ መፅኀፍት የለመዱ ነበሩ ብላችሁ ታስባላችሁ (ኢሳ 43፡ 2) ? ከኢዮስያስ ዘመን መጨረሻ በዳን (1፡ 1-4) ወደ ባቢሎን የተወሰዱ እስከ መሆን ድረስ ምን ያክል ጊዜ ነበር ? (2ነገ 24፡ 1-5, 2ዜና 36፡ 1-6)
  4. ናቡከደነፆር በዳንኤል መፅኀፍት የተመዘገበ ህልሞች እና ራዕዮች ሁለቱም ነበሩት ፤ ማን ላካቸው (ዳን 2፡ 28-29, 4፡ 24) ? ይህ ስለ ህልም እና ስለ ራዕይ እምነታችሁን እና መረዳታችሁን ይፈትናችኋል ? እነርሱን የሚገልፅ የአዲስ ኪዳን መፅሀፍ አንብባችኋል ? (ማቴ 1፡ 20, 2፡ 12, ሐዋ 10፡ 3, 11፡ 5, 16፡ 9)
  5. በዳን (4፡ 5) ናቡከደነፆር አይቶት የነበረዉ ህልም እና ራዕይ አላማዉ ምን ነበር (ዳን 4፡ 17, 32, 37) ? በዳን (4፡ 27) ዳንኤል ንጉሱ ምን እንዲያደርግ መከረው ? የህልሙ መፈፀም ምን አስከተለ/ምን አመጣ ? (ዳን 4፡ 29-31)
  6. በዳን (4፡ 30) ናቡከደነፆር “ ታላቂቱ ባቢሎን “ የሚለዉን ቃል ተጠቅሟል ፤ ይህ ቃል ሌላ የት ስፍራ ጥቅም ላይ ዉሏል ስለ ተመሳሳይ ስፍራስ የሚያወራ ነው ? (ራዕ 17፡ 5, 18፡ 2)
  7. በዳንኤል (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Daniel 3:28, 29b

“Nebuchadnezzar exclaimed, ‘Praise to the God of Shadrach, Meshach, and Abednego! He sent His angel and rescued His servants who trusted in Him. They violated the King’s command and risked their lives rather than serve or worship any god except their own God . . . For there is no other god who is able to deliver like this.’”

ንጉሥ ናቡከደነፆር ህዝቡ ሁሉ እርሱ ላሰራው ለወርቅ ምስል እንድሰግዱ አዘዘ ፡፡ ማንም ይህን ለማድረግ እምቢ ቢል ወደ ሚነድድ የእሳት እቶን እንደሚጣልም ተናገረ ፡፡ ምንም እንኳ ይህ አዋጅ ቢነገርም ሲድራቅ ፣ ሚሳቅና አብድናጎ ለአምላካቸው በመታመን ለዚህ ጣኦት ከመስገድ እምቢ አሉ ፡፡ ስለዚህም ወደ ሚነድደው እሳትም ተጥለው ነበር ፡፡ ሆኖም ግን እነርሱ እግዚአብሔር ባያድናቸውም እንኳ የናቡከደነፆርን አምላክ እንዳማያመልኩ በመናገር በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን ተስፋ አጸኑ ፡፡ በሚነድደውም የእቶን አሳት ተጥለው ከቆዩ በኋላ ፣ በእሳቱና በሙቀቱ ምንም ሳይነኩና ሳይጎዱ ከእሳቱ ወጡ ! እግዚአብሔር አዳናቸው ፡፡ ንጉሡም ይህን ታምራት ባየ ጊዜ የአንዱን እውነተኛ አምላክ ታላቅ ስራ አወጀ ፡፡

ከባድ ፈተና በፊታችሁ ሲጋረጥባችሁ ፣ እርሱ እንደሚያድናችሁ በማመን እምነታችሁን በእግዚአብሔር ላይ ታደርጋላችሁን ? ተስፋችሁ በእርሱ ዘንድ ብቻ ነውን ? ዛሬ የገጠማችሁ ምንም አይነት ፈተና ይሁን ፣ ያድናችሁ ዘንድ እግዚአብሔር ቻይ እንደሆነ እመኑ ፡፡ እርሱ ነጻ አውጫችሁ ነው ፡፡ እርሱ አጠገባችሁ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ዓለታችሁ ፣ ዓምባችሁና ጋሻችሁ እንደሚሆን እመኑ ፡፡ አሁን ስሙን ጥሩ ፡፡ ለእግዚአብሔር የምታቀርቡትን አምልኮና መሰጠት ለሌላው ከመስጠት እምቢ በሉ ፡፡ ከዚህ እሳት ውስጥ እንሚያድናችሁ እመኑ ፡፡ ባያድናችሁም እንኳ የእግዚአብሔርን ስም ማወደሳችሁን ቀጥሉ ፡፡ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡ አሁኑኑ “ እሳት “ በሆነባችሁ ነገር ውስጥ ቆማችሁ ስሙን አመስግኑ ፡፡

“ ናቡከደነፆርም መልሶ ፦ መልአኩን የላከ ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ …… እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና ፡፡ “

  • ዳንኤል 3:28, 29b

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 18:2 — “ እግዚአብሔር ዓለቴ ፥ አምባዬ ፥ መድኃኒቴ ፥ አምላኬ ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው ። “

ኢሳይያስ 43:2 — “ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም ፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም ፥ ነበልባሉም አይፈጅህም ። “

ዳንኤል 3:18 — “ ነገር ግን ፥ ንጉሥ ሆይ ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት ። “