Major Prophets Daniel

Nebuchadnezzar's Dream

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Stone Daniel 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 648 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ የጀመርነዉ የዳንኤል ጥናት የታላላቅ ነቢያት ጥናታችንን ያጠቃልልንናል ፡፡ ብዙ የክርስቶስን መልክ የያዙት በዳንኤል ዉስጥ ሁሉም ምዕራፎች አስፈላጊ ናቸው ፡፡ ለጠቅላላ መፅሀፉ ትኩረት የምናደርግበት ድንጋዩ የሚል ነው (ዳን 2፡ 45) ፡፡

ማክአርቱር “ እንደ ዕብራዊያን ልምድ የዳንኤል ርዕስ በመፅሀፉቱ ዉስጥ ከእግዚአብሄር ራዕይን ከተቀበለዉ ነቢይ የተወሰደ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ በእርግጥ “ ከአስራሁለቱ ምዕራፎች ዘጠኙ በህልም እና በራዕይ ከመገለጥ ጋር የተገናኙ ናቸው “ ፡፡ የዳንኤል መፅሀፍ በትክክል ሁሉንም ሰባዉን የባቢሎን የምርኮ አመታትን ይሸፍናል (ዳን 9፡ 1-2) ፡፡ ዳንኤል “ ለአሕዛብ እና ለአይሁዶች አለም የእግዚአብሄርን የወቅቱን እና የወደፊቱን በማወጅ የእግዚአብሄር ቃል አቀባይ ሆነ “ ፡፡ የዳንኤል ስም “ እግዚአብሄር ዳኛዬ ነው “ ማለት ነው ፡፡

ዳንኤል በመጀመሪያዉ ስደተኞች ወደ ምርኮ በተወሰዱበት ማዕበል ዉስጥ ነበር ፤ አስራአምስት አመት አካባቢ ወደ ምርኮ በመወሰድ ወደ ባቢሎን “ ወደ ሀገሪቱ የገቡትን አይሁዶች በማገዝ ተግባር ወደ ባቢሎናዊያን ባህል አድስ ሀሳብ አምጪ ለመሆን ወደ ባቢሎን ተላከ ፤ በዚያ የቀረዉን ረጅም ህይወቱን አሳለፈ (ከስምንንት-አምስት አመት ወይም ከዚያ በላይ )” ፡፡ ዳንኤል በባቢሎን መልካም አደረገ እዉቅናንም በማሳደግ ለአይሁዶች እንደ ቃል አቀባይ አገለገለ ፤ ዳንኤል በመፅሀፉ ላይ ተመዝግቦ ከነበረዉ በላይ ኖረ (ዳን 10፡ 1) ፡፡ ዳንኤል ከሕዝቅኤል፣ ከዕንባቆም፣ ከኤርምያስ እና ከሶፎንያስ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ትንቢትን ተናግሯል ፡፡

የዳንኤል መፅሀፍ ባቢሎን ኢየሩሳሌምን በመያዝ የመጀመሪያዉ የስደተኛ ማዕበል ወደ ባቢሎን ተልከዉ በነበር ጊዜ ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት ጀመረ ፡፡ ዳንኤል ቂሮስ እና ሜዶ-ፋሪስ ባቢሎንን እስኪይዟት ድረስ እና ቂሮስ ከክርስቶስ ልደት 539 በፊት በግዞት ያሉትን ነፃ እስኪያወጣ ድረስ መተንበዩን ቀጥሏል ፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ የመጨረሻዎቹን ሰዎስቱን የይሁዳ ነገስታቶችን በመዘርዘር ለዳንኤል ዳራን/መነሻ ኃሳብን ጠቅሷል (ኤር 1፡ 1-3) በተጨማሪም ነቢዩ ሕዝቅኤልም ዳንኤልን እንደ አስተዋይ እና ፃድቅ ሰዉ ጠቅሶታል (ሕዝ 14፡ 14, 20, 28፡ 3) ፡፡ በተጨማሪም ዳንኤል በዕብ (11፡ 32-33) የተጠቀሰ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ዳንኤል በአለም ላይ በአሕዛብ የስልጣን ጊዜ እና ከዚያ በኋላ በሁለቱም ለእነርሱ የእግዚአብሄርን እቅድ በመግለጥ በግዞት ያሉትን አይሁዶችን ለማበርታት የተፃፈ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ስለ አለመታዘዛቸዉ ሊቀጣ የአሕዛብን ኃይል ተጠቀመ ፡፡

ትምህርት

ዳንኤል 1፡ ባቢሎን በኢየሩሳሌም ላይ ከበባን ጣለች እግዚአብሄርም የይሁዳን ንጉስ ኢዮአቄምን የእግዚአብሄር ከሆኑት እቃዎችም ጋር ለናቡከደነጾር አሳልፎ ሰጠው ፡፡ ናቡከደነፆር አለቆቹን መልካም እይታ፣ ጠንካራና በንጉሱ ቤት ማገልገል የሚችሉትን ጎበዛዝት ሰዎችን የንጉሱን ጎበዛዝት ሰዎች እና ታዋቂ ቤተሰቦችን ወደ ባቢሎን እንዲወስዱ አዘዛቸው ፡፡ እነዚህ ጎበዛዝት ሰዎች በንጉሱ አደባባዮች ለማገልገል ከንጉሳዊያን ምግቦች የሚመገቡ እና ለሰዎስት አመት የሚሰለጥኑ ነበሩ ፤ ጎበዛዝቶቹ ሰዎች የባቢሎናዊያን ስምም የተሰጣቸዉ ነበሩ፡ ብልጣሶር (ዳንኤል)፣ ሲድራቅ (አናንያ)፣ ሚሳቅ (ሚሳኤል) እና አብድናጎ (አዛርያስ) (ቁጥር 1-7) ፡፡ በቁጥር 8-16 ዳንኤል እና ሌሎች እግዚአብሄር አዞአቸዉ የነበረዉን ብቻ ለመብላት መረጡ ፤ የፈተና/የሙከራ ጊዜዉን አለፉ በአስረኛዉ ቀንም የንጉስን/ የመሳፍንትን ምግብ በልተዉ ከነበሩት የተሸለ ጤነኛ እና ጠንካራ ነበሩ ፡፡ ከስልጠና ጊዜዉ መጨረሻም ላይ ከይሁዳ የመጡት ሁሉም ጎበዛዝት ሰዎች በንጉሱ ፊት ቀረቡ ፤ ሁሉም ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸዉ በኋላ ከዳንኤል እና ከጓደኞቹ ጋር እኩል የሚሆን አልተገኘም ነበር ፤ ንጉሱ በተለያዬ ነገር/ጉዳይ ላይ ባማከራቸዉ ጊዜ በመንግስቱ ዉስጥ ካሉት ህልም ፈቺዎች እና አስማተኞች አራቱ የተሸሉ ሆነዉ አገኛቸው (ቁጥር 17-21) ፡፡

ዳንኤል (2፡ 1-26)፡ ናቡከደነፆር እንቅልፉን የነሳዉ ህልም ነበረው ፤ ህልም ተርጓሚዎቹን እና አስማተኞቹን ህልሙን ከመፍታታቸዉ በፊት ህልሙ ምን እንደ ነበር እንዲነግሩት ፈለገ ነገር ግን እርሱን መጀመሪያ ህልሙን እንዲነግራቸዉ ጠየቁት ፤ ንጉሱም ህልሙን እና ትርጓሜዉን መናገር የማይችሉ ከሆነ የተቆራረጡ እንደሚሆኑ መለሰላቸው ፡፡ እንደ ጠየቃቸዉ ማድረግ ከቻሉ ታላቅ ሽልማት ይሆንላቸዋል (ቁጥር 1-6) ፡፡ የንጉሱ ህልም ተርጓሚዎች ጊዜዉን አስረዘሙ ነገር ግን ንጉሱ ቃሉ የመጨረሻ እንደ ነበር ነገራቸው ፤ ትርጉማቸዉን ማምን እንዲችል መጀመሪያ ህልሙን እንዲነግሩት ፈለገ (ቁጥር 7-9) ፡፡ የንጉሱ ህልም ፈቺዎችም ንጉሱ የፈለገዉ ነገር የማይቻል እንደ ነበር መለሱለት - ያን እግዚአብሄር ብቻ ማድረግ እንደሚችል (ቁጥር 10-11) ፡፡ ንጉሱም በጣም በመበሳጨት የነበሩትን ህልም ፈችዎች እና አስተዋዮች ሁሉ ለመገድን የተወሰዱ እንዲሆኑና ዳንኤል እና ጓደኞቹም ሳይቀሩ እንዲገደሉ ፈለጓቸው (ቁጥር 12-13) ፡፡

ዳንኤል ጥበበኛ ሰዎች በሙሉ እንደተገደሉ በጥበብ ጠየቀ ምን እንደ ተፈጠረም ተነገረው ፤ ዳንኤል ንጉሱ ጠይቆት እንደ ነበረዉ ማድረግ እንዲችል ጊዜ እንዲሰጠዉ ጠየቀው (ቁጥር 14-16) ፡፡ ዳንኤል ሰዎስት ጓደኞቹን ስለ ሆነዉ ነገር በመንገር እንዳይገደሉ ሚስጥሩን እግዚአብሄር እንዲገልጥ ምህረቱን በመጠየቅ እንዲፀልዩ ጠየቃቸው (ቁጥር 17-18) ፡፡ ሚስጥሩ በራዕይ ለዳንኤል ተገለጠለት ዳንኤልም ስለ ጥበቡ እና ኃይሉ እግዚአብሄርን አመሰገነ (ቁጥር 19-23) ፡፡ ዳንኤል አስተዋይ ሰዎችን እንዲገድል አሳይመንት ተሰጥቶት ወደ ነበረዉ አርዮክ በመሄድ ንጉሱ የሚፈልገዉን ትርጓሜ ስለ ነበረዉ እንዳይገድላቸዉ ነገረው ፡፡ አርዮክ ዳንኤልን ወደ ንጉሱ በመዉሰድ ከአይሁድ ምርኮዮች ዳንኤል ማድረግ እንደሚችል ገለፀለት ፤ ንጉሱም ዳንኤልን ሕልሙን እና ትርጓሜዉን ያዉቀዉ እንደሆን ጠየቀው ፤ ዳንኤልም እሱ እንዳልሆነ ነገር ግን በሰማይ ላይ ያለዉ አምላኩ እንዳሳየው እና ለንጉሱም ህልሙን እንደገለፀለት ነገረው ፡፡ የንጉሱ ሕልም የወደፊት/የመጪዉ ዘመን እንደ ነበር እና የዳንኤል አምላክ እዉቀቱን እና እንዲገልፀዉ ጥበብን ሰጥቶት ነበር (ቁጥር 24-30) ፡፡

ዳንኤል ህልሙ ታላቅ ግርማ የነበረዉ እና ለመመልከት ያስፈራ ነበር አለ ፤ ራሱ ንፁህ ወርቅ፣ ደረቱና ክንዶቹ ብር፣ ሆዱና ወገቡ ናስ፣ ጭኖቹም ብረት እና እግሮቹም እኩል ብረት እና እኩል ሸክላ ነበሩ ፡፡ ንጉሱ ህልሙን እያዬ በሸክላዉ እግር ላይ አንዲት አለት/ድንጋይ በመምታት ተቆራረጠ ምስሉም በንፋስ በተወሰደ ወደ ቁርጥራጭ ትንንሽ ነገር ተፈጨ (ቁጥር 31-35) ፡፡ ከዚያም ዳንኤል ህልሙን ተረጎመ ፤ ንጉሱ ከሰማይ አምላክ ስልጣን እና ኃይል ተሰጥቶት ነበር ፤ ባቢሎን የምስሉ የወርቅ ራስ እንደ ነበረች እና ሌሎች ከእርሱ የሚያንሱ መንግስታት እንደሚነሱና እያንዳንዶቹን እቃዎች ይወክላሉ፡ ሜዶ-ፋሪስ -ብር፣ ግሪክ - ነሀስ ፡፡ የብረቱ እግሮች የሮማን ግዛት ነበሩ የሸክላዉ/የብረቱ እግር እና ጫፎች አሁንም በዉስጡ ባለዉ ጥቂት ብረት የተከፋፈለ መንግስት ይሆናል የሮማዉያን ኢምየርንም ይወክላሉ ፡፡ ከተከፈሉት መንግስት ዉስጥ አንዱ ብረቱ ሌለኛዉ ደግሞ ደካማ ይሆናሉ ፡፡ ህልሙ የመንግስቱ መዉደቅ ነበር ፤ ይሁን እንጂ የሰማይ አምላክ መንግስት በፍፁም አይጠፋም ሁሉንም መንግስቶች ይሰብራቸዋል/ያደቃቸዋል (ቁጥር 36-45) ፡፡ ክርስቶስ በእርሱ ላይ የተነሱትን ሁሉንም መንግስታት የሚያደቅቅ ድንጋይ ነው ፡፡

ንጉሱም በመደፋት ለዳንኤል ክብርን አቀረበ ምክንያቱም የዳንኤል አማላክ “ የአማልዕክት አምላክ፣ የነገስታትም ጌታ ምስጢርንም ገላጭ ስለሆነ “ (ቁጥር 46-47) ፡፡ ከዚያም ንጉሱ ዳንኤልን ከፍ አድርጎ በመሸለም በመላዉ በባቢሎን ግዛት ሁሉ ላይ ሾመዉ/አስቀመጠው (ቁጥር 48) ፡፡

መደምደሚያ

መንግስታት ይመጣሉ ይሄዳሉ ፤ ክርስቶስ ድንጋዩ ግን ሊጠፋ በማይችለዉ በመጨረሻዉ መንግስት ይመጣል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 947.

  2. MacArthur, p. 947.

  3. MacArthur, p. 947.

  4. MacArthur, p. 947.

  5. MacArthur, p. 947-948.

ጥያቄዎች

  1. የባቢሎን ንጉስ አለቃ መሳፍንቱን ወደ እርሱ እነማን እንዲያመጡለት አዘዘ ? የእነዚህ ሰዎች አላማ ምን ነበር ? (ዳን 1፡ 3-5)
  2. በዳ (1፡ 8) ዳንኤል የንጉሱን ምግብ መብላት እና ወይን መጠጣትን ለምን አልፈለገም ? ዳንኤል የመሳፍንቶቹን አለቃ ሌላ ነገር እንዲበላ እንዲፈቅድለት እንዴት አሳመነው ? ከአስር ቀናት በኋላ ምን ሆኖ ነበር ? (ዳን 1፡ 9-14)
  3. እግዚአብሄር የዳንኤልን እና የሰዎስት ጓደኞቹን መታመን እንዴት ሸለመ ? ዳን (1፡ 17) እግዚአብሄር ለመታዘዛችሁ እና ለመታመናችሁ እንዴት ሲሸልማችሁ አይታችኋል ?
  4. በዳንኤል 2 የንጉስ ናቡከደነፆር ህልሞች ምን ነበሩ ? ከለደዉያን ንጉሱን ስለ ህልሙ ምን አሉት (ዳን 2፡ 10) ? የንጉሱ ምላሽ ምን ነበር ? ዳንኤል ህልሙን በመተርጎም እንዴት አጠናቀቀ ? እግዚአብሄር የህልሙን ሚስጥር ለዳንኤል መቼ ገለፀለት ? (ዳን 2፡ 19)
  5. በዳን (2፡ 27-28) ዳንኤል ንጉሱ እየጠየቀ ስለ ነበረዉ ሚስጥር ማን ብቻ መተርጎም ይችላል ? ዳንኤል የሰጠው የህልሙ ትርጓሜ ምን ነበር ንጉሱስ እንዴት ምላሽ ሰጠ ? (ዳን 2፡ 31-49)
  6. በዳንኤል (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Daniel 1:8–9

“Daniel determined that he would not defile himself with the king’s food or with the wine he drank. So he asked permission from the chief official not to defile himself. God had granted Daniel favor and compassion from the chief official.”

የንጉሥ ነቡከደነጾር መሳፍንት ከብዙ እስራኤላዊ ወጣቶች መካከል የነበረውን ዳንኤልን በባቢሎን በንጉሡ ፊት ለማገልገል እንድሰለጥን መረጡት ፡፡ ንጉሡም የተመረጡት ከንጉሥ ገበታ እንድበሉና እንድጠጡ አዘዘ ይህም የዳንኤልን እምነት የሚፈታተን ነበረ ፡፡ ዳንኤልም በድፍረት ጥራጥሬና ውኃ ብቻ እንድበላ እንድፈቀድለት ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም ለዳንኤልና ከእርሱ ጋር ላሉት ለሶስቱ በአለቃው ፊት ሞገስን ሰጣቸው ፡፡ በስልጠናውም መጨረሻ ዳንኤልና ጓደኞቹ በአካል ብቻ አልነበረም ታሽለው የተገኙት ነገር ግን እግዚአብሔር አስር እጥፍ ጥበብና ማስተዋልን ሰጥቷውም ነበር ፡፡

እግዚአብሔር ሰውን ሳይሆን ራሱን እግዚአብሔርን የሚፈራ ልብን ይወዳል ፡፡ ኢየሱስ ማንም እርሱን መከተል ቢፈልግ ፡ - ራሱን መካድ ፣ መስቀሉንም መሸከምና እርሱን መከተል እንዳለበት ተናግሯል ፡፡ እንደ ዳንኤል ሁሉ ይሄ ማለት ከአብዛኛው ሰው የተለየ ውሳኔ መወሰንና ምንም መንገድ በሌለበት ጊዜ እግዚአብሔር መንገድ እንደሚያዘጋጅ ማመን ማለት ነው ፡፡ ይሄን ማመን አለብህ እርሱን ስታከብረውና በፊቱ በቅንነት ስትመላለስ ፣ እርሱ ከአንተ ጋር ይሆናል ፡፡ ምንም እንኳ ይህን ማድረግ ሞኝነት ፣ የማያዋጣ እና ብቸኛ የሚያደርግ ቢመስልም ፣ ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ውሳኔ ውስን ፡፡ እርሱ እንድትከተለው ፣ በመንገዱ እንድትሄድና በእምነትህ እንዳትደራደር ያዝሃል ፡፡ ዛሬ ባለህበት ዓለም ውስጥ ዳንኤልን ሁን !

“ዳንኤልም በንጉሡ መብልና በሚጠጣው ጠጅ እንዳይረክስ በልቡ አሰበ፤ እንዳይረክስም የጃንደረቦቹን አለቃ ለመነ።እግዚአብሔርም በጃንደረቦቹ አለቃ ፊት ለዳንኤል ሞገስንና ምሕረትን ሰጠው ። “

  • ዳንኤል 1፡8-9

ተጨማሪ ጥቅስ

ዳንኤል 1:17, 20 — “ለእነዚህም ለአራቱ ብላቴኖች እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ ። …..ንጉሡም በጠየቃቸው በጥበብና በማስተዋል ነገር ሁሉ በግዛቱ ሁሉ ከሚኖሩ የሕልም ተርጓሚዎችና አስማተኞች ሁሉ እነርሱ አሥር እጅ የበለጡ ሆነው አገኘባቸው ። “

ማቴዎስ 16:24 — “ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ። “

ሉቃስ 16:10 — “ ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው ፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው ። “