Major Prophets Ezekiel

Rivers Of Living Water

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 47-48 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 647 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ በመጨረሻም በሚያስፈሩ ነገሮች፣ በሚያስደንቁ ትንቢቶች እና ራዕዮች የሕዝቅኤልን መጨረሻ እናደርጋለን ፡፡ በምዕራፍ 37 በደረቁ አጥንቶች ስለተሞላዉ ሸለቆ አጥንተናል እናም ከጥቂት ቀናት በኋላ በምዕራፍ (47-48) ላይ በመሆን ስለ አዲስ ህይወት እናወራለን ፡፡ በሕዝቅኤል ላይ የምናጠናዉ ከየት ሆነን ነው፣ በመልከዓ ምድር ትላልቅ ለዉጦችን እንመለከታለን ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ምድሪቱ ከአብርኃም ጋር ኪዳን አደረገ ከዚያም በመቀጠል እንደ ገና ከአብርኃም ልጅ ከይስሐቅ ጋር እና ከያዕቆብ ጋር አደረገ ይህም በአብርሐም ዘር ዉስጥ ታዉቋል/ተገልጠዋል ፡፡ ሁልጊዜ ኪዳን ሁኔታ ነበረው - ሕዝቡ ለኪዳኑ የታመኑ ባልነበሩ ጊዜ ከምድሪቱ ይወገዳሉ፣ በሚታመኑ ጊዜ ደግሞ በመቀበል ምድሪቱን ይጠብቃሉ (ዘዳ 7፡ 12) ፡፡

ትናትና በምዕራፍ (45-46) እግዚአብሄር ምድሪቱ የእርሱ እንደ ሆነች እና በምድሪቱም መካከል ላይ የእርሱ ቤተ መቅደስ እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ በአዲሱ ቤተ መቅደስ መቅደሱን የሚቆጣጠረዉን አለቃ እና የምድሪቱን ተስፋ እግዚአብሄር በግልፅ ኪዳኑን እየጠበቀ ነበር ፡፡ ዛሬ የእግዚአብሄርን በረከት እናያለን ፡፡ በምዕራፍ 47 በሺዉ አመት ጊዜ የሚከናወንባት ምድር ላይ ለዉጦችን እናያለን ፡፡

ሕዝቅኤል አሁንም በባቢሎን ቢያንስ አስር ሺህ ከሚሞሎ ሌሎች ስደተኞች ጋር በምርኮ ነበር ፤ የሕዝቅኤል መልዕክት በመጨረሻም ከባቢሎን እንደሚወጡ እና በሆነ መጥን ወደ ምትታደሰዉ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ነበር ፡፡ ቤተ መቅደሱ ከክርስቶስ ልደት 587 በፊት ከፈረሰ በኋላ መልሶ ይገነባል (የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ) ፤ ከክርስቶስ ሞት 70 አመት በኋላ ቤተ መቅደሱ እንደ ገና ይፈርሳል ፤ የሕዝቅኤል መልዕክት እንደ ገና ስለሚፈርሰዉ ቤተ መቅደስ አይደለም ስለ አዲሱ ቤተ መቅደስ ነበር - ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ የሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ነው ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (47)፡ ሕዝቅኤል ተመልሶ ወደ ሺዉ አመት ቤተ መቅደስ መግቢያ የተወሰደ ነበር በዚያም በመድረኩ ስር ወደ ምስራቅ የሚፈስስ ዉኃም ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ከዚያም ሕዝቅኤል ከቅጥሩ ወጪ ወደ ሰሜን በር ተወስዶ ስለ ነበር ዉኃዉ ከደቡብ ሲፈስስ ተመለከተ (ቁጥር 2) ፤ የሚመራዉም መልዓክ ሕዝቅኤልን ሌላ የአንድ ማይል ሰዎስተኛ በመለካት ወደ ምስራቅ ወሰደው ፤ ሕዝቅኤል ቁርምጭምጭሚት በሚደርሰዉ ዉኃ ዉስጥ አለፉ (ቁጥር 3) ፡፡ ሕዝቅኤል ቁርጭምጭሚቱ ጋር በሚደርሰዉ ዉኃ ዉስጥ ሌላ የአንድ ማይል ሰዎስተኛን ተመራ ፤ ከዚያም ሌላ የአንድ ማይል ሰዎስተኛ ተመራ ዉኁም ጉልበቱ ደረሰ (ቁጥር 4) ፡፡ ሕዝቅኤል ሌላ የአንድ ማይል ሰዎስተኛ ተወሰደ ዉኁም ለመዋኘት በቂ ነበር (ቁጥር 5) ፤ ከዚያም መልዓኩ ሕዝቅኤልን ምን ተፈጥሮ እንደ ነበር ያየዉን ጠየቀው (ቁጥር 6) ፡፡

ዘካ (14፡ 1-9) የደብረ ዘይት ተራራ እንዴት ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ወደ ግማሽ በመከፈል ትልቅ ሸለቆ እንደሚፈጥር ይገልፅዓል ፡፡ በዚያም ቀን የህይወት ዉኃ ከኢየሩሳሌም ይፈስሳል ግማሹ ወደ ምስራቅ ባህር እና ግማሹ ወደ ምዕራብ ባህር ይፈስሳል እግዚአብሄርም በምድር ላይ ንጉስ ይሆናል (ዘካ 14፡ 8-9) ፡፡ ዘካሪያስ ስለ ጠብታ ሳይሆን ወደ ምስራቅ እና ምዕራብ ባህር ስለሚሄድ ወንዝ ይገልፃል ፡፡ ክርስቶስ በፍፁም የማይጠፋ የህይወት ዉኃን ይሰጧል (ዮሐ 7፡ 37-38) ፡፡ በሺዉ አመት የህይወት ዉኃ ይኖረናል በክርስቶስ የህይወት ዉኃዉን እናየዋለን፡፡

ጄ.ቬሮና ማክጊ ከእነዚህ ጥቅሶች ሊስብ ስለሚችሉ መንፈሳዊ ትምህርቶች ላይ ያተኩራል፡ “ ዉኃዉ ቁርምጭምጪቱ ይደርስ ነበር (ቁጥር 3) - በመንፈስ የአማኞችን መመላለስ ያመለክታል ፤ “ ጉልበት ጋር ሲደርስ “ (ቁጥር 4) የፀሎትን ንግግር ያመለክታል ፤ “ ወገብ ላይ ሲደርስ “ (ቁጥር 4) የአገልግሎት ንግግር (ሽንጣችሁን ሲይዛችሁ) ሲያመለክት ፤ “ ዉኃዉ ለመዋኘት ሲደርስ “ (ቁጥር 5) በሺዉ አመት ሙሉ መባረክን /በረከትን ያመለክታል “ ፡፡ በዚህ የማንመላለስ ከሆነ የእግዚአብሄርን ሙሉነት አንቀምሰዉም / አንለምደዉም ፡፡

ሕዝቅኤል ወደ ወንዙ ዳርቻ በተመለሰ ጊዜ ከሁሉም መንገድ ወደ ጨዉ ባህር በሚፈስሰው ወንዝ በሁለቱም ዳርቻ በኩል ዛፎችን አዬ ከጨዉ ባህር የመጣዉ ዉኃ ከህይወት ዉኃ የተነሳ ይፈወሳል (ቁጥር 7-8) ፤ ጨዉ ባህር በዉኃዉ ዉስጥ ህይወት መኖር የማይችልበት የጨዉ መጠን አለዉ ይሁን እንጂ አንድ ቀንህያዉ እና በአሳ የተሞላ ይሆናል (ቁጥር 9) ፡፡ አሳ አጥማጆች በታላቁ ባህር/በሜደትራሊያ ባህሪ እነደሚያደርጉት በዚያም ያጠምዳሉ (ቁጥር 10) ፤ ይሁን እንጂ እረግረጉና እቋሪዉ ለቤተ መቅደሱ ጨዉ ለመስጠት እንዳለ ይቀራሉ (ቁጥር 11) ፡፡ ሁሉም ዛፎች አመቱን ሙሉ ምግብን ሲሸከሙ/ሲያፈሩ ቅጠላቸዉ ደግሞ ለመድኃኒትነት ይሆናል ፡፡ በእያንዳንዱ ወር ዛፎቹ ከቤተ መቅደስ ከሚወጣዉ ዉኃ የተነሳ አዲስ ፍሬን ያፈራሉ (ቁጥር 12) ፡፡

በዘፍ (2፡ 10) ወንዙ ከኤደን ገነት በመዉጣት ወደ አራት ወንዞች ተከፋፍሏል ፤ ራዕ (22፡ 1-2) በከተማዋ መንገድ መካከል ላይ ወደ ታች በመፍሰስ በሁለቱም በኩል ፍሬና መድኃኒት የሚያመነጩ ዛፎች ስላሉት የህይወት ዉኃ ወንዝ ይናገራል ፤ ይህ ከሕዝቅኤል ወንዝ ጋር ይመሳሰላል ፡፡ ዋይርስቤ በሕዝቅኤል እና በራዕይ ሁለቱም ወንዞች ከእግዚአብሄር እንደሚፈስሱ ይገልፃል ፡፡ በሺዉ አመት ጊዜ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የሚኖር ቢሆንም በዘላላማዊዉ መንግስት ግን ቤተ መቅደስ አይኖርም (ራዕ 21፡ 22) ፤ ሺዉ አመት ለዘላለማዊ መንግስት ዝግጅት ነው ፡፡ ከሺህ አመት በኋላበምድር ላይ ቤተ መቅደስ አይኖርም ፡፡

ለሕዝቅኤል ቃላችን አዲስ ዳዊት እንደሆነ እናስታዉሳለን ፤ በሕዝቅኤል 34 ሕዝቅኤል በጎቹን መልሶ ወደ በጉ ለማምጣት እየሰበሰበ የነበር እንደ ነበር እንደ እንደ እረኛ የተሳለ/የታዬ ነበር ፡፡ ክርስቶስ በሚመለስ ጊዜ ለተሰበሰቡት በጎች (ለአስራ ሁለቱ ነገዶች) ምድር ከምድሪቱ እኩል ድርሻቸዉን ይሰጣቸዋል (ሕዝ47፡ 13-23) ፤ የእያንዳንዱ ዝርዝር ነገር የተሰጡ ናቸው ፡፡ ይህ ሁሉ በሺዉ አመት ዘመን ጊዜ የሚሆን ነው ፡፡ በቁጥር 22 ልጆች የነበሯቸዉ በእነርሱ መካከል የሚኖሩ መፃተኞች/እንግዶች (አይሁድ ያልሆኑት) እነርሱም መሬት ይሰጣቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

በሕዝቅኤል 48 የተመለከተዉ አንድ እዉነት በቁጥር (1-2) ነው ፤ የዳን ነገድ በሺዉ አመት ጊዜ ይገኛል ነገር ግን በራዕ (7፡ 4-8) በታላቁ መከራ ከታተሙት ዉስጥ የሌሉ ናቸው ፤ ያ ማለት ዳን በታላቁ መከራ አያገለግልም ነገር ግን እግዚአብሄር ወደ ሱ አመት ዘመን እንዲመጡ ፈቅዶላቸዋል ማለት ነው ፡፡ ለሁሉም አካል ተስፋ አለ ፡፡

  1. J. Vernon McGee, “Outline for Ezekiel”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/ezekiel/ezekiel-outline.cfm.

  2. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 244.

ጥያቄዎች

  1. በመጨረሻዉ መንግስት በእስራኤል እና በምድር ላይ በተለይም በዉኃ የሚከሰቱ አንዳንድ አስደናቂ አካላዊ ስዕላዉ/አቀማመጣው ለዉጦች ምንድን ናቸው ? (ሕዝ 47፡ 1-12)
  2. በወንዙ በሁለቱም ዳርቻ ያሉት ዛፎች አላማቸዉ/ጥቅማቸዉ ምን ነበር ? በሕዝቅኤል 47 በመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ጥቅሶች መሰረት ህይወት ከየት ነዉ የሚመጣው ?
  3. ስለ ህይወት ሰጪ ወንዝ በመፅኀፍ ላይ ሌሎች ማሳያዎች ምንድን ናቸው (ዘፍ 2፡ 10-14, ኢሳ 55፡ 1, ዮሐ 7፡ 37-39, ራዕ 22፡ 1-2) ? እንደ ህይወት ዉኃ ምልክት ኢየሱስ ማንን ገለፀ ?
  4. በሺዉ አመት መንግስት ዉስጥ የኢየሩሳሌም አዲስ ስም ምን ይሆናል ? (ሕዝ 48፡ 35)
  5. በሕዝቅኤል (47-48) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 47:8–9

“He said to me, ‘This water flows out to the eastern region and goes down to the Arabah. When it enters the sea, the sea of foul water, the water of the sea becomes fresh. Every kind of living creature that swarms will live wherever the river flows, and there will be a huge number of fish because this water goes there. Since the water will become fresh, there will be life everywhere the river goes.’”

ሕዝቅኤልም እያንዳንዱን ነገር ተራ በተራ እያሳየው ካለው ሰው ጋር በራዕይ ቆየ ፡፡ በመጨረሻም ሰውየው ሕዝቅኤልን ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ወደ ሙት ባህር በሚሄድ ወንዝ ውስጥ አሻገረው ፡፡ በመጀመሪያ እስከ ቁርጭምጭሚታቸው በሚደርስ ጥልቀት ውስት ተሻገሩ ፣ ከዚያም አስከ ጉልበታቸው ፣ ከዚያ አስከ ወገባቸው እናም ከዚያ ዋኙ ፡፡ በዚህ ትንቢታዊ ራዕይ ውስጥ ውኃው በፈሰሰበት ቦታ ሁሉ ህይወትን ይሰጥ ነበር ፡፡

ደስ ሲል ! ይህ ለዚህ ዘመን የሚሆን ስዕል ነው ! ኢየሱስ ህያው ምንጭህ ነው ፡፡ የህይወት ውኃ ወንዝ በሆነው በኢየሱስ ላይ ስትተክል ፣ እርሱ የሞተውን ወደ ህይወት ይመልሳል ደግሞም ሁሉን ነገር አዲስ ያደርጋል ፡፡ ኢየሱስ የተትረፈረፈ የህይወት ስጦታን ይሰጣል ፡፡ ራስህን ጠይቅ እስኪ ፡- እኔ በወንዝ ውኃ ውስጥ ነኝን ? ከኢየሱስ ጋር ስትመላለስ እና በእርሱ ስታምን እስከ ቁርጭምጪሚትህ ነውን ? ጥልቀቱ እስከ ጉልበትህ ነውን ፣ ምናልባት በዚህ ጊዜ ተንበርክከህ በልብህ ውስጥ ስለሚመላለሰው ጉዳይ እየጸለይክ ይሆናል ? ወይስ እስከ ወገብ ባለ ጥልቀት ውስጥ ነህ ማለትም እንዴ ከጸለይክ በኋላ እግዚአብሔርን በኃይል እያገለገልክ ? ወይም ምናልባት በውኃው ውስጥ እየዋኘኽ ነው እግሮችህ እንኳ ሳይቀሩ መሬትን ሳይነኩ ፡፡ የእርሱ ህያው ውኃ በቀንህ ውስጥ ባለችው በእያንዳንዷ አጋጣሚ እንደሚያበረታህ ስታምን የእግዚአብሔርን ሙላት ታያለህ ደግሞም ለእርሱ በፍጹም መሰጠት ትኖራለህ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ወደ ወንዝ ውኃው ውስጥ ግባ ፡፡ በእርሱ ውስጥ ስትኖር ፣ እርሱ ከጥልቅ ወደ ጥልቁ ይወስድሃል ፡፡

“እርሱም እንዲህ አለኝ ፦ ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይወጣል ወደ ዓረባም ይወርዳል ወደ ባሕሩም ይገባል ፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃው ይፈወሳል ። ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል ፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል ፥ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል ። “

  • ሕዝቅኤል 47፡8-9

ተጨማሪ ጥቅስ

ሕዝቅኤል 47:3–5 — “ ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ ። ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ ። ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ ። “

ዮሐንስ 7:38 — “ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ ። “

ኤፌሶን 3:19 — “ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።