The Lord's Portion Of The Land
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 45-46 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሕዝቅኤልን ነገ በመጨረስ በመጨረሱ በታላላቅ ነቢያት በዳንኤል ላይ እንጀምራለን ፡፡ ሕዝቅኤልን ስናጠናቅቅ በመንግስቱ ዘመን ጊዜ ምድሪቱ እንዴት እንደምትከፋፈል እናያለን ፤ ንብረት ለአስራ ሁለቱ ነገዶች ይከፋፈላል፣ ንብረት ለአለቆች ይከፋፈላል፣ ንብረት ለሳዶቅ ካህናት እና ነቢያት ይከፋፈላል እንዲሁም ደግሞ የከተማዋ ሰራተኞች እንዲኖሩባት ምድሪቱ ትሰጣቸዋለች ፡፡
በይበልጥ አስፈላጊዉ እግዚአብሄር ከምድሪቱ የራሱ የሆነ ድርሻ አለው ፤ ለዚህ ማክአርቱር ሀምሳ አምስት ካሬ ጫማ ስፍራን “ እንደ ቅዱስ አዉራጃ “ ይጠቅሰዋል ፤ አራት መዓዘን ቅርፅ ሲሆን የይሁዳ ስፍራ በስተ ሰሜን በኩል ሲሆን የቢንያም ስፍራ ደግሞ በስተ ደቡብ በኩል ነው ፡፡ የካህናቱ ስፍራዎች ደግሞ በስተ ምስራቅ እና ምዕራብ በኩል ናቸው ፤ የመካከለኛዉ ስፍራ ለሌዋዊያን፣ ለሳዶቅ ካህናት እና ለከተማዋ ሰራተኞች ወደ ሰዎስት ዋና ዋና ስፍራ የተከፋፈሉ ናቸው ፡፡ ቤተ መቅደሱ በሳዶቅ ካህናት ስፍራ ላይ የሚገኝ ይሆናል ፤ ያም ካህናቱን በቤተ መቅደሱ ዙሪያ እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል ፡፡
እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር በገቡ ጊዜ ስለ ምድሪቱ የመጀመሪያዉ አሳይመንት/ስራ በእጣ እና በእያንዳንዱ ነገድ የቁጥር መጠና ክፍፍልን ማድረግ ነበር (ዘኁ 26፡ 52-56, 34፡ 16-29) ፡፡ 1ነገ (4፡ 7-19) ሰለሞን ምድሪቱን እንዴት ወደ 12 የነገስታት ነገዶች እያንዳንዳቸዉ ለንጉሱና ለንጉሱ ለቤተሰቡ አባል በሙሉ በያመቱ አንድ ወር ምግባቸዉን በሚያቀርቡበት መስፈርት መሰረት ድሪቱን እንዳከፋፈለ ይገልፃል ፡፡ ይሁን እንጂ በሕዝቅኤል 45 ምድሪቱ እንዴት እንደምትከፋፈል የተቀየረ ነገር አለ ፤ በሕዝቅኤል ላይ ብቻ ቅዱስ አዉራጃ/ሰፈር የተሰጠ ነው ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (45፡ 1-6)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (1-6) “ የእግዚአብሄር እጣ/እድል ፋንታ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ የምድሪቱ የእግዚአብሄር ድርሻ ቅዱስ እንደሆነ የሚቀመጥ እና 8-1/3 ማይል ርዝመት እና 6-2/3 ወርድ የሚሆን ሲሆን በክፍት ቦታ የሚከበብን የመቅደሱን ስፍራ ክፍልን ያካትታል (ቁጥር 1-3) ፡፡ ክፍቱ ስፍራ ለመቅደሱ ቅዱስ ስፍራ እና ለካህናቶቹ ቤትነት የሚጠቅም ነበር (ቁጥር 4) ፤ ሌላዉ ስፍራ ደግሞ ለሌዋዊያን ቤት ይሆናል (ቁጥር 5)፡፡ የከተማዋም መሬት ለመላዉ ለእስራኤል ቤት ይሆናል (ቁጥር 6) (ሕዝ 48፡ 15) ፡፡ የሰራተኞች ድርሻ በሕዝ (48፡ 18-20) የተገለፀ ነው ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ “ እግዚአብሄር በዚያ አለ “ የሚል ስም የተሰጠው ነው (ሕዝ 48፡ 35) ፡፡
ኢየሱስ በሚመለስ ጊዜ የእግዚአብሄርን እቅድ በስፍራዉ ያስቀምጠዋል - ከተማና መሬት አለው ፤ ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው ለእርሱ የታቀደ/የተሰራ ነው ፡፡
ሕዝቅኤል (45፡ 7-17)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶችን እንደ “ የአለቆች ድርሻ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፤ ድርሻቸው በምስራቅ እና በምዕራብ አዉራጃ/ክልል ላይ እንደሆነ የተገለፀ ነው (ቁጥር 7) ፡፡ ምድሪቱም ለሕዝቡ ቀድሞ መጥፎ እና ክፉ መሪዎችን በመቃወም መልካም አስተዳዳሪ ለሚሆነው ስሙ ባልተጠቀሰዉ አንድ አለቃ ትያዛለች (ቁጥር 8)፡፡ የእስራኤል አስተዳዳሪዎች ከግፍ፣ ከጭቆና እና ሕዝቡን ከማፈናቀል በመራቅ የሚቀመጡ ነበሩ (ቁጥር 9) ፤ ስርዓት ያለዉን ነገር እና ወጥ የሆነ ተግባራት ይጠቀሙ ነበር (ቁጥር10-12) ፡፡ እግዚአብሄርም ለአለቆቹ የሚያስፈልገዉን መዋጮ አስቀመጠ/ተናገረ (ቁጥር 13-17) ፡፡ አለቆች ለሕዝቡ ከመዋጮዉ መስዋዕትን ያደርጋሉ ፡፡
ሕዝቅኤል (45፡ 18-25)፡ በቁጥር 18 መጀመሪያ ላይ እግዚአብሄር ኃይማኖታዊ መስዋዕቶችን እና ፆሞችን አስቀምጧል/አሳይቷል ፡፡
ሕዝቅኤል አንድ አለቃን/ልዑልን በማስተዋወቅ በመፅኀፉ ዉስጥ ቢያንስ ራሱን አስራ ስድስት ጊዜ ጠቅሷል ፡፡ ይህ አለቃ/ልዑል ማነው ? እስካሁን ሕዝቡ መስዋዕት እንደሚሰጡት አይተናል ፤ ማክአርቱር “ ካህንም ንጉስም እንዳልሆነ ነገር ግን በአንድ ጎን ንጉሱን (ኢየሱስ ክርስቶስን) በመወከል መንግስቱን እንደሚያስተዳድር በተጨማሪም በግል አስራ ሁለቱን ነገዶች እንደሚመራ ልዑል/አለቃ ፤ ምናልባትም የዳዊት ዘር እንደሚሆን “ ይገልፀዋል ፡፡ በሕዝ (34፡ 24) አለቃዉ “ አገልጋዬ ዳዊት “ በማለት የተጠቀሰ ነው ፡፡ ማክአርቱር አለቃዉ/ልዑሉ ምናልባትም ከዳዊት ዘር አንዱ እንደሚሆን ያመለክታል ፡፡ ሕዝ (46፡ 16-18) አለቃዉ ያገባ እና ልጆች ያሉት እንደሚሆን ስለሚያመለክት ኢየሱስ አይሆንም ፡፡ ዋይርስቤ፡ “ የትም ስፍራ ላይ ከንጉሳዊዉ ቤተሰብ አባል፣ ከካህናት ወይም ደግሞ ከሌዋዊያን ወገን እንደሆነ አልተገለፀም ፤ ከማን ነገድ እንኳን እንደሚመጣ አልተነገረንም ፤ በግልፅ ከመሲሁ ስልጣን ስር እንደ ምክትል እንደ ራሴ ሲቪል መሪ እንደሚሆን ሆኖም ግን አብዛኻኛው ተግባሩ ኃይማኖታዊ እንደሚሆን “ ይናገራል ፡፡
ሕዝ (45፡ 21-22) የዚህን የኃይማኖታዊ ኃላፊነቶችን መልክን ያረጋግጣል ፡፡ አለቃው በቅዱሱ አዉራጃ/ግዛት ዉስጥ በሺዉ አመት ጊዜ የኃይማኖታዊ ድግሶችን እና በዓላት የመቆጣጠር ኃላፊነቶች እና ግዴታዎች ይኖሩታል ፡፡
ማክአርቱር “ የሺዉ አመት ድግሶች ከስድስቱ ሌዋዊያን በዓላት ሰዎስቱን ያካትታል፡ 1) ፋሲካን፣ 2) የቂጣ በዓልን እና 3) የዳስ በዓል ናቸው ፤ የማይከበሩት ሰዎስቱ የሌዋዊያን በዓላት ደግሞ፡ 1) በዓለ ሀምሳ ቀን፣ 2) መለከት እና 3) የስርየት በዓላት ናቸው ፤ ያልተካተቱበት ምክንያትም በትንቢታዊነት ወደ ፊት ያመለክቱ የነበሩ የተፈፀሙ ሲሆኑ አሁን ደግሞ ምንም የማስታወስ አላማ አገልግሎት ስሌለቻዉ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡
እንዲቀጥሉ ለድግሶቹ/ለበዓላቱ ምክንያታቸዉ አስፈላጊነታቸው ነው ፤ ማክአርቱር “ ፋሲካ እና የቂጣ በዓል በአዲስ ኪዳን በመጣመር ሕዝቡን ከግብፅ የእግዚአብሄርን ነፃ ማዉጣት እና ከኃጢዓት የክርስቶስ ሞት ነፃ ማዉጣት ላይ እንዳተኩሩ “ ይናገራል ፡፡ በተጨማሪም “ አዲሱን አመት “ የሚያከበር አዲስ በዓል ይመሰረታል ፤ ይህ አዲስ በዓል “ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በቅዱስነት ላይ ማብራሪያ ይኖረዋል “ ፡፡
ሕዝ (45፡ 22) አለቃዉ ለራሱና በምድሪቱ ላይ ለሁሉም ሕዝብ የኃጢዓት መስዋዕት እንደሚያደርግ ይናገራል ፡፡ ዋይርስቤ የኃጢዓት መስዋዕት ማድረግ “ መሲሁ የማያደርገዉ ነገር እንደ ሆነ “ ያመለክታል ፡፡
መደምደሚያ
ዛሬ በጌታ ድርሻ (በሺዉ አመት በምድሩ ላይ) እና የአለቃዉ ድርሻ ላይ ተመልክተናል ፡፡ መሲሁ በግል አስተዳዳሪ ነው ፤ አለቃው በቅዱስ ሕዝቦች ላይ በማፍሰስ ተግባር የተሾመ ነው ፡፡ የሕዝቅኤል የመጨረሻ ሁለቱ ምዕራፎች እንዲያልፋችሁ እንዳትፈልጉ ፤ የሚያስደንቁ ናቸው !
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 243.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 942.
MacArthur, p. 942.
Wiersbe, p. 243.
Wiersbe, p. 243.
MacArthur, p. 940.
MacArthur, p. 940.
Wiersbe, p. 243.
MacArthur, p. 942.
MacArthur, p. 943.
MacArthur, p. 942.
Wiersbe, p. 243.
ጥያቄዎች
-
በሕዝቅኤል (45-46) “ አለቃ “ የሚለዉ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰ ነው ፤ በግል አስተያየታችሁ ስለማን የተነገረ ይመስላችኋል ? ለምን ያን ታስባላችሁ ?
-
የሕዝ (46፡ 11) መስዋዕት ከዘኁ (15፡ 1-9) መስዋዕት ጋር ሲወዳደር ልዩነቶቹ ምን ምን ነበሩ ? የዚህ አስፈላጊነት ምንድን ነው ?
-
በሕዝቅኤል (45-46) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 45:1
“When you divide the land by lot as an inheritance, you must set aside a donation to the LORD, a holy portion of the land, 81/3 miles long and 62/3 miles wide. This entire tract of land will be holy.”
ሕዝቅኤል መሬት ለርስትነት ሲከፋፈል ለእግዚአብሔር የሆነው ተለይቶ እንድቀመጥ ፣ ቅዱስ የሆነውም መሬት ለእግዚአብሔር ዓላማ እንድውል የሚያዝ ትዕዛዝን ተቀበለ ፡፡ ይህም የተሰጠው መሬት በቅድስተ ቅዱሳን ለሚያገለግሉና ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡ ካህናት ይሆናል ፡፡ ለካህናቱ መኖሪያ የሚሆን ቤት ደግሞም ለቅድስተ ቅዱሳን የሚሆን የተቀደሰ ቦታም ይሆናል ፡፡ ሆኖም ግን መጀመሪያ መሬቱ መተውና ለእግዚአብሔር እንደ መባ መሰጠት አለበት ፡፡
እግዚአብሔር በአደራ ለብቻው ለይታችሁ ማለትም ልክ እንደ “ ቅዱስ ስጦታ ወይም መባ “ እንድታስቀምጡት የሰጣችሁ ነገር እንዳለ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ ? ምናልባት እርሱ እንድትገለገሉበት ለሰጣችሁ ነገር እርሱ ዓላማና ዕቅድ ይኖረው ይሆናል ፡፡ የሃብታችሁን እኩሌታ ፣ ንብረታችሁን ፣ ጊዜያችሁን ወይም ለእግዚአብሔር ለእርሱ የተገባውን ነገር መስጠት ነው ፤ ይህ ልትጸልዩበት የሚገባ ነገር ነው ፡፡ ስለዚህ ነገር እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ጊዜ ውሰዱ ፡፡ ከዚያም አድርጉት ፡፡ እርሱን በመታመንና እያንዳንዱ መልካምና ፍጹም ስጦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሆነ በማመን ፣ ያለ ዋጋ በነጻ ስጡ ፡፡ ሌሎችን በመተቸትና እነርሱ የሰጡትን አይቶ በመስጠት ራሳችሁን አትፈትኑ ፡፡ እግዚአብሔርን በራሳችሁ ፈልጉት እናም እንዴት በልዩነት ለእርሱ ዓላማ መስጠት እንዳለባችሁ ጠይቁት ፡፡ እርሱ የልዩነት አምላክ ነው ፡፡ እርሱ የሚታመን አምላክ ነው ፡፡ እርሱ ስትጠይቁት የሚመልስ አምላክ ነው ፡፡ ዛሬ እርሱን ጠይቁት !
“ ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል ፤ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል ። “
- ሕዝቅኤል 45፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 3:9–10 — “ እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር ፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት ፤ ጐተራህም እህልን ይሞላል ፥ መጥመቂያህም በወይን ጠጅ ሞልታ ትትረፈረፋለች ። “
ሕዝቅኤል 45:4 — “ ከምድርም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል ፤ እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል ፥ ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል ። “
ማርቆስ 12:43–44 — “ ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ ፦ እውነት እላችኋለሁ ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች ፤ ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና ፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።