Sacrifices In The Millennial Temple
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 42-44 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በታላላቅ ነቢያት መፅሀፍት መጨረሻዉን ዳንኤልን ከመመልከታችን በፊት በሕዝቅኤል ተጨማሪ ሰዎስት ቀን አለን፡፡ የሕዝቅኤል ጥናት በተማሪዎች ዉስጥ ለመጨረሻ ዘመን ለመዘጋጀት በመፅኀፍቱ ትልቅ ርሀብን እንደፈጠረ አስባለሁ ፡፡
የትናትናዉ ትምህርት በሕዝቅኤል (40-41) በቤተ መቅደሱ ልኬት ላይ ነበር ፡፡ ኢየሩሳሌም በታሪኳ ሰዎስት ቤተ መቅደሶች ነበሯት ፤ የመጀመሪያዉ በሰለሞን የተገነባ ነበር (1ነገ 6፡ 1 – 9፡ 9) ፤ ይህ ቤተ መቅደስ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት የጠፋ እና በምድር ላይ የተቃጠለ ነበር ፡፡ በባቢሎን በምርኮ ያሉት በሀሳባቸው ዉስጥ ቤተ መቅደስ ስላልነበራቸዉ ተስፋ እንደሌላቸዉ ነበር ፡፡ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ በዘሩባቤል የተገነባ እና ክክርስቶስ ሞት 70 አመት በኋላ የፈረሰ ነበር ፡፡ ሕዝቅኤል ሁለተኛዉን ቤተ መቅደስ በመግለፅ ሳይሆን የሺዉ አመት አካል የሚሆነዉን ሰዎስተኛዉን ወይም የመጨረሻዉን ቤተ መቅደስ በመግለፅ ለሕዝቡ ተስፋን አመጣ ፡፡ የሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ክርስቶስ ከተመለሰ በኋላ ለሺአመት ሲገዛ የሚያድርበት ስፍራ ይሆናል ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (43፡ 1-9)፡ ሕዝቅኤል እንደ ነቢዩ ዘካሪያስ ገለፃ (ዘካ 14፡ 4) ክርስቶስ በሚመለስበት ስፍራ በደብረ ዘይት ተራራ በኩል በምስራቁ በር በኩል ተመራ ፤ በዚያ ሕዝቅኤል የእግዚአብሄር ክብር ሲቀርብ ተመለከተ ፤ ድምፁ እንደ ብዙ ዉኃ ድምፅ ይጮኃል ምድርም በክብሩ አብርታለች (ቁጥር 1-2) ፡፡ ሕዝቅኤል በእግዚአብሄር ፊት በግንባሩ ተደፋ (ቁጥር 3) ፡፡ በምዕራፍ (8-11) የእግዚአብሄር ክብር ቤተ መቅደሱን ትቶ እንደሄደ እና መገኘቱ ከአይሁዶች ተለይቶ እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፤ በሕዝቅኤል ራዕይ የእግዚአብሄር መገኘት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡ ይህ ከክርስቶስ መመለስ በፊት ከሰባቱ የመከራ አመታት በኋላ ወዲያዉኑ ይሆናል (ሰዎስት አመት ከግማሹ የሰላም እና በመቀጠል ሰዎስት አመት ከግማሹ ደግሞ የመዓት/የቁጣ) ፡፡ ከእነዚህ ነገሮች ዉስጥ ምንም አይጀምር እንጂ አሁን እኛ በዚያ ዘመን/ጊዜ ላይ ነን ፡፡ የእግዚአብሄር ክብር ወደ ቤተ መቅደሱ እንደ ገና ገባ (ቁጥር 4) ፤ ከዚያም ሕዝቅኤል የእግዚአብሄር ክብር ወደ ሞላበት ቤተ መቅደስ በመነሳት ወደ ቤተ መቅደሱ ተወሰደ (ቁጥር 5) ፡፡
ማይክ ቤንቴት ከማቴዎስ 24 የእግዚአብሄር ክር ወደ ቤተ መቅደሱ ከመመለሱ በፊት መጀመሪያ ምን እንደሚሆን አስቀምጧል፡
- የኃይማኖት አሳቾች (ማቴ 24፡ 4-5) ፡፡
- ጦርነት እና የጦርነት ወሬዎች (ማቴ 24፡ 6-7) ፡፡
- ርኃብ/ድርቅ (ማቴ 24፡ 7) ፡፡
- ቸነፈር (ማቴ 24፡ 7) ፡፡
- የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል (ማቴ 24፡ 7) ፡፡
- በክርስቶስ ተከታዮች ላይ መከራ ይሆናል (ማቴ 24፡ 9-10) ፡፡
- ፍቅር ይቀዘቅዛል/ዓመፅ ይሆናል (ማቴ 24፡ 12) ፡፡
- የመንግስቱ ወንጌል ይሰበካል (ማቴ 24፡ 14) ፡፡
- ኢየሩሳሌም የተከበበች በመሆን የጥፋት እርኩሰት ይቆማል/ይዘጋጃል (ማቴ 24፡ 15, ሉቃ 21፡ 20) ፡፡
የሚካተቱት ሌሎች ምልክቶች፡ መከራው ህይወት ያለዉን ሰብዓዊ ፍጥረት ያስፈራራል (ማቴ 24፡ 15, ሉቃ 21፡ 20)፣ ምልክቶች በሰማይ ሲታዩ (ማቴ 24፡ 29) ኢየሱስ በመለከት ድምፅ ተመልሶ ይመጣል (ማቴ 24፡ 30-31, 1ቆሮ 15፡ 52, ራዕ 11፡ 15) ፡፡
በቁጥር 6 ራዕዩ ቀጠለ ሕዝቅኤል አሁንም አጠገቡ በቆመዉ “ ሰዉዬ “ በቀጥታ ለእርሱ የሚነገረዉን ሰማ ፤ ይህ ቤተ መቅደስ ለዘላለም በእስራኤላዊያንየሚኖርበት ስፍራ እንደ ሆነና ከዚህ በኋላም በጣዖት ስሜን አያረክሱም ያለዉ ተናጋሪዉ እግዚአብሄር ነበር (ቁጥር 7-8) (መዝ 132፡ 12) ፡፡ የእግዚአብሄር ምህረት እና ቸርነት/ይቅር ባይነት ከእነርሱ ጋር ለዘላለም እንዲኖር ፈቀደለት (ቁጥር 9) ፡፡
ሕዝቅኤል (43፡ 10-17)፡ በመቀጠልም እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ከኃጢዓታቸዉ የተነሳ እንዲያፍሩ ለሕዝቡ የዚህን ቤተ መቅደስ ልኬት/ስፋት እንዲገልፅላቸዉ አዘዘው (ቁጥር 10) ፡፡ ሕዝቅኤል የቤተ መቅደሱን ቅዱስነት የተራራዉ አናት እና በዙሪያዉ ያሉት ሁሉ በተለዬ ቅዱስ እንደሚሆኑ እንዲገልጥ ተነገረው (ቁጥር 11-12) ፡፡ ሁሉም ሕዝቅኤል ለምርኮኞቹ እንዲገልጥላቸው ተነግሮት የነበሩት ቀድሞ በቁጥር (13-18) ለእርሱ የተሰጠ ነበር (ሕዝቅኤል 40-42) ፡፡ ቁጥር 13 ስለሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያ መግለጫዎች ይጀምራል ፡፡
በአሁኑ ሰዓት የተራራዉ ቤተ መቅደስ በአይሁዶች፣ በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች በቅዱስነት ተይዟል ፡፡ በዚህ ጊዜ የሆነ ስፍራ ላይ እግዚአብሄር ለማደሪያዉ እስኪመለስ ድረስ ተራራዉን ያናዉጠዋል ፡፡ ብሉይ ኪዳን ከዘፍጥረት እንስቶ እስከ ሚልክያስ ድረስ ስለ መሲሁ መምጣት ያመለክታል ፤ አዲስ ኪዳን ከማቴዎስ እስከ ዮሐንስ ራዕይ መሲሁን በመግለጥ ሁለተኛ መምጣቱን ያመለክታል ፡፡ የሺዉ አመት ቤተ መቅደስ እነዚህን ሁለቱንም አለሞች እና በሆነ መጠን ያክል የአይሁዶችን እና የክርስቲያኖችን እምነት ያመጣል በአንድ ላይ ያመጣል ፤ በትክክል ያ ምን ማለት እንደሆነ ለማጠንጠን አስቸጋሪ ነው ፤ ያ ማለት ኢየሱስ በሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ዉስጥ ይሆናል በተመሳሳይም በዚያ መስዋዕት ይደረጋል ማለት ነው ፡፡ ይህ በእኛ ጊዜ ይሆናል !
ሕዝቅኤል (43፡ 18-27)፡ እነዚህ ጥቅሶች የሚቃጠለዉ መስዋዕት ምን መሆን እንዳለበት እና እንዴት እንደሚያቀርቡት ይገልፃሉ ፡፡ በእነዚህ መስዋዕቶች ጨዉን በመጠቀም የደብረ ዘይትን ተራራ በሚከፍለዉ በሸለቆዉ ዙሪያ የተዘጋጀ ስፍራ ይኖራል ፡፡ ቁጥር 25 መስዋዕቱ ለሰባት ቀን መቅረብ እንዳለበት ይጠይቃል ፡፡
መደምደሚያ
ቶም ኮንስታብል በሕዝ (44፡ 1-9) ቤተ መቅደሱን እንዴት እንደምትጠቀሙት እና በቁጥር (10-31) ካህናት ቤተ መቅደሱን እንዴት ይጠቀሙት እንደ ነበር ማየት እንጀምራለን ይላል ፡፡ ሕዝቅኤል በእነዚህ ምዕራፎች ያያቸዉ ሁሉም ነገሮች በሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ዉስጥ ይሆናሉ ፤ ከክርስቲያን በሚበልጥም እግዚአብሄር የሚመስለዉን መልክ ይመስላል ፡፡
Mike Bennett, “Discerning the Signs of the Times,” available at https://lifehopeandtruth.com/prophecy/end-times/discerning-signs-of-the-times/.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Ezekiel, p. 336; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.
ጥያቄዎች
-
በሕዝ (44፡ 8) እግዚአብሄር እነማን እየተናገረ ነበር (ዘኁ 3፡ 5-10) ? ኃላፊነቶቻቸዉ ምን ምን ነበሩ (ዘኁ 1፡ 50-53 ) ? ኃላፊነቶቻቸዉን ለምን ችላ አሉ ? (ነህምያ 13)
-
በሕዝ (44፡ 10-14) የእግዚአብሄር ምህረት ለሌዋዊያን እንዴት ነበር የታየው ? በዚህ እንዲጀምሩ ለማድረግ ምን ሆነ ?
-
በሕዝ (44፡ 15) ሳዶቅ ማን ነበር ? በመፅኀፍት ላይ ሌላ የት ስፍራ የተጠቀሰ ነው ለምንስ ? (2ሳሙ 8፡ 17, 1ዜና 12፡ 28)
-
በሕዝቅኤል (42-44) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 43:6–7a
“While the man was standing beside me, I heard someone speaking to me from the temple. He said to me: ‘Son of man, this is the place of My throne and the place for the soles of My feet, where I will dwell among the Israelites forever.’”
ሕዝቅኤል በራዕዩ የእግዚአብሔር ዙፋን የሚቀመጥበትንና በእስራኤላውያን መካከል ለዘላለም የእግሮቹ መረገጫ የሆነውን ቤተ መቅደስ አየ ፡፡ የእስራኤል ቤትም ከእንግዲህ ወድያ ስሙን አያረክሱም ነገር ግን ይልቁንም ሰሙን ከስሞች ሁሉ በላይ ለዘላለም ያመልኩታል ፡፡ ቤተ መቅደሱ በእግዚአብሔር ክብር ይሞላል ፤ ድምጹም እንደ ብዙ ውኆች ድምጽ ይተምማል ፣ ምድርም ክብሩን ታበራለች ፡፡
ምን ያህል ጊዜ ስለ ዘላለም ታስባላችሁ ? ሰውነታችሁ ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ቤተ መቅደስ እንደሆነና መንፈሱም በእናንተ ውስጥ እንደሚኖር አስታውሱ ፡፡ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋናን መስጠት ትችላላችሁ ደግሞም ለዘላለም ለእናንተ ስላዘጋጀው ነገር ሁሉም እንዲሁ ! እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ አማኝ ለዘላለም በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ትኖራላችሁ ምድርም በክብሩ ትሞላለች ፡፡ ስለ ዘላለማዊ ድህንነት እግዚአብሔርን አመስግኑ ፡፡ ስለ ዘላለማዊ ተስፋ ስጦታው እግዚአብሔርን አመስግኑ ፡፡ እግዚአብሔርን ስለ ክብሩ ብዛት በውበትም ስለተገለጠው ቅዱስነቱ አመስግኑት ፡፡ በዙሪያችሁ ስላለው ውብ ተፈጥሮ ፤ በሰዎች ህይወት ውስጥ ስላለው የእጁ ስራ ፣ ስለ ፍጥረቱ ደግሞም እንዲሁ ጸጋውንና ምህረቱን ስለሚያሳዩ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት ፡፡ ዛሬ በምስጋና ወደ መገኘቱ ግቡ ፡፡ በምስጋና ወደፊቱ ቅረቡ ፡፡ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ኃያሉ እግዚአብሔር ! ዛሬ ቅዱስ ስሙን አወድሱ !
“ በመቅደሱም ሆኖ የሚናገረኝን ሰማሁ ፥ በአጠገቤም ሰው ቆሞ ነበር ። እንዲህም አለኝ ፦ የሰው ልጅ ሆይ ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው ። “
- ሕዝቅኤል 43፡6-7
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 6:3 — “ አንዱም ለአንዱ ፦ ቅዱስ ፥ ቅዱስ ፥ ቅዱስ ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር ። “
ሕዝቅኤል 43:2–3 — “ እነሆም ፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ መንገድ መጣ ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተምም ነበር ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር ። ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንዳየሁት ራእይ ነበረ ፤ ራእዩም በኮበር ወንዝ እንዳየሁት ራእይ ነበረ ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 3:16 — “ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።