Major Prophets Ezekiel

Details That Give Hope

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 40-41 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 644 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዛሬ ሕዝቅኤል (40-41) ፅኁፋችን በሆነ ያክል በስልክ መፅኀፍ በኩል ከመስበክ ጋር ልክ እንደ መስበክ ነው ፡፡ በመጀመሪያ እይታ እነዚህ ጥቅሶች በቀጥታ ስለ ቤተ መቅደሱ ርዝመት እና ቁመት ስለሆኑ ተገቢ፣ ሊረዳ የሚችል እና ከዉስጢ ሊታይ የሚችል ነገር ለማግኘት አስቸጋሪ የሚሆን ይመስላል ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ በዚህ ጥያቄ ማስቀመጥ እፈልጋለሁ፡ በመፅኀፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ክስተት ዉስጥ መጓዝ የምትችሉ ከሆነ - ማየት፣ መስማት እና ነገሩን መልመድ ትችላላችሁ - ያ ክስተት ምን ይሆናል ? ልክ የኢያሪኮ ቅጥር መዉደቅን ስለመመልከት ወይም ኤልያስ በቀርሜልዎስ ተራራ ላይ በነቢያቶቹ ላይ ያደረገዉን ክስተት ማሰብ እንችላለን ፤ ወይም ደግሞ የመጨረሻዉን ስፍራ ወይም ክስተት ወደ መፅኀፍ ቅዱስ ታሪክ ዉስጥ መጓዝ የምትፈልጉበትን ተመልከቱ ፡፡ ከመለቀቁ በፊት ወይም በምርኮ ጊዜ አስፈሪ ልምምድን ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ዉስጥ እንደ ሆነዉ አይነት ክስተት ፡፡ የመፅኀፍት አቀማመጥ እና ትርጓሜአቸው መፅኀፉን ራሱን ለመረዳት ለእኛ በጣም ጠቃሚ ነው ፡፡ ዛሬ በምዕራፎቹ ዉስጥ ፅሁፉን ለመረዳት በአቀማመጡ ዙሪያ መረዳት አስፈላጊ ነው ፡፡

የአብርሃም በረከት ከነበረባት ምድር ጋር የሚገናኝ ነበር (ዘፍ 12፡ 1-3) ፤ አብርኃም ምድሪቱን በለቀቀ ጊዜ መጥፎ ነገር ሆነ ፡፡ በዮሴፍ ታሪክ በርኃቡ ጊዜ ቤተሰቦቹ ምድሪቱን ለቀቁ መጥፎ ነገርም ሆነ ፡፡ ላየዉ እፈልገዉ የነበረዉ ክስተት ሕዝቡ ፈርዖንን እና ግብፅን ትቶ ሲሄድ ነበር ፤ የሚያስደንቅም አንድ በአል ይኖራል ፡፡

በምድረበዳ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ማደር የሚችልበትን ስፍራ የማደሪያዉን ድንኳን ተከለ ፤ ይህ የዕብራዊያን ህይወት ማዕከል ነበር ፤ ስርዓት እና ቅደም ተከተል ነበረው ፡፡ ከአስራ ሁለቱ ነገዶች ሰዎስት ሰዎስቱ በድንኳኑ ማደሪያ በእያንዳንዱ ጎን የተቀመጡ ነበሩ ፤ በዉስጡም ታቦቱ፣ የገብስ እንጀራዉ፣ ቅዱስ ስፍራዉ እና የቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ ነበር ፡፡ ሰለሞንየመጀመሪያዉን ቤተ መቅደስ ገነባ/ሰራ፣ የታቦቱን ማደሪያ እና የሰለሞንን ቤተ መቅደስ ማሳያዎች በምታወዳድሩ ጊዜ እንዴት ይመሳሰሉ እንደ ነበር ታያላችሁ ፡፡ የሰለሞን ቤተ መቅደስ በባቢሎናዊያን ጠፍቶ ነበር ፤ ቤተ መቅደሱ በጣም ለአይሁዶች ህይወት መሰረት/ማዕከል ስለ ነበር በመፈራረሱ አይሁዶች በግዞት የቀራቸዉ ተስፋ አልነበራቸዉም ፤ ለእነርሱ የቀረላቸዉ ምንም ነገር ስላልነበር ተንከራተቱ ፡፡ አዲሱን ቤተ መቅደስ ለመገንባት ሕዝቅኤል ያቀረበዉ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ በታሪክ በዚህ ክስተት ላይ ነው ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (40፡ 1-4)፡ ሕዝቅኤል ቀጣዮን ራዕዩን እግዚአብሄር እነዚህን ትዕዛዞች በመናገር አዲሱን ቤተ መቅደስ እንዲያይ በወሰደዉ ጊዜ ካለዉ የተለዩ ቀኖች ጋር አገናኝቶታል/አስተሳስሮታል (ቁጥር 1) ፡፡ በጣም ዝርዝር የተሰጠው መልዕክቱም በጣም የታመነ ይሆናል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን በአንድ ረጅም ተራራ ላይ ስላስቀመጠው ወደታች በመመልከት የአዲሱን ቤተ መቅደስ ዝርዝር/በጥልቀት ማየት ይችላል (ቁጥር 2) ፤ ከላይ አንድ ከተማን ይመስላል ፡፡ ሕዝቅኤል መልኩ ንኃስ በሚመስል እና በእጁ የመለኪያ መሳሪያዎች በነበሩት አንድ ሰው ቅኝት ተሰጥቶት ነበር ፤ ሰዉዬውም ሕዝቅኤልን የቀረበ ትኩረትን በመስጠት በአይኖቹ እንዲያይ እና በጆሮቹ እንዲሰማ ከዚያም ለሕዝቡ ያየዉን ነገር ሪፖርት ማድረግ እንደሚችል ነገረው (ቁጥር 3-4) ፡፡

ሕዝቅኤል (40፡ 5 – 41፡ 26)፡ የሕዝቅኤል ቤተ መቅደስ መልክ (በድህረ ገፅ “ የሕዝቅኤል ቤተ መቅደስ “ ) የምታገኙ ከሆነ እና እንደ ሰማችሁት በመልኩ ላይ ስትመለከቱ በተሸለ የሚያስረዳ ነው ፡፡ ቅጥር የቤተ መቅደሱን ስፍራ ዙሪያዉን ከብቦታል (ቁጥር 5) ፤ ሰዉዬውም የምስራቁን በር ቅጥር እና ወለሉን ለካ (ቁጥር 6) ፡፡ የእግዚአብሄር እቅድ በሁሉም ዝርዝር ነገር በኃይለኞዉ ጥልቅ ነበር ፤ የሕዝቅኤልን ቤተ መቅደስ እና የሰለሞን ቤተ መቅደስን ተመሳሳይነት አስታዉሉ ፤ ቤተ መቅደሱ እንዴት ቅዱሱን እና ቅድስተ ቅዱሳን ስፍራን እንደያዘ ማየት ትችላላችሁ ፡፡ መሰዊያዉን ማየት ትችላላችሁ ፤ የታቦቱን ማደሪያ በገነቡ ጊዜ እግዚአብሄር እንዲሰሩ ከነገራቸዉ ጋር ይመሳሰላል ፡፡ ስለ ሕዝቅኤል ቤተ መቅደስ ለመመለስ አስቸጋሪዉ/ከባዱ ጥያቄ የት ነዉ ያለዉ ወይስ የት ነዉ የሚሰራዉ ? የሚለዉ ነው ፤ ይህ ቤተ መቅደስ በራዕይ ተስፋ እንደ ነበር የታዬ ሊሆን ይችላል ፤ ይህ ቤተ መቅደስ በዕዝራ ዘመን የተሰራ እና በኢየሱስ ጊዜ የነበረ የሔሮድስ ቤተ መቅደስ መልክ ሊሆን ይችላል ፡፡ ጉዳዩ ያ ከነበር ምርከኞቹን ያበረታታል ፤ በተጨማሪም የሔሮድስ ቤተ መቅደስ በኢየሱስ ሞት ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ ወደ ታች በተቀደደ ጊዜ የትንቢት ስፍራ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ እይታ ዉስጥ አንዳንድ ችግሮች አሉ ፤ ይህ ቤተ መቅደስ የሔሮድስ ቤተ መቅደስ እንደ ነበረው በመጠን ትልቅ እና በጥልቀት/በዝርዝር ግዙፍ ነው ፤ ስለሆነም ብዙዎች ለእኛም ጭምር ወደፊት የሚገነባ እንደሆነ የወደፊት እንደሆነ ያምናሉ ፤ ያ እንዴት ያግዘናል/ይረዳናል ?

ለኢየሱስ ተመልሶ መምጣት የሚቋቋመው የሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ከሆነ በዚያ ተስፋ አለ ፤ ይህ እንደ እግዚአብሄር ሰዎች በፊታችን ጨለማ/ክፉ ቀን ስላለ በእዉነት ሊያበረታታን ይችላል ፤ ነገር ግን ወደፊት የክርስቶስን ድል ማድረግ መመልከት እንችላለን ፡፡ ከዚህም የተነሳ በዚህ ቤተ መቅደስ እና በሚመጣው ነገር በሚናገረዉ ትንቢት ዉስጥ የሚያስደንቅ ተስፋ አለ ፡፡

በታቦቱ ማደሪያ እና በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ያየናቸዉ ሰዎስት የተለዩ ስፍራዎች አሉ፡

  • አደባባዩ፡ ከሁሉም ዉስጥ ትልቁ ስፍራ አደባባዩ ነበር ፡፡ የዉስጥ እና የዉጭ አደባባዮች ነበሩ በተጨማሪም የአሕዛብ፣ የሴቶች እና የወንዶች አደባባዮችም ነበሩ ፡፡ ሰዎች በአንድ ላይ የተገናኙ ስለነበሩ በአደባባዩ ላይ ህይወት እየተወሰደ ይወሰድ/ይገኝ ነበር ፡፡
  • መሰዊያው፡ ክርስቶስ ቀድሞ ለእኛ ስለሞተ ለምን መሰዊያ ያስፈልጋል ? በእርግጥ ተጨማሪ መስዋዕት የሚያስፈልግ ስለማይሆን ይህ በሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ዉስጥ መገኘቱ ሰዎች ከሚፈተኑበት ዋነኛዉ ምክንያት አንዱ ነው ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ለእኔ ቢሞትም እንኳን አሁንም ያለማቋረጥ ነገሮችን በመሰዊያዉ ላይ አስቀምጣለሁ/እጥላለሁ - እንከን የሌለበትን የእኔን ምርጡን ፡፡ በህይወታችሁ ሰላም የምትፈልጉ ከሆነ ሁል ጊዜ የእናንተን የመጀመሪያችሁን እና ምርጣችሁን ለኢየሱስ መስጠታችሁን ቀጥሉ ፡፡
  • የቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ፡ የእግዚአብሄር መገኛ ስፍራ እንደ ዙፋኑ ይታሰባል ፤ ሊቀ ካህኑ ብቻ በአመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ መግባት ይችላል ፤ ይህ ለእግዚአብሄር የተቀመጠ/የተዘጋጀ ነበር ፡፡ በህይወታችሁ የሆነ ነገር ወደ ተቀደሰ ስፍራ ገብቶ ካገኛችሁት የእግዚአብሄር እንዳልሆነ ታዉቁታላችሁ ፤ በዚያ መሆን ስለሌለበት ትጨነቃላችሁ ትበሳጫላችሁም ፡፡ በዚያ ስራችሁ፣ ዝናችሁን እና ገንዘባችሁ የእናንተ አይደለም ፡፡

በቅዱስተ ቅዱስ ስፍራ መብራት እና ህብስት አለ ፤ ክርስቶስ የአለም ብርኃን እና የህይወት እንጀራ እንደ ነበር ተናግሯል ፡፡ እነዚህ ሁለቱም በቤተ መቅደሱ እና በታቦቱ ማደሪያ ዉስጥ ለህይወቱ ምሳሌ በምሳሌነት በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ተቀምጠዉ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

የቤተ ክርስቲያንን መልክ ቤተ መቅደስ በማድረግ መመልከት ጀምረናል፣ እኛ ቤተ መቅደሶቹ ስለሆንን በእኛ ዉስጥ ይኖራል ፤ በአሁኑ ሰዓት በአለም ላይ ቤተ ክርስቲያን የእርሱ መገኘት ናት ፡፡ ሰዎች በአደባባዩ ላይ በመሰብሰብ ነገሮችን በመሰዊያዉ ላይ ይጥላሉ ፤ ይህ በተስፋ ከተመላለስን ተስፋ የሚሰጠን ታሪክ ነው ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት ከሕዝቦቹ አጠገብ ነበር ከዚያም ዛሬ ከእኛ ጋር ነው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በሕዝቅኤል 40 ሕዝቅኤል ስለ አዲሱ ቤተ መቅደስ ራዕይ የነበረዉ መቼ ነበር ? እግዚአብሄር የትስ ወሰደው?
  2. እግዚአብሄር እነዚህን ራዕዮች ለሕዝቅኤል በሰጠው ጊዜ አይሁዶች በባቢሎን ምርኮ ለምን ያክል ጊዜ ነበሩ ?
  3. በእነዚህ ራዕዮች በኩል እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ለመናገር የፋሲካን የመጀመሪያዉን ያን የተለየዉን ቀን ለምን እንደመረጠ ስለ አስፈላጊነቱ ምን ታስባላችሁ ? (ዘጸ 12፡ 2)
  4. በሕዝቅኤል 41 በተጠቀሰዉ ቤተ መቅደስ ከዉስጠኛዉ ክፍል እና በ 1ነገስት (6-7) በሰለሞን ቤተ መቅደስ አንዳንድ ልዩነቶቹ ምንድን ናቸው ? ምን ምን ነገሮችስ ተመሳሳይ ናቸው ?
  5. በሕዝቅኤል (40-41) የተጠቀሰ ታቦት እና መጋረጃ የለም ፤ እነዚህ ሁለት ነገሮች በሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ዉስጥ ለምን የሚያስፈልጉ አልሆኑም ? (ሕዝ 41፡ 4)
  6. በሕዝቅኤል (40-41) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 40:4

“He spoke to me: ‘Son of man, look with your eyes, listen with your ears, and pay attention to everything I am going to show you, for you have been brought here so that I might show it to you. Report everything you see to the house of Israel.’”

እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ስለሚሰራው አዲስ ቤተ መቅደስ ለሕዝቅኤል ራዕይን ሰጠው ፡፡ ሕዝቅኤልንም በከተማዋ እንድያዞረው ፤ ቤተ መቅደሱን ፣ መሰውያውን ፣ አደባባዩን ፣ በሮቹንና እያንዳንዱን ዝርዝር ነገር እንድያሳየው እግዚአብሔር ሰውን አዘጋጀ ፡፡ ሰውየውም ሕዝቅኤልን “ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ ተመርተሃልና በዓይንህ እይ በጆሮህም ስማ በማሳይህም ሁሉ ላይ ልብህን አድርግ ፡፡ “ እግዚአብሔርም ለሕዝቅኤል ብዙ ዝርዝር ነገርን አሳየው ፡፡ ሕዝቅኤል አይኑን ለአንድ ጊዜ ቢጨፍን ኖሮ ፣ ይጠፉበት ነበር ፡፡ እግዚአብሔርም እርሱ ካዘጋጀው ወሳኝ ነገሮች ውስጥ ሕዝቅኤል አንዷንም ነገር እንዳይስት ፈልጎ ነበር ፡፡

እግዚአብሔር ለአንተ በልዩነት ይናገርሃል ፡፡ ትጠይቅ ይሆናል……… ያ የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ነበርን ? ወይም እንዲህ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል……ያ ምንድን ነበር ? ጠላት ተስፋ ሊያስቆርጥህ ፣ በግራ መጋባትና በፍርኃት ውስጥ ሊያስቀምጥህ ደግሞም ደስታህን ፣ ጊዜህንና ኃይልህን ሊወስድብህ ይፈልጋል ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር እውነትን ፣ ተስፋንና ከልብ የሆነ ልዩ ምስክርነትን ይናገራል ፡፡ እርሱ ያውቅሃል ደግሞም ያለህበትን ሁኔታም እንዲሁ ፡፡ እርሱ ስትቀመጥና ስትተኛም ያውቃል ፡፡ እያንዳንዷ እርምጃ የጸናችው በእግዚአብሔር ነው ምክንያቱም እርሱ በመንገድህ ደስ ስለሚሰኝ ፡፡ ዛሬ አይኖችህን ክፈት ፣ በጆሮችህም አድምጥ እናም ለእያንዳንዷ ነገር ትኩረት አድርግ ፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ ሊናገርህ ይፈልጋል ፡፡ እርሱን ስትናፍቅ አብዝተህ በሌላ ነገር አትጠመድ ፡፡

“ ሰውዬውም ፦ የሰው ልጅ ሆይ ፥ ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ ተመርተሃልና በዓይንህ እይ በጆሮህም ስማ በማሳይህም ሁሉ ላይ ልብህን አድርግ ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር አለኝ ። “

  • ሕዝቅኤል 40፡4

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 37:23 — “ የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል ፥ መንገዱንም ይወድዳል ። “

መዝሙር 95:7 — “ እርሱ አምላካችን ነውና ፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና ። “

መዝሙር 139:13–17 — “ አቤቱ ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና ፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ፤ ሥራህ ድንቅ ነው ፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች ። እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ። ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ ። አቤቱ ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ ! “