God Invades Israel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 39 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሕዝቅኤል ያለፈዉ ምዕራፍ በአንድ ላይ ስለመጡት እና እንደ ታላቅ ሰራዊት ስለ ተነሱት በሰፊዉ ሸለቆ ዉስጥ ስላሉት አጥንቶች መግለጫን ተናግሯል ፡፡ ሕዝቅኤል ወደ ንፋሱ ትንቢትን ተናገረ ሰራዊቱም ወደ ህይወት መጣ ፡፡ ራዕይ 20 በመጨረሻዉ ዘመን መግለጫ ከሕዝቅኤል (38-39) ጋር ሰምና ወርቅ ነው ፡፡ የሕዝቅኤልን የመጨረሻዉን ጊዜ ነገሮች ለመረዳት አስቸጋሪ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ማንኛዉንም የመጨረሻዉ ጊዜ ጥናቶችን እና መፅኀፍትን ማስወገድን ይመርጣሉ ፡፡ አስፈላጊነቱ ለሁሉም አማኞች መፅኀፍት የመጨረሻዉን ዘመን እንዲገልፅ መፍቀድ ነው ፡፡
በሕዝቅኤል (38-39) ከወደፊት ጊዜ ጋር እና በራዕይ ካሉፅሁፎች ጋር የሚገናኙ አንዳንድ አስገራሚ ፍሬ ነገሮች አሉ ፡፡ እነዚህ ምዕራፎች በመጨረሻዉ ዘመን ምን እንደሚጠበቅ መግለጫን ይሰጣሉ ፤ ስለ ማንኛዉም የመጨረሻዉ ዘመን ሁኔታ ጥናቶች ቸልተኝነቶች አሉ ፡፡ ሕዝቅኤል (38-39) ስለ መጨረሱ ዘመን ክስተቶች እይታዎችን ያቀርባሉ ፡፡
አንዳንዶች የሐዋሪያት ስራ መፅኀፍ ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ፕላን ከነበረች የራዕይ መፅኀፍት ደግሞ በመጨረሻዉ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ምን ልትመስል እንደምትችል መሪ ፕላን እንደሆነ ያመለክታሉ ፡፡ በራዕይ 20 አዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳንን ያረጋግጣል ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (38፡ 1-3)፡ በቁጥር 1 ሕዝቅኤል ከማንጉግ ስፍራ ወደ ነበረዉ ሰዉ ወደ ጎግ ፊቱን እንዲያዞር ተነገረው ፡፡ ሁለቱ የማንጎግ ሁለት ዋና ከተማዎች ሞሳሕና ቶቤል ናቸው ፤ ማንጎግ በመልክዓምድር አቀማመጡ በትክክል የት ስፍራ እንደነበር ብዙ ቴዎሪዎች አሉ ፤ ማጎግ የት ስፍራ ይገኝ እንደ ነበር በመፅሃፍት ላይ እንድናዉቅ ብዙ ማስረጃዎች የሉም ፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ከመቶ አመታቶች በፊት ናፖሊኖ ቦነፓርት ጦርነትን ለመዋጋት ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ህብረትን አድርጎ በነበር ጊዜ ከማጎግ ጎግ እንደሆነ (እንደ አንድ ምሳሌ) ይታመን ነበር ፡፡
ሕዝቅኤል (38፡ 4-6)፡ በቁጥር 4 እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን የሁሉም ጦርነት መጨረሻ ስለሚሆነዉ አንድ ጦርነት ነገረው ፡፡ እግዚአብሄር በዙሪያዉ የሚመልሰው በሙሉ የጦር እቃ፣ በሰይፍ እና በፈረሶች የታጠቀ ታላቅ ሰራዊት ይኖራል ፡፡ የጎግ ሰራዊት እና የብዙ ሕዝቦች ሰራዊት ፋሪስን፣ ኩሽን እና ፉጥን በማካተት በአንድ ሰራዊት ላይ ብቻ በአንድ ላይ የተሰበሰቡ ነበሩ ፤ እነዚህ ሁሉም ሕዝቦች የጎግ አጋር ነበሩ ፡፡
ሕዝቅኤል (38፡ 7-23)፡ ቁጥር 7 እግዚአብሄር እነዚህን ሰራዊቶች እንዲዘጋጁና እንዲጠብቁ እንዳዘዛቸዉ ይገልፃል ፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ በመጨረሻም ሰራዊቶቹ ይሰበሰባሉ ፤ በመጨረሻዉም አመት ከጦርነት ወደ ታደሰችዉ ምድር ይገባሉ ፤ ከሰሜን እስራኤልን ያጠቃሉ ፡፡ እስራኤል በተራሮች ላይ በእረፍት ትገኛለች - ሕዝቦቿ ሙሉ በሙሉ በመታደስ አሁን ሕዝቦቹ በሰላም ይኖሩ ነበር ፤ ያለ ቅጥር እና በሮች እየኖሩ ነበር ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር ስለ ነበር በጎግ አለቃ እና ሰራዊቱ ላይ ጥፋትን ያመጣበታል (ሕዝቅኤል 39) ፡፡
እነዚህ ሰራዊቶች የእስራኤልን ምድር ለማጥፋት እና ለመዝረፍ የሚወጡ ነበሩ ፤ በደህና ሲኖሩ ሳሉ እስራኤልን በመክበብ እስራኤልን ለማጥቃት ይዘጋጃሉ ፡፡ ይህ ከባድ የጨለማ ዳመና በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሄር ቀን የሆነ ጨለማ ቀን ነበር ፡፡ እስራኤል በሰላም ያለ ድንበር፣ ያለ ቅጥር እና ያለ በሮች እየኖረች ነበር ፡፡
እግዚአብሄር ጎግን እና የኃያላንን መንጋ በእስራኤል ላይ እያመጣ ስለ ነበር ሕዝቦቹ/አሕዛቦቹ መላዉ አለም ራሱን በሚገልጥ ጊዜ እርሱን ያውቁታል ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሄር በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉስ ነበር ፤ ጎግ እና ሰራዊቱ በበቀል ልብ እና ትምክህት በእስራኤል ላይ መጥተዉ ነበር ፡፡
ይህ የእግዚአብሄር ተመሳሳይ መንፈስ በራዕይ 20 እና በሌሎች በብሉይ ኪዳን መፅኀፍት ላይ የተገኘ ነበር ፤ ግንኙነት ያላቸዉ ጥቅሶች የሚያካትቷቸው፡ ሌዋታን ተገኝቶበት የነበረው እና እግዚአብሄር ዘንዶዉን የሚያርድበት/የሚገድልበት ኢሳ (27፡ 1)፣ በሚክ (5፡ 5) እግዚአብሄር ሰላማቸዉ በሚሆንበት አሶራዊያን በሚገኙበት፣ የግብፅ ንጉስ ፈርዖን ሁለቱ ክንዶቾ ተሰብረዉ ስለ ነበር ሰይፉ ከእጁ የሚወድቅበት ሕዝ (30፡ 20-26)፣ ስለ ጢሮስ ንጉስ (ሕዝ 28፡ 12-15) እና እንደ ጨቋኝ የባቢሎን ንጉስ ፀጥ ያለበት እና ደካማ በሆነበት ጊዜ (ኢሳ 14፡ 3-12) ፤ ተመሳሳይ የሆነዉ የእግዚአብሄር መንፈስ በእነዚህ በተለያዩ ጥቅሶች ዉስጥ የታወቀ ነበር ፡፡ እነዚህ ጠላቶች እስራኤልን ለመግደል፣ ለመስረቅ እና ለማጥፋት የመጡ ነበሩ ፤ በመጨረሻም ጦርነቶቹ ከተከናወኑ በኋላ ለእስራኤል ሰላም ይሆናል ፡፡
ራዕ (19፡ 17-21) እና (ሕዝ 39፡ 17-20) እንደ በላይ አምላክ ተገልፆ እንደ ነበረዉ በትክክል ተመሳሳይ ስለሆነ ሁኔታ ይገልፃሉ ፤ ተመሳሳይ ቋንቋን በመጠቀ ቃል በቃል በእነዚህ በሁለቱም ፁሁፎች ተመሳሳይነት አለ ፡፡
ራዕይ 20 ከኢየሱስ ተመልሶ መምጣት በኋላ ሐሰተኛዉ ነቢይ እና አዉሬዉ በእስር እንደሚቀመጥ እና የቀረዉም ሰራዊት በሰይፍ እንደሚወድቁ ያረጋግጣል ፡፡ ከዚያ በኋላ ሰይጣን ሕዝቦችን አያስትም ፡፡
መደምደሚያ
በራዕይ 20 የሙታን ትንሳኤ የተጠቀሰ ነው ፡፡ ዮሐ (14፡ 3) ክርስቶስ ለእኛ ስፍራን ሊያዘጋጅልን እንደሄደ ይናገራል ፡፡ ክርስቶስ ለአሕዛቦች እና ለአይሁዶች እያወራ ነበር ፡፡ ማቴ (24፡ 30-31) ክርስቶስ በታላቅ ክብር እና ኃይል ይገለጣል ይላል ፤ በእግዚአብሄር ላይ እንደገፋለን ወይም ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ የምንነሳ እንሆናለን ፡፡
በዚህ አለም ችግር ይኖረናል ነገር ግን ልብን እንገዛለን ! ክርስቶስ አለምን አሸንፎታል (ዮሐ 16፡ 33) ፡፡ በሕይወት ዘመኑ መጨረሻ አካባቢ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ ክርስቶስን እና የትንሳኤ ኃይል እና በመከራዉ ለመምሰል እንደሚፈልግ ተናገረ (ፊል 3፡ 7-11) ፤ ፊል (3፡ 18-21) ክርስቶስ አለምን እንዳሸነፈ ያረጋግጥልናል ፡፡ ዜግነታችን በሰማይ ነው ፤ የክብሩን አካል ወደ መምሰል እንቀየራለን ፤ የክርስቶስ ተስፋ ያላቸዉ ይህ ሁሉ አላቸው ፡፡ የክርስቶስን መምጣት ስንጠባበቅ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው ፡፡
ጥያቄዎች
-
የእስራኤልን ሕዝብ ማጥቃት ለመሞከር ጎግን ወደ ምድሪቱ ማን ያመጣዋል ? ከዚያስ ምን ይሆናል ?
-
ለእግዚአብሄር ሕዝብ ለእስራኤል እና ከጎግ ማጥቃቱ ለሆኑት ሕዝቦች ዉጤቱ ምን ነበር ? (ሕዝ 39፡ 7, 21, 28-29)
-
ምድሪቱን ለማንፃት የእስራኤል ቤት ሰባት ወር ምን እያደረገ ያሳልፋል ? ይህ ለምን አደረጉ ?
-
በሕዝ (39፡ 14-16) በመንፃጽ ላይ ማብራሪያ ለምን ተቀመጠ ? (ዘሌ 11፡ 45)
-
ሕዝ (39፡ 21-29) ለእግዚአብሄር የእስራኤልን መታደስ ይናገራል ፤ የዚህ ትንቢት መፈፀም ምንድን ነው ? (ዘካ 12፡ 10 – 13፡ 9, ሮሜ 11፡ 25-27)
-
በሕዝቅኤል 39 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 39:21–22
“I will display My glory among the nations, and all the nations will see the judgment I have executed and the hand I have laid on them. From that day forward the house of Israel will know that I am Yahweh their God.”
ሕዝቅኤል በትንቢት እግዚአብሔር በጎግና በምድሩ በማንጎግ ላይ መጨረሻን እንደሚያደርግ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔር ከሚወደው ህዝብ ከእስራኤል ጎን ይቆማል ፣ በእስራኤል ጠላቶችም ላይ ጥፋትን ያመጣል ፡፡ እናም ከዚያ እግዚአብሔር እስራኤልን መልሶ በማቆምና ለእስራኤል ርህራሄን በማሳየት በህዝቦች ሁሉ መካከል ክብሩን ይገልጣል ፡፡ እስራኤላውያንም ያህዌ እርሱ አምላካቸው እንደነበር ያውቃሉ ፣ እርሱም ከእነርሱ ፊቱን አይሰውርም ፡፡ መንፈሱንም በእስራኤላውያን ሁሉ ላይ ያፈሳል ፡፡
ምናልባት ዙሪያችሁን ሁሉ በጠላት እንደተከበባችሁና የእናንተ ዓለም እንደወደቀች ሊሰማችሁ ይችላል ፡፡ ሰዎች በእናንተ ላይ ይነሳሉ ፡፡ ንግዳችሁ ይከስራል ፡፡ የጤና ምርመራ ውጤታችሁ ግራ ያጋባችኋል እናም ፍርኃት ይፈጠርባቿኋል ፡፡ የተመረጣችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ ይህንን አስታውሱ ፣ ጌታ ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ በመካከላችሁ ይቆማል ፡፡ እርሱ ጠላቶቻችሁን ያያል ፡፡ እርሱ የጤና ምርመራ ውጤቱን ያያል ፡፡ እርሱ ሁኔታውን ያውቃል ፡፡ እርሱ ይጠብቃችኋል ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋል ፡፡ ዛሬ እርሱ መሸሸጊያችሁና ሰላም ያለበት መረፊያችሁ ነው ፡፡ እርሱ ለእናንተ ባለው ታላቅ ርህራሄ ውስጥ መደበቅ ትችላላችሁ ፡፡ እርሱ ይቀድምላችኋል ፣ እናንተም አምላካችሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ ፡፡ እርሱ ለሚወዱትና እርሱን ለሚሹት ምርኮን ይመልሳል ፡፡ በእናንተ ላይ የፍቅር መንፈሱን በማፍሰስ ለሁሉም ክብሩን ይገልጣል ፡፡
“ ክብሬንም በአሕዛብ መካከል አኖራለሁ አሕዛብም ሁሉ ያደርግሁትን ፍርዴን ፥ በላያቸውም ያኖርኋትን እጄን ያያሉ ። ከእንግዲህም ወዲያ የእስራኤል ቤት እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ ። “
- ሕዝቅኤል 39፡21-22
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 5:11 — “ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ ። “
መዝሙር 89:18 — “ ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ከንጉሣችንም ከእስራኤል ቅዱስ ነውና ። “
ሕዝቅኤል 39:28–29 — “ እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና ፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ ፤ በዚያም ከእነርሱ አንድ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ አልተውም ፥ ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልሸሽግም ፤ መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።