The Valley Of Dry Bones
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 37-38 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምዕራፍ 37 ከሕዝቅኤል መፅኀፍ ዉስጥ በጣም የተለመደዉ እና ታዋቂ የሆነ ምዕራፍ ነው ነገር ግን ጥቂት ግለሰቦች ብቻ ምን ማለት እንደ ሆነ ያዉቃሉ ፤ ግምት/እሳቤው ለእኛ አተገባበር እንደሌለዉ ነው ፤ ስለዚህ ዝንባሌዉ የሕዝቅኤልን መፅሀፍት ለማንበብ አይሆንም ፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም መፅሀፍት ወደ ኢየሱስ ለማመልከት በማዘጋጀት ይረዱናል ፡፡
በሕዝቅኤል 36 ሕዝቅኤል ለተራሮቹ ተናገረ ፤ በመጀመሪያ ስለ ምድሪቱ መታደስ ተናገረ ፤ ሁለተኛው ሕዝቅኤል 36 ስለ ልብ መታደስ ነው ፡፡ ሕዝቅኤል በቀጥታ በግዞት ለነበሩት ተናገረ ፤ የእስራኤልን ሰዎችየሆነ ቀን እንደሚለቀቁ እና በመጨረሻም ህይወት ወደ እነርሱ ተመልሶ እንደሚመጣ ነገራቸው ፡፡ መልዕክቱ በተለዬ ለእነርሱ ነበር ፤ ሕዝቅኤል ዛሬ ለአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን እያወራ አልነበረም ፤ መልዕክቱ በሕዝቅኤል ዘመን ጊዜ በምርኮ ለነበሩት ነበር ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል 37፡ ሕዝቅኤል በደረቁ አጥንቶች ወደተሞላ ሸለቆ መካከል ላይ ተወሰደ ፤ ሕዝቅኤል የዚህን ሸለቆ መልክ እና በአጥንቶቹ ዙሪያ ሁሉንም እንዴት መርቶ እንደ ነበር ይስላል ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር (1-14) “ ሕዝቦቹ እንደ ገና የተወለዱ “ ስለሚሆኑ እንደሆኑ ይናገራል ፤ እንደ ገና ሕዝቅኤል በቀጥታ የእስራኤልን ሕዝቦች እያወራ ነበር ፡፡
እንደ ማክአርቱር አገላለፅ “ ይህ ቋንቋ የሞቱት ሕዝቦች ህይወት አልባነትን፣ መበታተንን እና እንደ ደረቀ ዛፍ መንጣታቸዉን ያሳያል (ሕዝ 17፡ 24) ፤ እግዚአብሄር ብቻ ህይወት ሊሰጣቸዉ የሚችሉትን የሞቱትን ሕዝቦች ያሳያል ፡፡ አብዛኞቹ የደረቁት አጥንቶች (ቁጥር 2) በግልፅ በመበታተናቸዉ የሞቱትን እና ሀገራዊ ትንሳኤ የሚፈልጉትን ትንሳኤን የሚጠብቁትን የእስራኤልን ሕዝቦች ያሳያሉ ፤ ሕዝቡ ስለ ግለሰብ ትንሳኤ ያዉቃሉ ከዚያ ዉጪ ትንቢቱ ትርጉም አልነበረዉም (1ነገስት 17, 2ነገስት 4, 13፡ 21, ኢሳ 25፡ 8, 26፡ 19, ዳን 12፡ 2, ሆሴ 13፡ 14) “ ፡፡ እግዚአብሄር ብቻ በሸለቆ ላሉት የደረቁ አጥንቶች ህይወት መስጠት ይችላል ፡፡ መልኩ/ስዕሉ እግዚአብሄር ብቻ ህይወቱን ሊያድስ እንደሚችለዉ እንደ ሞተ እንጨት ነበር ፡፡
በቁጥር (4-8) ሕዝቅኤል በደረቁት አጥንቶች ላይ እንዲተነብይባቸው ተነገረው ፤ ሕዝቅኤል ለደረቁት አጥንቶች “ የእግዚአብሄርን ቃል ስሙ ! “ አላቸው ፤ ሕዝቅኤል ያለምንም ማመንታት የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለመከተል መንፈስ ቅዱስን ለመስማት በጣም የተዘጋጀ ነበር ፡፡ ምሳ (18፡ 21) ህይወት እና ሞት በአንደበት ኃይል እንደሆኑ ይናገራል ፤ ዮሐ (6፡ 63) ህይወት ስለሚሰጥ መንፈስ ማጣቀሻ ነው ፡፡ ሕዝቅኤል በእግዚአብሄር መንፈስ የተሞላ ነበር ፤ መንፈስ ህይወትን የሚሰጥ እንጂ ስጋ አይደለም ፡፡
ሕዝቅኤል ምንም ነገር ቢናገር ወደ ፍሬ እንደሚመጣ ያምናል ፤ በዚያ መንፈስ/ተስፋም የእግዚአብሄርን ቃል ተናገረ ፡፡ ምሳ (10፡ 11) የፃድቃን አንደበት ቃልን በማምጣት ህይወትን እንደሚያመጣ ይጠቅሳል ፤ የፃድቅ ቃል ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር ያመለክታል ፡፡
ሕዝቅኤል (37፡ 7-8)፡ ሕዝቅኤል እየተናገረ በነበረበት ጊዜ የአጥንቶቹ ሁኔታ ወደ ህይወት መጥቶ ነበር ፤ አጥንቶቹ አጥንት በአጥንት በአንድ ላይ መጡ ፤ ሰዎችን ሰርተዉ ነበር ነገር ግን በእነርሱ ዉስጥ እስትንፋስ አልነበረም ፡፡
ሕዝቅኤል (37፡ 9-10)፡ በቁጥር 9 ላይ ሕዝቅኤል ከአራቱም ለሚመጡት ነፋሳት ለእስትንፋስ ህይወት የሌላቸዉ አካላት ወደ ህይወት እንዲመጡ ትንቢት እንዲናገርባቸዉ ተነገረው ፡፡ ሕዝቅኤል መጀመሪያ ከአጥንቶቹ ጋር አወራ በመቀጠል ደግሞ ከእስትንፋስ ጋር አወራ ፡፡ እየተመለከተ እንዳለ አጥንቶቹ አካል ሆኑ ፤ አካሎቹም እስትንፋስ የተሰጣቸዉ ነበሩ ታላቅ ሰራዊትም ወደ ህይወት መጣ ፡፡
ሕዝቅኤል (37፡ 11-14)፡ ቁጥር 11 ሰራዊቱን ከመላዉ የእስራኤል ቤት ጋር ያወዳድራል ፤ በሕዝቅኤል በኩል እግዚአብሄር የእስራኤልን ሕዝብ በምዕራፍ 36 ትንቢት ተነግሮ እንደ ነበረው ወደ እስራኤል ምድር እንደሚመራቸዉ ነገራቸው ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር አዋጅ ነበር ፤ ይህ መልዕክት ለእስራኤል ሕዝብ ነበር ነገር ግን ለአሁን ሁኔታችንም የአተገባበር ሀሳብ አለው ፡፡
ሕዝቅኤል (37፡ 15-23)፡ በቁጥር 16 ሕዝቅኤል በበትር ላይ ፅፏል ፤ አንዷ በትር እስራኤልን ስትወክል ሌለኛዉ በትር ደግሞ ይሁዳን ይወክላል ፡፡ ከዚያም በትሮቹ በሕዝቅኤል እጅ ወደ አንድ ተደረጉ ፤ ይህ የይሁዳ እና የእስራኤል መንግስት ተመልሰዉ በአንድ ላይ እንደሚመጡ ያመለክታል ፡፡ መንግስቶቹ ከሰለሞን ዘመን በኋላ ለ390 አመታት ያክል የተከፋፈሉ ነበሩ ፤ እግዚአብሄር ተበታትነዉ የነበሩትን ሕዝቦች ስለሚሰበስባቸው ሁለት ሕዝቦች አይሆኑም ፤ አንድ ሕዝብ ይሆናሉ አንድም ንጉስ ይኖራቸዋል ( ቁጥር 21-22) ፡፡ የነገስታት ንጉሱን ኢየሱስን እየጠበቁ ነበር ፤ ማቴዎስ ስለ ኢየሱስ በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉስ ስለ መሆን ፅፏል ፡፡
ሕዝቅኤል (37፡ 24-28)፡ ቁጥር 25 ሕዝቡ ለያዕቆብ ተሰጥታ በነበረችዉ ምድር ላይ እንደሚኖሩ ያናገራል ፤ ልጆቻቸዉ እና የልጅ ልጆቻቸው በምድሪቱ ላይ ይኖራሉ ፤ የእግዚአብሄር አገልጋይ አዲሱ ዳዊት መሲሁ ለዘላለም ልዑላቸዉ ለመሆን ይመጣል ፡፡
የሰላም ኪዳን ተስፋ ተገብቶ ነበር ፤ እግዚአብሄር አምላካቸዉ ይሆናል እነርሱም የእግዚአብሄር ሕዝቦች ይሆናሉ ፡፡ ቤተ መቅደሱም ይመሰረታል ፡፡ አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሄር እስራኤልን ቀድሷት እንደ ነበር ያውቃሉ ፡፡
የሰላሙ ኪዳን የታደሰ ነበር ፤ ኤር (16፡ 5) እግዚአብሄር ሰላሙን ከሕዝቡ ላይ አስወግዶ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ በኢሳይያስ 9 ሕዝቡ የሰላም አለቃ እንዲመጣ እንዲፀልዩ ተነግሯቸዋል ፤ ከመዝሙር አብዛኞቹም ሕዝቡን ለኢየሩሳሌም ሰላም እንዲፀለይ ያዝዟቸዋል ፡፡ ከዚህ ዉስጥ ማንኛዉም ሊከናወን የሚችልበት እና የሰላም ኪዳን እንደ ገና ሊመሰረትበት የሚችለዉ ብቸኛዉ መንገድ በራሱ በሰላም ንጉስ በንጉሱ ኢየሱስ ብቻ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ተወስዶ የነበረዉን ሰላም መመለስ/ማደስ የሚችል እርሱ ብቻ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ኢየሱስ በእግዚአብሄር መንፈስ በኩል ህይወትን ሊሰጠን ችሏል ፤ በደረቁ አጥንቶች የተሞላዉን ሸለቆ ያየነዉም ያንን ነው ፤ በሁለቱ በትሮች አንድነት የምናየዉ ያንን ነው ፤ የተከፋፈሉት መንግስታት በአንድ ላይ ሲመጡየምናየዉ ያንን ነው ፡፡ አንድነት በነበረ ጊዜ እግዚአብሄር የዚህ ሁሉ አካል እንደ ነበር ሕዝቡ ያውቅ ነበር ፡፡ ኢየሱስ በመንፈስ አንድ እንድንሆን ይፈልጋል ፤ ስለ እስራኤል አንድ መሆን አወራ ነገር ግን የክርስቶስ አካል አንድ እንድትሆን ይፈልጋል ፡፡
በመፅሀፍ ላይ ይህ መግለጫ ተስፋን ይሰጣል ፡፡ የሚከተሉት ምዕራፎች ምንም እንኳን ያንን ሰላም ከማግኘት የተከለከሉ እንዲሆኑ የሚፈልግ የእስራኤል ጠላት ጎግ መግለጫ የነበረ ቢሆንም የሰላም መልዕክት አላቸው ፡፡ በመጨረሻም ያህዌ በመምጣት በእግዚአብሄር ሕዝቦች ላይ በተነሱት ላይ ፍርዱን ያመጣል ፡፡
በሰላም አለቃዉ ላይ እምነት በሚኖራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ምንም ነገር ቢነሳ አንድ ነገር የተረጋገጠ ነው በፍፁም አይተዋችሁም ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 230.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 711.
ጥያቄዎች
-
በሕዝ (37፡ 1-14) በደረቆ አጥንቶች የተሞላዉ ሸለቆ ራዕይ በክርስቶስ ወደ አዲስ ህይወት ስለሚመጣ የማያምን ሰዉ ምሳሌ ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ?
-
በሕዝ (37፡ 25-28) ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር “ ለዘላለም “ ይላል ፤ በዚያ ትዉልድ ለዘላለም ይኖራል፣ ቤተ መቅደሱም በዚያ ለዘላለም ይሆናል ፡፡ ይህ አሁንም እዉነት ሊሆን እንደሚችል ታምናላችሁ ? ትዉልዱ እና ቤተ መቅደሱ አሁንም በዚያ እንደሆነ ታስባላችሁ ? ለምን በዚያ ታምናላችሁ ?
-
በሕዝቅኤል 38 እግዚአብሄር ጎግን እስራኤልን ባጠቃ ጊዜ ሰራዊቱ እንደሚጠፋ ነገረው ፤ ስለዚህ ዉጤቱ የጠፉ እንደሚሆኑ እያወቁ ለምን በከበባቸዉ ይቀጥላሉ ? የእግዚአብሄርን ቃል አያምኑም ? ልክ እንደ ጎግ ወደፊት ምን እንደሚሆን እያወቃችሁ ነገር ግን ምን ይሁን ነገሩን ማድረግ በመምረጥ አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
-
በኤርምያስ (37-38) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 37:3–5
“Then He said to me, ‘Son of man, can these bones live?’ I replied, ‘Lord GOD, only You know.’ He said to me, ‘Prophesy concerning these bones and say to them: Dry bones, hear the word of the LORD! This is what the Lord GOD says to these bones: I will cause breath to enter you, and you will live.’”
የእግዚአብሔር እጅ በሕዝቅኤል ላይ ሆነች መንፈሱም የደረቁ አጥንቶች ወዳሉበትም ሸለቆ መራው ፡፡ እግዚአብሔርም ሕዝቅኤልን በደረቁት አጥንቶች ላይ ትንቢትን እንድናገር አዘዘው ፡-እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ !......ትንፋሽን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ ! “ ሕዝቅኤልም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ የደረቁት አጥንቶችም ሕያው ሆኑ ፡፡
እንደ አማኝ ፣ ኢየሱስ ህይወትን ይሰጣችኋል ፡፡ እርሱ በእናንተ ውስጥ ይኖራል ፡፡ ፈጽሞ እንደሚመልሳችሁ እንደሚያቆማችሁ ይናገራል ፡፡ ሕዝቅኤል የእግዚአብሔርን የተለየ ትዕዛዝ በመከተል ፣ በአጥንቶቹ ላይ ህይወትን ተናገረ አጥንቶቹም ሕያው ሆኑ ፡፡ ዛሬ በዙሪያችሁ ስላሉ ህይወትን ማግኘት ስለሚገባቸው ሰዎችና ሁኔታዎች ስታስቡ ፣ ህይወትን የሚሰጠው የኢየሱስ ኋይል መገኛ መኖሪያ ለመሆን ወስኑ ፡፡ የተስፋንና የፍቅርን ቃል በቤታችሁ ላይ ፣ በባለቤታችሁ ላይ ፣ በልጆቻችሁ ላይ እና በጓደኞቻችሁ ላይ መናገር ጀምሩ ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በኢየሱስ ስም በህይወት ፣ በኃይልና በፍቅር ያንሳቸው ፡፡ ከእንግድህ ሰዎች ሙት ሆነው አይኖሩም ፡፡ ዛሬ ወደ ኢየሱስ በቃሉ ፣ በመገኘቱ ደግሞም ከእርሱ ህዝብ ጋር በመሆን ተመለሱ ፤ መንፈሱም ወደ እናንተ እና በዙሪያችሁ ወዳሉት ህይወትን እንድዘራባችሁ ፍቀዱ ፡፡
“ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ትንፋሽን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ። “
- ሕዝቅኤል 37፡3-5
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 18:21 — “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
ሕዝቅእል 37:10 — “እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።
ዮሐንስ 6:63 — “ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው ፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም ፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።