Restoration Of Israel's People
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 35-36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሪቫይቭ ት/ቤት ግብ በማቴ (5፡ 17) ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ሪቫይቭ ት/ቤት ወደ ክፍል የተከፋፈለ ሲሆን አሁን በታላላቅ ነቢያት ክፍል ላይ ነን ፤ ከታላላቅ ነቢያት የሆኑት ትንቢቶች ወደ ኢየሱስ ወደ አዲሱ ዳዊት ያመለክታሉ ፡፡ ክርስቶስ ነቢያት ብለዉ የነበሩትን አልተፃረረም ትንቢታቸዉን ፈፀመዉ እንጂ ፡፡
እስካሁን ትንቢተ ኢሳይያስን፣ ኤርምያስን እና ሕዝቅኤልን ከእግዚአብሄር እየመጣ ለነበረዉ ቃል ትኩረትን ለመጥራት ጥብቅ የሆነ ነገርን በማድረግ አይተናል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትንቢቶች በአንድ ላይ ሊሄዱ ስለሚችሉ ማን እንዳደረገው ለማስታወስ አስቸጋሪ ይሆናል ፤ ስለዚህ እንከልሰው ፤ በሕዝቅኤል (30-32) ሕዝቅኤል ባቢሎን እንዴት ግብፅን እንደምታሸንፋት ሸክምን፣ ማስጠንቀቂያን እና ፍርድን ሰጥቷል ፡፡
ሕዝ (33፡ 6) የጉበኛ/የጥበቃን መልክ በማቅረብ አዲስ የነቢዩ ተልዕኮ ነበር ፤ የነቢዩ ተግባር ይመጣ ስለ ነበረዉ ነገር ማስጠንቀቂያ መናገሩን መቀጠል ነበር ፡፡
ሕዝቅኤል 34 ኃሰተኛ ነቢያቶች እዉነት ያልነበረዉን የእስራኤል ሕዝብን ከምርኮ በፍጥነት እንደሚወጡ መናገራቸዉን ቀጥለዉ ስለ ነበር አዲስ ማስጠንቀቂያዎችን አካትቷል ፡፡ ከእዉነተኛ ነቢያቶች ሕዝቡ ቃሉን እንዴትም ቢቀበሉት አሁንም ነቢያቶች እዉነቱን እንዲናገሩ በእግዚአብሄር የታዘዙ ነበሩ ፡፡
ሕዝቅኤል 35 ከኤሳዉ ዘር በነበሩት በኤዶምያስ እና በኤዶማዊያን ላይ የተነገረን ትንቢትን ይይዛል ፡፡ ሴይር ተራራ ለኤዶም ምድር ሌላ ስም ነበር ፡፡ የኤዶም ሰዎች ስለሚወገዱ/ስለሚጠፉ እስራኤል የታደሰች ትሆናለች ፤ በሕዝ (35፡ 9) ሕዝቅኤል በኤሳዎ ሕዝቦች/ሰዎች ላይ የማያቋርጠዉን ፍርድ አወጀ/ተናገረ ፡፡ ስፍራዉም የጠፋ ስለሚሆን እግዚአብሄር ምድሪቱን ለሕዝቡ መልሶ መስጠት ይችላል ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉም በቁጥጥሩ ስር ነበር ፤ ሕዝቅኤል ለዚህ ሁሉ ቃል አቀባይ/ተናጋሪ ነበር ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (36፡ 1)፡ ቁጥር (1-15) ስለ ምድሪቱ መታደስ ይገልል ፡፡ አብዛኛዉ ሰዎች በኢየሩሳሌም ጠፍተዉ ነበር ወይም ደግሞ በባቢሎን በምርኮ ነበሩ ፡፡ ሕዝቅኤል በእስራኤል ተራራ ላይ እንዲተነብይ ተነገረው ፤ ሕዝቅኤል ተራራዉን የእግዚአብሄርን ቃል እንዲሰማ ነገረው ፡፡
ሕዝቅኤል (36፡ 2-15)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ እግዚአብሄር በቀረዉ ሕዝብ እና በሁሉም ኤዶምያስ ልይ ይናገራል ፡፡ እነዚህ ትዕዛዞች ስለ እስራኤል መታደስ ትልቅ ስዕልን ይፈጥራሉ ፡፡ በዛ መሆን የሌለባቸው ሕዝቦች በምድሪቱ ላይ ነበሩ ፤ በመጨረሻም የእግዚአብሄር ቅናት ስለሚገለጥ ምድሪቱ ወደ እግዚአብሄር ሕዝቦች ትመለሳለች ፤ ያቸ ምድርም መታደስን/መልሶ መገንባትን እና በዚያን ጊዜ በምድሪቱ ላይ ለነበሩት ሁሉ መታደስ ሲሆን ታያለች፣ ከእግዚአብሄር የነበረዉ መልዕክት ምድሪቱን መልሶ ለሕዝቡ እንደሚሰጣቸዉ ነበር ፡፡ ጥያቄዉ እነዚህ ሁሉ ነገሮች መቼ ይከናወናሉ የሚል ነበር ?
ዮሐንስ ማክአርቱር “ በመታደስ አላማ ዉስጥ(ቁጥር 8-38) የእስራኤል ምድር ምርታማ (ቁጥር 8-9)፣ በብዙ ሕዝብ የተሞላች/እንደሚበዙ (ቁጥር 10-11) እና ሰላም (12-15) ትሆናለች ፤ እነዚህ ገፅታዎችን ሙሉ በሙሉ በመሲሁ መንግስት ዉስጥ ይታወቃሉ/ያታያሉ ፤ ከባቢሎን መመለስ በወደፊቱ መንግስት ከሚመጣዉ ዉስጥ በከፊል መፈፀም እንደ ነበር “ ይፅፋል ፤ ይህ በኤዶም ላይ ሆኖ ከነበረዉ ነገር ተቃራኒ ነበር ፡፡
በሕዝ (33፡ 21) ሕዝቅኤል ከእስራኤል በመጡና የኢየሩሳሌም ከተማ ተመትታ እንደ ነበር ከተናገረው እንግዳ ሰዉ ዜናን ሰምቶ ነበር ፤ ኢየሩሳሌም ብሎት እንደ ነበረዉ ወደቃ ነበር ፤ የእግዚአብሄርም ሰዉ እንደ ነበር አረጋገጠ ፤ አሁንሕዝቡ እያለ የነበረዉን አመኑ ፡፡
ሕዝቡ ኢየሩሳሌም ወድቃ እንደ ነበር ሰሙ ፤ ነገር ግን አሁን ከሕዝቅኤል ኢየሩሳሌም እንደምትታደስ ስለ ሰሙ መታደሱ በፍጥነት እንደሚሆን አሰቡ ፤ ይህ ኢየሩሳሌምን እና ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ከመመለስ የበለጠ ነው ፤ ይህ ማለት ጠላቶቻቸዉ ከዚህ በኋላ ስለማይኖሩ ማምረት፣ ሰላም፣ ደህንነት እና መትረፍረፍ ይኖራል ማለት ነው ፡፡ በአንድ መንገድ ትንቢቱ አሁንም ለኤዶማዊያን የተደረሰ ነበር ፤ አሁን የእግዚአብሄር ሰዎች ምድሪቱን ይቆጣጠራሉ ፡፡ ግድያዎች ይቆማሉ፣ ለጣዖት መስዋዕት ማቅረብ ይቀራል የእስራኤልም ሰዎች አዲስ ነፃነት ይኖራቸዋል ፡፡
ሕዝ (36፡ 15) የምድሪቱን መታደስ አጠቃሎታል ፤ የእስራኤል ሰዎች ለዘላለም ግዞተኝነትን/ምርኮን አይሸከሙም ፡፡ እግዚአብሄር የኤዶማዊያንን ችግር እንዲሁም በሌሎች ሕዝቦች የሆነዉን ችግር ያስባል/ይወስዳል ፤ እንደ ሕዝብ የኢየሩሳሌምን መዉደቅ ሰምተዉም ቢሆንም እንኳን በእነዚያ ክስተቶች መካከል ላይ እግዚአብሄር ሕዝቡን ተስፋ ሰጠ ፡፡
ሕዝቅኤል (36፡ 16-38)፡ ዋይርስቤ ሕዝ(36፡ 16-38) “ እንደ ማቆጥቆጥ ሕዝቡ እንደ ነፃ “ ይለያቸዋል ፡፡ በቀጣዮቹ የተለያዩ ቁጥሮች ሕዝቅኤል ተመልሶ ወደ አለፈዉ ነገር ይመለከታል ፤ ቁጥር (16-31) እስራኤላዊያን ለምን በምርኮ እንደ ነበሩ ተመልሶ ስለተመለከት የመፅኀፍ የተለዬ ክፍል ነው ፡፡ በአዉዱ እና ከምርኮአቸዉ በፊት በአቀማመጡ ሕዝቅኤል ለምን በምርኮ እንደ ነበሩ ይገልፃል - ምድራቸዉን በባህሪያቸዉ እና በድርጊታቸዉ አርክሰዉ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ እስራኤል በሁለት ትልቅ ኃጢዓቶች የመጀመሪያዉ የእግዚአብሄርን ምድር በመበከል (ቁጥር 16-19) ጥፋተኛ ነበረች ፤ ሁለተኛዉ ኃጢዓታቸዉ ደግሞ በአሕዛብ ፊት የእግዚአብሄርን ስም ማሰደባቸው ነበር (ቁጥር 20-23) “ በማለት ተናግሯል ፡፡ እየኖሩበት ከነበረዉ መንገድ የተነሳ እግዚአብሄር ቁጣዉን በእነርሱ ላይ አፈሰሰ ፡፡ ተመልሶ በመመልከት ሕዝቅኤል ሕዝቡ በምድራቸዉ ላይ ባደረጉት ነገር የተነሳ አሁን በምርኮ እንደ ነበሩና ሕዝቡ በእግዚአብሄር ፍርድ ስርም እንደተበታተኑ ይገልፃል ፡፡
እግዚአብሄር በትኗቸዉ በነበሩት ምድሮች ሕዝቡ በሚደርስ ጊዜ የእግዚአብሄርን ስም አረከሱ/አሰደቡ ፡፡ ሕዝቡ ለመበታተናቸዉ እግዚአብሄርን ወቀሱ ፤ በቁጥር (21-25) እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ሕዝቡን ወደ ምድራቸዉ እንደሚመለሱ ነገር ግን በእነርሱ ስራ እንዳልሆነ እንዲነግራቸዉ ነገረው ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር ስሙን ለማክበር እና ለመቀደስ ስለሚፈልግ ብቻ ሕዝቡን እንደሚቀይራቸዉ ቃል እንደገባ (ቁጥር 22) “ ይገልፃል ፡፡
እግዚአብሄር የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምድራቸዉ መልሶ በማደስ ስሙን ያከብራል ፤ ይህ ከቀድሞዉ ወደ አዲሱ መንፃት የሚሆን ነበር ፡፡ ሕዝቡ አዲስ ልብ ይሰጣቸል አዲስ መንፈስንም ይቀበላሉ (ቁጥር 26-27) ፤ እግዚአብሄርም ሕዝቡን ከርኩስነታቸዉ ያድናቸዋል ፡፡
ሕዝቅኤል እግዚአብሄር የሕዝቡን ትዕቢት እንደሚያስወግድ ተናገረ ፤ እንደ አዲስ ኪዳን የሚታይ በነበረው ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ይሰራል ፡፡ እግዚአብሄር ለአይሁድ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እየሰጠ ነበር ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ አዲሱን ዳዊት በሚይዙት ሕዝቦች ላይ መጣ ፡፡
መደምደሚያ
ማክአርቱር “ የአዲስ ልብ ስጦታ በመንፈስ ቅዱስ የሚያቆጠቁጥን አዲስ ዉልደት ያሳያል (11፡ 18-20) ፤ ልብ ስለ ሁሉ ፍጥረት ይቆማል ፤ መንፈስ ባህሪን እና ሀሳብን የሚመራን የአዕምሮን አስተዳዳሪ ኃይልን ያመለክታል ፡፡ ድንጋይ ልብ ትዕቢተኛ/ግትረኛ እና የራሱን ፍላጎት የሚያሟላ ነው ፤ የስጋ ልብ ተለጣፊ እና ምላሽ የሚሰጥ ነው “ በማለት አመልክቷል ፡፡
ሰዎች/ግለሰቦች የአዲሱን ዳዊት የክርስቶስን መሞት፣ መቀበር እና መነሳት በሚ/በሚያምኑ ጊዜ አዲስ ልብ እና አዲስ መንፈስ የተሰጣቸዉ ናቸው ፤ ያ በሚሆንበት ጊዜ እግዚአብሄር በሕዝቅኤል 36 ላይ የሚናገረዉን ነፃነት ይቀምስታል ፡፡ ይህን የክርስቶስን መልዕክት የመያዝ እድል በፊታችን የተቀመጠ ነው ፤ ይህን ሁሉ እግዚአብሄር ለክብሩ ያደርጋል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary, (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 930.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 228.
Wiersbe, p. 228.
Wiersbe, p. 228.
MacArthur, p. 931.
ጥያቄዎች
-
ሕዝ (36፡ 25) በማንበብ ከዮሐ (3፡ 3-5) ጋር እንዴት እንደሚዛመድ/እንደሚገናኝ ግለፁ ፤ የዚህን ጥቅስ መፈፀም ለማሳየት ምን ሌላ መፅኀፍት መጠቀም እንችላለል ? (ዮሐ 13፡ 8, 1ቆሮ 6፡ 11, ኤፌ 5፡ 25-27, ቲቶ 3፡ 5, 1ዮሐ 1፡ 9)
-
ለድንጋይ ልብ አዲስ የስጋ ልብ የተሰጠ መሆን ምንን ያመለክታል/ይወክላል ? (ሕዝ 11፡ 19, 36፡ 26, ሮሜ 2፡ 29, 2ቆሮ 5፡ 17, ኤፌ 4፡ 22-24)
-
በመንገዱ እንድንሄድ ምክንያት እንዲሆነን እግዚአብሄር መንፈሱን እንዴት በእኛ ዉስጥ ያስቀምጣል ? (ሕዝ 36፡ 27, ሮሜ 8፡ 9, 1ዮሐ 3፡ 24)
-
በሕዝቅኤል (35-36) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 36:26–27
“I will give you a new heart and put a new spirit within you; I will remove your heart of stone and give you a heart of flesh. I will place My Spirit within you and cause you to follow My statutes and carefully observe My ordinances.”
የእግዚአብሔር ህዝብ በእርሱና በህጉ ላይ አምጸው ነበር ፡፡ ንጹህ ያልሆነ መንገድና ባህሪም ነበራቸው ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ቁጣውን አፈሰሰ ፡፡ ህዝቡንም ወደ ተለያዩ ሀገራት በታተናቸው በእነርሱም ላይ እንደ ስራቸውና ድርጊታቸው ፈረደባቸው ፡፡ ሆኖም ግን በምህረትና በጸጋ ባለጸጋ የሆነው እግዚአብሔር ፣ ወደ ምድራቸው ሊመልሳቸውና ከበደላቸው ሊያነጻቸው ቃል ገባ ፡፡ አዲስ ልብንና መንፈስንም እንደሚሰጣቸው ተናገረ ፡፡ ድንጋይ የሆነውን ልባቸውንም በማስወገድ የስጋን ልብ እንደሚሰጣቸውም ተናገረ ፡፡ የእርሱን መንገድ መከተል የሚያስችላቸውን መንፈሱን በእነርሱ ውስጥ ያስቀምጣል ፡፡
እግዚአብሔር ለእናንተ የሚሻው ምህረቱንና የተትረፈረፈ ጸጋውን እንድትቀበሉ ነው ፡፡ ለእግዚአብሔር ደንዳና እንደሆናችሁ ከተሰማችሁ ፣ እርሱ ድንጋይ የሆነውን ልብ አስወግዶ አዲስን ልብ በእናንተ ውስጥ ማኖር ይችላል ፡፡ እርሱ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ይችላል ፡፡ በእምነት ይህን ጸጋ ለህይወታችሁ ተቀበሉ ፡፡ በቁጣ ፣ በመዳራት ፣ በገንዘብ ፣ በቂምና ራስን በመውደድ የተሞላው ደንዳና ልባችሁ ነጻ ይወጣል ፡፡ ልክ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የልብ ንቅለ ተከላ ሲያደርግላችሁ መንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ታዛዥ ያደርጋል ፡፡ እርሱ ልባችሁን በደህንነታችሁ ደስታ እና በአዳኛችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ይሞላል ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ከእናንተ ጋር ይሆናል ደግሞም ፍቅር የአዲሱ ልባችሁ መገለጫ ይሆናል ፡፡ ዛሬ ይህን የልብ ንቅለ ተከላ ተቀበሉ ፡፡
“ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ ። “
- ሕዝቅኤል 36፡26-27
ተጨማሪ ጥቅስ
ገላትያ 2:20 — “ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል ፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ። “
ኤፌሶን 2:3–5 — “ በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን ፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን ። ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፥ በጸጋ ድናችኋልና ፡፡ “
ዕብራውያን 8:10 — “ ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።