The Watchman And The Shepherd
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 33-34 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሪቫይቭ ት/ቤት ከ600 በላይ የሚሆኑ ክፍሎችን ጨርሰናል በዚህ ጊዜያት እግዚአብሄር እንዴት ህይወታችሁን እንደ ቀየረዉ ማሰብ እችላለሁ ፡፡ በማንኛዉም ጊዜ በቃሉ ዉስጥ ለመቆፈር ተዘጋጅቻለሁ፣ 2ጢሞ (3፡ 16) የእግዚአብሄር ቃል በእግዚአብሄር የተነሳሳ እንደ ሆነና ለማስተማር፣ ለመገሰፅ እና በፅድቅ ለማስልጠን አስፈላጊ እንደ ሆነ እንደሚነግረን አስታዉሳለሁ ፤ ስለዚህ እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች እጠይቃችኋለሁ፡ 1) የእግዚአብሄር ቃል ምን እያስተማረ ነው ? 2) ይህ ለእኔ እንዴት ይሰራል ? በጥናታችሁ ተመሳሳይ ጥያቄ እንድትጠይቁ አበረታታችኋለሁ - የእግዚአብሄር ትምህርት ምን እንደ ሆነና ለእናንት ይህ ምን ማለት ነው ?
ትምህርት
ሕዝቅኤል 33፡ በሕዝቅኤል 33 እግዚአብሄር በሰዎች (በአሁኑም ጊዜ በእኛ ላይ) ኑሮ ላይ ሁለት ጥሪዎች እንደ ነበሩት ገልፆአል ፤ የመጀመሪያዉ ጥሪ ጉበኛ/ጥበቃ እንዲሆኑ ፡፡ ሕዝቅኤል በቅጥሩ ላይ እንደ ጠባቂ/እንደ ጉበኛ በመሆን እንዲያገለግል ሾሞት ለነበረዉ ሰው በሕዝቦች ላይ እግዚአብሄር ሰይፍን(ጦርን) እንደሚያመጣ እንዲነግራቸዉ ነገረው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ያ ጠባቂ የሰይፉን መምጣት በመመልከት የማስጠንቀቂያዉን መለከት ከነፋ ነገር ግን ሕዝቡ ማስጠንቀቂያዉን ችላ ካሉት ደማቸዉ በራሳቸዉ ስህተት ይሆናል (ቁጥር 3-5) ፤ ይሁን እንጂ ያ ዘበኛ የሰይፉን መምጣት አይቶ ችላ ካለ ግን ሕዝቡ ማስጠንቀቂያ ደርሳቸዉ ስላልነበር ዘበኛዉ በሕዝቡ ላይ በሚሆነዉ ማንኛዉም ነገር ተጠያቂ ይሆናል (ቁጥር 6) ፡፡ ሕዝቅኤል እያለዉ የነበረው በሚያደርጉት ነገር እና እንደ እግዚአብሄር በማይኖረበት ነገር ሰዎችን የማስጠንቀቅ ምርጫ አለን ነው ፤ እያደረጉ ስላሉት ነገር ምርጫ የሚያመጣዉን ዉጤት እንዲያዉቁ ማድረግ ኃላፊነታችን ነው ፤ ስለ ኑሮአቸዉ ለእግዚአብሄር ተጠያቂዎች እንሆናለን ፡፡
ዘበኛ/ጎበኛ/አንቂ ሰዉ በመሆን በዚህ ጥሪ ዉስጥ ለሰዎች የማይረዱ እና በኑሮአቸዉ ዉስጥ ፍሬ የማያመጡ ሰዎስት አይነት ማስጠንቀቂያዎች አሉ፡
- የመጀመሪያዉ የማያግዘዉ/ርዳታ ያማያደርገዉ ማስጠንቀቂያ ያልደረሰ ማስጠንቀቂያ ነው ፡፡ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ችላ ካልን ለሚመጣዉ ዉጤት ለእግዚአብሄር ተጠያቂዎች ነን ፡፡ ፍሬድ ሁልጊዜ ማታ በቤቱ ስለሚጠፋው የጭስ ደዉል ታሪክ ተናገረ ፤ በመጨረሻም ሲተኛ ከቤተ ክርስቲያን አንድ ሴት በቤቱ ዉስጥ እሳት እንደ ነበር ለመጠየቅ ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ደወለችለት ፤ በአንድ እሁድ ማለዳ ላይ ለፓስተሩ 4፡00 ሰዓት ላይ መደወሏ ሆድን አሸብሯል ፤ የእግዚአብሄር መልዕክት በቤቱ ዉስጥ ሳይሆን እሳት እንደ ነበር ብቻ ነበር (ቁጥር 2-11) ፡፡
ሁለተኛው የማያግዘዉ/ርዳታ የማያደርገዉ ማስጠንቀቂያ ግልፅ/የታወቀ/የተለመደ የሆነዉ ነው ፡፡ ግልፅ የሆኑ ማስጠንቀቂያዎች ርዳታ የማያደርጉ ናቸው ፤ ለምሳሌ አሳ ከሚይዝ ሰዉ ጋር በተገናኜ “ አደጋዉ ከሰመጥክ ነው “ የሚል ማስጠንቀቂያ ፤ ይህ ግልፅ የሆነ ዉጤት ስላለዉ ጥሩ አይደለም ፡፡ ማስጠንቀቂያው ሰዉዬዉ የኃጢዓት ሁኔታ ጋር የተጋነኜ መሆኑን እርግጠኛሰ መሆን (ቁጥር 12-20) ፤ ፓስተሮች ይህን ስህተት ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያን በሚሰጡ ጊዜ ይህን ስህተት ይሰሩታል ነገር ግን ይህ ለተሳሳቱ ሰዎች ለምሳሌ ከ60 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ስለ ዉርጃ ወይም ስለ ስካር ኃጢዓት በማዉራት በመናገር አይነት እየሰጡ ናቸው ፡፡ አድማጮቻችሁን እወቁ ፡፡
ሰዎስተኛዉ የማያግዘዉ/ርዳታ የማያደርገዉ ማስጠንቀቂያ በማስጠንቀቂያዉ ላይ ተቃዉሞ እና ክርሰክር ለሚያነሳ ሰዉ ማድረስ ነው ፡፡ ነቢዩ ናታን ከቤርሳቤህ የተነሳ ንጉስ ዳዊትን በህይወቱ ስለ ኃጢዓት ስያስጠነቅቀዉ አስተዋይ ነበር ዳዊትም በመስማት ስህተቱን ተቀበለ ፡፡ ናታን ለዳዊት ኃጢዓቱን ለመግለፅ ታሪክን ተጠቀመ (2ሳሙ 12፡ 1-9) ፤ ኢየሱስ ጠቃሚና ተፅኖ የሚያመጡ ማስጠንቀቂያዎችን ለመስጠት ታሪኮችን ተጠቀመ ፡፡
እንደ አንቂ/ጉበኛ እግዚአብሄር በማን ላይ አስቀመጣችሁ ? በመላዉ አለም ባሉት ሁሉም ሰዎች ላይ ላይሆን ይችላል፡፡
ሕዝቅኤል (34፡ 1-9)፡ ለሕዝቅኤል የእግዚአብሄር ሁለተኛዉ ጥሪ መመልከት/መጠበቅ ምን ማለት እንደ ነበር ምሳሌ እንዲሆን ነበር ፡፡ ሕዝቅኤል በእስራኤል እረኞች (ካህናቶች) ላይ ትንቢትን እንዲናገር ተነገረው ( ቁጥር 1-2) ፤ በቁጥር 4 የአንድ እረኛ/ጠባቂ ኃላፊነቶች የተሰጡ ናቸው፡ የደከሙትን ማበርታት፣ የታመሙትን መፈወስ፣ የተጎዱትን መጠገን፣ የሳቱትን መልሶ ማምጣት እና የጠፉትን መፈለግ ናቸው ፡፡ እንድትጠብቋቸዉ እግዚአብሄር የሰጣችሁ ማንን ነው ? አበርትታችሁ፣ ፈዉሳችሁ፣ ጠግናችሁ፣ መልሳችሁ እና ከኃላቸዉ ተመልክታችሁ እንደሆነ ራሳችሁን ጠይቁ ፡፡
ሕዝቅኤል (34፡ 10-19)፡ ፓስተሮች መንጎቻቸዉን -ጉባኤአቸዉን እንዲጠብቁ የተጠሩ ናቸው ፡፡ ቤተ ክርስታኗ ትልቅ ከሆነች ይህን ሁሉንም በራሳቸዉ ማድረግ አይችሉም ፤ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ስራን እንዴት ማከፋፈል እንደሚቻል ትልቅ ምሳሌን ስለሚሰጥ ፓስተሮች መስበክ ይችላሉ ዳቆናት ደግሞ የአስተዳደራዊ ዝርዝርን መቆጣጠር ይችላሉ ፡፡
በቁጥር 10 ሕዝቅኤል ለበጎቹ በመጠንቀቅ/በማሰብ ፋንታ እረኞቹ በበጎቹ እየተጠበቁ የነበሩ እንደ ሆኑ ገልፆአል ፤ እግዚአብሄር ለበጎቹ የሚበላ ይፈልጋል እረኛም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርግ ይጠበቃል ፡፡ እግዚአብሄር እረኛ እሆናለሁ አለ (ቁጥር 11-16) ፤ እግዚአብሄር ለመንጎቻቸዉ የማይጠነቀቁትን የኃይማኖት መሪዎች በእነርሱ ፋንታ እርሱ በመጠንቀቅ እቀይራቸዋለሁ እያለ ነበር ፡፡
እንደ ልጅ የሚጠነቀቁልን/የሚያስቡልን፣ የሚመግቡን፣ የሚያሳድጉ እና መሰረታዊ ፍላጎታችንን የሚያሟሉ ሰዎች ያስፈልጉናል ፤ ነገር ግን ባደግን ጊዜ ለሌላ ሰዉ ማሰብ/መጠንቀቅ አለብን ፡፡ “ ጥንቃቄ የሚደረግለት ከመሆን “ ለሌሎች ጥንቃቄ ወደ ማድረግ መቀየር ሊሆን የሚችለዉ እግዚአብሄር እረኛችን ሲሆን ብቻ ነው ፡፡ በእረኛ ካልተመገብን እና ካልተጠበቅን ከአካላዊ፣ ከመንፈሳዊ እና በመንፈሳዊ ነገር እንወጣለን ፤ በእረኛ ላይ ከተደገፍን ለሌሎች መጠንቀቅ እንችላለን ፡፡
ሕዝቅኤል (34፡ 1-9)፡ በቁጥር 20 እግዚአብሄር እንደ እረኛ የበጎቹ ዳኛ እንደሚሆን አወጀ ፤ በእነርሱም ላይ እረኛን ይሾምላቸዋል - አገላጋዩን ዳዊትን (መሲሁ ኢየሱስ) ፡፡ እዚህ ለዉጥ እንደሆነ ይሰማችኋል ? ስራቸዉን እየሰሩ ስላልነበሩት እረኞች አይደለም ነገር ግን ይመጣ ስለ ነበረዉ እረኛ ተስፋ ነበር ፡፡ ኢየሱስ እረኛ በሚሆን ጊዜ “ የበረከት ዝና “ ይመጣል (ቁጥር 26) ፡፡
መደምደሚያ
የመፅኀፍ ቅዱሱን እያንዳንዱን መፅኀፍት ስናጠና በእያንዳንዱ መፅኀፍ ኢየሱስን በምናይበት ስፍራ ላይ እንመለከታለን ፤ ለሕዝቅኤል መፅኀፍት ሀረጉ አዲስ ዳዊት የሚል ነው ፤ ከሕዝቅኤል ከዚህ ምዕራፋ ነው የሚመጣው ፡፡ ኢየሱስ በጎቹን የሚጠብቅ እረኛ አዲስ ዳዊት ነው ፡፡ እንደ ጉበኛ/ጥበቃ በማገልገል ዉስጥ እረኛ ለሆንናቸዉ መጠንቀቅ ከመሞከራችን እና ከማስጠንቀቃችን በፊት በእረኛ የተመገብን እንደሆንን እርግጠኞች እንሁን ፡፡
ጥያቄዎች
-
በሕዝ (33፡ 2-3, 7) የጉበኛ/የጥበቃ ኃላፊነቶች ምን ምን ነበሩ ? በሕዝ (33፡ 6, 8) እግዚአብሄር ጉበኛዉን በምን ነገር ተጠያቂ አደረገው ?
-
አማኞች በኃጢዓታቸዉ ምክንያት ስለጠፉት ከጉበኛዉ/ከዘበኛዉ ጋር ተመሳሳይ ኃላፊነት አለባቸዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ማቴ 4፡ 17, 10፡ 7, 28፡ 19-20)
-
እስራኤላዊያን በፈረሰዉ በእስራኤል ምድር የሚኖሩት የእስራኤልን ምድር እንደሚይዙ ያምናሉ ፤ በሕዝ (33፡ 25-26) እግዚአብሄር ስለ እነርሱ በማመልከት “ የምድሪቱን ኃብት ትቀበላላችሁ “ ብሎ ለመጠየቅ ምን አደረገ ? ከርስታችሁ የሚከለክላችሁ ነገር እንዳለ እግዚአብሄር እንዲመረምራችሁ እና እንዲመለከታችሁ ጠይቁት ፤ (መዝ 139፡ 23-24, ኤፌ 5፡ 5)
-
ሕዝ (34፡ 11-12) እንዴት ወደ መሲሁ ያመለክታል (ሉቃ 15፡ 4-5, ዮሐ 10፡ 11-14, 1ጴጥ 2፡ 25) ? መሲሁ እረኛ ብቻ ሳይሆን አዳኛችን ለመሆን በግ/የሚታረድ በግ እንዲሆን መመረጡ እንዴት የሚያስደንቅ/የሚያስገርም ነው ? (ኢሳ 53፡ 7, ዮሐ 1፡ 35-36, ራዕ 5፡ 8-10, 7፡ 17)
-
በሕዝ (34፡ 23-24) ሕዝቅኤል የዳዊትን ስም በመጠቀም ስለ መሲሁ ለምን ትንቢትን ተናገረ (ኤር 30፡ 9, ሕዝ 37፡ 24, ማቴ 1፡ 1, 2፡ 6, ራዕ 5፡ 5) ? ከዘር ግንዳቸው በተጨማሪ ንጉስ ዳዊት እና ኢየሱስ በጋራ ምን አደረጉ ?
-
የሕዝ (34፡ 27) ሁለተኛዉን ግማሽ አንብቡ ፤ እነዚህን መፅሀፍት እንደ መንፈሳዊ ነፃ መዉጣት ይህን ማጣቀሻ ይደግፉታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ኢሳ 61፡ 1, ሉቃ 4፡ 17-21, ዮሐ 8፡ 34-36)
-
በሕዝቅኤል (33-34) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 34:30–31
“‘Then they will know that I, Yahweh their God, am with them, and that they, the house of Israel, are My people.’ This is the declaration of the Lord GOD. ‘You are My flock, the human flock of My pasture, and I am your God.’ This is the declaration of the Lord GOD.”
በእስራኤል እረኞች ላይ የእግዚአብሔር ቃል በሕዝቅኤል በኩል መጣ ፡፡ እርሱም እነርሱ ለእግዚአብሔር ሕዝብ እረኞች ሆነው ሳሉ እንዴት የተሰጣቸውን ሀላፊነት ሳይወጡ እንደቀሩ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔር ያዘዛቸው የደከመውን እንድያበረቱ ፣ የታመመውን እንድፈውሱ ፣ የተሰበረውን እንድጠግኑ ፣ መንገድ የጠፋበትን የሚቅበዘበዘውን እንድመልሱና የጠፋውን እንድፈልጉ ነው ፡፡ እነርሱም ይህንን ስላላደረጉ ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን ለማዳን ለመታደግ ቃል ገባ ፣ እንዲህም አለ ፡- “ እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ ፡፡ “ እግዚአብሔርም በቅርቡ እውነተኛውን እረኛ ከዳዊት ነገድ የሆነውን ኢየሱስን ለህዝቡ ይልካል ፡፡ ኢየሱስ በእርግጥም ያበረታል ፣ ይፈውሳል ፣ ይጠግናል ፣ ይመልሳል ደግሞም የተመረጡትን ህዝቦች በጎቹን ይፈልጋል ፡፡
ምናልባት እግዚአብሔር እረኛችሁ እንደሆነ መስማት ያስፈልጋችኋል ፡፡ በክርስቶስ ምንም አልጎደለባችሁም ፡፡ በለመለመ መስክ ያሳድራችኋል ነፍሳችሁንም ይመልሳል ፡፡ አዎን ! ኢየሱስ መልካም እረኛችሁ ነው እርሱ ይጠነቀቅላችኋል ፣ ያበረታችኋል ፣ ቁስላችሁን ይፈውሳል ፣ ስትበተኑም እርሱ መልሶ ይሰበስባችኋል ስትጠፉም ይፈልጋችኋል ፡፡ ኢየሱስ ይወዳችኋል ፡፡ ዛሬ ይህንን እውነት ለህይወታችሁ ተቀበሉ ፡- እግዚአብሔር እረኛችሁ ነው በእርሱም ታይታችኋል ፡፡
“ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ከእነርሱ ጋር እንዳለሁ ፥ እነርሱም የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እንደ ሆኑ ያውቃሉ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ እናንተም በጎቼ ፥ የማሰማርያዬ በጎች ፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ “
- ሕዝቅኤል 34፡30-31
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 23:1–2 — “ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ፥ የሚያሳጣኝም የለም ።በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል ። “
ሕዝቅኤል 34:15–16 — “ እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ የጠፋውንም እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ ፤ የወፈረውንና የበረታውንም አጠፋለሁ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ ። “
ዮሐንስ 10:14–15 — “ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል ፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።