Major Prophets Ezekiel

Personal Responsibility For Sin

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 30-32 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 639 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ወደ ምዕራፍ (30-32) ከመግባታችን በፊት ትንሽ መነሻ ሀሳብን መስጠት እፈልጋለሁ ፤ ሕዝቅኤል በምርኮ በባቢሎን በነበር ጊዜ እግዚአብሄር በሕዝቡ ላይ ትንቢታዊ ፍርዱን ማፍሰሱን ቀጠለ ፡፡ ከምዕራፍ (25-32) የባቢሎን ንጉስ አድርጓቸዉ የነበሩትን ጦርነቶች የሚያሳዩ በሕዝቅኤል የተሰጡ ዉጤቶች አሉ ፤ በሜንዲ ስዕል ሰይፉ የባቢሎናዊያን አስተዳደር ቁጣን ይወክላል ፡፡ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን እና ይሁዳን ባሸነፈ ጊዜ አልጨረሰም ነገር ግን በዙሪያዉ ባሉም ሌሎች ሕዝቦች በመቀጠል ሄደ ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (25)፡ እግዚአብሄር እስራኤል እና ይሁዳ በወደቁ ጊዜ የተደሰቱትን ሕዝቦች ለማጥፋት የናቡከደነፆርን ሰራዊት ተጠቀመ ፡፡ አሞናዊያን በእስራኤል ላይ ስላደረጉት ድርጊት ጠፍተዋል (ቁጥር 6-7) ፤ ጥፋታቸው እግዚአብሄር አምላክ እንደ ሆነ እንዲያዉቁ ያደርጋቸዋል (ቁጥር 7) ፡፡ የሞዓብያዊያን ፍርድ ታወቀ - እነርሱም ለባቢሎናዊያ ተላልፈዉ ስለሚሰጡ እግዚአብሄር አምላክ እንደ ሆነ ያውቃሉ (ቁጥር 10-11) ፡፡ የኤዶምያስ ቅጣት የተሰጠ ነበር (ቁጥር 14) እንዲሁም የፍልስጤም ቅጣት የተሰጠ ነበር (ቁጥር 15) ፡፡

ሕዝቅኤል 26፡ የጢሮስ ቅጣት ታዉቆ/ታዉጆ ነበር (ቁጥር 2, 7) ፡፡ በምዕራፍ 26 ላይ ያለዉ ትምህርት አጠቃላይ ምዕራፉ ስለ ጢሮስ ንጉስ እንደ ሆነ ወይስ ግማሽ ክፍሉ ስለ ሰይጣን እንደ ሆነ ጥያቄዎች እንዳሉ ይናገራል ፤ ወይም ደግሞ የንጉሱን ሀሳብ ተፅዕኖ በማድረግ ስለተቆጣጠረዉ ሰይጣን ሊሆን ይችላል ፡፡

ሕዝቅኤል 28፡ እግዚአብሄር ለሰዶም ቅጣት የናቡከደነፆርን ሰይፍ ሳይሆን በሽት/ወረርሽኝ እንደ ሆነ ቃል ገባ (ቁጥር 27) ፡፡

ሕዝቅኤል 29፡ በቁጥር (3-5) እግዚአብሄር የግብፅን እና “በወንዙ መካከል ላይ በተቀመጠዉ ታላቅ ዘንዶ “የፈርዖኗን ፍርድ “ ተናገረ ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህ የፈርዖን መገለጫ በናይል ላይ ስለተቀመጠ ተሳቢ ዘንዶ ነዉ ይላል ፤ ፈርዖን ናይልን/ወንዙን ራሱ እንደ ፈጠረ ዋጋዉን ለራሱ ወሰደ ፡፡ እግዚአብሄር በዘንዶዉ ዉስጥ መጥለፊያን/መቃጥን በማስገባት ከእርሱ ቆዳ ጋር ከተገናኙት ከሁሉም አሳዎች ጋር በማዉጣት በበርኃ የተበሉ እንዲሆኑ እንደሚተዋቸዉ ቃል ገባ ፡፡ በቁጥር 19 እግዚአብሄር የግብፅን ምድር ለናቡከደነፆር እንድትዘረፍ እሰጣታለሁ አለ ፤ ባቢሎን የእስራኤልም ጠላት ስለ ነበር ይህ እንግዳ ነገር ይመስላል ፤ እግዚአብሄር የእስራኤልን ጠላት በመጠቀም በእስራኤል ሌሎች ጠላቶች ላይ መለሳቸው ፡፡

ሕዝቅኤል 30፡ ሕዝቅኤል የእግዚአብሄር የሆነዉ ቀን ቅርብ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 3) ፡፡ “ የእግዚአብሄር ቀን “ የሚለዉ በግብፅ ላይ ስለሚሆንበት ጊዜ እንዲሁም ደግሞ አሕዛቦች የእግዚአብሄርን ልጅ ለመዋጋት በአንድ ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደፊት ይመጣ የነበረዉን ነገር ሁለቱንም ያመለክታል ፡፡ ኩሽ፣ ፉጥ፣ ሉድ እና ሊቢያ አናሳ ሕዝቦች ነበሩ - ትንንሽ ሰዎች ነበሩ ፤ አንዳንዶች እንደ ተደባለቀ ሕዝብ ጠቅሰዋቸዋል ፤ ትንቢታዊ ፅሁፎች ልክ እንደ ፕሪዝም ናቸው ፡፡ እስከ ብርኃን በመያዝ በዉስጡ የብርኃን ተኩስን በዉስጡ በማየት ከዚያም ወደ ሌላ መንገድ በማዞር ብርኃኑ የተለያዩ እይታዎችን ያሳያል ፡፡

በእርግጥ ባቢሎን ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት በካርሞሽ ዉጊያ ላይ ግብፅን እና የአሶራዊያንን ቅሬቶች አጥፍታቸዋለች ፡፡ ይህ በፈርዖን ኒካዑ ሁለተኛ ላይ ለባቢሎናዊያን/ለሜዶ-ለፋሪሳዊያን ወሳኝ ድል ነበር ፤ 40,000 የሚሆኑ ግብፃዊያን እና አሶራዊያን ወታደሮች በ18,000 ባቢሎናዊያን ወታደሮች ላይ ነበሩ ነገር ግን ጉዳቱ ለግብፅ አደገኛ/ታላቅ ነበር አሶራዊያንም ጠፋ ፡፡

ሕዝቅኤል በዚያ የጊዜ መዋቅር ዉስጥ ስሌካሄደዉ ክስተት እየተነበዬ ነበር ፤ ምናልባትም ሕዝቅኤል በመቶዎች በሚቆጠር ማይል ርቀት እየሆነ ስለ ነበረዉ ነገር እና ማወቅ ስለማይችለዉ ነገር ከእግዚአብሄር ቃልን እየተቀበለ/እያገኘ ነበር ፡፡

ስለ ጌታ ቀን ስምንት ባህሪዎች አሉ፡ በግብፃዊያን እና በእርሱ ላይ ከተነሱ አሕዛቦች ጋር ለመዋጋት በክርስቶስ መመለስ ከምዕራፍ 30፡

  1. የእግዚአብሄር የቁጣ ቀን፣ የጦርነት ቀን እና የኃዘን/የለቅሶ ቀን ነው (ቁጥር 2) ፡፡
  2. የጨለማ ቀን ነው (ቁጥር 3, 18-19, አሞ 5፡ 18-20, ሐዋ 2፡ 19-20) ፡፡
  3. ለአሕዛብ የጨለማ ቀን ነው (ቁጥር 3) ፡፡
  4. ሕዝቦች በአንድ ላይ ከእግዚአብሄር ጋር ለመዋጋት ይመጣሉ (ቁጥር 4-6) ፡፡
  5. የባድማነት/የባዶነት ቀን ነው (ቁጥር 7-8) ፡፡
  6. ጣዖቶች ይበዛሉ/ይሞላሉ ብልግናም ከቁጥጥር ዉጪ ይሆናል በእግዚአብሄርም ቀን ላይ ጣዖቶች ይጠፋሉ (ቁጥር 13) ፡፡
  7. የጠላት “ ሰራዊት “ የተሰበረ ይሆናል (ቁጥር 21-25) ፡፡
  8. ሕዝቦች የተበታተኑ ይሆናሉ (ቁጥር 26) ፡፡

መደምደሚያ

1ጴጥ (4፡ 17) “ ፍርድ ከእግዚአብሄር ቤት ተነስቶ የሚጀምርበት ጊዜ ደርሶአል ፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀምር ከሆነ ለእግዚአብሄር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸዉ ምን ይሆን ? “

ስለነዚህ ሁሉም ክፉ ነግስታቶች እና ከእግዚአብሄር ጋር ስለሚዋጉት ሕዝቦች ስናስብ በአሁኑ ዘመን እግዚአብሄር ለቤተ ክርስቲያን በሚለዉ ነገር እደነቃለሁ ፡፡ የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን በአለመ እና በአለም ነገሮች ሰላምን አድርጋለች ፡፡ እግዚአብሄር የክርስቶስ አካልን ወደ እርሱ እንድንመለስ እየጠራን እንደ ሆነ አስባለሁ ፡፡

ራዕይ (3፡ 14-22)፡ “ በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልዓክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡- አሜን የሆነው የታመነውና እዉነተኛው ምስክር በእግዚአብሄርም ፍጥረት የመጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል ፡- በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህስራህን አዉቃለሁ ፡፡ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር ፡፡ እንዲሁ ለብስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆን ከአፌ ልተፋህ ነው ፡፡ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለሆንህ ጎስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕዉርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታዉቅ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ ተጎናፅፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለዉን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ ፡፡ እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገስጻቸዋለሁ እቀጣቸዉማለሁ ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ ፡፡ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ፤ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል ፡፡ እኔ ደግሞ ድል እንደነሳሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥሁ ድል ለነሳው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ ፡፡ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለዉን ጆሮ ያለዉ ይስማ “ ይላል ፡፡

በታሪክ ዉስጥ ለሕዝቦች ራሱን ማሳየት የእግዚአብሄር እቅድ ነው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሰዎች በእናንተ የእግዚአብሄርን ክብር እንዲያዩ ከህይወታችሁ ምን ነገር ማስወገድ ያስፈልጋችኋል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ሕዝ (30፡ 5) አንብቡ ፤ ይህ ምንም እንኳን በራሳቸዉ ተመሳሳይ ነገር ባያደርጉም ከክፉ ሀገራት ጋር ራሳቸዉን ስለሚያወዳጁ ሀገራት ምን ይነግረናል ?
  2. ሕዝ (31፡ 13) ከራዕ (19፡ 17-18) ጋር አወዳድሩ ፤ እነዚህ ጥቅሶች ስለ ተመሳሳይ ነገር ሊያወሩ ይችላሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ተመሳሳይ መልዕክትን የተነበየዉ ሌለኛዉ ነቢይ ኢሳይያስ ነበር (ኢሳ 18፡ 6) ፤ ይህን የሚያደርጉ አንድ ወይም ሁለት ነቢያት ጥሩ፡ እግዚአብሄር ተመሳሳይ መልዕክትን ለመናገር የተለያዩ ነቢያቶችን ለምን እንደተጠቀመ ምን ታምናላችሁ ?
  3. ራሳችሁን እንደ ሕዝቅኤል በመቁጠር በሕዝቦች እና በነገስታቶች ላይ እነዚህን ክፉና፣ አስደንጋጭ ነገሮች ተንብዩ/ተናገሩ ፤ ነገስታቶች እና የአሕዛብ ሰዎች ስለ እናንተ ምን እንደሚያስቡ ምን ታስባላችሁ ? ቤተሰቦቻችሁ እና ጓደኞቻችሁስ ? የዕለት ከዕለት ኑሮአችሁ ምን እንደሚመስል አሰላስሉት
  4. በሕዝቅኤል (30-32) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 30:21

“Son of man, I have broken the arm of Pharaoh king of Egypt. Look, it has not been bandaged—no medicine has been applied and no splint put on to bandage it so that it can grow strong enough to handle a sword.”

የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ በማለት ወደ ሕዝቅኤል መጣ ፡- ግብጽ እየደከመች ትሄዳለች ፡፡ አንዱ እጅ ቀድሞ ከተሰበረ ፣ እግዚአብሔር ደግሞ የተቀረውን ይሰብራል ፡፡ ቁስላቸው አይታሰርም ወይም መድሃኒትን አያገኙም ፤ ግብጽ መልሳ ትዋጋ ዘንድ ምንም አቅም አይቀርላትም ፡፡ ግብጻውያን ይቀጣሉ ምክንያቱም እግዚአብሔርን እምቢ ስላሉ ደግሞም እንዲሁ ጣዖት አምላኪ ስለሆኑና እግዚአብሔር የመረጠውን ህዝብ በመቃረን ስለቆሙ ፡፡ ግብጻውያን ፈጽመው ጉልበታቸውን ያጣሉ ፣ ባቢሎናውያንም ድልን ይቀዳጁባቸዋል ፡፡

በዙሪያችሁ የተበላሹ የወደቁ ነገሮች አሉን ? ምናልባትም መኪናችሁ ፣ ቤታችሁና ጤናችሁ ? ቆም ብላችሁ እግዚአብሔርን ጠይቃችኋል ፡- የሆነ ነገር ልትነግረኝ እየሞከርክ ነውን ? ብላችሁታል ፡፡ ለማቆም ፣ ለማዳመጥና በእግዚአብሔር ለመደገፍ ፣ ትህትና ራስን ማዋረድ ያስፈልጋል ፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር ሊያጠራችሁ እየሞከረ ይሆናል ፡፡ ወይም ደግሞ ይህ የሆነው ምናልባት ልክ እንደ ግብጻውያን ሁሉ በህይወታችሁ እግዚአብሔርን ስለተዋችሁ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሆኖም በየትኛውም አጋጣሚ ቆም ብላችሁ የእርሱን እቅድ ፣ አሳብ እና በዚህ ጊዜ እርሱ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልግ ይገልጥላችሁ ዘንድ ጠይቁት ፡፡ ሊያሳያችሁ ወይም ሊያስተምራችሁ የፈለገው ምን እንደሆነ ጠይቁ ፡፡ ከጌታ ጋር ስትጓዙ ይህንን አስታውሱ እያንዳንዷ ወቅት ምክንያት ዓለማ አላት ፡፡

“ የሰው ልጅ ሆይ ፥ የግብጽን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬያለሁ ፤ እነሆም ፥ በጨርቅ በመጠቅለል ይፈወስ ዘንድ ሰይፉንም ለመያዝ እንዲበረታ አልታሰረም ። “

  • ሕዝቅኤል 30፡21

ተጨማሪ ጥቅስ

መክብብ 3:11 — “ ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው ፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው ። “

ዮሐንስ 15:2 — “ ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል ፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል ። “

ዮሐንስ 16:13 — “ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል ፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል ። “