Major Prophets Ezekiel

The Fall Of Tyre's Ruler

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 27-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 638 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የታላላቅ እና የታናናሽ ነቢያቶች እና የራዕይ መፅኀፍት መልዕክቶች ተመሳሳይ ናቸው ፡፡ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር እንደሚለሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸዉ ቢሆንም እንኳን ባለመታዘዝ እና በአመፅ ኖሩ ፤ የእግዚአብሄርን ፍርድ እንደሚቀምሱ ተነግሯቸዉ ነበር ነገር ግን አሁን በክርስቶስ መምጣት ዉስጥ ተስፋ አለ ፡፡ ይህ ሁሉ የዳዊትን ዘር መስር መፈፀምን ያመለክታሉ - አዲሱን ዳዊት የሚመጣዉን መሲህ ፡፡

በምዕራፍ 24 በሚፈላዉ/በጋለዉ መንቸት እና በሕዝቅኤል ሚስት መሞት ምሳሌ ላይ ተመልክተናል ፡፡ ምዕራፍ (25- 26) በእስራኤል ላይ ድርጊትን አድርገዉ ስለ ነበሩት ሕዝቦች ትንቢቶችን ይይዛሉ ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን የሰጠዉን ምሳሌዎች አቅርቧቸዋል/አሳይቷቸዋል፡

  1. የወይኑን እንጨት/ግንዱን (ሕዝ 15፡ 1-5) ፤ ወይኑ ጥቅም የሌለዉ ነበር ፡፡
  2. መስራቹን ህፃል ልጅ (ሕዝቅኤል 16) ፤ ህፃኑ እስራኤል እንዴት ከእግዚአብሄር ፍቅር ዞር ብላ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡
  3. ንስሩን እና የዝግባ ዛፉን (ሕዝቅኤል 17) ፤ በባቢሎን የሚመጣዉን ጥፋት ያሳያል ፡፡
  4. በእሳት የብረት ማቅለጫዉ ( ሕዝ 22፡ 17-22) ፤ እግዚአብሄር ሕዝቡን በእሳት ዉስጥ እንደሚያነፃ ነበር ፡፡
  5. ሁለቱ ጋለሞታዎች (ሕዝቅኤል 23) ፤ ጋለሞታዎቹ ለወጪ ኃያላን ሕዝቦች ፊት ራሳቸዉን ያጋደሙትን የይሁዳን እና የእስራኤልን ምንዝርና ወክሏል ፡፡
  6. የሚፈላዉ/የጋለው ምንቸት (ሕዝ 24፡ 1-14)፡ ምንቸቱ/እንስራዉ የኢየሩሳሌምን መርከስ ያሳያል ፡፡
  7. የመርከብ መፈራረስን/አደጋዉን (ሕዝቅኤል 27) ፤ ፍርድ በጢሮስ ላይ እንደሚወርድ ይወክላል ፡፡
  8. ግድ የለሽ እረኞቹ(ሕዝቅኤል 34) ፤ ከነገዶች/ከሕዝቦች ሁሉ የጠፉትን መንጎችን የሚሰበስበዉን እረኛዉን አዲሱን ዳዊት እንደ ግዴለሽ እረኛ ተቃራኒ ሀረጉን/ዓ ነገሩን ይይዛል ፡፡
  9. የደረቁት አጥንቶች (ሕዝቅኤል 37) ፡፡

በምዕራፍ 27 ፍርድ በጢሮስ ላይ እየመጣ እንደ ነበርና በኋላም ዛሬ ላይ በሰዶም ላይ ፍርድ እንደሚመጣ እናገኛለን ፤ ምዕራፍ 27 ስለ መርከብ መፈራረስ ነው ፡፡ ኮንስታብል ምዕራፍ 27 በእነዚህ ክፍሎች ያጠቃልላቸዋል፡ “ ታላቅ መርከብ “ (ቁጥር 1-11)፣ “ የጢሮስ የንግድ ግዛት መጠን “ (ቁጥር 12-14) እና “ የታላቁ መርከብ መስመጥ “ (ቁጥር 25-36) ፡፡ ሰዎስተኛዉ ክፍል የሚመጣው ጥፋት እንዲት እንደሚያበቃ ይመዝግባል ፤ የጢሮስ ሕዝብ ዝም ይላሉ ፤ ቁጥር 36 እንደ ገና ጢሮስ አትኖርም ይላል ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (28፡ 1-10)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ ፍርድ በጢሮስ አለቆች ላይ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፤ ይህ መፅኃፍ ቅዱስ ምሁራን የማይስማሙበት የሚያወዛግብ ፅኁፍ ነው ፡፡ የመጀመሪያዉ ሰው የተወራለት የጢሮስ ንጉስ ነው ነገር ግን ሁለተኛዉ ሰዉ ምናልባትም ሰይጣን ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን የጢሮስን ገዢ ራሱን እንደ አማልዕክት በማየት የገዢዉ ልብ በትዕቢት የተነፋ እንደ ነበር እንዲነግረዉ ነገረው (ቁጥር 1-2) ፡፡ እነዚህ ትንቢታዊ ቃሎች ስለሆኑ ለንጉሱ በአካል እንደ አስፈላጊነታቸዉ አልተሰጡትም ነበር ለእርሱ ተልከዉለት ነበር እንጂ ፤ ለንጉሱ መልዕክቱ ከዳንኤል የተሸለ ጥበበኛ እንደ ነበር ነገር ግን አማልዕክት እንዳልነበር ነገረው (ቁጥር 3) ፡፡ ንጉሱ ገንዘብን እና ኃብትን ለማግኘት ጥበቡን ተጠቀመ ነገር ግን ብልፅግናው ከመጠን በላይ ባለዉ ነገር እንዲታበይ ምክንያት ሆነው (ቁጥር 5) ፡፡ በቁጥር (6-7) እግዚአብሄርም በንጉሱ ላይ ክብሩን የሚያረክሱ ሰይፍ የያዙ ሰዎችን ያመጣበታል፡፡

ይህ ትንቢት በአጭሩ ከክርስቶስ ልደት (585-575) በፊት በባቢሎኑ ናቡከደነፆር ከጢሮስ መከበብ በፊት የተሰጠ ነበር ፤ በዚያን ጊዜ ኢቶ ባዖል ሁለተኛ ንጉስ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ንጉሱ አሁንም በባቢሎናዊያኑ እጅ ላይ ለመሞት ተቀምጦ በነበረበት ጊዜም ራሱን እንደ አምላክ ያይ እንደሆነ ጠየቀው (ቁጥር 8-10) ፡፡

ሕዝቅኤል (28፡ 11-19)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (11-18) “ ፍርድ በጢሮስ ንጉስ ላይ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ቀጣዩ መግለጫ የተለዬ ለሚሆን ሰዉ ይመስላል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ለጢሮስ ንጉስ በማዘን “ ጥበብን የተሞላህ ዉበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነበርህ “(ቁጥር 12) በማለት እንዲነግረዉ ነገረው ፡፡ መግለጫው ይህ ንጉስ በኤደን እንደ ነበርና በዘጠኝ በወርቅ ዉስጥ በተቀመጡ የከበሩ ድንጋዮች የተሸፈነ እንደ ነበር ይቀጥላል (ቁጥር 13) ፡፡ ይህ ንጉስ የተመረጠ የኪሩብ ጋርድ ነበር፣ በእግዚአብሄር ቅዱስ ተራራ ላይ ነበር (ቁጥር 14) እና ክፋት በእርሱ እስኪገኝበት ድረስ ያለ እንከን ሆኖ የተገኘ ነበር (ቁጥር 15) ፡፡ በዚህ ንጉስ ሁከት እና ኃጢዓት ምክንያት እግዚአብሄር ከእግዚአብሄር ተራራ ላይ አወርዶ በማዉረድ እንደ ምትጋርድ ኪሩብ አጥፍቶት ነበር (ቁጥር 16) ፡፡ ይህ ንጉስ በጣም የታበዬ ስለሆነ በምድር ነገስታቶች ፊት መነፅር/ማሳያ እንዲሆን በምድር ላይ ወረወረው (ቁጥር 17) ፡፡ የማስፈራሪያ/የማስደንገጫ ነገር/እቃ ሆነ እንደ ገና በፍፁም አይገኝምም (ቁጥር 19) ፡፡ “ የምትጋርድ ኪሩብ “ መጠቀም የተወረወረዉን የቀድሞዉን መለዓክት ሰይጣንን ያመለክታል ፤ ይህ የጢሮስን ንጉስ እንደ ሰይጣን ጥላ ስታዩት ትርጉም ይሰጣል (ቁጥር 1-11) ፡፡

በዘፍጥረት ሰይጣን የእግዚአብሄርን ዙፉና ለመዉሰድ በመፈለግ እንደ ወደቀ መለዓክት የተገለፀ ነው ፡፡ “ የተመረጠ ኩሩብ “ የሚለዉ ሀረግ በአንድ ጊዜ የእግዚአብሄርን መገኘት የነበረዉ ማለት ነው ፤ ማክአርቱር እግዚአብሄር ሰይጣንን እና የጢሮስን ንጉስ ሁለቱንም ተቋቋሙ እንዲሁም ሰይጣን በእግዚአብሄር ቅዱስ ተራራ ላይ የመሆን እድል ነበረው ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ሰይጣንን ከተራራዉ ላይ ወደ ታች በመወርወር ከገነት አስወጣው ፡፡ “ የፍፁምነት መደምደሚያ “ የሚለዉን ንግግር ሰይጣን እስካሁን እግዚአብሄር ከፈጠራቸው የበለጠ እንደ ነበር ያብራራል ፡፡ ጄ.ቬርኖን ማክጊ መደምደሚያ የሚለዉ ቃል ሰይጣን በጣም የሚያምር ቆንጆም እንደ ነበር ያሳያል ፡፡

ሕዝቅኤል (28፡ 20-26)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (20-24) “ በሰዶም ላይ እንዳለ ፍርድ “ ሲገልፃቸዉ ቁጥር (25-26) “ የእስራኤል እንደ ገና መሰባሰብ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

ምንም እንኳን ይህ ስለ ሰይጣን እንደተፃፈ ባንቀበልም እንኳን ሰይጣን ልክ እንደ ጢሮስ ንጉስ በሌላ ሰዉ ቃል ሊናገረን ይችላል (ማቴ 16፡ 23) ፡፡ ጠላት ሊሰርቅ፣ ሊገድል እና ሊያጠፋ ይመጣል እንዲሁም ራሱን እንደ አምላክ ስለሚያይ ያ እንዲሆን ማንኛዉንም መንገድ ይጠቀማል ፡፡ ኩራት አማልዕክት እንደ ሆንን እንዲሰማን እንዲያደርገን ስንፈቅድ ሰይጣን ደስ ይለዋል ከእግዚአብሄርም እንወድቃለን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 921.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Ezekiel, pp. 214–218; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.

  3. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 215.

  4. MacArthur, p. 922.

  5. Wiersbe, p. 215.

  6. MacArthur, p. 922.

  7. J. Vernon McGee, “Outline for Ezekiel”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/ezekiel/ezekiel-outline.cfm.

  8. Wiersbe, p. 216.

  9. Wiersbe, p. 216.

ጥያቄዎች

  1. በሕዝቅኤል 27 ሕዝቅኤል ከጢሮስ ጋር ምንን አወዳደረ ? ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ? በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ተነፃፃሪ ታሪክ ልታገኙ ትችላላችሁ ? (ማቴ 7፡ 24-27, 13፡ 3-8, ማር 4፡ 3-8, ሉቃ 6፡ 46-49)
  2. የጢሮስ ከተማ መዉደቅ ምን ነበር (ሕዝ 27፡ 3-4) ? በጢሮስ ሕዝቦች መካከል ለዚህ እግር ምክንያቱ ምን ይሆናል ? በአሁኑ ዘመን ከተማ ላይ ስትመለከቱ ትዕቢት ሰዎችን ከእግዚአብሄር መንገድ ዞር በማለት በዚያ ፋንታ በራሳቸዉ ዉበት፣ ኃብት፣ ኃይል እና ስኬት ላይ እንዲደገፉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይሰማችኋል? በግል አስተያየታችሁ በዙሪያቸዉ ከተሞች እንዲወድቁ እንዴት ምክንያት ሊሆን ይችላል ?
  3. በሕዝቅኤል 28 በትዕቢቱና ባለመታዘዙ ምክንያት በጢሮስ ንጉስ ላይ ምን ሆነበት ?
  4. በሕዝ (28፡ 24-26) ላይ ያለዉ ትንቢት ተፈፅሟል ? አልተፈፀመም ከሆነ መቼ ይሆናል ? (አሞ 9፡ 11-15)
  5. በሕዝ (29፡ 17-20) መሰረት እግዚአብሄር በጢሮስ እና በግብፅ ላይ የትኛዉን ክፉ መንግስት ተጠቀመ ? ይህን ለማድረግ ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ ?
  6. በሕዝቅኤል (27-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 28:17

“Your heart became proud because of your beauty; for the sake of your splendor you corrupted your wisdom. So I threw you down to the earth; I made you a spectacle before kings.”

የጢሮስ መንግስት በንጉሡ ጥበብ ፣ ማስተዋል ፣ ሀብትና የንግድ ጥበብ አማካኝነት አደገ ፡፡ ምንም እንኳ ንጉሡ ጥበበኛ ቢሆንም ፣ እግዚአብሔር ግን እንዴት ልቡ እንደታበየ አየ ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ፍርድና ጥፋትን አመጣ ፣ የጢሮስም መንግስት ወደቀ ፡፡

እንድህ አይነት ነገር የራስህን መንግስት ለመገንባት የሚደረግ ጥረት ነው ፡፡ ምናልባት ሁሉም ሰው የራሱን መንግስት ለመገንባት እየጣረ ነው በማለት ጥረትህ ትክክል እንደሆነ ለማሳየት ትሞክር ይሆናል ፡፡ እስኪ ራስህን ጠይቅ ፡- ከእግዚአብሔር ይልቅ ከስራዬ ፣ ከትዳሬ ፣ ከቤተሰቤ ፣ ወይም ከራሴ ነው ብዙ መጽናናትንና ሰላምን የማገኘው ? እግዚአብሔር እውነቱን ያውቃል ለአንተም ይገልጥልሃል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምን ያህል ታብየህ እንደነበር ለማወቅ ወደ ታች ዝቅ ማለት ያስፈልግሃል ፡፡ እግዚአብሔር በመንግስትህ ውስጥ እንደ አምላክ ራስህን እንዲትቆጥር አይፈልግም ፡፡ እርሱ በመንግስቱ ውስጥ ለአንተ የተለየ ስራና ዓለማ አለው ፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል ፡- “ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ። “ እግዚአብሔር እንድትጠይቀው ፣ በእርሱ እንድትደገፍ እናም እርሱ የሰጠውን ተስፋ እንድታምን ይፈልጋል ፡፡ አስታውስ እርሱ ከዚህ የበለጠ ማድረግ ይችላል አንተ ከምታስበውም በላይ እንዲሁም እርሱ የህይወት መስመርህን ያሳይሃል ፡፡ ህይወትህን ለእርሱ አሳልፈህ ስጥ እናም መጀመሪያ እርሱን ፈልግ ፡፡

“በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ ። “

  • ሕዝቅኤል 28፡17

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 25:4— “ አቤቱ ፥ መንገድህን አመልክተኝ ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ ። “

ምሳሌ 11:2 — “ ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች ፤ በትሑታን ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች ። “

ማቴዎስ 6:33 — “ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ። “