The Parable Of The Boiling Pot
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 24-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሕዝቅኤልን ጥናታችንን ስንቀጥል እዚህ ስፍራ ላይ ምርኮኞቹ ኢየሩሳሌም ወድቃ እንደ ነበር እንደማያዉቁ እናስታዉሳለን ፡፡ ማክአርቱር የሕዝቅኤልን ህይወት ክስተቶች እና ጊዜያት መዝግቧል፡
- ከክርስቶስ ልደት 622-621 በፊት፡ ንጉስ ኢዮስያስ በይሁዳ ላይ መንፈሳዊ ተሀድሶን ባመጣ ጊዜ በዚያን ዘመን ሕዝቅኤል አደገ ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት፡ ነንዌ/አሶር በባቢሎን ወደቀች ፤ ይህ የአሶራዊያን ኢምፓየር ማብቂያ ነው ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 609 በፊት፡ ንጉስ ኢዮስያስ በዉጊያ ተገደለ ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት፡ ባቢሎን ግብፅን በካርሞሽ በጋለ ዉጊያ አሸነፈች ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 599-597 በፊት፡ በአስራስምንት አመቱ ንጉስ ዮአኪን በባቢሎን በምርኮ ተወሰደ ፤ ምናልባትም ሕዝቅኤል በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ምርኮ በመወሰድ ወደ ባቢሎን ተሰደደ (2ነገ 24፡ 1) ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 593 በፊት፡ ሕዝቅኤል በባቢሎን በሰላሳ አመቱ የእግዚአብሄር ነቢይ እንዲሆን ተጠራ (ሕዝቅኤል 1-3) ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 592 በፊት፡ ሕዝቅኤል በኢየሩሳሌም የተተገበሩ የጣዖት ድርጊት ራዕይ ተሰጠው (ሕዝቅኤል 8) ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 588 በፊት፡ የኢየሩሳሌም ከተማ የመጨረሻዉ ከበባ ተጀመረ ፤ ሕዝቅኤል እንዲሰጥ የሚቀቀልን ምንቸት ትንቢት ተሰጠው (ሕዝ 24፡ 1-8) ፤ የሕዝቅኤል ሚስት ሞተች ነገር ግን በኃይል እንዲያዝን ወይም ስለ እርሷ በተለመደዉ የኃይማኖት ስርዓት ሐዘኑን እንዲያሳይ አልተፈቀደለትም ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 587 በፊት፡ ሕዝቅኤል የፈርዖን ሰራዊት የተሰበረ እንደሚሆን ትንቢትን ተናግሯል (ሕዝ 30፡ 20-26) ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 573 በፊት፡ ሕዝቅኤል የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም እና የአዲስ ቤተ መቅደስ ራዕይ ነበረው (ሕዝቅኤል 40-48) ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 571 በፊት፡ ሕዝቅኤል በጢሮስ እና በግብፅ ላይ የናቡከደነፆርን ድል ማድረግን ተንብዮአል (ሕዝ 29፡ 17-21) ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (24፡ 1-14)፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ባቢሎን በተመሳሳይ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ከበባን ጥሎ ስለ ነበር (ከክርስቶስ ልደት 588 በፊት ጥር 15) ይህን ቀን እንዲፅፍ ነገረው (ቁጥር 1-2) ፡፡ እግዚአብሄርም ሕዝቅኤልን ለግዞተኞቹ ሌላ ምሳሌ እንዲያሳያቸው የተለዬ ትዕዛዝን ሰጠው ፤ ትዕዛዙ እንዲፈላ በምንቸት ዉስጥ ዉኃ እንዲያስቀምጥ እና የተመረጠ የተቆራረጠ ስጋ እና አጥንት እንዲጨምርበት ነበር (ቁጥር 3-5) ፡፡ ከዚያም እግዚአብሄር ምሳሌዉን አብራራው (ቁጥር 6) ፡፡
ምንቸቱ/እንስራው “ የዛገች “ ሆና የነበረችዉን ወይም በዉስጧ ታማ የነበረችዉን የኢየሩሳሌምን ከተማ ይወክላል ፤ ማክአርቱር “ የከተማዋ ደም (የኃጢዓት አጠቃላይ ምልክት) በፍላጎት እንደሚታይ በአለት አናት ላይ ሳይደበቅ በግልፅ የሚታይ ነበርሰ ፤ ደም በአፈር/በቆሻሻ ከልተሸፈነ ሕጉ ተጥሷል (ዘሌ 17፡ 13) ፤ የእግዚአብሄር በቀል በባቢሎን ሰራዊት እንደሚመጣ “ ፅፏል (ቁጥር 7-8) ፡፡
በቁጥር 9 መጀመሪያ ላይ እግዚአብሄር የሚመጣዉን ፍርድን ይገልፃል ፡፡ ታላቁ እሳታ/ማገዶ ሕዝቡ እንደሚሞት ይወክላል ፤ ቁጥር (10-13) ከእሳቱ በኋላ ምንቸቱ ዝገቱ እስኪቃጠል/እስኪጠፋ ድረስ የጋለ እንደሚሆን - ከከታማዋ ክፉን እና የተበከለዉን እስከሚያነፃ ድረስ የጋለ እንደሚሆን ይነግረናል ፡፡ ዘሌ (14፡ 34-35) በኢየሩሳሌም ሁሉም ነገር ይጠፋል (ቁጥር 14) ፡፡ ሕዝቅኤል በግልፅ የእግዚአብሄርን ቃል እየተናገረ ነበር ፡፡
ሕዝቅኤል (24፡ 15-27)፡ በቀጣዩ ክፍል እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን “ የአይኖቹን ደስታ እንደሚወስድበት “ -ሚስቱን ነገረው ፤ ይሁን እንጂ እርሷን በማጣት ሕዝቅኤል ስለ እርሷ እንዲያለቅስ ወይም እንዲያዝን አልተፈቀደለትም (ቁጥር 15-16) ፤ ሕዝቅኤል በፀጥታ እንዲያቃስት/እንዲያዝን እንጂ ምንም አይነት ስርዓት እንዲያሳይ ወይም ለሞቱ ሰዎች የሚለበስ የኃዘን ልብስ መልበስ እንደማይችል ተነግሮት ነበር (ቁጥር 17) ፡፡ በቀጣዩም ቀን ሕዝቅኤል በማለደ ለሕዝቡ ማታ ሚስቱ እንደሞተች ተናገረ ፤ ሕዝቅኤልም ታዞት እንደ ነበረዉ አደረገ (ቁጥር 18) ፡፡ ሌሎች ስደተኞችም ድርጊቱን በማየት ምን ማለት እንደ ሆነ ጠየቁት (ቁጥር 19) ፡፡ ማክአርቱር “ ሕዝቅኤል ለሚስቱ መሞት እንዳላዘነ እስራኤልም እንዲሁ ለሞቱት ቤተሰቦቿ አታዝንም “ በማለት ይናገራል ፡፡
እግዚአብሄር የራሱን ማደሪያመቅደሱን እንደሚያረክስ እና የሚወዷቸዉንም በሰይፍ እንደሚገድላቸው ገለፀ (ቁጥር 20-21) ፡፡ ሕዝቅኤል አድርጎት እንደ ነበረዉ ኃዘናቸዉን ይሸከማሉ (ቁጥር 22-24) ፡፡
በመቀጠልም እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን የኢየሩሳሌም ከተማ በተያዘችበት እና በዚያ ያሉት ሕዝቦች ተገድለዉ በነበሩበት ቀን ዜናዉን ሪፖርት ሊያደርጉለት እንግዳ ሰዎች እንደሚመጡ ነገረው (ቁጥር 25-26) ፡፡ በዚያም ቀን የሕዝቅኤል አፍ የተከፈተ ይሆናል ከዚያ በኋላም ዝም አይልም ፤ እንደ ገና ሕዝቅኤል ምርኮኞቹን ወደ እግዚአብሄር ያመለከተ የሚታይ ምልክት ይሆናል (ቁጥር 27) ፡፡ ሕዝቅኤል ይህን ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ከሆነ ከአስራ ስምንት ወራት በኋላ ፅፎታል ፡፡ በመቀጠልም ሕዝቅኤል በዝምታ ሁለት አመታትን አሳልፏል (ኤር 52፡ 1-16, ሕዝ 33፡ 21) ፤ ከሁለት አመታት በኋላ ሕዝቅኤል መናገር ቻለ ነገር ግን ቀድመዉ በፍርድ ስር ስለ ነበሩ ለመስጠት ምንም መልዕክት አልነበረም ፡፡
መደምደሚያ
ሕዝቅኤል እንደ እግዚአብሄር ነቢይ ሰብኮት ከነበረዉ ጨለማ በኋላ አዲስ ስዕል መሳል ይችል ስለ ነበር እግዚአብሄር ይመስገን ፤ አዲስ ኢየሩሳሌም እና አዲስ ቤተ መቅደስ እንደሚኖር መናገር ቻለ ፡፡ ምዕራፍ 24 ከላይ በተመዘገበው የማክአርቱር የሕዝቅኤል ሕይወት ማሳያ በቁጥር 9 የተሸፈነ ነው ፡፡ ሕዝቅኤል ነቢይ እንዲሆን ከተጠራበት ከክርስቶስ ልደት 593 በፊት ጊዜ እና የኢየሩሳሌምን ከበባ መጀመሪያ ተነግሮበት ከነበረዉ ከክርስቶስ ልደት 588 በፊት ጊዜ እስከ እነዚህ ትንቢቶች ወደ መፈፀም መምጣታቸዉን ከማየቱ በፊት ከክርስቶስ ልደት 585 በፊት ጊዜ ድረስ እንደሚጠብቅ አስተዉሉ ፡፡ እግዚአብሄር ለሚመጣዉ ጥፋት እና በኋላ ለምትመጣዉ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም መላዉን ሕዝብ ለማዘጋጀት የተጠቀመበት ታዛዥ ሕይወት ነበር ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 916.
MacArthur, p. 917.
MacArthur, p. 917.
ጥያቄዎች
-
በሕዝ (24፡ 16) እግዚአብሄር ሕዝቅኤል ሚስቱ እንደምትሞት ነገር ግን ለእርሷ እንዳያዝን ታዝዞ እንደ ነበር ነገረው ፤ እግዚአብሄር ይህን ለምን አደረገ (ሕዝ 24፡ 24) ? በጣም ጥብቅ የሆነ ነገር ልታደርጉ ትችላላችሁ ? ምንም ያክል ዋጋ ቢያስከፍልም እግዚአብሄር እንድታደርጉት የነገራችሁን ነገር ለማድረግ ፍቃደኞች ናችሁ ?
-
በሕዝቅኤል 25 ላይ በተጠቀሱት እያንዳንዳቸዉ ሕዝቦች ላይ በመመልከት ለምን የተፈረደባቸዉ እንደ ነበሩ ዘርዝሩ ፤ ከእነዚህ ሕዝቦች ጋር ተመሳሳይ የሆኑት ሕዝቦች( በአሁኑ ጊዜ ስማቸዉ) አሁንም የኃጢዓታቸዉን ሰንከር አሁንም ይገጥማችኋል ብላችሁ ታምናላችሁ ? ከዚህ ምን ልንማር እንችላለን ? ካስፈለጋችሁ የመፅኀፍ ቅዱስን ካርታ ከአሁኑ/ከዘመናዊዉ ካርታ ጋር በማወዳደር ይህን ጥያቄ ለመመለስ እንዲረዳችሁ በዜናዉ ላይ በወቅታዊዉ ክስተት ላይ ትኩረትን ስጡ ፡፡
-
በሕዝቅኤል (24-26) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 24:13
“Because of the indecency of your uncleanness—since I tried to purify you, but you would not be purified from your uncleanness—you will not be pure again until I have satisfied My wrath on you."
እግዚአብሔር ነቢዩ ሕዝቅኤልን በኢየሩሌም ለቀሩት ለእነዚህ ለአመጸኞቹ ቤት በእሳት ላይ ስለተጣደ ምንቸት ምሳሌን ይናገር ዘንድ አዘዘው ፡፡ በመጨረሻ ህዝቡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ለማንጻት ስላልወደዱ ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ፍርድና ቁጣውን አደረገ ፡፡ ሕዝቅኤልም ያለምንም ፍርኃት በእግዚአብሔር ላይ በመታመንና እርሱን በመታዘዝ ተነበየ ፡፡ ያም የእግዚአብሔር ህዝብ ሊሰሙት የሚገባ መራር እውነት ነበር ፡፡
እስኪ ህይወታችሁን እንደ ተጣደ ምንቸት አሰቡት ፡፡ የእግዚአብሔር “ የሞቀ ውሃ “ ልባችሁን ፣ አሳባችሁንና አካላችሁን እንድያነጻ ትፈቅዳላችሁን ? የእግዚአብሔር ፍቅርና ጸጋ ከውስጥ ወደ ውጭ ያጥባችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን ? ይህም ማለት በልባችሁ ውስጥ ያለውን የትኛውንም ንጹህ ያልሆነ በእርሱ ፊት ምርኮኛ ማድረግ ማለት ነው ፡- ትዕቢት ፣ ቅናት ፣ ቁጣ ፣ ራስን መውደድ ወይም ጣዖትን ማምለክ ፡፡ እግዚአብሔር የራሱ መንገድ ስላለው ፡፡ እርሱ ይቅር ይላችኋል ፡፡ እርሱ ያነጻችኋል ፡፡ እርሱ በፍቅሩ ያጥባችኋል ፡፡ የመጀመሪያው ነገር ወደ እርሱ መመለስ ነው ፣ ኋጢአታችሁን መናዘዝ እናም ከዚያ በእርሱ ኋይል ወደ ፊት መራመድ ፡፡ ወደ ፍቅሩና ወደ ብዙ ታማኝነቱም ዘልቃችሁ ትገባላችሁ ፡፡
“ በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ ፤ አነጻሁሽ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም ። “
- ሕዝቅኤል 24፡13
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 51:10–13 — “ አቤቱ ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ ። ከፊትህ አትጣለኝ ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ።የማዳንህን ደስታ ስጠኝ ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ ። ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ ። “
2ኛ ቆሮንቶስ 7:1 — “ እንግዲህ ፥ ወዳጆች ሆይ ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን ፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ ። “
1ኛ ዮሐንስ 1:9 — “ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።