Major Prophets Ezekiel

The Two Immoral Sisters

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 22-23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 636 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሕዝቅኤል አገልግሎት ባይሰሙትም እንኳን በግዞት ላሉት ምን እየገጠማቸዉ እንደ ነበር ስዕልን መስጠት ነበር ፡፡ ጂ.ቬርኖን ማክጊ ምዕራፍ 22፡ “ መሪዎቹ በክህደት እና በኃጢዓት ብዛት የሚሰሩ ነበሩ - ሉዑሎቹ (ነገስታቶቹ) (ቁጥር 6, 27)፣ ነቢያቶች (በኃሰተኛ ራዕይ ኃሰተኛ ነቢያቶች ) (ቁጥር 25) እና ካህናቶች (ኃሰተኛ ካህናቶች ) (ቁጥር 26) ፤ በክፍተቱ ላይ የሚቆም አንድም ሰዉ ሊገኝ አይችልም “ በማለት ያጠቃልለዋል ፡፡ ማክአርቱር “ ሕዝቅኤል እና ኤርምያስ የታመኑ ነበሩ ነገር ግንከእነርሱ በተለዬ እስካሁን እስራኤል አድርጋዉ ስለ ነበረዉ ኃጢዓት ማስታወቅ የሚችል አንድ ሰዉ እንዳለ እንደ ተመለከተ “ ያመለክታል ፡፡ ሕዝ (22፡ 30) በአጠቃላይ ከመፅኀፉ ዉስጥ አንዱ ቁልፍ ጥቅስ ነው፡ “ ቅጥርን የሚጠግንን ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ ነገር ግን አላገኘሁም “ ፤ በመጨረሻም ክርስቶስን አዲሱን ዳዊት እየጠበቅን ነው (ኢሳ 59፡ 15-19, 63፡ 5, ዘካ 12፡ 10) ፡፡

በምዕራፍ 23 “ እስራኤል (የሰሜኑ መንግስት) እና ይሁዳን (የደቡቡን መንግስት) ሁለቱንም ጋለሞታነትን በመጫዎት ለእርዳታ እንዲመራቸዉ እና እንዲያድናቸዉ በእግዚአብሄር አምላክ ላይ ከመደገፍ ይልቅ ለእርዳታ ከአሶር፣ ከባቢሎን እና ከግብፅ ሲፈልጉ እናገኛቸዋል “ ፤ ሁለቱም ሕዝቦች እነርሱን እንዲያድናቸዉ ከዉጪ ሌላ ኃይልን ለማግኘት እየሞከሩ ነበር ፡፡ የሚፈልጉትን ለማግኘት ራሳቸዉን ለሌሎች ሕዝቦች ለመሸጥ ፍቃደኞች ስለ ነበሩ በሕዝቅኤል 16 እና 23 እንደ አመንዝራ ተስለዋል ፡፡ ኮንስታብል፡ “

“ በምዕራፍ 16 ከነዓን መንፈሳዊ አመንዝራነቷን ማለትም ጣዖት አምልኮን ወይም ሌሎች አማልዕክቶችን መደገፍን በማስተማር ልጇን ያበላሸችዉ የእስራኤል እናት ነች ፤ በምዕራፍ 23 እስራኤል በራሷ በሌሎች ሕዝቦች ላይ በራሷ ፍላጎት ከሌሎች ኃይላት ጋር በጥምረት በኩል በአብዛኛዎቹ የፖለቲካ ምንዝርናን በመከታተሏ ኃላፊነት ትወስዳለች ፡፡ በምዕራፍ 16 የእስራኤል ያለመታመን መጀመሪያ ብዙ ትኩረቶችን መቀበል ሲሆን በምዕራፍ 23 ደግሞ ሁሉም የእስራኤል አለመታመን በእይታ ነው ፡፡ ምዕራፍ 16 በይሁዳ ላይ ብቻ ያወራል ነገር ግን ምዕራፍ 23 በእስራኤል እና በይሁዳ በሁለቱም ላይ ያተኩራል “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ሕዝቅኤል 23 ከሕዝቅኤል 16 በኋላ በጣም የመደጋገም ስሜት ያለዉ ይመስላል ነገር ግን በይበልጥ ስዕላዊ ነው ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (23፡ 1-4)፡ የእግዚአብሄር ቃል ለሕዝቅኤል እንደ ገና እህትማማቾች በነበሩ በሁለት ሴቶች ምሳሌ መጣ፡፡ እህቶቹ እስራኤል የተከፈለች መንግስት ከመሆኗ በፊት ያለዉን ጊዜ ወክለዋል (ቁጥር 1-2) ፤ ሁለቱም ሴቶች እንደ ሴተኛ አዳሪ በዚያን ጊዜ በነበሩበት ስፍራ በግብፅ በልጅነታቸዉ በሴሰኝነት ተገበሩ (ቁጥር 3) ፡፡ “ ዖሖላ ከቤተ መቅደሱ የተለዬ የራሷ የነበረ የማደሪያ ስፍራ ሰማሪያን የሚወክል የራሷ ድንኳን ማለት ነው ፤ ዖሖሊባ እግዚአብሄር አምልኮን የመሰረተባትን ኢየሩሳሌምን ሲወክል ድንኳኔ በእርሷ ዉስጥ ነው ማለት ነው “ (ቁጥር 4) ፡፡

ሕዝቅኤል (23፡ 5-10)፡ በቁጥር (5-10) ሕዝቅኤል የእስራኤልን አመንዝራነት ከአስራዊያን ጋር አስቀምጦታል ፤ በታሪክ አሶራዊያን እስራኤልን በማሸነፍ ሕዝቡን ወደ ምርኮ ወስደዋል ፡፡ ቀጥር 5 “ በፍቅር በመከተል ገለሞተች “፣ በቁጥር (5-6) ተለይተዋል ፤ ዖሖል (እስራኤል) ለእነርሱ ራሷን ብቻ አይደለም የሸጠችዉ ጣዖቶቻቸዉንም አመለክችም (ቁጥር 7-8) ፡፡ ቁጥር 9 ለደስታ የሰጠችዉ ነገር ሲያጠፋት ነዉ የሚያመለክተዉ ፤ አሶራዊያን ከሴት እና ከወንድ ልጆቿ ጋር እንድትሞት አደረጓት (ቁጥር 10) ፤ ይህ ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት ሆነ ፡፡ ሕዝቅኤል ለሰሜኑ መንግስት መሞት ምክንያት በመሆን ተፈጥሮ የነበረዉነረ ነገር መልክ እየሳለ ነበር ፡፡

ሕዝቅኤል (23፡ 11-21)፡ ዖሖሊባ (ይሁዳ) በእቷ (በእስራኤል) ላይ የሆነዉን አይታለች ነገር ግን ከእህቷ ይበልጥ አመንዝራ እና በጣም ነዉረኛም ነበረች (ቁጥር 11) ፤ በይበልጥ አሶራዊያን በመከተል አመነዘረች (ቁጥር 12-13) ፡፡

ቁጥር (14-15) የማይታመን የፖርኖ ግሪፊ መልኮች ናቸው - ዖሖሊባ በቅጥሮች ላይ የተሳሉትን የወንዶች ስዕል ባዬች ጊዜ አመንዝራነቷን ጨመረች ፤ ስዕሎቹ ብዙ ኃጢዓት ዉስጥ እንድትገባ ምክንያት ሆኗት ፡፡ የይሁዳ ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች ይበልጥ ኃጢዓትን አድርገዉ ነበር ፤ ሕዝቡ ለእነርሱ አድርገዉት ከነበረዉ የተሻለ የሚመስልን አዩ፡፡ ይሁዳ ወደ ባቢሎናዊያን ዞረች ወደ እርሷም በመምጣት አረከሷት ፤ ከዚያ በኋላ ከእነርሱ በመዋረድ / በመጥላት ተመለሰች (ቁጥር 16-17) ፡፡ እግዚአብሄርም ከሰማሪያ/ከእስራኤል ተለይቶት እንደ ነበረዉ በመጥላት ከእርሷም ተለዬ (ቁጥር 18) ፡፡ በምላሹም ዖሖሊባ በይበልጥ ኃጢዓትን በመስራት እንደ አህዮች እና ፈረሶች ተከታተለች (ቁጥር 19-21) ፡፡ ይህ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያንን እየገደለ ነው ፤ ፖርኖ ግራፊ ሰዎች ከዚህ በፊት በፍፁም አድርገዉት የማያዉቁትን ነገር እንዲያደርጉ ምክንያት እየሆነ ያለና በራሳቸዉ የሚያደርጉት አይደለም ፡፡

ሕዝቅኤል (23፡ 22-34)፡ ስለዚህም የደቡቡም መንግስት የእግዚአብሄር ፍርድ ይደርሰበታል ፡፡ “ አፍቃሪዎቿን “ በእርሷ ላይ እንደሚመጡ ያነሳሳል (ቁጥር 22-24) ፤ ወዳጆቿ በይሁዳ ላይ በጥምረት በመምጣት ያጠፋታል ይለያዩአታልም (ቁጥር 25-26) ፡፡ በሰይፋቸዉም በኩል እግዚአብሄር የይሁዳን ብልግና መጨረሻ ያስቀምጥለታል (ቁጥር 27-30) ፡፡ ይሁዳ የእህቷን መንገድ ተከትላ ስለ ነበር፣ ይሁዳ “ ከእህቷ ፅዋ ትጠጣለች “ ማለትም የቁጣ ፅዋን በኃይለኛዉም እንደምትጠፋ እና ባድማ እንደምትሆን ያመለክታል (ቁጥር 32-34) ፡፡

መደምደሚያ

ይሁዳ እግዚአብሄርን ረስታ እና ከእርሱ ዞር ብላ ስለ ነበር ሕዝቡ የዚያን ኃጢዓት ዉጤት ይገጥማቸዋል (ቁጥር 35) ፡፡ ከአሕዛብ አማልዕክት ጋር የላቸዉ የፍቅር ጉዳያቸው የተወደደች ከተማቸዉ እንድትጠፋ ምክንያት ይሆናል ፤ ይህ ፍርድ እና ጥፋት በኢየሩሳሌም ላይ እየመጣ እንደ ነበር ትንቢታዊ ቃል ነበር ፤ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ተከናወነ፡፡

  1. J. Vernon McGee, Ezekiel: Notes & Outlines, n.p.; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/ezekiel/ezekiel-outline.cfm.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 914–915.

  3. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 206.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Ezekiel, p. 180; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.

  5. MacArthur, p. 915.

ጥያቄዎች

  1. በሕዝቅኤል 22 የኢየሩሳሌም ሰዎች እያደረጉአቸዉ የነበሯቸዉ አንዳንድ ኃጢዓቶች ምን ነበሩ ? በአሁኑ ዘመን ልምድ ከእነዚህ ኃጢዓት ማንኛዉን ወይም ሁሉንም ታያላችሁ ? ከእነዚህ ኃጢዓቶች ዉስጥ በአንድኛዉ ራሳችሁ ተሰናክላችሁ ታውቃላችሁ ?
  2. ሕዝ (22፡ 9-11) አንብቡ ፤ እነዚህ የተለዩ ኃጢዓቶች ከሌሎች በበለጠ ይከሷችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አይከሷችሁም ? ስለ እነዚህ ኃጢዓቶች እግዚአብሄር ምን አለ (ዘሌ 19፡ 16, 20፡ 18, ሕዝ 18፡ 6, 11) ? እግዚአብሄር በሰዉነት ላይ የሚሰራ ኃጢዓት ከሌላ ኃጢዓት የከፋ እንደሆነ ያስባል ብላችሁ ታስባላችሁ (1ቆሮ 6፡ 15-20) ? ለምን ወይስ ለምን አያስብም ?
  3. በሕዝ (22፡ 23-27) ምን እየሆነ ነበር ? በቀድሞ ዘመን ይህ ችግር ነበር ? በፊት እግዚአብሄር በዚህ ላይ አስጠንቅቋቸዉ ነበር (2ዜና 28፡ 22፣ ኤር 2፡ 34፣ ሆሴ 9፡ 8-9) ? በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሄር ሕዝቡን የሚያስጠነቅቅባቸዉ ጥቂት መንገዶች ምንድን ናቸው ? አሁን እግዚአብሄርን በማዳመጥ የተሸላ ነገር እናደርጋለን ?
  4. በሕዝቅኤል 23 ሕዝቅኤል እንደ ጋለሞታ ጠቅሷቸዉ የነበሩት ሁለት እትማማቾች እነማን ነበሩ ? ማን/ምን ከእግዚአብሄር አርቆ ሳባቸው ? ታናሺቱ እህት ከታላቂቱ እህቷ ማንኛዉንም ነገር ተምራለች ?
  5. ሕዝ (23፡ 39) እስራኤላዊያን እንዴት ልጆቻቸዉን እንዴት እንደሚሰዉ እና በዚያዉ በተመሳሳይ ቀንም እንዴት ወደ እግዚአብሄር ቤት እንደሚሄዱ ያገናኘዋል ፤ በፍቃደኝነት ኃጢዓት በመስራት በተመሳሳይ ጊዜ እግዚአብሄርን ማምለክ እንችላለን ብላችሁ ታምናላችሁ ?
  6. በሕዝቅኤል (22-23) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 22:30

“I searched for a man among them who would repair the wall and stand in the gap before Me on behalf of the land so that I might not destroy it, but I found no one.”

እግዚአብሔር አንድ ሰው ብቻ በመሀል ጣልቃ እንድገባና በምድር ላይ ያሉትን ሁሉ ወክሎ በእርሱ ፊት እንድቆም ፈለገ ፡፡ አንድ ጻድቅ ሰው ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ እንኳ ሰው ሊያገኝ አልቻለም ፡፡ ስለዚህም ቁጣውን አፈሰሰው የቁጣውም እሳት እስራኤልን በላ ፡፡

እግዚአብሔር ህዝቡ በጨለማና በብርሃን መካከል ያለውን ክፍተት በመዝጋት ይቆሙ ዘንድ ይሻል ፡፡ እርሱ ሰዎች ለልጆቹ ጠባቂና ማላጅ እንድሆኑ ይፈልጋል ፡፡ እርሱ ሰዎች እንድያስጠነቅቁና ክርስቶስ ዳግም እስኪመጣ እውነትን እንድናገሩ ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሔር እናንተ እንድትጠነክሩና እንድትጸኑ ፤ አይኖቻችሁን በእርሱ ላይ እንድታደርጉ ፤ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልም በድፍረትና በእምነት እንድትኖሩ ያዛችኋል ፡፡ እናንተ እግዚአብሔር ለህዝቡ ምልጃን እንድያደርጉ ከሚጠራቸው መካከል ናችሁ ፡፡ ስለ ቤተሰባችሁ ፣ ስለ ማህበረሰባችሁ እና ስለ ሀገራችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ ፡፡ ሰዎች እርሱን ብቻ እውነተኛ አምላክ አድርገው በመቀበል ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ ጸልዩ ፡፡ ዛሬ ለዚህ ትውልድ እውነትን ተናገሩ ፡፡ በመካከል ያለውን ክፍተት እርቀት ለመሙላት የሚቆም ሰው ሁኑ ፡፡

“ ቅጥርን የሚጠግንን ፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ ፥ ነገር ግን አላገኘሁም ። “

  • ሕዝቅኤል 22፡30

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 1:1 — “ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ። “

ኢሳይያስ 59:16 — “ ሰውም እንደሌለ አየ ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት ፥ ጽድቁም አገዘው ። “

ኤፌሶን 6:13 — “ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ ። “