Major Prophets Ezekiel

The Final Judgment

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 20-21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 635 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እንደ ነቢይ ሕዝቅኤል ሌሎች ታላላቅ ነቢያቶች እንዲያደርጉት ተጠይቀዉ ያልነበሩትን መልዕክቱን በድራማ መልክ እንዲያሳይ ተጠየቀ ፤ ለተወዳጅ ማጥናት ያደርጋል ፡፡ ኢሳይያስ (1-39) ሁሉም ስለ መርገም እና ጨለማ ነው ፡፡ ሕዝቅኤል ተመሳሳይ መልዕክት ይሰጣል ነገር ግን የሽማግሌዎቹን ልብ ያውቃል ፡፡ ኮንስታብል በምዕራፍ 19 ለሕዝቅኤል መልዕክት ሁለት ክፍሎች እንዳሉ ይገልፃል፡ “ የመጀመሪያዉ ክፍል (ቁጥር 1-9) የዳዊትን መስመር እና ሁለቱን መንግስቶች ለመግለፅ የአንበሳን እና ልጆቿን ስዕል ይጠቀማል ፤ ሁለተኛዉ ክፍል (ቁጥር 10-14) የመጨረሻዉን ጠንካራ ቁጥቋጦ ወይም ንጉስ በማካተት እስራኤልን ለመግለፅ የወይን ስዕልን ይጠቀማል “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (20፡ 1-4)፡ ቁጥር 1፡ “ በሰባተኛዉ አመት በአምስተኛዉ ወር በወሩም በአስረኛዉ ቀን “ በሚለዉ ቀን ይጀምራል ፤ ያ ቀን ከክርስቶስ ልደት 591 በፊት ነሐሴ 14 ይሆናል ፡፡ በዚያ ቀን አንዳንድ ሽማግሌዎች እግዚአብሄርን ለማማከር ወደ ሕዝቅኤል መጡ (ቁጥር 1) ፡፡ በግዞት ለነበሩት ለሌሎቹ በኃላፊነት እንደ ነበሩና የኃይማኖት ስራቸዉን ለመስራት እየተጫወቱ እንደ ነበር ለማሳየት እየሞከሩ ነበሩ ፤ ዋይርስቤ ሕዝቅኤል “ ልባቸዉ ከእግዚአብሄር ጋር በትክክል እንዳልነበር እና ለትዕዛዝ እግዚአብሄርን የመጠየቅ መብት እንዳልነበራቸዉ ያዉቃል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ወደ ሕዝቅኤል በመምጣት (ቁጥር 2) ሕዝቅኤልን “ እንደ ሰዉ ልጅ “ በማለት ደረሰው (ቁጥር 3) ፤ ያን ቃል አብዛኛዉን ጊዜ በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ እና በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ ጥቅም ላይ የዋለ ነበር ፡፡ ሕዝቅኤል የክርስቶስ ጥላ የነበርና ክርስቶስ ምን ሊያደርግ እንደሚመጣ ጥላ ነበር ፡፡

እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ሽማግሌዎቹን እግዚአብሄርን በፍፁም ማማከር እንደማይችሉ እንዲነግራቸዉ ነገረው - “ እኔ ሕያዉ ነኝና በእናንተ ዘንድ አልጠየቅም “ (ቁጥር 3) ፤ እግዚአብሄር ዘላለማዊ ስለሆነ ለምክር እድል አልነበረም ፡፡ በምዕራፍ 18 ሕዝቡ ንስኃ መግባት ስላልነበራቸዉ እና ከጣዖት መመልስ ስላልነበር ወደ እርሱ ለመመለስ ፍቃደኞች እንዳልነበሩ አሁንም ያውቃል ፡፡ በቁጥር 4 እግዚአብሄር ሕዝቅኤል ለሕዝቡ የቀድሞዉን ታሪክ “ የአባቶቻቸዉን የርኩሰት ተግባር “ እንዲገልፅላቸዉ ነገረው ፡፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄር አባቶቻቸዉ አድርገዉት በነበረዉ ነገር እየፈረደባቸዉ እንዳልነበር (18፡ 20) ነገር ግን “ በተመሳሳይ ያለማመን እና በአመፅ ኃጢዓት ጥፋተኞች ስለ ነበሩ የወቅቱ ትዉልድ ላይ እየፈረደባቸዉ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡ ቀድሞ ምን ሆኖ እንደ ነበር በማየት ተመሳሳይ ስህተት እንዳያደርጉ ፈለገ ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 5-8)፡ የታሪካቸዉ ማጠቃለያ በቁጥር 5 ይጀምራል ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን በመምረጥ ከእነርሱ ጋር ኪዳንን አደረገ ፤ ከግብፅ ወደ ተስፋይቱ ምድር አወጣቸዉ ነገር ግንጣዖቶቻቸዉን በመጣል ትዕዛዙን አላከበሩም (ቁጥር 5-8) ፡፡ ዋይርስቤ በግብፅ የያዕቆብ ቤተሰብን እድገት ያሳያል ፤ ግብፅ በገቡ ጊዜ 66 የቤተሰብ አባላት ነበሩ ከዮሴፍ ቤተሰብ ጋር 70 ነበር ቁጥራቸው (ዘፍ 46፡ 8-26) ፤ “ ነገር ግን አይሁዶች ከግብፅ በወጡ ጊዜ ተዋጊ ወንዶቹ ብቻ ቁጥራቸው ከ600,000 በላይ ሲሆኑ (ዘኁ 1፡ 46) ስለዚህም በሕዝቡ ዉስጥ 2ሚሊዮን ሕዝብ ይሆናሉ “ ፤ እግዚአብሄር በታላቅነት ባርኳቸዉ ስለ ነበር ከግብፅ ከመዉጣታቸዉ በፊት ጣዖታቸዉን እንዲጥሉ ብቻ ጠየቃቸው ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 9-10)፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር በመታመን ከግብፅ በማወጣት በምድረበዳ መራቸው (ኢሳ 66፡ 5) ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ቁጣዉን ለማፍሰስ በቂ የሆነ ምክንያት ነበረዉ ነገር ግን ስለ ስሙ ሲል ሕዝቡን አዳናቸው ፤ እግዚአብሄር ስለሚገባቸዉ ሳይሆን ስለ ራሱ ስም ሲል ስለ እስራኤል እንደ ሰራ “ አብራርቷል ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 11-12)፡ እግዚአብሄር ትዕዛዙን እና እንዴት እንደሚኖሩና ሰንበቱን እንዴት እንደሚጠብቁ ተስፋዉን ወደ ሰጠባቸዉ ስፍራ ወደ ሲና መራቸው (ቁጥር 11-12) ፤ ዋይርስቤ “ እስራኤል እግዚአብሄር ክብሩን በገለጠላቸዉ እና ሕጉን በሰጣቸዉ ስፍራ በሲና ለሁለት አመት እንደ ዘገዩ “ ይናገራል ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 13-26)፡ አንድ ጊዜ ሕዝቡ የእግዚአብሄርን ሕግ እና ስርዓትን ከነበራቸዉ በኋላ ሲናን በመተው ወደ ምድረበዳ ሄዱ ፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ሕጉን ባለማክበር እና ሰንበቱን ባለመጠበቅ በምድረበዳ በእርሱ ላይ አመፀ (ቁጥር 13) ፡፡ ዋይርስቤ “ ከሲና ከሄዱ በኋላ አይሁዶች እግዚአብሄር ወደ ከነዓን እንደሚገቡ እና ተስፋ የተገቡላቸዉን ርስቶች ወደ ነገራቸዉ ስፍራ በቃዴስ በርና ሰፈሩ (ዘኁልቁ 13-14) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ በዚያ እግዚአብሄር እንደሚሰጣቸዉ ተስፋ ገብቶላቸዉ ወደነበረችዉ ምድር 12 ሰላዮች ተልከዉ ነበር ሁለቱ እንጂ ሁሉም ቀድመዉ በነበሩት ሕዝቦች በፍራት ተመልሰዉ መጡ ፤ ካለመታዘዛቸዉም የተነሳ እግዚአብሄር ሊያጠፋቸዉ ተመለከተ ነገር ግን እስራኤልን ከግብፁ ሲያድን ያዩት ሁሉም ሕዛቦች ክብሩን እንዲያዩት አደረገ (ቁጥር 14) ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ወደ ምድረበዳ በመመለስ እንደ ገና አባቶቻቸዉ ሲያመልኳቸዉ የነበሩትን የጣዖት ርኩሰትን ሳይሆን ሕጉን እንዲከተሉ ነገራቸው (ቁጥር 17-18) ፡፡ እግዚአብሄር እንዲከተሉት ነገራቸው (ቁጥር 19) ፤ ልጆቹ በእርሱ ላይ ቢያምፁበትም እንኳን (ቁጥር 21) እግዚአብሄር በአሕዛብ ፊት ስሙ እንዳይረክስ ፍርዱን አዘገየው/ያዘው (ቁጥር 22) ፡፡ በአመፅም ምክንያት የሕዝቡ መበታተን መጣ (ቁጥር 23-25) ፡፡ ቁጥር 26 የኃሰት አምልኮን ይጠቅሳል ፡፡ በሁሉም ደረጃ ላይ እግዚአብሄር አይኖቻቸዉን ከጣዖት ላይ በማንሳት በእርሱ ላይ እንዲያስቀምጡ አስጠነቀቃቸው ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 27-31)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች “ እስራኤል በተስፋይቱ ምድር “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን በአብዛኛዉ ስለ እስራኤላዊያን ሰጠው (ቁጥር 27) ፤ ሕዝቡ ተስፋይቱ ምድር በገባ ጊዜ በሁሉም ዛፍ እና ኮረብታ ስፍራዎች ጣዖትን አመለኩ ልጆቻቸዉንም እንደ መስዋዕት አቀረቧቸው (ቁጥር 28-29, 31) ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 31-32)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች “ በባቢሎን እስራኤልን እንደ ስደተኛ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፤ ሕዝቅኤል ያለፈዉን ወደ ኋላ በመተው አሁንም በእግዚአብሄር ላይ እያመፁ እንደ ሆነ አመለከተ ፤ እግዚአብሄር እነርሱን ለመምከር እምቢ ያለበት ምክንያት ነበር (ቁጥር 31) ፡፡ ዋይርስቤ “ ልክ እንደ አባቶቻቸወ እየኖሩ ነበር ! “ አለ ፡፡

ሕዝቅኤል (20፡ 33-44)፡ ሕዝቅኤል ካለፈወ እና በወቅቱ ካለዉ ወደ ወደፊቱ ቀጠለ/ተጓዘ ፡፡ ዋይርስቤ እነዚህ ጥቅሶችን “ የእስራኤል የወደፊት መንግስት “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ በቁጥር (33-34) እግዚአብሄር በሚመጣዉ ዘመን በአንድ ላይ የተበታተነዉን ሕዝብ መልሶ በመሰብሰብ በበረታች እጅ፣ በተዘረጋ ክንድ እና በፈሰሰች መዓት እገዛቸዋለሁ ይላል (2ቆሮ 6፡ 17) ፡፡ እግዚአብሄር ከኃጢዓታቸዉ ፍርድ ሕዝቡን በአንድ ላይ ያመጣቸዋል (ቁጥር 35) ፡፡ በክርስቶስ መመለስ በኩል እያንዳንዱ ግለሰብ ስላደረገዉ ነገር ፍርድ ይመጣል (ቁጥር 36) ፤ ማክአርቱር “ ከበትርም በታች ታልፋላችሁ “ የሚለዉን ሀረግ በመጠቀም “ እግዚአብሄር ታላቅ እረኛ በመሆን ተገቢ ስለ ነበር የእረኛን መልክ ጠጠቀመ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ ያመፁትን ይቃወማቸዋል ወደ መንግስቱም እንዲሆኑ አይፈቀድላቸዉም (ቁጥር ቁጥር 38) ፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሄር አመፅን በድነት በመንፈሱ ሳይታደስ ማንም ሰዉ በመሲሁ መንግስት አካል ለመሆን ተመልሶ ወደ ፍልስጤም ሲመጣ እንደማያይ “ ይገልፃል አንድ ቀን ሁሉም እግዚአብሄርን ያገለግላሉ (ቁጥር 39-44) ፡፡

መደምደሚያ

አይሁዶች በአዲስ ኪዳን ክርስቶስ ወደ ራሱ ህዝቡን ለመሰብሰብ እስኪመለስ ድረስ የተበታተኑ እንደሆኑ የሚያሳየዉን መልክ አይረዱትም ፡፡ ሕዝ (21፡ 27) ምዕራፍ 20፡ “ ባድማ ባድማ ባድማ አደርጋታለሁ ፤ ፍርድ ያለዉ እስኪመጣ ድረስ ይህች ደግሞ አትሆንም ለእርሱም እሰጣታለሁ “ በማለት ያጠቃልለዋል ፤ ክርስቶስ እስኪመለስ ድረስ ተስፋ የለም ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Ezekiel, p. 150; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 199.

  3. Wiersbe, p. 199.

  4. Wiersbe, p. 199.

  5. Wiersbe, p. 200.

  6. Wiersbe, p. 200.

  7. Wiersbe, p. 200.

  8. Wiersbe, p. 200.

  9. Wiersbe, p. 201.

  10. Wiersbe, p. 201.

  11. Wiersbe, p. 201.

  12. Wiersbe, p. 201.

  13. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 911.

  14. MacArthur, pp. 911–912.

ጥያቄዎች

  1. ሕዝ (20፡ 11) ላይ ተመልከቱ ፤ በአጠቃላይ 613 ሕጎች እንዳሉ እናዉቃለን ፤ በዚህ ጥቅስ መሰረት ሰዉ ለመኖር ምንያክሉን መጠበቅ እንደሚያስፈልገዉ ታስባላችሁ ? ያዕ (2፡ 10) ይህን ጥቅስ እንዴት ያጠናክረዋል ?
  2. በሕዝ (20፡ 25) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን መልካም ያልነበረ ስርዓትን እና መኖር የማይችሉበትን ሕግ ሰጠኋችሁ አላቸዉ ፤ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ግለፁ ፤ (ዘዳ 28፡ 15-68)
  3. በሕዝ (21፡ 25-27) ለመሲሁ ማጣቀሻን ታያላችሁ ? የቁጥር 27 ትንቢት ስለ መሲሁ ምን ማለት ነው ? (ሉቃ 1፡ 32)
  4. በሕዝቅኤል (20-21) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 20:31

“‘When you offer your gifts, making your children pass through the fire, you continue to defile yourselves with all your idols to this day. So should I be consulted by you, house of Israel? As I live’—this is the declaration of the Lord GOD—‘I will not be consulted by you!’”

የእስራኤል ሽማግሌዎች እግዚአብሔርን ይጠይቁ ዘንድ መጡ ፡፡ በምላሹም እግዚአብሔር ከእርሱ ፊታቸውን በማዞር ስለተመላለሱባቸው መንገዶች ደግሞም እንዲሁ ለራሳቸው ብቻ እንደኖሩ አስታወሳቸው ፡፡ እግዚአብሔር ለተመረጡ ህዝቦቹ እንደዚህ ያሉ ትልልቅ አሳቦችና ተስፋዎች አሉት ፡፡ ልክ ሽማግሌዎቹ እግዚአብሔርን በጠየቁ ጊዜ ፣ እርሱ ደግሞ ወደ አመጸኛ ልባቸው ተመለከተ ፡፡ እነርሱ ሁሉንም ነገር ተመልክተው ፈልገው ነበር ነገር ግን እግዚአብሔርን አልተመለከቱም አልፈለጉም እናም አሁን ከእርሱ አዲስ ቃልን መልዕክትን ሻቱ ፡፡ እርሱም በቀጥታ በነቢዩ ሕዝቅኤል መለሰላቸው ፡- “እኔ ሕያው ነኝና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም ፡፡ “

ምናልባትም እናንተም ልክ እንደ እስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ እግዚአብሔር አዲስን ነገር ይናገራችሁ ዘንድ በመናፈቅ ወደ እርሱ ትመጡ ይሆናል ፡፡ እርሱንም ለማየት ወይም ለመስማት ለምን እንዳልቻላችሁ ትጠይቁም ይሆናል ፡፡ ሆኖም ግን ሁለት ጎን ያለውን ህይወት እየኖራችሁ ከሆነና አንድኛውን እግራችሁን ከኢየሱስ ሌላኛውን ደግሞ ከአለም ጋር አድርጋችሁ እየተራመዳችሁ ከሆነ ተደናቅፋችሁ ትወድቃላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር ግማሹ ሳይሆን ሙሉ ልባችሁ ከእርሱ ጋር እንድሆን ይፈልጋል ፡፡ ምናልባት እርሱን በደንብ ማየትና መስማት ትችሉ ዘንድ ራሳችሁን ትሁት ለማድረግና ልባችሁን ለማንጻት ጊዜው አሁን ይሆናል ፡፡ ልባችሁን ትሁት በማድረግ ፣ ውድ የሆነውን የእግዚአብሄርን ጥሪ ከውኑ ፡፡ እርሱ ያውቃችኋል ፣ ያያችኋል ደግሞም እናንተን ሁላችሁን ይወዳችኋል ፡፡ እርሱ ከእናንተ የሚፈልገው ትህትናችሁን ፣ ታማኝነታችሁን ፣ በፍጹም ልባችሁ የሆነ መሰጠትን አምልኮን ብቻ ነው ፡፡

“ ቍርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን ? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ “

  • ሕዝቅኤል 20፡31

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 13:11–14 — “ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና ። ሌሊቱ አልፎአል ፥ ቀኑም ቀርቦአል ። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን ፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን ፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ ። “

ቆላስያስ 1:10–11 — “ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ ፡፡ “

1ኛ ጴጥሮስ 5:5–6 — “እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፡፡ “