Individual Responsibility For Sin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 18-19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምዕራፍ 18 በባቢሎን ለስደተኞቹ ሌላ ትንቢት ነው ፡፡ ዛሬ በሚመጣዉ ዉጤት ላይ ያሉ ጥያቄዎችን እናያለን - በቤተሰቦቻችን ወይም በአያቶቻችን ድርጊት ምክንያት ችግር/ስቃይ ይደርስብናል ወይስ በራሳችን ድርጊት ነው የሚደርስብን ? ሕዝቅኤል ሕዝቡን በበፊት መኖር እንዲያቆሙና ስለ ራሳቸዉ ኃጢዓት ኃላፊነት እንዲወስዱ ነገራቸው ፡፡ ይኖራሉ ወይም ህያዉ ይሆናሉ የሚለዉን ቃል 13 ጊዜ ሲጠቀም ትሞታላችሁ ወይም በህይወት አትኖሩም የሚለዉን ቃል ደግሞ 14 ጊዜ ተጠቅሟል ፤ ማክጊ እነዚህ ቃሎች “ ህይወት እና ሞት በእስራኤል ፊት እንደ ተቀመጠ “ ለመግለፅ የሚጠቅሙ እንደሆኑ አመልክቷል ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (18፡ 1-4)፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን “ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ብለዉ “ ምሳሌዉን ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በማገናኘት ለምን እየተጠቀሙ እንደ ነበር ጠየቀው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ኤርምያስ ላይ እግዚአብሄር “ በዚያ ዘመን ሰዉ ዳግመኛ እንዲህ አይልም ፡- አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉየልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ፤ ነገር ግን ሰዉ ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል ፤ መራራዉን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶች ይጠርሳሉ “ በማለት ተናግሯል (ኤር 31፡ 29-30) ፡፡
ማክአርቱር “ እግዚአብሄር አስቀድሞ ሀገራዊ ቅጣቱን ተናግሮ ነበር ነገር ግን ለዚህ መሰረቱ የግል ኃጢዓት እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ ሕዝቅኤልም “ ከዚህ በኋላ ይህን መስመር አይጠቀምም ! የጥፋተኝነትን ካርድም አይጫወትም “ አለ ፤ እግዚአብሄር ነፍስ ሁሉ የእርሱ እንደሆነና ጥፋተኛ ሰዉ ብቻ እንደሚሞት አብራራ (ቁጥር 4) ፡፡ ሁሉም ሰዉ ኃጢዓት ያደርጋል (መክ 7፡ 20, ሮሜ 3፡ 23)ኃጢዓት የሰራ ሁሉ ይሞታል (ሕዝ 18፡ 4, ሮሜ 6፡ 23) ፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሄር አድሎን አልሰራም ነገር ግን እያንዳንዱን ሰዉ ስለ ራሱ ኃጢዓት ተጠያቂ በማድረግ በመያዝ ፍትሀዊ ነበር “ በማለት ይናገራል ፡፡
ሕዝቅኤል (18፡ 5-18)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮችን “ አባቶቻችሁን መዉቀስ አትችሉም “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ሕዝቅኤል በቁጥር (5-13) ልክ ስለሆነ አባትና ልክ ስላልሆነ ልጅ ተናገረ ፤ ልክ የሆነዉ አባት ጣዖትን አላመለከም የእግዚአብሄርን ሕግ እና ስርዓቱንም ጠበቁ (ቁጥር 5-8) ፡፡ ዋይርስቤ ሕዝቅኤል አባትዬዉ ያላደረጋቸዉ ስምንት አሉታዊ ነገሮችን እና ያደረጋቸዉን ስምንንት አዎንታዊ ነገሮችን እንደ ዘረዘረ ያመለክታል ፡፡ አባትዬው ፃድቅ እና የታመነ ስለ ነበር በህይወት ይኖራል (ቁጥር 9) ፡፡
ይሁን እንጂ ልክ የሆነዉ አባት ደም በሚያፈስሰው እና ብዙ መጥፎ ነገር ባደረገዉ አመፀኛ ልጁ ልክ አልነበረም ፤ አባቱ ላለማድረግ መርጧቸዉ የነበሩትን ሁሉንም ነገር አደረገ በጣዖት አምልኮም በመሳተፍ ሁሉንም የእግዚአብሄርን ሕግ እና ስርዓት ችላ አለ (ቁጥር 10-12) ፡፡ ይህ ልክ ያልሆነ ልጅ የርኩሰትን ተግባር አድርጎ ስለ ነበር በሕይወት አይኖርም (ቁጥር 13) ፡፡
በቁጥር (14-15) ሕዝቅኤል ልክ ያልሆነዉ ልጅ አባት እንደሆነና ልክ የሆነ ልጅ እንደ ነበረው ገለፀ ፤ ልጁ (ልክ የሆነዉ አባት የልጅ ልጅ) አባቱ የፈፀመዉን ልክ ያልሆነ ድርጊት በመመልከት አለማድረግን መረጠ (ቁጥር 14) ፤ ልጁም አባቱ የጀመረዉን የኃጢዓት ኡደት ሰበረው ፡፡ ጣዖትን አላመለከም የእግዚአብሄርን ሕግ እና ስርዓትን መጠበቅን መረጠ (ቁጥር 15-18) ፤ እዚህ ጋር አንድ ምሳሌ አለ፡ ንጉስ ሕዝቅያስ እንደ እግዚአብሄር የሆነ አስተዳዳሪ ነበር ነገር ግን ልጁ ምናሴ ክፉ ነበር ፤ የምናሴ ልጅ አሞጽ ክፉ ነበር ነገር ግን ልጁ ኢዮስያስ እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ነበር (ማቴ 1፡ 10-11) ፡፡
ሕዝቅኤል (18፡ 19-24)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ ራሳችሁን መዉቀስ/መተቸት ትችላላችሁ “ በሚል ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ሕዝቅኤል ለኃጢዓት የግል ተጠያቂነት መኖሩን እንደ ገና ለመናገር ልጅን ተጠቅሟል (ቁጥር 19) ፤ ሕዝቅኤል ሁሉም ሰው ለራሱ ወይም ለራሷ ኃጢዓት ተጠያቂ እንደሆነና ክፉ ሰዉ ከኃጢዓቱ በመመለስ የእግዚአብሄርን ሕግ በመጠበቅ በፅድቅ ከኖረ በህይወት እንደሚኖር አጠንክሮ ተናገረ ((ቁጥር 20-21) ፡፡ “ የበደለዉ በደል ሁሉ አይታሰብበትም በሰራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል “ (ቁጥር 22) ፤ ያ ማለት ምናሴና አሞፅ አስከፊ ነገሮችን ቢያደርጉም በንስኃ ወደ እግዚአብሄር መመለስ ከቻሉ ይኖራሉ ማለት ነው ፡፡
እግዚአብሄር በግዞት ያሉት ከባለፈዉ ነገር እንዲማሩ ፈለገ ፡፡ ቁጥር 23 እግዚአብሄር ሰዎች ከእርሱ ዞር ባሉ ጊዜ ደስ እንደማይለዉ ነገር ግን ሰዎች ወደ እርሱ በመመለስ በህይወት ሲኖሩ ደስ ይለዋል ይላል (1ጢሞ 2፡ 3-4, 2ጴጥ 3፡ 9) ፡፡
ነገር ግን አንድ ፃድቅ ሰዉ ከእግዚአብሄር በተመለሰ ጊዜ ወደ እግዚአብሄር ሳይመለስ እንደ ክፉ ሰዉ ርኩስ ነገር ቢያደርግ ይሞታል/አይኖርም ፡፡ በእርግጥ ፅድቅን ያደረገዉም ሰዉ ምንም ነገር አይታሰብለትም (ቁጥር 24) ፤ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር መልካሙን ከክፉዉ ያለፅድቅ ለመቆየት ምክንያት አልነበረዉም ፡፡ ማክአርቱር “ የቀድሞ ግልፅ ቅድስና የቀና/እዉነተኛ አልነበረም እግዚአብሄርም እንደ እዉነተኛ የእምነት ማረጋገጫ አያስታዉሰውም “ በማለት ይናገራል ፡፡
ሕዝቅኤል (18፡ 25-32)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ እግዚአብሄርን መዉቀስ/መተቸት አትችሉም “ ፤ በግልፅ ሕዝቡ እግዚአብሄር ትክክል አይደለም እያሉ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ትክክል ያልነበረ የእነርሱ መንገድ እንዳልነበር ጠየቃቸው (ቁጥር 25) ፤ ፃድቃን የነበሩ ይሁን እንጂ ወደ ኃጢዓት ዞር ማለትን የመረጡ ነበሩ ፡፡ ስለዚህም ጥፋተኞች ስለነበሩ ይቀጣሉ ይሞታሉም (ቁጥር 26) ፤ ነገር ግን ከክፋታቸዉ በመመለስ ወደ እግዚአብሄር ከተመለሱ በህይወት ይኖራሉ (ቁጥር 27) ፡፡ ሕዝቅኤል በግዞት እያሉ በህይወታቸዉ እና በንስኃቸው ዉስጥ ለማሰብ ጊዜ እንደ ነበራቸው ገልፆአል (ቁጥር 28) ፡፡ ለማብራራት ቁጥር 29 ቁጥር 25 ይደግማል ፡፡
በቁጥር (30-32) ኮንስታብል እግዚአብሄር “ ለሕዝቡ ሕጉን ከመተላለፋቸው እንዲመለሱ እና ያ ከሆነ ኃጢዓታቸው በህይወታቸዉ እንቅፋት እንደማይሆንባቸው አያረጋግጥም “ በማለት ልመናን አደረገ ፡፡ እግዚአብሄር አዲስ ልብ እና አዲስ መንፈስ እንዲኖራቸዉ እንደሚያስፈልጋቸዉ ነገራቸው (ቁጥር 30-31) ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቦቹ እንዲሞቱ አይፈልግም ፡፡
መደምደሚያ
ሕዝቅኤል እንዴት ከባርነት እንደሚወጣ እያወራ ነበር ፤ ከባርነት መዉጫዉ ብቸኛዉ መንገድ በአዲስ መንፈስ በኩል ነው ፡፡ ሕዝ (36፡ 26) “ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በዉስጣችሁ አኖራለሁ ፤ የድንጋዩንም ልብ ከስጋችሁ አወጣለሁ የስጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ “ ፤ ያ የሚሆንበት ብቸኛዉ መንገድ በአዲሱ ዳዊት - በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው ፡፡
J. Vernon McGee, “Outline for Ezekiel”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/ezekiel/ezekiel-outline.cfm.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 909.
MacArthur, p. 909.
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 196.
Wiersbe, p. 196.
Wiersbe, p. 197.
MacArthur, p. 910.
Wiersbe, p. 197.
Thomas Constable, Dr. Constables Expository Bible Study Notes: Ezekiel, p. 148; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.
ጥያቄዎች
-
በሕዝ (18፡ 2) እግዚአብሄር በእስራኤል ከዚህ በኋላ እንዳይጠቀሙት ያለዉ ምሳሌ ምን ነበር ? ይህ ምሳሌ ምን ማለት ነው ?
-
በሕዝ (18፡ 20) እግዚአብሄር ኃጢዓት ከሰራ ማን እንደሚሞት እና ማን አይሞት አለ ?
-
በሕዝ (18፡ 23 እና 32) በሁለቱም በክፉዎች ሞት ደስ እንደማይሰኝ ሕዝቡን ነገራቸው ፤ ስለዚህ ከእነርሱ ዉስጥ አብዛኞቹን ለምን በመቅጣት አጠፋቸው ? በሕዝ (18፡ 32) መሰረት ያን እንዴት ማስወገድ ይችላሉ?
-
እግዚአብሄር የእስራኤልን እናት ለመግለፅ የተጠቀመባቸዉ ሁለት አባባሎች ምንድን ናቸው (ሕዝ 19፡ 2, 10) ? ምን ማለት እንደሆኑ ግለፁ ?
-
በሕዝቅኤል (18-19) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 18:30–32
“‘Therefore, house of Israel, I will judge each one of you according to his ways.’ This is the declaration of the Lord GOD. ‘Repent and turn from all your transgressions, so they will not be a stumbling block that causes your punishment. Throw off all the transgressions you have committed, and get yourselves a new heart and a new spirit. Why should you die, house of Israel? For I take no pleasure in anyone’s death.’ This is the declaration of the Lord GOD. ‘So repent and live!’”
እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እርሱ ከባርነት ነጻ ሊያወጣቸው የሚችለው ወደ እርሱ ከተመለሱ ብቻ እንደሆነ ግልጽ አድርጎ ይነግራቸዋል ፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ ትላንትናቸው እነርሱን ሊገልጻቸውም እንደማይችል እንዲሁ ፡፡ እግዚአብሔር ህይወትን ይሰጣቸው ዘንድ ናፈቀ ! እግዚአብሔር ፍትሐዊ ነው እናም ህዝቡን የሚዳኘው መንገዳቸውን በማየት ነው እናም እግዚአብሔር ህዝቡ ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው ከእርሱ ጋር መኖር ሲጀምሩ ፣ ህዝቡን ነጻ በማውጣት ደስ ይሰኛል ፡፡
ዛሬም ቢሆን የእግዚአብሔር ቃል ያው ነው ፡፡ ቤተሰቦቻችሁም ሆኑ ትላንታችሁ እናንተን አይገልጹዋችሁም ፡፡ በቤተሰባችሁ ውስጥ ካለ የትውልድ ኃጢአት ነጻ መውጣት ትችላላችሁ ፡፡ በመጠጥ ሱስ ውስጥ የነበረ ቤተሰባችሁ የእናንተን የዛሬ ማንነት ሊገልጽ አይችልም ፡፡ የቤተሰቦቻችሁ እዳ የእናንተን ማንነት ሊሰራ አይችልም ፡፡ በቤተሰባችሁ ውስጥ ያለ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ፍቺ እናንተ ጋር ሲደርስ በጌታ በኢየሱስ ኃይል ይቆማል ፡፡ ደሙ በደልን ሁሉ ይሸፍናል ፡፡ ጌታ የመጣው ከኃጢአትና ከበደል ነጻ ሊያወጣችሁ ነው ፡፡ ጌታ በዘር ውስጥ ያለ የኃጢአት ባርነትን መርገምን መስበር ይችላል ፡፡ ፍላጎታችሁ ይህ እንዲሆን ከሆነ ፣ ወደ እርሱ ተመልሳችሁ እርሱን መፈለግ አለባችሁ ፡፡ ንሰሀ ግቡ ፣ ከመተላለፋችሁ ከበደላችሁም ተመለሱ እናም ጌታን ፈልጉ ፡፡ ነጻ ትወጣላችሁ ደግሞም በቤተሰባችሁ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ይጀምራል ፡፡
“ የእስራኤል ቤት ሆይ ፥ ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፤ ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ ። የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ ? የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ ። “
- ሕዝቅኤል 18፡30-32
ተጨማሪ ጥቅስ
ሕዝቅኤል 18:23 — “‘ በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን ? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን ? “
1ኛ ጢሞቲዎስ 2:3–4 — “ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው ። “
2ኛ ጴጥሮስ 3:9 — “ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።