Major Prophets Ezekiel

The Parable Of The Adulterous Wife

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 16-17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 633 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትን ምዕራፍ 14 ብቻ ሸፍነናል ፤ ምዕራፍ 15 ስምንንት ቁጥሮች ብቻ እና ጥቅም ስለሌለዉ የወይን ምሳሌ ነው፡፡ በሕዝቅኤል መፅኀፍ ዉስጥ በባቢሎን በምርኮ ሳሉ ለሕዝቡ በስዕል እንዲያሳያቸዉ/እንዲነግራቸው እግዚአብሄር ከአንዱ ራዕይ በኋላ ሌላ ይሰጠዋል ፡፡ በምዕራፍ 4 ሕዝቅኤል ሮብዓም ንጉስ ከሆነበት ጊዜ እስከ የሴዴቅያስ አገዛዝ ቆይቶ 394 አመታት እስከወደቀበት ጊዜ የአለመታዘዛቸዉን ጊዜ ለመወከል 390 ቀናት በግራ ጎኑ መተኛት አስፈልጎት ነበር ፤ ዋይርስቤ ሮብዓም ለእግዚአብሄር ታማኝ ከነበረባቸዉ ሰዎስት አመታት ጀምሮ ጠቅላላ ያለመታዘዝ ጊዜው 390 አመታት ያክል ነበር ፡፡

በስምንንት ቁጥሮች ብቻ ምዕራፍ 15 የማይጠቅም ወይን ምሳሌ ለእርሱ ጥቅም የሌላቸዉ ሆነዎ ስለ ነበር ከእስራኤል ጋር ወደፊት መጓዝ እንደማይችል የእግዚአብሄር አዋጅ/ንግግር ነው ፡፡ ምዕራፍ 16 በመፅኀፉ ዉስጥ ረጅሙ ምዕራፍ ነው (63 ቁጥሮችን ይረዝማል) ፡፡ ታማኝ/እዉነተኛ ለመሆን 24 ቁጥሮች ብቻ ባሉት በምዕራፍ 17 ላይ ለማስተማር ፈለኩ ነገር ግን እግዚአብሄር አይፈቅድልኝም ፤ ምዕራፍ 16 በእግዚአብሄር አመንዝራ ሚስት የተሰየመ ነው ፡፡

ታላላቅ ነቢያቶች ተልዕኮዉን አጋርተዋል ፤ ኢሳይያስ ስለሚመጣዉ ጥፋት ትንቢትን ተናግሯል ነገር ግን ሲሆን አላዬም ፤ ኤርምያስ ስለመምጣቱም ትንቢትን ተናግሯልም ከመወሰዱም ለጥቂቶቹ ምስክር/በአይኑ አይቷል ፤ ልምምዱን/የደረሰበትን እና ስሜቱን በሰቆቃዉ ኤርምያስ እንሰማል ፡፡ ሕዝቅኤል በመጀመሪያዉ ስደት ወደ ባቢሎን የተወሰደ ስለ ነበር በባቢሎን ዉስጥ እና እግዚአብሄር በሰጠዉ ራዕይ በኩል ቀምሶታል/አይቶታል ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (16፡ 1-7)፡ ዋይርስቤ በቁጥር (1-14) “ እስራኤል ታላቅ ፍቅር እንዳገኘች “ ያመለክታል ፡፡ መፅኀፍ ቅዱስን በምናጠና ጊዜ በቀጥታ መጀመሪያ መጥፎ ዜና ከዚያ ደግሞ መልካም ዜናን እናገኛለን ፤ በሕዝቅኤል በተቃራኒዉ እዉነት ነው ፡፡ መልካም ዜና እናያለን ከዚያ በመቀጠል መጥፎ ዜናን እናያለን ፡፡ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ቁጥሮች ዉስጥ እስራኤል የእግዚአብሄርን ፍቅር ቀመሰች ፤ የእግዚአብሄር ቃል ምሳሌ ሲሆን አመንዝራ የሆነችዉን ሴት ምታሳይ ኢየሩሳሌም ዋናዋ ገፀ ባህሪይ ነበረች ፡፡ ሕዝቅኤል ሕዝቡን ትናትናቸዉን ያሳስባቸዋል ፤ አይሁዶች “ ዉሾች “ ብለዉ ከሚጠሯቸው ጣዖት ከሚያመልኩት ቤተሰቦች በከነዓንምድር የመጡ ነበሩ (ቁጥር 1-3) ፤ ሲወለዱ ለእነርሱ ማንም ርህራሄ አልነበረውም (ቁጥር 4-5) ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር የሚያስፈልጋቸዉን በማየት ወደዳቸው ፡፡ ኮንስታብል፡

“ ከነዓን የኢየሩሳሌም መነሻና መወለጃ ስፍራና በሕገወጥነት የታወቀች ምድር ነበረች ፤ ስለሆነም እስራኤላዊያን ወደ ጣዖት አምላኪነት ማዘንበላቸዉ ግልፅ ነገር ነበር ፡፡ በቅድመ ጳጳስ ዘመናት የኢየሩሳሌም መስራቾች ዕብራዊያን ሳይሆኑ አሞራዊያን እና ኬጢያዊያን ነበሩ ፤ አሞራዊያን እና ኬጣዊያን ሁለቱም የከነዓን ሰዎች የነበሩና ብዙጊዜ በብሉያ ኪዳን ዉስጥ ሁሉንም ከነዓናዊያን እንደሚወክሉ “ ይገልፃል ፡፡

በቁጥር 6 እግዚአብሄር “ በደምሽ እንዳለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ “ ይላል ፤ አንዳንድ ምሁራን ቁጥር 6 በእግዚአብሄር እና በእስራኤል መካከል የኪዳኑ መጀመርን እንደሚወክል ያመለክታሉ ፡፡ ማክአርቱር “ መኖር ! “ “ ምናልባትም እግዚአብሄር ሕዝቡን በመሰረተ ጊዜ የአህርኃምን፣ የይስሐቅን እና የያዕቆብን የጳጳስነት ዘመን ያመለክታል “ በማለት ይናገራል ፡፡ በእግዚአብሄር ሴቷ(እስራኤል) በዛች (ቁጥር 7) ፤ በዛች የሚለዉ ቃል ሕዝቡን በማመልከት “ በግብፅ በተቀመጠችበት 430 አመታት ጊዜ የእስራኤልን የእድገት ጊዜ የሚገልፅ፣ ባዶ ነገር ግን ያደገች እና የምታምር፣ እስራኤል ያለምንም የባህል እና ስልጣኔ ጥቅም እርቃኗን እንደ ነበረች ይገልፃል “ ፡፡

ሕዝቅኤል (16፡ 8-14)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ ከህፃንነት ወደ ትዳር መመስረቻ እድሜ ላይ የመቀየር ስዕል ናቸው ፡፡ ቁጥር 8 በእርሷ ላይ ተቤዢዋን በመጎናፀፊያ በመሸፈን ከሩት (3፡ 9) ጋር ተመሳሳይ ቋንቋን ይጠቀማል ፡፡ እግዚአብሄር ራሱን ለእርሷ(ለእስራኤል) በሕዝቡና በእግዚአብሄር መካከል በኪዳናዊ ስምምነት ሰጣት (ቁጥር 8) ፤ አጠባት፣ ቀባት በሚያምር ልብሶች እና ጌጦች አለበሳት በራሷም ላይ የራስ ጌጥ/አክሊል አስቀመጠባት (ቁጥር 9-12)፡፡ ማክአርቱር “ እነዚህ በተለመዶ የሚቀርቡ ለንግስት የጋብቻ ስጦታዎች እንደ ነበሩ “ ያመለክታል ፡፡ ከሁሉም ነገር በምርጡ አጌጠች እንዲሁም የተገኘዉን ምርጡን ምግብ ተመገበች ፤ ይህ በኢያሱ እና በዳዊትም ዘመን የምድሪቱን መያዝ የሚያመለክት ነው (ቁጥር 13) ፡፡ በቁጥር 14 እግዚአብሄር በረከቱን በእርሷ ላይ ስላፈሰሰ ዝናዋ በአሕዛብ/በአለም ሕዝብ መካከል ተሰማ ፡፡

ሕዝቅኤል (16፡ 15-22)፡ ይሁን እንጂ እስራኤል በራሷ የታመነች በመሆን አጠገቧ ከሚመጡት ሁሉም ጋር በማመንዘር ፍላጎት በመጋደም አመንዝራ መሰለች (ቁጥር 15) ፤ ዋይርስቤ “ ከሌሎች አመንዝራዎች በተለዬ እስራኤል አፍቃሪዎቿን በመመልከት ከእርሷ ጋር ኃጢዓት እንዲሰሩ ከፈለቻቸው ! እግዚአብሄር በቸርነት ለእርሷ የሰጣትን በረከቶች እና ንብረቶችን በመዉሰድ ጣኦትን ለመስራት እና ለማምለክ አዋለቻቸው - ጌጧን እና ልብሷን፣ ምግቧን እና ልጆቿንም “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ሁሉንም በመርሳት በረከሰ እና በማይታዘዝ ባሀሪያቸው ወደ ጣዖት ተመለሱ (ቁጥር 16-22) ፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ በአሜሪካ ይህ አብዛኞቹን አማኞቻችንን ይገልፃል - ሁሉንም የእግዚአብሄርን በረከት የተቀበሉ ነገር ግን በራሳቸዉ ትዕቢት ከእግዚአብሄር ዞር በማለት በእግዚአብሄር ላይ የማይታዘዙና አመፀኞች የሆኑትን ይገልፃል ፤ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ክርስትና ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር ከመምራት ይልቅ የራስን ስም/ዝና መገንባት እንደሆነ ይመስላል ፡፡ በራሳችን ጣዖት በምንመላለስ/በምንሰራ ጊዜ ሁልጊዜ ልጆቻችን ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል !

ሕዝቅኤል (16፡ 23-34)፡ እግዚአብሄር የፍርድ አምላክ ነው እስራኤልም በእነርሱ ላይ እንዲፈርድ ገፍታዉ ነበር (ቁጥር 23-25) ፡፡ በቁጥር (26-29) ሕዝቅኤል እስራኤል ከእግዚአብሄር ዉጪ እንዴት እርዳታን ለማግኘት ሞክራ እንደ ነበር አስቀምጧል/አሳይቷል ፤ ከጥቅስ ወደ ጥቅስ እስራኤል እንዴት ከጣዖት እና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር እንዳመነዘረች ይገልፃል ፡፡ እስራኤል አንድ አመንዝራ ሰዉ አገልግሎቷን ለመቀበል ለሆነ ሰዉ እንደሚከፍለዉ በተመሳሳይ መንገድ እንዲረዷት ለእነርሱም ከፈለች (ቁጥር 30-34) ፡፡

ሕዝቅኤል (16፡ 35-42)፡ በእነዚህ ቁጥሮች የእስራኤል ያለመታዘዝ ፍርዶች ታዉቀዉ/ተገልፀው ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም “ ወዳጆቿን “ ሲያመልኳቸዉም የነበሩትን ጣዖቶች በአንድ ላይ በእስራኤል ላይ በመሰብሰብ እርቃናቸዉን እገልጣለሁ አለ (ቁጥር 37) ፡፡ እግዚአብሄር ጣዖቶቻችሁን ሁሉ በፊታችሁ ሲያስቀምጥ ! ከዚያም በእነርሱ ላይ በመፍረድ ደም አፍሳሾቻቸዉን ሲያመጣ አስቡት (ቀጥር 38-41) ፡፡ ቁጥር 40 ለአንድ አመንዝራ የሚያስፈልገዉን በድንጋይ ተወግሮ መሞትን ያመለክታል ፤ ከዚያም የእግዚአብሄር ቁጣ ያበቃል (ቁጥር 42) ፡፡

ሕዝቅኤል (16፡ 43-52)፡ እግዚአብሄር የእርሱ ድርጊት ለምን አስፈላጊ እንደ ነበር መከላከያን ሰጠ (ቁጥር 43) ፡፡ እግዚአብሄር “ ልክ እንደ እናት፣ ልክ እንደ እሕት “ ምሳሌን በመጠቀም እስራኤልን ከሰዶም እና ከሰማሪያ ጋር አወዳደራት (ቁጥር 44-52) ፡፡

ሕዝቅኤል (16፡ 53-60)፡ እግዚአብሄርም ሰዶምንና ሰማሪያን እንደሚያድሳቸዉ ቃል ገባ (ቁጥር 53-59) ፤ እስራኤልንም እንደሚያድሳት ቃል ገባ፡ “ ነገር ግን በሕፃንነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር ያደረገሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ የዘላለምንም ቃል ኪዳን አጸናልሻለሁ “ (ቁጥር 60) ፡፡

መደምደሚያ

ይህ ዘላለማዊ ኪዳን ሁለተኛዉ የክርስቶስ መምጣት ነው ፡፡ እምነታችሁን በክርስቶስ ላይ በምታስቀምጡ ጊዜ በፍፁም እንደ ገና ስለ እግዚአብሄር ፍርድ አትጨነቁም ፤ ቁጥር 63 “ ስላደረግሽዉም ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ ታስቢ ዘንድ ታፍሪም ዘንድ ስለ እፍረትሽም ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ቃል ኪዳኔን ከአንቺ ጋር አጸናለሁ እኔም እግዚአብሄር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ ይላል ጌታ እግዚአብሄር “ (ቁጥር 63) ፡፡

የሕዝቅኤል መልዕክት በአንድ ጥቅስ ሊጠቃለል ይችላል፡ “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረዉ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና “ (ዮሐ 3፡ 16) ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 173.

  2. Wiersbe, p. 191.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Ezekiel, pp. 122-123; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 907.

  5. MacArthur, p. 907.

  6. MacArthur, p. 907.

  7. Wiersbe, p. 191.

ጥያቄዎች

  1. በሕዝቅኤል 16 እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን ከማትታመን አንድ አመንዝራ ሚስት ጋር አወዳደራት ፤ በምዕራፉ ዉስጥ ስታጠኑ የት እንደምትኖሩ ተመሳሳይነትን ታስታዉላላችሁ ? አዎ ከሆነ በምን መንገድ ?
  2. በሕዝ (16፡ 60-63) እግዚአብሄር እንዴት ልዓላዊ፣ መሀሪ እና አፍቃሪ እንደሆነ እንዴት አሳዬ ?
  3. ሕዝ (17፡ 22-24) ለአዲስ ክርስቲያን እንዴት ትገልፁታላችሁ ? እነዚህ ቁጥሮች ከዮሐ (15፡ 1-5) ጋር ሊገናኙ ይችላሉ ? ለምን ወይስ ለምን አይገናኙም ? እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡ ጊዜ ምን ሌላ የመፅሀፍ ክፍል ወደ አይምሯችሁ ይመጣል ?
  4. በሕዝቅኤል (16-17) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 16:62–63

“‘I will establish My covenant with you, and you will know that I am Yahweh, so that when I make atonement for all you have done, you will remember and be ashamed, and never open your mouth again because of your disgrace.’ This is the declaration of the Lord GOD.”

በሕዝቅኤል በኩል የተነገረው የእግዚአብሔር መልዕክት የእስራኤልን ህዝብ እንደ ዘማዊ ሚስት መጨረሻም እንደ ሴት አዳሪ አድርጎ ይመስላቸዋል ፡፡ መጀመሪያ ላይ አስራኤል እግዚአብሔርን ተቀብሎ ይረዳውና ህይወትን ይሰጠው ዘንድ እርሱን ይፈልግ ነበር ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ እስራኤል በራሱ ተደገፈ ፣ ከጣዖት ጋርም አመነዘረ ፣ ከእግዚአብሔርም ፊቱን መለሰ ፡፡ ፊታቸውንም ከእርሱ ስለ መለሱ ተነቢውን ቁጣና ፍርድ ተቀበሉ ፡፡ ነገር ግን አሁንም በዘላለማዊ ኪዳኑ በኩል ተስፋን አቀረበላቸው ደግሞም እስራኤላውያን ለሰሩት ሁሉ ስርየትን ሰጠ ፡፡ እነርሱ የተመረጡ ህዝቦቹ ነበሩ ፡፡

እግዚአብሔር ልጁ አድርጎ መርጧችኋል ፡፡ እርሱ በእርሱ ዘንድ የሚገኘውን የተትረፈረፈ ህይወት ታገኙ ዘንድ ይሻል ፡፡ ምንም እንኳ ለራሳችሁ በቂ እንደሆናችሁ ብታስቡም ፣ ሌሎች አማልክትን ብትፈልጉም እንድሁም በዚህ አለም መንገድ ብትመላለሱም እንኳ ፣ ኢየሱስ እናንተን መውደዱን አያቋርጥም ፡፡ አግዚአብሔር ስለ እናንተ ይሞት ዘንድ ልጁን ላከ ፡፡ እናንተ ደህንነትንና የዘላለም ህይወትን ታገኙ ዘንድ ኢየሱስ ስለበደላችሁ መስዋዕት በመሆን ሞተ ፡፡ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ኪዳኑን ለመጠበቅ የታመነ ነው ፡፡ እናንተ ዝም ብላችሁ ይህንን መቀበል ብቻ ነው ያለባችሁ ፡፡ እንዲህ በሉ ፡- “ አዎን ፣ ኢየሱስ ከኃጢአቴ እንዳዳነኝ አምናለሁ ፡፡” አዎን በሉ የዘላለምም ህይወት ይኖራችኋል ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ለመኖር እሺ በሉ ፡፡ እርሱ ገና ድሮ ለእናንተ እሺ ብሎአል እናም እናንተን አብዝቶ ይወዳችኋል !

“ ስላደረግሽውም ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ ፥ ታስቢ ዘንድ ታፍሪም ዘንድ ስለ እፍረትሽም ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ፥ ቃል ኪዳኔን ከአንቺ ጋር አጸናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ “

  • ሕዝቅኤል 16፡62-63

ተጨማሪ ጥቅስ

ሕዝቅኤል 16:6–7 — “ በአንቺም ዘንድ ባለፍሁ ጊዜ በደምሽም ውስጥ ተለውሰሽ ባየሁሽ ጊዜ ፦ በደምሽ እንዳለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ ፤ አዎን ፦ በደምሽ እንዳለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ ። በእርሻ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ ፥ በእጅጉም አጌጥሽ ፤ ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆንሽ ፥ ተራቍተሽም ነበርሽ ። “

ዮሐንስ 3:16 — “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ። “

ሮሜ 5:8–9 — “ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ። ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን ። “