Devastating Judgements
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 14-15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሕዝቅኤል መፅሀፍ አጠቃላይ እይታ/ዳሰሳ፡ የእስራኤል ሕዝቦች ወደ ሁለት መንግስታት ተከፍለዉ ነበር ፤ የቀድሞዉቹ አብዛኞቹ ነገስታቶች በአጠቃላይ ጥሩ ነገስታት ስላልነበሩ በሕዝቅኤል ላይ ያለዉ ንግግር በአጠቃላይ ስለ ሕዝቡ ምርኮ ነው ፡፡ ሰዎስት ጊዜ ከአገር መወሰድ ደርሶአል - በዳንኤል ጊዜ፣ በኤርምያስ ጊዜ እና በሕዝቅኤል ጊዜ፡፡ መፅሀፉን በመዘገበ/በፃፈ ጊዜ ሕዝቅኤል በምርኮ ነበር ፤ ኢየሩሳሌም ጠፍታም እንደ ነበር አያዉቅም ፡፡ ምን እንደሚመጣ ትንቢትን እየተናገረ ስለ ነበር ንግግሩ/ቋንቋ የሚያወዛግብ ነው ፤ የታላላቅ ነቢያቶች የመፅኀፍ ቅዱስ መፅኀፍ ለመሲሁ መመለስ ሕዝቦቹን ዝግጁ ለማድረግ የተፃፉ ነበሩ ፡፡
ሕዝቡም ከትንቢቶቹ ዉስጥ ማንኛዉም መቼ ወደ እዉነት እንደሚመጡ ጠየቁ ፡፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ (12-14) ወደ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፍላቸዋል፡ “ የዉሸት ልበ ሙሉነት፣ የሀሰት ትንቢት፣ የዉሸት አምልኮት እና የሀሰት ተስፋ “ ፤ ዋይርስቤ “ በምዕራፍ 12 ስለ ዉሸት በራስ መተማመን ሲናገር በምዕራፍ 13 ደግሞ ስለ ኃሰተኛ ትንቢት ይናገራል ፤ በመጨረሻም በምዕራፍ (14፡ 1-11) ስለ ኃሰት አምልኮ ሲያወራ በ14፡ 12-23 ስለ ኃሰት ተስፋ ያወራል “ ፡፡ ስነምግባር/አምልኮ የዉሸጽ/ሀሰተኛ የሆነ የኃይማኖት አምልኮን ያመለክታል ፤ የኃሰት አምልኮ/ኃይማኖት ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት አልነበረውም ፡፡ በቁጥር (12-23) የኃሰተኛ ተስፋ ቋንቋ አለ ፡፡ በአመፀኞቹ ቤት ችግሩ የእግዚአብሄር በነበሩ ነገሮች ላይ ሳይሆኑ ኃሰተኛ በሆኑ ነገሮች ላይ መደገፋቸዉ ነበር ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (14፡ 1-11)፡ በሕዝ(3፡ 24) ሕዝቅኤል በቤቱ ነበር ፤ አብዛኛዉን አገልግሎቱን ከቤቱ በመሆን አደረገ ፡፡ ሽማግሌዎች ወደ ሕዝቅኤል በመምጣት በእርሱ ፊት ለፊት ተቀመጡ ፤ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን በቤቱ ዉስጥ እራሱን እንዲዘጋ አዘዘው ፤ የሚወጣበት ብቸኛዉ ጊዜ እግዚአብሄር እንዲሰራ ትዕዛዝን በሰጠዉ ጊዜ ብቻ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ እነዚህ መሪዎች ፊታቸዉን በማየት ክፉ መንገዳቸዉን ለመከተል እና የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለማርከስ እንደወሰኑ ላዩት ነቢያት እግዚአብሄር እንደ ገለጠው የእግዚአብሄርን ምክር በመፈለግ አስመሳዮች እንደሆኑ “ ተናገረ ፤ እነዚህ ሽማግሌዎች ክፍሉን ማየት/መመልከት ፈለጉ ነገር ግን በሚገባ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት አይፈልጉም ፡፡
እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን እነዚህ ሽማግሌዎች ኃሰተኛ ነቢያቶች እንደ ነበሩ ገለጠለት ፤ በልባቸዉ እና በፊታቸዉ ፊት ለፊት ጣኦቶችን እና የማሰናከያ ድንጋዮችን አስቀምጠዉ ነበር ፡፡ በቁጥር 4 ሕዝቅኤል ቃሉን በማዉራት እዉነትን ይናገራል ፤ እነዚህ ሽማግሌዎች ሁሉም ከጣዖታቸዉ የተነሳ ከእግዚአብሄር የራቁ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ልባቸዉ በነበረበት ስፍራ መሰረት ደረሳቸው ፤ ይህ ልምምድ ኢየሱስን ደርሶበት ከነበረዉ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ኢየሱስ በእርሱ ዘመን ፈሪሳዊያንም በተመሳሳይ ኃጢዓት ጥፋተኞች እንደ ነበሩ ተናግሯል (ማቴ 15፡ 8-9) እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ እንዳሉ አሳዉቋል “ ብሏል ፡፡ ሁሉም ታላላቅ ነቢያቶች የሚመጣዉ ክርስቶስ ጥላ በመሆን አገልግለዋል ፤ ማቴ (15፡ 9) ከሕዝቡ ጋር የክርስቶስን ልምምድ ምሳሌ ነው ፡፡
የኃይማኖተኝነት መንፈስ አስከፊ/ኃይለኛ ቅጣትን አምጥቷል ፡፡ አሁን በሕዝቡ ላይ ከኃይማኖት መንፈሳዊነት ጋር የተገናኜ ጉዳይ ተነሳ ፤ ሕዝቅኤል በቤቱ በሽማግሌዎቹ ገጥሞት የነበረዉ ነገር የዉሸት አምልኮ ነበር ፡፡ ይህ የኃሰተኛ የኃይማኖት መንፈስ መታወቅን ተረድተዉ ከነበር መነቃቃትን ለመለማመድ አንድ እድል ይኖራል ፡፡
ከሕዝቅኤል የነበረዉ ቃል ንስኃ እንዲገቡና ከጣዖት እንዲመለሱ ነበር ፤ አሁንም ንስኃ የመግባት ጊዜ እድል ነበር ፡፡ በእነዚህ ቁጥሮች ያሉት ጣዖቶች ለእግዚአብሄር ክብር የማይሆኑ ብዙ ቁጥር ያላቸዉን ነገሮች መወከል ይችላሉ ፤ የተለያዩት ነገሮች ቀስ በቀስ በጊዜ ብዛት ጣዖቶች ሆነዋል ፡፡ ዛሬ ለእግዚአብሄር መሰጠት ያለበትን ጊዜ የወሰዱ ጣዖቶቻችን ላይ ትኩረት ተሰጥቷል ፤ ዋይርስቤም “ በአሁኑ ጊዜ አማኞች ለሆነ ምስል በልባቸዉ ፍቅር ሲኖራቸዉ አይደለም ነገር ግን በፍቅራችን እና በመታዘዛችን እግዚአብሄርን የሚተካ ነገር በእርግጠኝነት ጣዖት ነው “ ብሏል ፡፡
በቁጥር 6 የሕዝቅኤል መልዕክት ከሁሉም ጣዖቶች ንስኃ መግባትና መመለስ እንደሚያስፈልጋቸው ግልፅ ነበር ፡፡ ጣዖት ከእግዚአብሄር ላይ ፍቅራቸዉን እና ጊዜአቸዉን ይወስዳል ፡፡
ለእግዚአብሄር ከሚሰጠዉ ትኩረት በላይ ለሌሎች ነገሮች ትኩረት ከተሰጠ ንስኃ መግባት ያስፈልጋል ፡፡ በቁጥር 7 መልዕክቱ “ የአይሁድ ስደተኞች ስለ ጣዖት እና ጣዖቶችን የማምለከ ኃጢዓትን ሀሳባቸዉን በመቀየር ብቻዉን በአምልኮ ዋጋ ወዳለዉ እግዚአብሄር መመለስ አስፈለጋቸው ፤ እግዚአብሄር እያንዳንዱን ኃጢዓተኛ በግል በመዳኘት እያንዳንዱን በግል በመመልከት (ቁጥር 7) ከእነርሱ ዉስጥ ጥቂቶቹን ሌሎቹን ምርኮኞች ለማስጠንቀቅ እንደ ምሳሌ እንደሚጠበቅባቸዉ (ቁጥር 8) “ ነበር ፡፡
ማክአርቱር “ እግዚአብሄር ሐሰተኛ ነቢያቶችን ብቻ የተጣራ በሚመስል ሁኔታ ብቻ ያስታቸዋል ፤ በፍቃደኝነት የእግዚአብሄር ቃልን በገፋ ጊዜ የዚያን ዉጤት የጨለማ ደመናን በማስቀመጥ ወይም በዚሁ እንዲቀጥል በመፍቀድ እዉነቱን ስለሚደብቀው ሰዉዬው በራሱ የግትርነት ፍቃድ ራሱን ያስታል “ በማለት ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ሐሰተኛ ነቢያቶች አሳሳታቸው ፤ ማክአርቱር “ ይህ እግዚአብሄር እስራኤልን ቃሉን በጥላቸ በመግፋት ሙጭጭ ላሉት ክፉ ጣዖቶች አማካሪዎች ከሰጣቸዉ ጊዜ ጋር ተመሳሳይ መርህ እንደሆነ (ቁጥር 20፡ 24, 26) “ ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር “ ሰዎች እዉነትን በገፉ ጊዜ ከራሳቸዉ ዝንባሌ ኋላ እንዲፈልጉ በመፍቀድ ለሀሰትም አሳልፎ ይሰጣቸዋል (20፡ 39) ፤ ይህ በሮሜ (1፡ 18-32) የተመዘገበ የመተዉ ቅጣት እንደሆነ “ ይቀጥላል ፡፡ በተጨማሪም ይህ እግዚአብሄር ምርጫ እንዲደረግ መፍቀዱን ያሳያል ፡፡
ዋይርስቤ “ በእስራኤል ሁሉም ሰዉ አስዕርቱን ትዕዛዞች እንደሚያዉቁ እና ጣዖትን ማድረግ እና ማምለክ ኃጢዓት እንደሆነ እንደሚያስተዉሉ (ዘጸ 20፡ 1-6) “ ፅፏል ፡፡ ቅጣታቸዉን እና የምርጫቸዉን ዉጤት ይሸከማሉ ፡፡
በቁጥር 11 ሕዝቡ በቅጣታት ዉስጥ እና በብቸኝነት/በመተዉ መዓት ዉስጥ ያልፋሉ ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና የእግዚአብሄር ሕዝብ ይሆናሉ ፡፡ በመጀመሪያዎቹ 11 ቁጥሮች ሽማግሌዎቹ በሕዝቅኤል ፊት በመቀመጥ ኃይማኖተኛነትን እየተገበሩ ነበር ፡፡ በቁጥር 12 የተስፋ ቋንቋ የተሰጠ ነበር ፡፡
በቁጥር 12 የእግዚአብሄር ቃል እንደ ገና ወደ ሕዝቅኤል መጣ ፤ ዋይርስቤ አራት የፍርድ ድርጊቶች እንደ ነበሩ ይገልፃል፡
“ የመጀመሪያዉ ፍርድ ርኃብ ነበር (ቁጥር 12-14)፡ እግዚአብሄር የእንጀራዋን በትር በመስበር የሰዉን እና የእንስሳትን ህይወት ያጠፋል፣ ሁለተኛዉ ፍርድ በምድሪቱ የዱር አዉሬ ነበር (ሕዝ 14፡ 15-6)፣ ሰዎስተኛዉ ፍርድ ሰይፍ ነበር ማለትም ጦርነት (ሕዝ 14፡ 17-18) የመጨረሱ ፍርድ ቸነፈር ነበር (ሕዝ 14፡ 19-20) ብዙ ጊዜ ጦርነትን እና ርኃብን የያዘ (ራዕ 6፡ 3-8) “ ፡፡
ኖኽ፣ ዳንኤል እና ኢዮብም እንኳን ከመጥፋት ኢየሩሳሌምን እና ሕዝቧን ማዳን አይችሉም ፤ እነዚህ ሁሉም ሰዎስቱም ጠንካራ እምነት ነበራቸው ፡፡ በእግዚአብሄር በሚመጣዉ ፍርድ እንኳን የሚቀሩ እና የሚያዝኑ ቅሬታዎች ይኖራሉ ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ሕዝቡን ወደ እርሱ መልሶ ለማምጣት ፍርድን ለማምጣት ወስኖ ነበር ፡፡ በራሱ ምክንያት እግዚአብሄር ያደርጋል ፤ የእግዚአብሄር ፍርድ የተረጋገጠ እና የሚረጋገጥ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ትኩረታችንን ለማግኘት ሲሞክር እናየዋለን ?
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), pp. 184–188.
Wiersbe, pp. 184–188.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 906.
Wiersbe, p. 187.
Wiersbe, p. 187.
Wiersbe, p. 187.
MacArthur, p. 906.
MacArthur, p. 906.
MacArthur, p. 906.
Wiersbe, p. 187.
Wiersbe, p. 188-189.
ጥያቄዎች
-
ሕዝቅኤል 14 በሽማግሌዎች እና በጣዖቶቻቸዉ ላይ ይናገራል ፤ ትንሽ ደቂቃ በመዉሰድ በራሳችሁ ህይወት ጣዖት እንዳለባችሁ እግዚአብሄርን ጠይቁት ፤ የሆነ ነገር ወደ አይምሯችሁ ካመጣ ይቅርታን በመጠየቅ አዉርዳችሁ ጣሉት
-
በግል አስተያየታችሁ ለጣዖት አንዳንድ ምሳሌዎች ምን ሊሆነ ይችላሉ ?
-
ሕዝ (14፡ 13-20) በምታነቡ ጊዜ ስለ ኖኽ፣ ስለ ዳንኤል እና ስለ ኢዮብ እግዚአብሄር ምን የሚል ይመስላል ? ስለ ልጆቻቸዉ እና ስለ ቤተሰባቸዉስ ?
-
በሕዝ (15፡ 6) እግዚአብሄር የኢየሩሳሌምን ሰዎች በደን መካከል ካለ ከወይን ዛፍ ጋር አወዳደራቸው ፤ እስከዚህ ስፍራ ድረስ ከእግዚአብሄር ጋር ያላችሁን መመላለስ መርምሩ ፤ ራሳችሁን እንደ ወይኑ ወይስ በደን ዉስጥ እንዳሉ ዛፎች ትመለከታላችሁ ? ለምን ?
-
በሕዝቅኤል (14-15) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 14:6
“Therefore, say to the house of Israel: This is what the Lord GOD says: Repent and turn away from your idols; turn your faces away from all your detestable things.”
የእስራኤል ሽማግሌዎች መጥተው በነቢዩ ሕዝቅኤል ፊት ተቀመጡ :: እግዚአብሔርም ሽማግሌዎቹን እንዲህ አላቸው ፡- “ ንስሐ ግቡ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ ፥ ፊታችሁንም ከርኵሰታችሁ ሁሉ መልሱ ። “ እምቢ ካሉም ፣ ያህዌ ፊቱን በእነርሱ ላይ ያዞራል ከራሱ ህዝብም ይቆርጣቸዋል ፡፡ እግዚአብሔር ያቆሙትን ጣዖት ማየት ይችላል ፣ በውጭ አይደለም ነገር ግን በውስጥ በልባቸው እንጂ ፡፡ እርሱ ለአምልኮ የተከፋፈለ ልባቸውን ያውቃል ፡፡ ሽማግሌዎቹ እግዚአብሔርን እንዳልታዘዙ ቢያውቁም ነገር ግን ክፉ ከማድረግ መመለስን አልወደዱም ፡፡
እናንተም ልክ እንደ እስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ ጎበዝ ክርስቲያን የሚያስመስሏችሁን መልካም መልካም የሚመስሉ ነገሮችን መናገር ፣ በሁሉም የክርስቲያኖች ሁነቶች አገልግሎቶች ላይ ልትገኙ ትችላላችሁ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን ማታለል አትችሉም ፡፡ እግዚአብሔር ልባችሁን ያያል ፡፡ እርሱ ልባችሁን ያውቃል ፣ አጥብቃችሁ ለመደበቅ የምትሞክሩትን የህይወት ክፍላችሁንም ጭምር ፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ውጭ ሌሎች አማልክትን እንድታመልኩ አይፈልግም ፡፡ ዛሬ እንድህ በማለት እግዚአብሔርን ለምን ፡- “ በህይወቴ ውስጥ ንስሀ እንድገባበት ደግሞም ከእርሱ አንድመለስ የምትፈልገው ነገር አለን ? “ ከኢየሱስ ጋር ያለህን ግንኙነት ሀሰተኛ አማልክት ወይም ጣዖት እንድያደናቅፍብህ እንድከለክልህ አትፍቀድ ፡፡ እርሱ ለአንተ አንተ ከምታስበው በላይ አለው ፡፡ አሁን አንተ ማየት ከምትችለው በላይ እርሱ ለአንታ ስጦታና መልካምነት አለው ፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ በረከቱን ከማየትና ከመቅመስህ በፊት ፣ በህይወትህ እውነተኛውን አምላክ ለማወቅ ጊዜና ቦታ መስጠት አለብህ ፡፡
“ ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ንስሐ ግቡ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ ፥ ፊታችሁንም ከርኵሰታችሁ ሁሉ መልሱ ። “
- ሕዝቅኤል 14፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
ሕዝቅኤል 14:4–5 — “ ስለዚህ ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ከእኔ ተለይተዋልና የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዝ ዘንድ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር ፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 10:14 — “ ስለዚህ ፥ ወዳጆቼ ሆይ ፥ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ ። “
ራዕይ 9:20 — “ በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።