Major Prophets Ezekiel

Ezekiel Dramatizes The Exile

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 11-13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 631 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በእነዚህ ምዕራፎች ያለዉ ፅሁፍ አሁንም በመጠኑ ድንገተኛ ናቸው ፤ ራዕዩ ቃሉን ተንግሮት እንደ ነበረው እየተገበረበት የሆነ እንደ ነበር ወይም ደግሞ ራዕዩ ቆይቶ ለመነገር የተቀመጠ እንደሆነ ግልፅ አልነበረም ፡፡ በምዕራፍ 12 በእግዚአብሄር ተሰጥቶት እንደ ነበረው ሕዝቅኤል ራዕዩን እየሰራበት እንደ ነበር ግልፅ ነው ፤ ምዕራፍ 11 የሚያበሳጭ ምዕራፍ ነው ምክንያቱም የእግዚአብሄር ክብር ከቤተ መቅደሱ ስለወጣ ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (11፡ 1-7)፡ መንፈስ ሕዝቅኤልን በማንሳት ወደ በቤተ መቅደሱ በምስራቅ በር ወሰደው ፡፡ ሕዝቅኤል ፀሐይን እያመለኩ የነበሩ 25 ክፉ ሰዎች ተገልጠዉለት ነበር ፤ ክፋትን በማቀድ ለንጉሱና ለከተማዋ ክፉ ምክሮችን ሰጥተዋል ፡፡

ሕዝቅኤል (11፡ 8-13)፡ ፍርድ በ25 ሰዎች ላይ ይመጣል ፤ በሰይፍም ይሞታሉ ፡፡

ሕዝቅኤል (11፡ 16-20)፡ እግዚአብሄር የተስፋዩትን ምድር መልሶ ለእስራኤል እንደሚሰጣቸዉ አረጋገጠላቸው ፤ እስራኤል ወደ ምድሪቱ በምትመለስ ጊዜ አዲስ ኪዳን እና አዲስ ዳዊት ይኖራቸዋል ፡፡

በምዕራፍ 34 መሲሁ ከዳዊት ዘር እንደሚሆን ተጠቅሷል ፤ ሕዝ (34፡ 23) በጎቹን ስለሚጠብቀዉ ስለ አዲሱ ዳዊት፣ ስለ አዲሱ እረኛ እና ስለ አዲሱ አገልጋይ ይናገራል ፡፡

ሕዝቅኤል (11፡ 22-25)፡ በአጠገባቸዉ ያለዉ በመንኮራኩር ላይ ያለዉ ኩሩቤል በእነርሱ ላይ የእግዚአብሄርን ክብር ገለጡ ፤ የእግዚአብሄር ክብር ከቤተ መቅደስ በመዉጣት ከከተማዋ በላይ ተነሳ ፤ የእግዚአብሄር ክብር ከደብረ ዘይት ተራራ በስተ ምስራቅ ቆመ ፡፡

በምዕራፍ 11 በክፉዎች ላይ የሚመጣ ፍርድ አለ ፤ ነገር ግን ቅሬታዎቹ በአዲሱ ዳዊት በኩል ይድናሉ ፡፡ እግዚአብሄር በአዲሱ ዳዊት በኩል መንጋዉን ያድናል ፤ ሕዝቅኤል ቃሉን በመናገር የእግዚአብሄር መገኘት ቤተ መቅደሱን ተለይቶ ሲሄድ ተመለከተ (ቁጥር 24-25) ፡፡ ምርኮኞቹም ንስኃ ይገባሉ ወይም እግዚአብሄርንም እንዲረዳቸዉ ጠየቁት ነገር ግን ምንም ነገር አልሆነም ፡፡

ሕዝቅኤል 12 ሌላ ራዕይን ያስተዋዉቃል ፤ የምዕራፍ 12 ቀጣዮቹ ሁለት ክፍሎች ወደ ቁጥር (1-16) እና ቁጥር (17-28) የተከፋፈሉ ናቸው ፡፡ ዋይርስቤ “ አንድ ያልተሰማ ድምፅ በኤርምያስ ኤርምያስ ነበር፣ በባቢሎን ሕዝቅኤል ነበር ፤ በድርጊቱ ስብከት እና በቃል መልዕክቱ በሁለቱም ሕዝቅኤል በቅዠት እየታመኑ የነበሩትን ሰዎች አስጠነቀቀ “ አለ ፡፡ በመላው ስብከቱም ላይ ተገበረ/ድርጊትን ፈፀመ ፤ በመቀጠለም መልዕክቱን ሰጠ ፤ መልዕክቱም በተለይ በቁጥር 12 ላይ ይገኛል ፡፡

እግዚአብሄር ሕዝቅኤል በማይሰሙ እና በማያዩ አመፀኛ ሕዝብ መካከል እንደ ኖረ ይናገራል ፤ ይህ ክርስቶስ ያደርግ ከነበረዉ ነገር ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ የአይሁድ ሰዎች ጠንካራ ልብ ስለ ነበራቸዉ ኢየሱስን አይሰሙትም ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ እና ሕዝቅኤል ሁሉም ለመሲሁ እንደ ጥላ አገልግለዋል ፡፡

ሕዝቅኤል በመልዕክቱ እንዲኖር/እንዲሰራ ታዝዞ ነበር ፤ እክቱን/ሻንጣዉን በማግኘት በዉጪ ስለሚሄድ ሕዝቡ ሊያዩት ይችላሉ ፤ የተማረከ ይመስል ነበር ፡፡ ሕዝቡም እክቱን/ሻንጣዉን ያያሉ ነገር ግን ሕዝቅኤል ሕዝቡ እየተመለከተዉ እንደ ገና ወደ ቤት ተመልሶ ይሄዳል ፡፡ በቤቱ ዉስጥ ቀዳዳን በማበጀት ይሸሽ እንደ ነበረዉ ሻንጣዉን በመዉሰድ ያወጣል ፡፡

እዚህ ስፍራ ላይ ኢየሩሳሌም አልወደቀችም ነበረ ፤ ብዙ ከሀገር መሰደዶች አሉ - ከክርስቶስ ልደት 590 በፊት፣ ሌላ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት እና እነዚህ የተከተለ ሌላ አንድ ፡፡ ይሁን እንጂ የመጨረሻዉ ከሀገር መወሰድ/መፍለስ የሆነ ስላልነበር ሕዝቅኤል የማስጠንቀቂያዉን መልዕክት እየተናገረ ነበር ፡፡

በቁጥር 7 ሕዝቅኤል እንዲ ደረግ አዝዞት የነበረዉን ምርኮኛ እንደ ነበር ሻንጣዉን በመዉሰድ እንዳደረገዉ ተናግሯል ፤ ሻንጣዉን መልሶ በመዉሰድ ጨለማ እንደ ነበር በቤቱ ቀዳዳ ዉስጥ ሄደ ፤ ይህ በትክክል ምን ይሆን እንደ ነበር መልክ ነበር ፡፡ የሚመለከቱትም ሰዎች “ ምን እያደረገ ነው ? “ በማለት ጠየቁ ፡፡

ሕዝቅኤል ይህ ለሕዝቡ ምልክት የሚሆን እንደ ነበረ ነገራቸው ፤ ይህ ለሕዝቡ ተመልሰዉ ወደ ግዞት ወደ ምርኮ እንደሚሄዱ የሚናገር ነበር ፡፡ ልዑሉም ሴዴቅያስ ሻንጣዉን በትካሻዉ ላይ በጨለማ በመሸከም ወጥቶ ይሄዳል ፤ ፊቱን ስለሚሸፈን ምድሪቱን ማየት አይችላም ፤ ይሁን እንጂ ይህ እስካሆን ሆኖ ስላልነበር ይህ ከእግዚአብሄር ትንቢታዊ ቃል ነበር ፡፡

2ነገ (25፡ 1-7) በሕዝቅኤል 12 እንደ ተከናወኑት የእነዚህን ክስተቶች መግለጫ ይመዘግባል ፤ ሕዝቅኤል ተንብዮት እንደ ነበረዉ ነበር ፡፡

ኤር(39፡ 4-7) የሴዴቅያስን እና የሁሉም ኃያላኖቹ መሸሽ መዝገብን ይይዛል ፤ በምሽት በቅጥሮች/በግንቦች መካከል ሸሹ ነገር ግን የከለዳዉያን(የባቢሎናዊያን) ሰራዊት ስለተቆጣጠሯቸው ተያዙ ፡፡ ሕዝቅኤል አድርጎት እንደ ነበረው በትክክል ያደርጋሉ ፤ በ 2ነገስት እና በኤርምያስ ያለዉ ንግግር ተመሳሳይ ነው ፡፡

ኤርምያስ እና ሕዝቅኤል በስዓቱ ስላልሆነ ነገር ፅፈዋል ነገር ግን የተነበዩት ሁሉም ነገር ቀስ በቀስ ግልፅ በሆነ መልኩ ይገለጣል ፤ ሕዝቅኤል ምን እንደሚሆን ሲናገር ኤርምያስ ደግሞ የሚሆነዉን ነገር ገለፀው ፡፡

ሕዝቅኤል እነዚህን መግለጫዎች በራሱ ያደርጋቸዉ ነበር ፤ ቁጥር 14 ሴዴቅያስ እና ጥቂት ሰዎች የሚያዙ ቢሆኑም - ቅሬታዎቹ ይቀራሉ ፡፡ ቅሬታዎቹ የሕዝቡ ተስፋ ይሆናሉ ፡፡

በቁጥር 17 ሕዝቅኤል የሚኖርበት ሌላ የስብከት ተግባር ተሰጥቶት ነበር ፤ እንጀራዉን በድንጋጤ ይበላል ፤ በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠ እንጀራዉን በላ ዉኃዉንም ጠጣ ፡፡ ይህ እየመጣ የነበረዉን ሙሉ ጥፋት ተስፋ በማድረግ የተፈፀመ ነበር ፤ ሕዝቅኤልም ከሕዝቡ ጋር በዚህ ልምምድ ዉስጥ ያልፋል ፡፡

የሕዝቅኤል ተግባር ልምምድኑ አድርጎ ከነበር በኋላ ምን ይሆን እንደ ነበር ለሕዝቡ መግለፅ ነበር ፡፡ ሕዝቡ ትንቢቱ ወደ እዉነት ሊመጣ እንደሚችል አያምኑም ፤ ቀናቶቹ ማለፋቸዉን ቀጠሉ ለማለፍ ራዕይ አልመጣም ፡፡ ማክአርቱር

“ መዘግየት የፍርዱ ቅጣት በፍፁም እንደ ማይመጣ የተሳሳተ እይታን ሰጥቷቸዉ ነበር ፤ በእርግጥ ምሳሌያዊ አባባሎች ታዋቂ ሆነዉ ስለ ነበር ሕዝቡ የሕዝቅኤልን ራዕዮች እና ትንቢቶችን እንዳይቀበሉ ምክንያት በሚሆኑ (ቁጥር 27) እና በራሳቸዉ ስፍራ ኃሰተኛ ሟርትን በሰጡ ሐሰተኛ ነቢያቶች ጥርጣሬን አላሳደጉም (ቁጥር 23, 24) “ በማለት ይናገራል ፡፡ እስካሁን የእግዚአብሄር ቃል እዉነት እንዳልነበር አላመኑም ፡፡

መደምደሚያ

የሕዝቡ አስተሳሰብ የሕዝቅኤል ራዕይ በፍፁም ወደ እዉነት እንደማይመጣ ነበር ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር መልዕክት እንደሚናገር እና በፍፁም እንደ ማያልፍ ተናገረ ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል አይዘገይም ፤ አሻፈዎች ይኖራሉ ነገር ግን አሁንም የእግዚአብሄር ቃል ወደ መሆን ይመጣል ፡፡ በአሁኑም ዘመን በማዕዘናቱ ዙሪያ ትክክል የሆነዉን የክርስቶስን ሁለተኛ መምጣት፣ የአዲሱ ዳዊት መምጣትን በሚገባ የምናምን ከሆነ መጠየቅ አለብን ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 184.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson 2005), p. 905.

ጥያቄዎች

  1. በሕዝቅኤል 11 መጀመሪያ ላይ መንፈስ ሕዝቅኤልን በማንሳት ወዴት ወሰደው ? ሕዝቅኤል ማንን አዬ ?
  2. በሕዝቅኤል 11 እግዚአብሄር እያመጣ/እያቀረበ የነበረዉ ኃጢዓት ምን ነበር ? የት ተከናወነ ? ለእስራኤል ተስፋዉ ምን ነበር ?
  3. ሕዝቅኤል እየተነበዬ በነበረበት ጊዜ በሕዝቅኤል 11 ምን ተፈጠረ ? መስተጋብሩ/ምላሹ ምን ነበር ?
  4. በሕዝቅኤል 12 በእስራኤል ለሕዝቡ ምልክት የሆነዉ እንዴት ነበር ? እግዚአብሄር አምላክ እንደሆነ ሕዝቡ እንዴት ያዉቃሉ ? ይህ ፍርድ ለአሕዛቦች እንዴት ምልክት ይሆናል ? እሱ ብቻ እዉነተኛ አምላክ እንደ ነበር ለእናንተ በምታዉቁት መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሄር ራሱን ገልጦላችሁ የነበረዉ መቼ ነበር ?
  5. እግዚአብሄር በእስራኤል ይጠቀም የነበረዉን ምሳሌያዊ አነጋገርን ማቆም ለምን ፈለገ (ሕዝ 12፡ 22-28) ? ምሳሌዎቹን ለምን እየተጠቀሙባቸዉ ነበር (ሮሜ 1፡ 25) ? ለምሳሌዉ የእግዚአብሄር መፍትሔ ምን ነበር? እግዚአብሄር ተስፋን እንደሰጣችሁ ነገር ግን እስካሁን እንዳልተፈፀመ ይሰማችኋል ? በመፅኀፍ የት ላይ እግዚአብሄር እንደማይረሳ ልታገኙ ትችላላችሁ ? (ዘፍ 8፡ 1, ዘጸ 2፡ 24-25, ሮሜ 15፡ 8)
  6. በሕዝቅኤል (11-13) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 12:22–23

“Son of man, what is this proverb you people have about the land of Israel, which goes: The days keep passing by, and every vision fails? Therefore say to them: This is what the Lord GOD says: I will put a stop to this proverb, and they will not use it again in Israel. But say to them: The days draw near,as well as the fulfillment of every vision.”

የእስራኤል ሰዎች አመጻቸውን ቀጠሉ በነቢዩ ሕዝቅኤልም በኩል በመጣው በእግዚአብሔር ድምጽ አለመኑም ነበር ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር የእያንዳንዱ ራዕይ ፍጻሜ እንደሚመጣ ግልጽ አድርጎታል ፡፡

የእግዚአብሔር ቃል “ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል ” በማለት ይናገራል ፡፡ የማታውቁት መቼ እንደሆነ ብቻ ነው ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታይ ለዳግም ምጻአቱ ዝግጁ ሆናችሁ መኖር ይገባችኋል ፡፡ ደክማችሁ እና እንቅልፍ እንቅልፍ እያላችሁ በህይወት አትመላለሱ ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነቅታችሁ ኑሩ ፡፡ በኢየሱስ እመኑ ፣ ህይወታችሁንም ለእርሱ አሳልፋችሁ ስጡ እናም መንፈሱ ይለውጣችሁ ዘንድ ፍቀዱለት ፡፡ የራሳችሁን ስራ ለመስራት ጊዜ እንዳላችሁ በማሰብ ፤ በህይወታችሁ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ በመተው ፣ ወደ ኢየሱስ ከመመለስ አትዘግዩ ፡፡ መጀመሪያ ንጹህ መሆን እንዳለባችሁ ወይም ወደ እርሱ ከመመለሳችሁ በፊት ህይወታችሁን ማስተካከል እንዳለባችሁ በማመን ወደ ኢየሱስ ከመምጣት አትከልከሉ ፡፡ እርሱ በህይወታችሁ የእርሱን ጸጋና ፍቅር እንድትቀበሉ ይፈልጋል ፡፡ ከዚያም ይለውጣችኋል በየቀኑም በኃይልና በጸጋ ያስታጥቃችኋል ፡፡ በውስጣችሁ በሚመላለሰው ኃይሉም ለዳግም ምጽዓቱ ዝግጁ ሆናችሁ ትኖራላችሁ ፡፡ ፍርኃት የለም ፣ ስቃይ የለም ፣ ጭንቀት የለም ያለው የኢየሱስ ሰላም ብቻ ነው ፡፡

“ የሰው ልጅ ሆይ ፥ በእስራኤል ምድር ፦ ዘመኑ ረዝሞአል ራእዩም ሁሉ ጠፍቶአል የምትሉት ምሳሌ ምንድር ነው ? ስለዚህ እንዲህ በላቸው ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ በእስራኤልም ዘንድ ደግሞ ምሳሌ አድርገው አይናገሩትም ፤ አንተ ግን ፦ ዘመኑና የራእዩ ሁሉ ነገር ቀርቦአል በላቸው ። “

  • ሕዝቅኤል 12፡22-23

ተጨማሪ ጥቅስ

ሕዝቅኤል 12:25 — “ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ፤ እናገራለሁ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል ፥ ደግሞም አይዘገይም ፤ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመውማለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ “

ማቴዎስ 25:10–13 — “ ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ ፥ ደጁም ተዘጋ ። በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ፥ ክፈትልን አሉ ። እርሱ ግን መልሶ ፦ እውነት እላችኋለሁ ፥ አላውቃችሁም አለ ። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ ። “

2ኛ ጴጥሮስ 3:3–4 — “ በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ ፤ እርሱም ፦ የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው ? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ፥ ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና ይላሉ ። “