Major Prophets Ezekiel

The Departure Of The Shekinah Glory Of God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 8-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 630 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሕዝቅኤል ጥናታችን እስካሁን እግዚአብሄር ለሕዝቅኤል የፍርድ መልዕክቱን መስጠቱን እንደቀጠለ አይተናል ፤ እስካሁን ሕዝቅኤል ብዙ ለሕዝቡ ሲናገር አላየነዉም ፡፡ እስካሁን ሕዝቅኤል እግዚአብሄር በሰጠው በራዕዩ እና በስዕሉ እና በስዕሉ መግለጫዎች በኩል ሰብኮ ነበር ፤ ሕዝቅኤል የሚያስገርሙ ስራዎችን ቢሰራም ሕዝቡ ስላልሰማዉ ምንም ጉዳያቸዉ አልነበረም ፡፡ አሁንም ምዕራፍ (8-9) በብዙ የሚመሳሰሉ ናቸው ፡፡

ጄ.ቬሮን ማክጊ ምዕራፍ 8 “ እንደ የክብር ራዕይ “ በመግለፅ “ በጣዖት የቤተ መቅደሱ መርከስ ጥፋቱን እንደሚገልፅ “ ይናገራል ፤ “ ራዕዩም ሕዝቅኤልን መልሶ ኢየሩሳሌም እንደ ወሰደው “ እና “ የእግዚአብሄር ክብር በኢየሩሳሌም በቤተ መቅደሱ ላይ እንደ ተከሰተ “ በመናገር ይቀጥላል (ቁጥር 2-4) ፡፡ በቁጥር (2-4) ያለዉ መግለጫ በምዕራፍ አንድ ያለዉ መግለጫ መስታወት ነው ፤ በተጨማሪም “ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ የተደረጉ ጣዖቶች መጋለጥ እግዚአብሄር ለምን እንደሚያጠፋዉ ይገልፃል “ (ቁጥር 16-18) ፡፡ ይህን ራዕይ በተቀበለ ጊዜ ሕዝቅኤል በባቢሎን ነበር ፤ በምድር እና በሰማይ መካከል ባለ ስፍራ ከፍ አደረገዉ/አነሳዉ እግዚአብሄርም በኢየሩሳሌም ምን እየሆነ እንደ ነበር አሳየው ፡፡

በምዕራፍ 9 ሕዝቅኤል የኢየሩሳሌም ከተማን ስድስት ገዳዮችን አዬ ፤ በኢየሩሳሌም ላይ የእግዚአብሄርን ፍርድ ሊያፅፈፅሙ የመጡት መልዓክቶች ነበሩ ፡፡ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በመግባት ከነኀስ መሰዊያዉ አጠገብ ቆሙ (ቁጥር 1-2) ፤ ሌላ ሰዉ ከመፃፊያ መሳሪያ ጋር ከእነርሱ ጋር መጣ ፡፡ የእግዚአብሄር ክብር (ሻካይና) ከላይ ካለዉ ከቤተ መቅደሱዉ ውስጥ በመነሳት ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ መጣ ፤ መፃፊያ መሳሪያ ወዳለዉ ሰዉዬ (ምናልባትም የእግዚአብሄር ልጅ ቅድመ ክርስቶስ ወደ ነበረው) በመጣራት በኢየሩሳሌም ዉስጥ በማለፍ በቤተ መቅደሱ ላይ ተፈፅሞ በነበረዉ ነገር በሚያስኑት እና በሚያለቅሱት ላይ ራሳቸዉን/ግናባራቸዉ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ነገራቸው (ቁጥር 3-4) ፡፡ እግዚአብሄር በቤተ መቅደሱ ላይ ሆኖ በነበረዉ ነገር ያዘኑትን (ቅሬታዎቹን) ማወቅ ይፈልጋል ፡፡

ይህ መግለጫ እኔን የእግዚአብሄር ሰዎችን ቤት ለማሳየት ፋሲካን እና በቤታቸዉ በሮች ላይ የደም መቀባቱን ያስታዉሰኛል ፡፡ የሞት መንፈስ በእነዚህ ቤቶች ላይ በማለፍ በዉስጡ ያሉትን ሰዎች ያድናል ፡፡ (ራዕ 13፡ 16 የጠላትን የተለያዩ አይነት ምልክቶችን ይገልፃል) ፡፡ በምዕራፍ 9 ገዳዮቹም/አስፈፃሚዉቹ ምልክት ያልተደረገባቸዉን በመግደል ነጭ ከያዘዉ ሰዉዬ ኋላ ይከተላሉ ፤ ቅሬታዎቹ ይድናሉ ነገር ግን ምልክት ላልተደረገላቸዉ ምንም አይነት ርህራሄ የተሰጠ አልነበረም ፡፡ በማይታመን ሁኔታ በባለ አደራነት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዉ ከነበሩት እና ቤተ መቅደሱን አርክሰዉት በነበሩት በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ላይ ጀመሩ (ቁጥር 6) ፡፡ ሕዝቅኤል እግዚአብሄርን የእስራኤልን ጠቅላላ ቅሬታዎችን ያጠፋ እንደሆነ ጠየቀው (ቁጥር 8) ፤ እግዚአብሄርም እርሱን እና ምድሪቱን ትተዉ ስለ ነበር “ ስራቸዉንም በራሳቸዉ ራስ ላይ እንደሚያወርደው “ (ቁጥር 9-10) በማለት ምላሽ ሰጠ ፡፡ በበፍታ የሆነዉ ሰዉዬ ተመልሶ በመምጣት ታዝዞ የነበረዉን እንደ ፈፀመ ሪፖርት አደረገ (ቁጥር 11) ፡፡

ይህንን በነቢያት ጥናታችን ዉስጥ ተመልክተናል ፤ በጊዜ ቅደም ተከተሉ ላይ እነዚህ ክስተቶች የት ላይ ይጣጣማሉ ? የሚያወዛግብ ነው ፡፡ ሕዝቅኤል በወንዙ አጠገብ በነበረ ጊዜ ስለ እግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ስለ ማደሪያዉ በኢየሩሳሌም ራዕይ ሊቀበል በሰማይ ሄደ ፤ በራዕዩም ሕዝቅኤል ኃጢዓታቸዉን እና በሆነዉ ነገር አዝነዉ በነበሩት ራስ ላይ ምልክት እንዲያደርግ በፍታ ለለበሰዉ ሰዉዬ የተሰጠዉን አሳይመንት አዬ ፤ ይህ ከክርስቶስ ልደት የ586 በፊት እና የኢየሩሳሌም መፈራረስ መልክ ነበር ፡፡ ይህ ራዕይ በጥፋቱ ጊዜ አቅራቢያ ተከናወነ (ምናልባትም ከክርስቶስ ልደት 592-588 በፊት) ፡፡ የክርስቶስ የመጀመሪያዉ መምጣት ከክርስቶስ ዉልደት (0-33) ነበር ፤ ከክርስቶስ ዉልደት 70 በኋላ ሮማዉያን ሁለተኛዉን ቤተ መቅደስ አፈረሱት/አጠፉት ፡፡ እስካሁን እስከምናዉቀው ድረስ በሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ መፈራረስ ጊዜ ምልክቶች ስላልተሰጡ ምናልባትም ይህ ስለ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደሱ አያወራም ፡፡ የክርስቶስ ሁለተኛዉ መምጣት አሁንም ገና ነዉ ይመጣል ነገር ግን መጀመሪያ መከራዉ ይመጣል ፡፡ የሕዝቅያስ ቃል ስለመጨረሻዉ ዘመን ትንቢታዊ እንደ ነበር ይህ ቀላል ነው ፤ በዘካ (12፡ 10) መሲሁ በመገደሉ ሕዝቡ አዘነ ፤ ይህ ለሁለቱም ሊሆን ይችላል ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (10፡ 1-8)፡ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 10 አሁንም በራዕዩ ዉስጥ ነበር ፡፡ ኮንስታብል ቁጥር 1-8 “ ከተማዋ ላይ ለመፍረድ የእግዚአብሄር ዝግጅት “ በማለት ይገልፃል ፤ እግዚአብሄር እንደ ገና በፍታ የለበሰዉን ሰዉዬ በመናገር በኪሩቤል መንኮራኩር ዉስጥ በመሄድ እጆቹን በፍም እሳት በመሙላት በከተማዋ ላይ እንዲበትነዉ ነገረው (ቁጥር 2) ፡፡ ማክአርቱር “ እነዚህ ፍሞች የእግዚአብሄር መለዓክቶች በኢየሩሳሌም ላይ የሚበትኑትን የእግዚአብሄርን እሳት መልክ ፤ በኢሳይያስ 6 ፍም ነቢዩን ለማንፃት ጥቅም ላይ ዉሎ ነበር፣ እዚህ ጋር ደግሞ ክፉዎችን ለማጥፋት እንደ ነበሩ “ ይገልፃል ፡፡ ኪሩቤል (ምናልባትም ከምዕራፍ 1 አንዱ አይደለም) በፍታ የለበሰዉ ሰዉዬው በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ሲሄድ ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ ቆመዉ ነበር በተጨማሪም “ ደመናዉም ዉስጠኛዉን አደባባይ ሞላ “ (ቁጥር 3) ፡፡

በመቀጠልም የእግዚአብሄር ክብር ከኩሩቤል በላይ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በማለፍ ወደ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ተጓዘ ፤ ቤተ መቅደሱም በክብሩ ደመና እና በሚናገር ጊዜ የእግዚአብሄርን ድምፅ በሚመስለዉ በኪሩቤል ክንፍ ድምፆች ተሞላ (ቁጥር 4-5) ፡፡ እግዚአብሄርም ሰዉዬው እንደ ገና ከመንኮራኩሩ ስራ ዉስጥ እሳት እንዲወስድ ነገረው ፤ በመሄድም ወደ እሳቱ በመድረስ በሰዉዬ ዉ እጅ ላይ ከሚያስቀምጥለት ከኪሩቤል በአንዱ አጠገብ ቆመ ከዚያም ከቤተ መቅደሱ ወጣ (ቁጥር 6-7) ፡፡ እነዚህ ለእግዚአብሄር ከቤተ መቅደሱ ለመለየት የጅማሪዎቹ ዝግጅቶች ነበሩ ፤ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ የነበረዉ ኪሩቤል በክንፎቹ ስር የሰዎ እጆች ነበሩት ፡፡

ሕዝቅኤል (10፡ 9-17)፡ የሕዝቅኤል ራዕይ በመንኮራኩሮቹ ኪሩቤል ላይ የብርሌ መልክን በማየት ቀጠለ (ቁጥር 9) ፤ የመንኮራኩር መግለጫዉ እንደ ገና በምዕራፍ አንዱ ራዕዩ ላይ ምን እንዳዬ ያሳያል (ቁጥር 10-13) ፤ የኪሩቤል ገለፃዉም እንደ ኪሩብ ተዘርዝሮ ከነበረዉ የበሬ ፊት ብቻ ምዕራፍ አንድን ያሳያል (ቁጥር 14) ፡፡ አራቱ ኪሩቤሎች በመንኮራኩራቸዉ ከፍ በማለት ቀድመዉ ተገልፀዉ እንደ ነበሩት አሁንም ሰሩ (ቁጥር 15-17) ፡፡

ሕዝቅኤል (10፡ 18-19)፡ ከዚያም የእግዚአብሄር ክብር ከቤተ መቅደሱ በመዉጣት ከኩሩቤል በላይ ቆመ ፡፡ ማክአርቱር “ ከቤ መቅደሱ የእግዚአብሄር ክብር የቀስ በቀስ መለየት በደረጃዎች እንደ ታዬ “ ይገልፃል፡

  1. ከክርስቶስ ልደት 592 በፊት ሕዝቅኤል በተመለከተዉ ጊዜ የእግዚአብሄር ክብር በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ነበር (ሕዝ 8፡ 4) ፡፡
  2. ከክርስቶስ ልደት 592 በፊት የእግዚአብሄር ክብር ከኪሩቤል ላይ ወደ ቤተ መቅደሱ መድርክ ተንቀሳቀሰ (ሕዝ 9፡ 3, 10፡ 4) ፡፡
  3. ከክርስቶስ ልደት 592 በፊት የእግዚአብሄር ክብር ከቤተ መቅደሱ መድረክ በኪሩቤል ላይ በመሄድ በዚያ ላይ ቆመ (ሕዝ 10፡ 18-19) ፡፡
  4. ከክርስቶስ ልደት 592 በፊት በምስራቅ በመሄድ ኢየሩሳሌም ተለዬ እስከ መሲሁ ሺህ አመት መንግስት ጊዜ አይመለስም (ሕዝ 11፡ 22-23) ፡፡
  5. በወደፊት ጊዜ የሆነ ጊዜ ላይ የሺዉን ዘመን ለመባረክ/ለመክፈት የእግዚአብሄር ክብር ከምስራቅ ወደ ቤተ መቅደሱ ይመለሳል (ሕዝ 43፡ 2-9, 44፡ 4) ፡፡

መደምደሚያ

ማክአርቱር በሕዝ (43፡ 2-9) ስለ እግዚአብሄር መመለስ የፃፈው፡ “ እዚህ በሺዉ አመት ቤተ መቅደስ ዉስጥ ለማደር የእግዚአብሄር ክብር ይመለሳል ፤ ክብሩ የከበረ ከሚሆነዉ ከጌታ ከሁለተኛዉ ምፅዓት በኋላ በወደፊት ዘመን መንግስቱ በሙሉነት የሚገለጥ ይሆናል “ ፡፡

ይህ የሺዉ አመት ዘመን መልክ ነው ፤ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል የእግዚአብሄርም ክብር ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል፡፡

  1. J. Vernon McGee, Ezekiel: Notes & Outlines, n.p.; available at https://ttb.org/docs/default-source/notes-outlines/no18_ezekiel.pdf?sfvrsn=2.

  2. McGee, n.p.

  3. McGee, n.p.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 902.

  5. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 85; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.

  6. MacArthur, p. 903.

  7. MacArthur, p. 902-903.

  8. MacArthur, p. 938.

ጥያቄዎች

  1. በሕዝ (8፡ 3) “ በዚያም ቅንዓት የሚያነሳሳ የቅንዓት ጣዖት ተተክሎ ነበር “ የሚለዉን ስታነቡ ይህ የእግዚአብሄር መግለጫ ይሆናል ብላችሁ ታምናላችሁ ? ስሙ ቀናተኛ ነዉ የሚለዉን ዘጸ (34፡ 14) አንብቡ ፤ እግዚአብሄርን እንደ ቀናተኛ አስባችሁት ታውቃላችሁ ? ቀናተኛ ያደርጉታል ብላችሁ የምታስቡት ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው ?
  2. በሕዝ (8፡ 14) እንደ ተነገረው አማልዕክት ተሙዝ ማን እንደ ነበርና ለምን ሴቶቹ ለእርሱ እያለቀሱለት እንደ ነበር ፈልጉ
  3. በሕዝ (9፡ 4) እንደተገለፀው በሚድኑት ላይ ምልክት ማስቀመጥ እንደተጀመረ በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ታዩታላችሁ ? (ዘጸ 12፡ 12-13)
  4. ሕዝቅኤል 10 በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ኩሩቤልን ይገልፀዋል ፤ በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ተገልፀዋል (ራዕ 4፡ 6-8) ? እነዚህ ተመሳሳይ ፍጥረቶች እንደሆኑ የምታምኑ ከሆነ በመግለጫዉ ለልዩነታቸዉ ምክንያቱ ምን ይሆናል ?
  5. ሕዝቅኤል (10፡ 4) የእግዚአብሄር ክብር በመድረኩ ላይ ቆመ ፤ በዚያ ቅፅበት ለልጆቹና ለእስራኤል ልቡ ተሰብሮ እንደ ነበር ታስባላችሁ ? ሌሎች አማልዕክቶችን ለማምለክ ጀርባቸዉን አዙረዉበት ነበር ፤ ኃዘኑን ሊሰማችሁ ይችላል ?
  6. በሕዝቅኤል (8-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 9:3b–4

“He called to the man clothed in linen with the writing equipment at his side. ‘Pass throughout the city of Jerusalem,’ the LORD said to him, ‘and put a mark on the foreheads of the men who sigh and groan over all the detestable practices committed in it.’”

ሕዝቅኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ባየው ራዕይ ፣ ሰዎች በቤተ መቅደሱ ውስጥ አስጸያፊና አስነዋሪ ነገር ሲያደርጉ አየ ፡፡ ለእግዚአብሔር ክብርና እግዚአብሔርን ለማምለኪያ ተብሎ የተሰራው ቦታ ጣዖታትን ማምለኪያ ሆኖ እንድሁም በየግርግዳውም አስጸያፊ ነገሮች ተቀርጸውበት ነበር ፡፡ ሕዝቅኤልም የእግዚአብሔር ቁጣ የኢየሩሳሌምን ሰዎች ሲያርድ ራዕይ አየ ፡፡ በተጨማሪም በከተማዋ ውስጥ አንድ ሰው ሲያልፍና በቤተ መቅደሱ ውስጥ ስለሚሰራው አስከፊ ነገር የሚያለቅሱና የሚተክዙ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክትን ሲያደርግ አየ ፡፡ እግዚአብሔርም የእነዚህን በክፉው ድርጊት ውስጥ ደስ ያልተሰኙትን ሰዎች ልብ ለየ ደግሞም እነርሱን ከሰይፍ ያድናቸዋል ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር መገኘቱን ከቤተ መቅደሱ ይወስዳል ፡፡

ሰዎች ክፉን ሲያደርጉ ስታዩ ፣ ምንድን ነው የምታደርጉት ? መራቅ ? መተንፈስና ማቃሰት ? ተቀላቅሎ ድርጊቱን መፈጸም ? እግዚአብሔርን መፈለግና የእርሱን ማስተዋልና ምሪት መጠየቅ ? እግዚአብሔር በእርሱ መንገድ እንድትሄዱ ደግሞም የእርሱን አሳብ ፣ ደስ የሚያሰኘውንና ፍጹም ፍቃዱን እንድትለዩ ያዛችኋል ፡፡ እርሱ ከክፉ ሽሹ ይላል ፡፡ ለዓለም ስርዓት አትመቹ ፡፡ በትዕቢትና በመዳራት የተሞላውን የዚህን ዓለም ነገር አትውደዱ ፡፡ ግብዝነት በሌለበት ፍቅር ፤ መልካም በሆነው ነገር ላይ ተጣበቁ ፡፡ ምንም እንኳ እውነት ላይ መጣበቅ “ብቸኛ “ እንደሚያደርጋችሁ ብታስቡም ፣ በዚያ ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ በጌታ ላይ ስትጣበቁ ፣ እግዚአብሔር በህይወት ዘመናችሁ ሁሉ እንደሚጠብቃችሁ ይናገራል ፡፡

“ በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ ። እግዚአብሔርም ፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው ። “

  • ሕዝቅኤል 9፡3-4

ተጨማሪ ጥቅስ

ሕዝቅኤል 9:6 — “ ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ ፡፡ “

ሮሜ 12:9 — “ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ ፡፡ “

1ኛ ዮሐንስ 2:15–17 — “ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም ። ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል ። “