Major Prophets Ezekiel

Announcement Of The End

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 6-7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 629 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሕዝቅኤል መፅሀፍት ዉስጥ የሚሆኑት ነገሮች ምናልባትም በመፅሀፍ ላይ በጣም ጋራ የሚያጋቡ ናቸው፡

  • በምዕራፍ 1 ሕዝቅኤል የእግዚአብሄርን ዙፋንን ከአራት ኩሩቤል እና ከሚያስደነግጡ አራት መንኮራኩሮች ጋር ያየዉ ራዕይ ነበረው ፡፡
  • ምዕራፍ 2 የሕዝቅኤልን መጠራት እንደ ካህን እና እንደ ነቢይ ይይዛል ፡፡
  • በምዕራፍ 3 እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን መፅኀፉን እንዲበላ አዘዘው ፡፡
  • በምዕራፍ 4 ሕዝቅኤል የእስራኤልን ኃጢዓት በመዉሰድ በግራ ጎኑ 390 ቀን ቀናት እንዲተኛ እና የይሁዳን ኃጢዓት በመዉሰድ ደግሞ 40 ቀናት በቀኝ ጎኑ እንዲተኛ ተነገረው ፡፡
  • በምዕራፍ 5 ሕዝቅኤል ራሱን እና ፂሙን በመላጨት በኢየሩሳሌም መጥፋት ጊዜ በሕዝቡ ላይ ምን እንደሚሆን ለማመለከት ተጠቀመበት ፡፡

ኢሳይያስ ከመሆኑ ከረጅም ጊዜ በፊት ስለሚመጣዉ የኢየሩሳሌም ጥፋት ትንቢትን ተናግሯል ፡፡ ኤርምያስ ይህ ከመሆኑ በፊት ተንብዮአልም በግልም ግዞቱን ቀምሶታል ፡፡ ሕዝቅኤል ከምርኮ ዉስጥ ትንቢትን በመናገር በዚያም እያለ የኢየሩሳሌምን የመዉደቅ ቃልንም ተቀበለ ፡፡

በሕዝ (6፡ 1-7) ሕዝቅኤል እስራኤል በሚያመልከዉ ጣዖት ላይ እና እስራኤል በራሷ ላይ አምጥታዉ ስለነበረዉ ጥፋት ትንቢት እንዲናገር ታዘዘ ፡፡ በቁጥር (8-10) ሕዝቅኤል የታመኑትን ቅሬታዎች ለማደን የእግዚአብሄርን ተስፋ ደግሞ ተናገረ ፤ በቁጥር (11-14) ሕዝቅኤል እግዚአብሄር በሕዝቡ ላይ በሚያመጣዉ ርሃብ፣ ሰይፍ እና ቁጣ በኢየሩሳሌም ዉድቀት ማዘን ጀመረ ፡፡ ከሕዝቡ አለመታዘዝ፣ አመፅ እና ጣዖት አምልኮ የተነሳ የእግዚአብሄር ፍርድ ተሰጠ ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (7፡ 1-9)፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ 7 በእስራኤል ላይ ስለሚመጣዉ ጥፋት የተነገረዉን ሁለተኛዉን መልዕክት እና ቁጥር (1-7) “ እንደ ጥፋት ማሳወቂያ “ በማስቀመጥ ይይዛል ፡፡ እግዚአብሄር መጨረሻዉ “ በምድሪቱ በአራቱም ማዕዘናት “ ላይ በእስራኤል ላይ እንደመጣ ተናገረ (ቁጥር 2) ማለትም በእስራኤል (በምድሪቱ) ላይ ያለ ሁሉም ሰዉ በባቢሎን ሰራዊት በኩል ፍርድና ጥፋት ይደርስባቸዋል ማለት ነው ፡፡ ዋይርስቤ እንደ እግዚአብሄር መሳሪያ “ የባቢሎናዊያን ሰራዊት ከሰሜን ምድሪቱን በመዉረር ለመዝረፍ እና ለማጥፋት መጥቶ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ በቁጥር 3 “ መጨረሻ “ የሚለዉ ቃል “ የትንቢቱ መፈፀም በእጁ ላይ እንደ ነበር አፅዕኖት ይሰጣል “ ፡፡ እግዚአብሄርም ሕዝቡን በርህራሄ እንደማያይ እና እንደማያያቸዉ ተናገረ ፤ ለማድረግ መርጠዋቸዉ ስለ ነበሩት ርኩስ ነገሮች የተቀጡ ይሆናሉ (ቁጥር 4) ፡፡ እግዚአብሄርም የእርሱን ቁጣ የቀመሱት ብቻ ይህን ያደረገዉ እግዚአብሄር(ያሕዌ) ብቻ እንደሆነ እንደሚያዉቁ በአፅዕኖት ተናገ ፡፡

በቁጥር 5-9 ሕዝቅኤል እንደ ገና በእስራኤል ላይ በሚመጣዉ የጥፋት መልዕክት ጀመረ ፤ ንግግሩ/ቋንቋው ተመሳሳይ ነዉ ነገር ግን ማስጠንቀቂያ በጣም አሳሳቢ እና በጣም አስፈላጊ ይመስላል (ሮሜ 13፡ 11) ፡፡ ፍፃሜዉ ከዚህ በፊት ከነበረዉ በጣም የቀረበ ነበር ፡፡

ሕዝቅኤል (7፡ 10-21)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች “ እንደ ጥፋት መልክ “ ያሳያቸዋል ፡፡ ሕዝቅኤል ቀኑ እየመጣ እንደ ነበር አሳወቀ - ትዕቢት አብቦበት የነበረዉ እና ግፍ ክፍታ ሆኖበት የነበረዉ ጊዜ (ቁጥር 10-11) ፡፡ የመጀመሪያዉ መልክ “ኃጢዓታቸዉ በስሎ እንደ ነበርና ሕዝቡ የዘራዉን ነገር እንደሚያጭድ “ ለማሳየት “ ያፈራ እንቢጥን “ ተጠቅሞ ነበር (ቁጥር 11) ፡፡

በቁጥር 13 ሁለተኛዉ መልክ ቢዝነስ ያል የተመሰረተ ነበር ፤ በሁሉም ሰባተኛ አመት በሰንበት አመታት ጊዜ ምድር አትታረስም ነበር እዳዎችም ይዘረዙ ነበር ፡፡ ከሰባተኛዉ የሰንበት አመት በኋላ ቀጣዩ አስራ አምስተኛዉ አመት “ ምድሪቱ ሳይዘራ በተቀመጠ፣ እዳዎች ተሰርዘዉ በነበር፣ አገልጋዮች ነፃ ወጥተዉ በነበሩበት ጊዜ እና መሬቱም ለመጀመሪያዉ ባለቤት የሚመለስበት “ የኢዩቤልዩ አመት ነበር ፡፡ ኤር (29፡ 10) ስደተኞቹ በባቢሎን ለ70 አመታት ይቀመጣሉ ይላል ፤ ይሁን እንጂ ለ70 አመታት በግዞት ስለሚሆኑ በሰንበት አመት ወይም በኢዩቤልዩ አመት ምንም ነገር አይታደስም ፤ ያ ማለት ፍርዱ እንደ ገና መጥራት እንደማይችል እና ሕዝቡ በምርኮ ጊዜአቸው እነዚህን የፀጋ ጊዜዎች አያገኙም ማለት ነው ፡፡

በቁጥር (14-15) የሕዝቡ ጥፋት በጉበኛዉ (በምዕራፍ 2 ላይ በተዋዬነው) መልክ የተገለፀ ነበር ፤ ሕዝቅኤል በቅጥሩ ላይ ያለዉ ዘበኛ የወራሪዎችን መምጣት ምልክት ለመስጠት ቀድሞ መለከቱን ነፍቶ እንደ ነበር ነገር ግን የእግዚአብሄር ቁጣ በእነርሱ ላይ ስለ ነበር በዚያ ማንም እንደ ማይኖር ገልፆአል (ቁጥር 14) ፡፡ ቁጥር 15 የሚወርር ሰራዊት ከነበር በሰይፍ እንደሚሞቱ እና በከተማዋ ዉስጥ ከተቀመጡ ደግሞ በርሀብ እና በመቅሰፍት እንደሚሞቱ ይናገራል ፡፡

በቁጥር (16-18) በራሳቸዉ ኃጢዓት ላይ በማቃሰት ልክ እንደ ሸለቆ እርግቦች ወደ ተራራዉ የሚያመልጡትን እንደ ጥቂት አምላጮች በእርግ መልክ ይገልፃቸዋል ፡፡ በኃዘን እና በማፈር ማቅ ልብስ ይለብሳሉ ፤ እንደ ገና እንዚህ ኃጢዓታቸዉን በማየት ንስኃ በመግባት ቅሬታዎች ነበሩ ፤ በዚህ ምስል ተስፋ አለ ፡፡

በቁጥር (19-21) ምስሉ እንደ ባለፀጋ ይዘዋቸዉ የነበሩትን ሁሉንም ነገር ለማጥፋት የሚሞክሩትን ሰዎች ይገልፃል ፡፡ ዋይርስቤ “ ሰዎች ዋጋ የነበራቸዉን ነገሮች ይወረዉሯቸዋል “ ምክንያቱም “ በይሁዳ መንግስት መጨረሻ ላይ ያለምንም ፍርድ ጣልቃ ገብነት በባለጠጋዎች ድሆችን በመዝረፍ ባለጠጎች እየበለፀጉ ድሆችም እየደኸዩ ስለ ነበር “፡፡ ባዕዶችም እንደ ብዝበዛ እንዚህን ነገሮች ይወስዳሉ ያረክሷቸዋልም (ቁጥር 21) ፡፡

ሕዝቅኤል (7፡ 22-27)፡ እግዚአብሄር ቅድስተ ቅሳን የሆነዉን “ ንብረቱ የሆነዉን ስፍራ “ ያረከሱት ላይ በክፉዎች በኩል ጥፋት እንዲመጣባቸው ይፈቅዳል ፡፡ ማክአርቱር “ በእግዚአብሄር ፊት በአመት አንድ ጊዜ ሊቀ ካህኑ ሊገባበት የሚችለዉ ስፍራ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ቅዱስተ ቅዱሳን በጣዖት አምላኪዎች እንደሚረክስ “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር የቤታቸዉን ንብረት እና ሀብታቸዉን ለመዉሰድ በጣም ክፉ የሆኑትን ሕዝቦች ባቢሎንን እያመጣ ነበር (ቁጥር 24) ፤ ጭንቀት እየመጣ እንደ ነበርና ያለ ስኬት ሰላምን ለመፈለግ እንደሚሞክሩ ቃል ገባ ፡፡ ዋይርስቤ “ ይሁዳ ከግብፅ ጋር ጥምረትን በማድረግ ለሰላም መንገድን ለመደራደር ሞከረ ነገር ግን እግዚአብሄር ሕዝቡ የተሳደዱ እንደሚሆኑ እና የእግዚአብሄርን ሉዓላዊ ፍቃድ ላይ ኃይል ሊኖራቸዉ እንደማይችል ቀድሞ ወስኖ ነበር “ (ቁጥር 25) ፡፡ በጥፋቱም ከጥፋት በኋላም ያለዉን ሁኔታ ደርሶባቸዉ ስለ ነበር ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ እንዲነግራቸዉ ነቢይ ፈለጉ “ ነገር ግን ከኃይማኖት መሪዎች፣ ከነቢያቶች ወይም ከካህናቶች እርዳታ አይኖርም “ (ቁጥር 26) ፡፡ ሕዝቅኤል መልዕክቱን “ የኃይማኖታዉ መዘበራረቅ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካዉ ስርዓትም በመለየት የወደቀ እንደሚሆን “ በመግለፅ አበቃ (ቁጥር 27) ፡፡

መደምደሚያ

ሕዝቅኤል ፍርድ እየመጣ እንደ ነበር እና ያ ፍርድ ደግሞ የሚያስፈራ እንደ ሆነ ተናገረ ፡፡ ፍርዱ እየመጣ ስለ ነበር ሕዝቡ እግዚአብሄር ታላቅ እና ያህዌ እንደ ሆነ ያውቃሉ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 175–176.

  2. Wiersbe, p. 176.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 964.

  4. Wiersbe, p. 176.

  5. Wiersbe, p. 176.

  6. Wiersbe, p. 176.

  7. Wiersbe, p. 176-177.

  8. Wiersbe, p. 177.

  9. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 901.

  10. Wiersbe, p. 177.

  11. Wiersbe, p. 177.

  12. Wiersbe, p. 177.

ጥያቄዎች

  1. በሕዝ (6፡ 8) እግዚአብሄር ቅሬታዎቹን እንደሚተዋቸዉ ለምን ቃል ገባ ? እግዚአብሄርን ይህን በአሁኑ ዘመንም እንደሚያደርግ ታምናላችሁ አዎ ከሆነ መልሳችሁ ለምን ? እግዚአብሄር ቅሬቶቹን ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን/ለመንግስቱ መልካም ነገር ሲጠቅምባቸዉ እንዴት ታዩታላችሁ ?
  2. እግዚአብሄር በህዝቅኤል ዉስጥ በተደጋጋሚ “ ከዚያም እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያዉቃሉ “ የሚለዉን ለምን እንደተናገረ ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር ሕዝቡን ከበቀል ዉጪ ወይም በሌላ ምክንያት ወይም ደግሞ በሁለቱም ምክንያት ይቀጣል ብላችሁ ታምናላችሁ ? (ምሳ 3፡ 1, ዕብ 12፡ 6)
  3. በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ከሕዝ (7፡ 19) ጋር ተመሳሳይ ነገር እንሰማለን (ምሳ 11፡ 4, ኢሳ 2፡ 20, ሶፎ 1፡ 8) ? ይህ ስለ ባለፀጎች ምን ይነግራችኋል ? ባለፀጋ የሆነ ከክፋት እና ከራስወዳድነት ይልቅ ለመልካም ነገር የሚጠቀሙም ሰዉ ታውቃላችሁ ?
  4. ሕዝ (7፡ 18) ሕዝቅኤል እየጠቀሰዉ ስለ ነበረዉ ስለዚህ የተለዬ ጊዜ ምን ይነግራችኋል (ኢዮ 21፡ 6, ኢሳ 15፡ 3, አሞ 8፡ 10) ? ይህን የእግዚአብሄርን የቁጣ ጊዜ (ሕዝቅኤል 7) ከሲዖል ጋር እንዴት እንደሚነፃፀር ምን ታስባላችሁ ?
  5. በሕዝቅኤል (6-7) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 7:24, 27

“So I will bring the most evil of nations to take possession of their houses. I will put an end to the pride of the strong, and their sacred places will be profaned . . . The king will mourn; the prince will be clothed in grief; and the hands of the people of the land will tremble. I will deal with them according to their own conduct, and I will judge them by their own standards. Then they will know that I am Yahweh.”

ሕዝቅኤል መጨረሻው እንደቀረበ ተናገረ ፡፡ ክፉው ቀን ደርሶ ነበር ፡፡ ሰዎች ከፍ ብለው ታብየው ነበር ፡፡ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሀብትን ተመልክተው ነበር ፡፡ ኃያሉን እግዚአብሔርን ከማምለክ ይልቅ ጣዖታትን ማምለክ አስቀድመው ነበር ፡፡ እናም አሁን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ፍርድንና ጥፋትን ሊያመጣ ነው ፡፡ እናም በስተመጨረሻ ጥፋት ሲመጣ ፣ እነርሱ እግዚአብሔር እርሱ ያህዌ እንደሆነ ያውቃሉ ፡፡ እርሱ አንዱና ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ነው ፡፡

ማንን ነው የምታመልኩት ? በፍጹም ልባችሁስ የምትፈልጉት ማንን ነው ወይስ ምንን ነው ? ሰላምንና ተስፋን ከዚህ ዓለም ነገሮች ለማግኘት ትፈልጋላችሁን ? ከጣዖታት ? ከሙያ ? ከሀብት ? ከማንነት ? አንዱና ብቸኛው ሰላምና ተስፋ የሚገኝበት ጌታ ብቻ ነው ፡፡ የተቀሩት ሁሉ የሚያስገኙት ጊዜያዊ ደስታን ነው ፡፡ እነዚህ ጣዕም ያሳጧችሁና ተጨማሪ እንድትፈልጉ ያደርጓችኋል ፡፡ የዚህ ዓለም ነገሮች ድንገት የሚናዱ ናቸው እናም በመጨረሻ ወደ ጥፋት ይመሯችኋል ፡፡ ሆኖም ግን ወደ ታች ስትወድቁ ፣ በእርግጠኝነት ያኔ እግዚአብሔር ያህዌ የመሆኑን እውነት ትረዳላችሁ ፡፡ እርሱ ፍጹም እርካታን የሚሰጥ አምላክ ነው ፡፡ ዛሬ እርሱን በፍጹም ልባችሁ በማምለክ የዚህ ዓለም ነገሮች አንድደበዝዙ እንድጠፉ አድርጉ ፡፡

“ ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ ፤ የኃያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ ፥ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ ……. ንጉሡም ያለቅሳል ፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል ፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች ፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ ። “

  • ሕዝቅኤል 7፡24 ፤ 7፡27

ተጨማሪ ጥቅስ

ሕዝቅኤል 7:19 — “ ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል ፤ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም ። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም ። “

ማቴዎስ 5:6 — “ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ፥ ይጠግባሉና ። “

1ኛ ዮሐንስ 2:15 — “ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ ፤ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም ። “