Major Prophets Ezekiel

Dramatically Sharing Jerusalem's Coming Fall

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 4-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 628 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ካጠናናቸዉ ሰዎስተኛዉ ታላቅ ነቢይ ሕዝቅኤል ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ዉስጥ አንዱ ነበር ፤ እንደ ካህን እና እንደ ነቢይ እንዲያገለግል የእግዚአብሄርን ጥሪ በተቀበለ ጊዜ 30 አመቱ እና ለአምስት አመታት በግዞት የቆዬ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን የእግዚአብሄርን መልዕክት ለሕዝቡ ቢያደርስም እንኳን እንደማይሰሙት እና ለማድረግ ብዙ እንደሚሰቃይ ነገረው ፡፡ የሕዝቅኤል ሕይወት ለሕዝቡ እንደ ምልክ የሚያገለግል ነበር ፡፡

በምዕራፍ 4 እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን የኢየሩሳሌም ከተማ ስዕል በመሳል በሁሉም በከተማዋ በኩል እንዲከብባት፣ እንዲደለድልባት፣ ምሽግ እንዲሰራበት እና የሚያፈርስ ግንድ በመገንባት “ ከበባብን እንዲያደርግባት “ ታዘዘ (ቁጥር 1-2) ፡፡ በእርሱና በከተማዋ መካከል የብረት ቅጥርን የሚወክለዉን የብረት ምጣድ በማስቀመጥ ከተማዋን በጦር ኃይል እንደተከበበች ይመለከት ነበር (ቁጥር 3) ፤ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ምን ይሆን እንደነበር ያሳያል ፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቅኤል በግራ ጎኑ በመተኛት በጎኑ የእስራኤልን ኃጢዓት እንዲያስቀምጥ ተነገረው ፤ በግራ ጎኙ በመተኛት ኃጢዓተኞቻቸዉን ለ390 ይሸከማል ፤ ከዚያም ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ በማድረስ በእነርሱ ላይ ትንቢት ለመናገር ስለ ይሁዳ ኃጢዓት በቀኝ ጎኑ 40 ቀን የሚተኛ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በሕዝቅኤል ላይ ገመድን ስላስቀመጠ በእዚህ ጊዜያት ጊዜ መዞር አይችልም (ቁጥር 4-8) ፡፡

በመቀጠልም እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን በእነዚህ ጊዜያት ዉስጥ ለመብላት እና ለመጠጣት እንዴት መዘጋጀት እንደ ነበረበት ቅደም ተከተልን ሰጠው ፡፡ በቁጥር 12 ሕዝቅኤል የተዘጋጀዉን እንጀራ በመዉሰድ እስራኤላዊያን እንዴት “ እንጀራዉን እንደሚበሉ - በበዓላት ንፁህ ያልሆነዉን በምቀጣቸዉ ህዝቦች ስፍራ መካከል “ ለማሳየት በሰዉ ሰገራ ላይ በማብሰል ያደርቀዋል ፡፡ ዋይርስቤ ይህን ሁሉ ስለሚመጣዉ ርሀብ “ አስከፊነትን “ እንደሚያሳይ ይገልፃል ፤ ሕዝቅኤል በአንድ ላይ የቀለቀላቸዉ ነገሮች “ በጣም የደከመ ምግብን ስለሚያመነጭ በኢየሩሳሌም መከበብ ጊዜ የምግብ እጥረትን ያመለክታል ፤ ሕዝቡ ሁሉንም ነገር በሚባል ደራጃ ይመገባሉ እርስ በእርሳቸዉም ሳይቀር “ ፡፡ ዋይርስብ “ የሰዉ ሰገራ ጥቅም የአሰቃቂ ርሀብ እና ፍላጎት ምልክት እንደ ነበር “ መግለፁን ይቀጥላል ፡፡

ለ390 ቀናት የሕዝቅያስ በጎን መተኛነት የምን ጊዜን 390 አመታት የሚወክል ነበር ? ዋይርስቤ፡

“ 390 አመቱ ከክርስቶስ ልደት በ930 በፊት የሰለሞን ልጆ ሮብዓም ንጉስ ከሆነበት ጊዜ ይጀምራል (1ነገ 14፡ 21) ፤ በ 1 እና በ2 ነገስት የተመዘገበዉን የይሁዳ ነገስታትን ዘመን ከሮብዓም እስከ ሴዴቅያስ ያለዉን በምትደምሩት ጊዜ በአጠቃላይ 394 አመት አላችሁ ፤ ሮብዓም ከዘመኑ ሰዎስት አመታትን ከእግዚአብሄር ጋር ስለተመላለስ (2ዜና 11፡ 16-17) ከሕዝቅያስ 390 አመታት ጋር በጣም በቀረበ ቁጥር እናበቃለን “ ይላል ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (5፡ 1-17)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (1-17) “ የሕዝቡ መዳረሻ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን በሰይፍ ራሱን እና ፂሙን እንዲላጭ እና ፀጉርንም በመመዘን ወደ ሰዎስት እኩል ክፍል እንዲከፍለዉ ነገረው (ቁጥር 1) ፡፡ ሕዝቅኤል ሲሶዉን በተከበበዉ ሸክላ ላይ እንዲያቃጥለው ፣ ሌለኛዉን ሲሶ ደግሞ በመቁረጥ በከተማዋ ዙሪያ እንዲበትነዉ እና የመጨረሻዉን ሲሶ ደግሞ በንፋስ እንዲበትነዉ ተነገረው ፤ ይሁን እንጂ በመጎናፀፊያዉ ጫፍ ላይ ጥቂት የፀጉሩን ክፍል ያድን ነበር (ቁጥር 2-3) ፡፡ ዋይርስቤ የእነዚህን የእያንዳንዳቸዉን አስፈላጊነት ይገልፅል ፤ የመጀመሪያዎ ሲሶ ከበባዉ በአለቀ ጊዜ ምን እንደሚሆን ይወክላል ከተማዋ እንደ ተቃጠለች እና ርሀብ በህዝቡ ላይ እንደ መጣ ፤ ሁለተኛዉ ሲሶ በባቢሎናዊያን እጅ በኃይለኛዉ የሚገደሉትን ይወክላል ፤ የመጨረሻዉ ሰዎስተኛዉ ሲሶ ደግሞ ምርኮኞቹ በመወሰድ በአሕዛብ ሁሉ የተበተኑ እንደሚሆኑ ይወክላል ፡፡ በሕዝቅኤል መጎናፀፊያ ላይ የተቀመጠዉ ፀጉር “ ወደ ምድራቸዉ እንዲመለሱ የሚያድናቸዉ ቅሬታ ሕዝቦቹ የእግዚአብሄርን የተለዬ ጥበቃን ያመለክታል “ ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ታላቅ እሳት በመላዉ የእስራኤል ቤት ዉስጥ ሁሉ እንደሚገባ ለማመልከት በመጎናፀፊያዉ ላይ ካለዉ ጥቂት ፀጉር እንዲያቃጥል ነገረው (ቁጥር 4) ፡፡

እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን በአሕዛቦች ሁሉ መካከል ላይ አስቀምጧት እንደ ነበር ነገር ግን ኢየሩሳሌም በእግዚአብሄር ላይ እንዳመፀች እና እርሱን ከማያዉቁት አሕዛቦች በላይ የከፋችም እንደ ነበረች ገለፀ (ቁጥር 5-6) ፡፡ ማክአርቱር “ ለከፉዎቹ/ለአረመኔዎቹ ሕዝቦች ምስክር ከመሆን ይልቅ እስራኤል በጣዖት ተግባራት ከእነርሱ የበለጠች ነበረች ፤ እስራኤል ከእዉነተኛዉ እና ህያዉ እግዚአብሄር ስታፈነግጥ ሕዝቦቹ/አሕዛቦቹ የሚያዉቁትን ጣዖት ጠበቁ ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች ከመንፈሳዉ እዉቀት እና እድል/መሰጠት የተነሳ ከጣዖት አምላኪዎች የከፉ ነበሩ “ በማለት ይናገራል ፡፡

ሰለዚህም ካለመታዘዛቸው፣ በጣዖት አምልኳቸው እና ከዓመፃቸዉ የተነሳ እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም ላይ በመዞር በዙሪያቸዉ ያሉት አሕዛቦች ምስክር የሚሆኑበት ፍርድን በእነርሱ ላይ እንደሚያመጣ ተናገረ (ቁጥር 7-8) ፤ ያም የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅኀፍ ታሪክ ነው ፡፡

እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣዉ ፍርድ ከዚህ በፊት መጥቶ የማያዉቅ እና ወደፊትም በፍፁም እንደ ገና የማይሆን እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 9) ፡፡ ሕዝቡም ዘግናኝ የሆነ ነገር ይደርስባቸዋል - ከርሀቡ ለመትረፍ አባቶች ልጆቻቸዉን ይበላሉ፣ ልጆች ደግሞ አባቶቻቸዉን ይበላሉ የተረፉትም በሁሉም አቅጣጫ ይበተናሉ (ቁጥር 10) ፡፡ “ በእድፈትሽና በእርኩሰትሽ መቅደሴን ስላረከሽ “ (ቁጥር 11) እግዚአብሄር ያለምንም መራራት እንደሚያሳንሳቸዉ ቃል ገባ ፡፡

እንደ ገና ቁጥር 11 ሕዝቡ ከኢየሩሳሌም የተወሰደባቸዉን ሰዎስት የምርኮ ጊዜያት አስቀምጧል ፤ አንድ ሰዎስተኛዉ በመቅሰፍት እና በርሀብ ይሞታሉ (ቁጥር 12) ፤ አንድ ሰዎስተኛዉ በሰይፍ ይሞታሉ (ቁጥር 12) ፤ አንድ ሰዎስተኞቹ ደግሞ በጦርነት ሰይፍ የተሳደዱ በመሆን በአሕዛብ ሁሉ ይበተናሉ (ቁጥር 12) ፡፡ በዚህ ጊዜ ሕዝቅኤል በምርኮ ተቀምጦ እንደ ነበርና የኢየሩሳሌም የመጨረሻ ዉድቀት አሁንም ገና እንዳልመጣ ቀድሞ እንደ ተናገረ ያስታዉሳል ፡፡ እግዚአብሄር ቁጣዉን ከፈፀመ በኋላ ማባበያን ይሰጣቸዋል በግዞት የነበረዉም ሕዝብ እግዚአብሄር ማን እንደ ነበርና አሁንም ማን እንደ ሆነ በእርግጠኝነት ያውቃሉ (ቁጥር 13) ፡፡

ቅሬታዎቹ በዚህ ፅኁፍ ላይ ሁለት ጊዜ ተጠቅሰዋል ፤ በቁጥር 12 እግዚአብሄር አንድ ሰዎስተኛዉን ሕዝብ እበትነዋለሁ አለ ነገር ግን ይህ ይተርፋሉ ማለት ነው ፡፡ በተጨማሪም በሕዝቅኤል መጎናፀፊያ ላይ ያለዉ ፀጉር ከቅሬታዎቹ አካል ዉስጥ በመሆን የሚተርፉትን ይወክላል ፡፡ ዋይርስቤ

“ የእስራኤል ሁሉም ሕዝም በሲና ተራራ ላይ የእግዚአብሄርን ኪዳን ተቀበልዋል (ዘጸ 20፡ 18-21) ነገር ግን ከእነርሱ ዉስጥ አብዛኞቹ እግዚአብሄርን ለመታዘዝ በመዉደቃቸው በምድረበዳ ሞቱ ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከሕዝቡ መግባት ተከትሎ ባሉት አመታት ሕዝቡ ቀስ በቀስ መንፈሳዊነት ሲቀንሱ የሚፀልዩ፣ የእግዚአብሄርን ቃል የሚታዘዙ እና ለእግዚአብሄር የታመኑ ሆነዉ የተቀመጡ ቅሬታዎች ነበሩ ፤ በእስራኤል የወደፊት ጊዜ አስፈላጊ ስራን የሚጫወተዉ ይህ ቅሬታ ነው (ኢሳ 1፡ 9, 11፡ 11, 37፡ 31, ኢዩ 2፡ 32, ሚክ 2፡ 12, 5፡ 7, ሶፎ 2፡ 4-7, ዘካ 8፡ 1-8, ሚል 3፡ 16, ሮሜ 9፡ 27, 11፡ 5) “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ለሕዝቅኤል ያለዉ ሀረግ/ቃል አዲስ ዳዊት ሲሆን አዲሱ እረኛ ማለትም ይቻላል ( ሕዝ 34፡ 22-24) ፡፡ ቅሬታዎቹን እንደ በጎች እና አዲሱን ዳዊት ለማዳን በጎቹን(ቅሬታዎቹን) ለመጠበቅ የመጣ እንደ ነበር አስቡ ፡፡

በቁጥር 14 እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን “ በአሕዛቦች መካከል የከሰረች እና የተዋረደች እንደሚያደርጋት “ እና በአጠገቧ የሚያልፉት ሁሉ እንደሚያዩአት ቃል ገባ ፤ ኢየሩሳሌም በሌሎች ሕዝቦች እንደ ዉርደት፣ እንደ ማስጠንቀቂያ እና እንደ መቀለጃ/ማፌዥያ የምትታይ ትሆናለች ፡፡ እግዚአብሄር ርሀቡን እንደሚያጠነክረዉ እና አደገኛ እንስሳቶችን እልክባቸዋለሁ አለ (ቁጥር 15-17) ፡፡

መደምደሚያ

የሕዝቅኤል ሚና መልዕክቱን ማድረስ ነበር ፤ ጥያቄዉ የቅሬታዎቹ አካል እንሆናለን ወይስ አንሆንም ? የሚል ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 172.

  2. Wiersbe, pp. 172-173.

  3. Wiersbe, p. 173.

  4. Wiersbe, p. 173.

  5. Wiersbe, p. 173.

  6. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 899–900.

  7. Wiersbe, p. 174.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ለ390 ቀናት በግራ ጎኑ እንዲተኛ ለምን ነገረው ? ለምንስ በቀኝ ጎኑ ለ40 ቀናት (ሕዝ 4፡ 4-6) ? ይህ ምንን ወክሏል/አመልክቷል ?
  2. በሕዝ (4፡ 14) ሕዝቅኤል እግዚአብሄርን በሰዉ ሰገራ/ፅዳጅ ላይ የበሰለ ምግብ እንዲበላ እንዳያደርገዉ ጠየቀዉ ፤ እግዚአብሄር ጥያቄዉን ተቀበለው አዎ ከሆነ ለምን ? (ዘሌ 17፡ 15, 22፡ 8, ዘዳ 14፡ 3-5, ኢሳ 66፡ 17, ሐዋ 10፡ 14)
  3. ሕዝ (5፡ 1-4) አንብቡ ፤ ይህ ለኢየሩሳሌም ምን መልዕክት እንዲደርስ ይመክር ነበር (ሕዝ 5፡ 11-12) ? እግዚአብሄር በሕዝቡ ለምን ተበሳጨ (ሕዝ 5፡ 5-10)
  4. በሕዝ (5፡ 9) እግዚአብሄር “ ስለ እርኩሰትሽም ሁሉ ያልሰራሁትን እርሱንም የሚመስል ደግሞ የማልሰራዉን ነገር እሰራብሻለሁ “ አለ ፤ እዚህ ላይ ምን እያመለከተ ነበር ? (ዘሌ 26፡ 26፡ 14-45, ሕዝ 5፡ 10)
  5. በግል አስተያየታችሁ ሕዝ (5፡ 3) ምንን ይወክላል/ያመለክታል ?
  6. በሕዝቅኤል (4-5) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 5:3

“But you are to take a few strands from the hair and secure them in the folds of your robe.”

ሕዝቅኤል የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ህዝብ ላይ በቅርቡ እንደሚገለጥ ተናገረ ፡፡ በአህዛብ መካከል የሆነችው ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ላይ ፣ በፍርዱና በትዕዛዛቱ ላይ አመጸች እርሱንም ተወች ፡፡ የእግዚአብሔር አሳብ ይፈጸማል ፣ ሲሶው ህዝብ በሰይፍ ይሞታል ፣ ሲሶው በቸነፈርና በራብ ይሞታል እንድሁም ሲሶው ይበተናል ሰይፍም ይከተለዋል ፡፡ ሆኖም ግን ከፍርዱ የሚተርፉት የእስራኤል ህዝብ ቅሬታዎች ፣ እነርሱ እግዚአብሔር የመረጠውን ህዝብ ፈጽሞ እንደማያጠፋ ያረጋግጣሉ ፡፡ ሕዝቅኤልም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከጺሙ ጥቂቱን ወስዶ በመጎናጸፊያው ውስጥ በመክተት ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ ፣ ኪዳን አሳወቀ ፡፡

ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር የክርስቶስ አማኝ ሆነው የእርሱን መንገድ በትክክል የሚከተሉትን ይፈልጋል ፡፡ አዎን በጸጋ ድናችኋል ፣ ነገር ግን ህይወታችሁን ፈጽማችሁ ለእርሱ አሳልፋችሁ በመስጠት እየኖራችሁ ነውን ? እርሱን ስትከተሉ የእግዚአብሔርን ሙላት መልካምነት ትቀምሳላችሁ ፡፡ ልክ ሕዝቅኤል ከጸጉሩ ትንስ ቆርጦ በመጎናጸፊያው ውስጥ እንደሸሸገ ሁሉ እናንተም እግዚአብሔርን ስትከተሉና ራሳችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ ስትሰጡ ፣ እርሱ በክንፎቹ ጥላ ስር ይሸሽጋችኋል ፡፡ እርሱ ይጠብቃችኋል ይጠነቀቅላችኋልም ፡፡ እርሱ መልካም እረኛ ነው ይወዳችሁማል ፡፡

“ ከዚያም በጥቂቱ ውሰድ በመጐናጸፊያህም ጫፍ ቋጥራቸው ። “

  • ሕዝቅኤል 5፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 1:9 — “ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር ። “

ሕዝቄኤል 5:11–12 — “ ስለዚህ ፥ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ፤ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም ። ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል ፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃል ፤ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ ። “

ኤፌሶን 3:17b–19 — “ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል ፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ ። “