Messenger, Sufferer, Watchman, And Sign
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሕዝቅኤል ጥልቅ እና ኃይለኛ ነበር ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ሕዝቅኤል “ ይህን እንዲበላው “ ተነግሮት ነበር ፤ ሕዝቅኤል ራዕይ ባዬ ጊዜ እያለቀሱ ከነበሩት ምርከኞች ጋር ነበር ፡፡ ሕዝቅኤል የሚያብረቀርቅ ብርሀን፣ ኪሩቤል፣ አራት ህያዋን ፍጥረቶች፣ አራት ፊት፣ ክንፎች፣ መንኮራኩሮች ያላቸዉ እና ሁሉም በሚያዝዛቸዉ በእግዚአብሄር መንፈስ እንደሚንቀሳቀሱ ያየዉ ራዕይ ነበረው ፡፡ በተጨማሪም በወገቡ ዙሪያ ላይ እሳት ያለዉ ከአንድ ሰዉ ጋር የሆነ ዙፋንም ነበር ፤ ይህ የሚያስደንቅ የእግዚአብሄር መገኘት ራዕይ ነበር ፡፡ “ መለኮታዊ መገለጥ/መታየት ለሕዝቅኤል በ (1፡ 1-28) ሲሆን ለሕዝቅኤል መለኮታዊ አሳይመንቱ ደግሞ በምዕራፍ (2፡ 1-3፡ 27) ነበር “ ፡፡ ሕዝቅኤል ወደ አመፀኞቹ እስራኤላዊያን የመሄድ አሳይመንትን አገኘ ፡፡
በሁለተኛዉ የግዞት መወሰድ ጊዜ ሕዝቅኤል እዛዉ ነበር ፡፡ የመጀመሪያዉ የስደት ጊዜ በዳንኤል ጊዜ ነበር ፤ ሁለተኛዉ ስደት ደግሞ በሕዝቅኤል ጊዜ ነበር ፤ ሰዎስተኛዉ ስደት ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት 586 ይሆናል ፡፡ ዉድቀቱ በተከናወነ ጊዜ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ጊዜ ሕዝቅኤል በኢየሩሳሌም ይሆናል ፤ እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን እስራኤላዊያን የማይወዱትን እና የማይቀበሉትን መልዕክት እየሰጠዉ እንደ ነበር እየነገረዉ ነበር ፡፡ ሕዝቅኤል ቃሉን የማይናገር ከሆነ በራሱ ላይ ይሆንበታል ፤ ቃሉን ከተናገረና በቃሉም ምንም ነገር ካላደረጉ በራሳቸዉ ላይ ይሆናል ፡፡ እግዚአብሄር ቃል ከተናገረና ከተቀበሉት ሁሉም ሰዉ ያሸንፋል ፤ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ማንም ይህን ሊቀበለዉ አልፈለገም ፡፡
ትምህርት
ሕዝቅኤል (3፡ 1-9)፡ ሕዝቅኤል ይህን መፅሐፍ እንዲበላ እና ለእስራኤል ቤት እንዲናገር ተነገረው ፡፡ በእግዚአብሄር ለእርሱ ተመግቦት የነበረዉን መፅኀፉን በበላዉ ጊዜ አሁንም ሕዝቅኤል በራዕይ ዉስጥ ነበር ፤ ጣዕሙ እንደ ማር ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ መልዕክቱ በእስራኤል ላይ ስለፍርድ ቢሆንም እንኳን መፅኀፉ ታፋጭ ነበር ምክንያቱም የእግዚአብሄር ቃል ስለ ነበርና (መዝ 19፡ 10, 119፡ 103) ኤርምያስም የተደሰተበትን በቅድስና፣ በፅድቅ፣ በታማኝነት እና በክብር እግዚአብሄርን ስላረጋገጠ (ኤር 15፡ 16) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ቃሉ አስቸጋሪ ይሆናል ነገር ግን በቃሉ ዉስጥ ጥፍጥና ነበር ምክንያቱም ከእግዚአብሄር ስለ ነበር ፡፡ ከፍርዱ የተነሳ በዉስጡ መራርነት ሊኖር ይችላል ነገር ግን ጣፋጭ ነበር ፡፡
በቁጥር (4-27) የእግዚአብሄር ቃል እወጃ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር መልዕክተኛ እንዲሆን ሕዝቅኤል አስፈለገው ፤ እስራኤል ተደራሻ ስትሆን መልዕክቱ የእግዚአብሄር ቃል ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ሕዝቅኤል መልዕክተኛዉ እንደ ነበር የእስራኤል ሰዎች ደግሞ ተደራሾቹ እንደ ነበሩና የእግዚአብሄር ቃል ደግሞ የሚደረሰዉ መልእክት እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ ሕዝቅኤልን የሰሙት አብዛኛዎቹ ሰዎች ከይሁዳ ከደቡቡ መንግስት ነበሩ ፡፡
እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ “ ነቢዩ የተተካን መልዕክተኛ እንዲልክ እንዲሁም ደግሞ መልዕክቱን እንዲቀይር እና ወደ ተለዩ ተደራሾች እንዲሄድ አልተፈቀደለትም ነበር “ ፡፡ ሕዝቅኤል አዋጅ ነጋሪ ነበር ፤ መልዕክቱን እንዴትም ይቀበሉት እንደ ነበር የሚጨነቅ/የሚያስብ አልነበረም፣ መሄድ ብቻ ነበረበት ፡፡ ምንም እንኳን እግዚአብሄር አይሰሙም ቢልም ሕዝቡ ምን እያለ እንደ ነበር መረዳት ይችላሉ ፡፡ ሕዝቅኤል የሄደበት ክርስቶስ ከሄደበት ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡
እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን ያበረታዋል ፤ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር ለነቢዩ በተቃዉሟቸዉ እና አለመታዘዛቸዉ ፊት መቆም እንዲችል የሚያስፈልገዉን ሁሉ እንደሚሰጠው አረጋገጠለት ፤ በሕዝ (3፡ 8) በሕዝቅኤል ስም ላይ የሚጠነጥን ቃል ጨዋታ ነዉ ማለትም “ እግዚአብሄር ኃያል ነው “ ወይም “ እግዚአብሄር ያበረታል ማለት ነው ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር ያጠነክራል ማለት ነው ፡፡ ሕዝቡ ልባቸዉን እና ፊታቸዉን ቢያጠነክሩም እግዚአብሄር አገልጋዩን በማጠንከር ለአገልግሎቱ/ለተልዕኮ የታመነ ያደርገዋል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ነቢዩን እንደ ስሙ ትርጉም እንዲኖር ያስችለዋል ፡፡
ሕዝቅኤል (3፡ 10-15)፡ በቁጥር 10-15 ሕዝቅኤል እንደ መከራ ተቀባይ እንዲሁም እንደ መልዕክተኛ እንደ አንድ ምሳሌ በመሆኑ ሽግግር ነበር ፡፡ ወደ ሰማይዊ ወደ ሆነ ራዕይ ዉስጥ ከፍ ተደርጎ ነበር ፤ በምዕራፍ 1 ሕዝቅኤል ራዕይ ነበረው፣ በምዕራፍ 2 እግዚአብሄር ራዕዩን እያቀረበለት ነበር፣ በምዕራፍ 3 ወደዚህ ራዕይ ዉስጥ ተነስቶ/ከፍ ተደርጎ ነበር ፡፡ ሕዝቅኤል ከፍ በተደረገ ጊዜ በተበሳጨ መንፈስ ዉስጥ ነበር ፤ የምሬት እና ከፍ የመደረግ እርግጠና አለመሆን በስሜታዊነት የመመለስ ዉጤትን ያመጣል ፡፡ ሕዝቅኤል ግራ ተጋብቶ እና ተበሳጭቶ ነበር ነገር ግን እግዚአብሄር የአይሁድ ምርኮኞች በነበሩበት ስፍራ በቴልአቢብ በሕዝቡ ፊት ለፊት አስቀመጠው ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሕዝቅኤል በዚያ ለሰባት ቀን ተቀመጠ ፡፡
እዚህ ስፍራ ላይ ሕዝቅኤል እያለፉበት በነበረዉ ሁኔታ ዉስጥ በሕዝቡ መካከል ነቢይ ነበር ፤ ለማይረዱት ሕዝቦች ቃሉን እያቀረበ ነበር ፡፡ ክርስቶስን ከገጠመዉ ነገር ጋር ተመሳሳይነት ነበረው ፡፡ ክርስቶስ ፈተና ምን እንደ ነበር፣ ድህነት ምን እንደ ነበር፣ ፍርኃት ምን እንደ ነበር፣ ድካም ምን እንደ ነበር እና መገፋት ምን እንደ ነበር ያውቃል ፤ ሕዝቅኤል ብስጭት ምን እንደ ነበር፣ ኃዘን ምን እንደ ነበር እና መናቅ/መዘለፍ ምን እንደ ነበር ያውቃል ፤ በተጨማሪም ብቸኝነት ምን እንደ ነበርም ያውቃል ፡፡ እኛ ባለፍንበት ሁሉ አልፏል ፡፡
ሕዝቅኤል (3፡ 16-17)፡ ዋይርስቤ ሕዝቅኤል “ መልዕክተኛ፣ መከራ ተቀባይ እና ጠባቂ “ እንደ ነበር ያመለክታል ፤ በእግዚአብሄር መገኘት ፊት ነበር አሁን ደግሞ ከሕዝቡ ጋር ተመልሶ ነበር ፡፡ ሕዝቡ አይሰሙትም ወይም አይቀበሉትም ፤ “ ይህ ተግባር በአንድ ከተማ ቅጥር ላይ የጠላትን መቅረብ በንቃት በመከታተል ነዋሪዎችን ለመከላከል እንዲሰበሰቡ ከሚያደርግ አንድ ዘበኛ ተግባር ጋር በመንፈሳዊነት ይመሳሰል ነበር ፤ ነብዩ ስለቀረበዉ ፍርድ በጊዜዉ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቷል ፡፡ የዘበኛ ስራ ቀድሞ በ2ሳሙ (18፡ 24-27) እና 2ነገ 9፡ 17-20) በግልፅ የተቀመጠ ነው “ ፡፡
ሕዝቅኤል (3፡ 18-21)፡ በቁጥር 18 ለክፉ ሰዉ ቃልን ተናግሯል ፤ ማስጠንቀቂያ የተሰጠዉ አንድ ክፉ ሰዉ ካልተቀየረ ይሞታል ነገር ግን ነቢዩ የራሱን ሕይወት ያድናል ፡፡ ከፅድቅ ስራዉ ዞር ያለ አንድ ፃድቅ ሰዉ መንገዱን ካልቀየረ ይሞታል ፤ ነገር ግን በቁጥር 21 ኃጢዓት እንዳይሰራ አንድ ጻድቅን ሰዉ ካስጠነቀቅከው እና ኃጢዓትን ካላደረገ እና ማስጠንቀቂያዉን እና ነቢዩን ከሰማ ህይወቱን ያድናል ፡፡ ዋይርስቤ “ አራቱ ሁኔታዎች/ችግሮች የሚይዙት፡ የመጀመሪያው ዘበኛዉ ያልታመነ ስለነበርና ስላላስጠነቀቃቸዉ ሕዝቡ ይሞታል፣ ሁለተኛው ዘበኛውክፉዎችን ለማስጠንቀቅ የታመነ ይሆናል ነገር ግን አይሰሙትም፣ ሰዎስተኛው ከኪዳን መታዘዛቸዉ በመመለሳቸዉ እና ዘበኛው ስላላስጠነቀቃቸዉ ፃድቃን ይሞታሉ እና የመጨረሻው ፃድቃን የዘበኛዉን ማስጠንቀቂያ የሰሙ ስለሚሆን የተፈረደባቸዉ አይሆኑም “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ሕዝቅኤል ቃሉን ካላደረሰ በራሱ ላይ ይሆንበታል ፡፡
ሕዝቅኤል (3፡ 22-27)፡ በተጨማሪም ሕዝቅኤል እንደ ምልክት አገለገለ ፤ ዋይርስቤ “ ሕዝቅኤል ለሕዝቡ የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ አልተናገረም ነገር ግን በፊታቸዉ የእግዚአብሄር መልዕክት ምን እንደሚመስል በሚያዩበት መንገድ በፊታቸዉ እንደ ኖረ “ ይላል ፡፡ በሜዳ ላይ የእግዚአብሄርን መገኘት እንደ ገና አገኘው ፤ መንፈስ ቅዱስ በመምጣት በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ አልፏል/ሄዷል ፡፡ ከፍተኛ የሆኑት የሕዝቅያስ አገልግሎቶች በቁጥር 24 ላይ በተጠቀሰዉ በቤቱ ዉስጥ የተፈፀሙ ነበሩ ፡፡ ማክአርቱር “ በላያችሁ ላይ ገመድን ያደርጉባችኋል ፤ እነዚህ ገመዶች በቀጥታ ቃል በቃል አልነበሩም መንፈሳዊ እንጂ ፡፡ በአንድኛዉ እጅ አመፀኞቹ አይሁዶች በመንፈሱ ላይ የሚያደርሱት ተፅዕኖ የሚጭኑ የዉስጣዊ ገመዶች ሊኖራቸዉ ይችላል ፤ ጠማማነታቸዉ ልክ እንደ ገመድ በስብከቱ ነፃነቱን አምቆ እንደሚይዘዉ “ ይገልፃል ፡፡
መደምደሚያ
ሕዝቅኤል እግዚአብሄር በእርሱ የሚለዉን ብቻ ለሕዝቡ ይናገር ነበር ፤ ጆሮ የነበረዉ ሁሉ ይሰማል ፡፡ እግዚአብሄር አፉን ሲከፍት ብቻ ይናገር ነበር ፡፡ “ ሁለት ምርጫዎች አሉ ልክ እንደሚታዘዝ አገልጋይ መኖር እና እዉነት መስማት እንደማይፈልጉት አመፀኛ ሰዎች መኖር “ ፤ ይህ ለቤተ ክርስቲያን መልዕክት ነው ፤ ይህ ለሕዝቅኤል አስደናቂ ጥሪ እና አገልግሎት ነበር ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 896.
MacArthur, p. 897.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (David C. Cook, Colorado Springs, 2002), p. 169.
Wiersbe, p. 168
Wiersbe, p. 168..
Wiersbe, p. 169.
MacArthur, p. 897.
Wiersbe, p. 169.
Wiersbe, p. 169.
MacArthur, p. 898.
Wiersbe, p. 169
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን መፅሀፉን እንዲበላ ለምን ነገረው ? ይህ ምንን ያመለክታል ?(ሕዝ 3፡ 3-4, ራዕ 10፡ 9-11)
-
እስራኤል እንደ ማትሰማዉ እግዚአብሄር ሕዝቅያስን የነገረዉ ምክንያት ምን ነበር ? የእስራኤላዉያን መከራ ወደ እግዚአብሄር እንዲቀርቡ ወይስ በይበልጥ እንዲርቁ አድርጓቸዋል ? ለዚህ ስራ እግዚአብሄር እንዴት አዘጋጀው ? (ሕዝ 3፡ 8-9)
-
እግዚአብሄር ነግሮት ስለ ነበረዉ ነገር የሕዝቅኤል ምላሽ ምን ነበር (ሕዝ 3፡ 14-15) ? ሕዝቅኤል ከሕዝቡ ጋር በኃዘናቸዉ እንዴት ተለዬ ? (ዘሌ 8፡ 33, ኢዮ 2፡ 13, መዝ 137፡ 1)
-
ሕዝቅኤልን ዘበኛ እንዲሆን የመሾመበት የእግዚአብሄር አላማ ምን ነበር ? ጠባቂነቱ ለማን ነበር (2ሳሙ 18፡ 24-27, 2ነገ 9፡ 17-20) ? በአዲስ ኪዳን ስሜት ለዚህ ተግባር እንዴት የተጠራችሁ ናቸው ? (ማቴ 28፡ 18-20)
-
ሕዝቅኤል ለሕዝቡ የሚናገርበት ብቸኛዉ ጊዜ መቼ ነበር (ሕዝ 3፡ 22-27) ? ከአመፀኞች ቤት ወይም ታዛዥ አገልጋዩ ሕዝቅኤል ራሳችሁን ከማን ጋር አገናኝታችሁ ታዩታላችሁ ?
-
በሕዝቅኤል 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezekiel 3:22–23
“Then the hand of the LORD was on me there, and He said to me, ‘Get up, go out to the plain, and I will speak with you there.’ So I got up and went out to the plain. The LORD’s glory was present there, like the glory I had seen by the Chebar Canal, and I fell facedown.”
እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንድያገለግለውና ለህዝቡ በተለያዩ መንገዶች እንድናገር ጠራው ፤ በእርሱም አፍ ውስጥ እንደ ማር የሚጣፍጠውን ቃሉን እንደሚያኖርም ተናገረው ፡፡ ከዚያም ሕዝቅኤል ህዝቡ ሊሰሙ የማይፈልጉትን መልዕክት ይናገራል ፡፡ ሕዝቅኤልም በእስራኤል ቤት ላይ ጉበኛ ይሆናል ፤ እርሱም ሊያስከፍለው የሚችለው ዋጋ ምንም ይሁን ፣ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን ለህዝቡ ይናገራል ፡፡ በዚህ ሁሉ ሕዝቅኤል ከእግዚአብሔር የሰማውን በመታዘዝ ተከተለ ፡፡
መታዘዝ ማለት እንድታደርግ የተነገረህን ነገር ስታደርግ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመስማትና ለማዳመጥ ጊዜን ሳትሰጥ ፣ እንዴት ነው ለእርሱ የምትታዘዘው ? ይህ ማለት ልክ አንድ ልጅ የቤተሰቦቹን ትዕዛዝ ለመስማት ጊዜ አልሰጥ ሲል እንደ ማለት ነው ፡፡ ራሰህን እግዚአብሔር ሲናገር መስማት በምትችልበት ቦታ ላይ ማስቀመጥ አለበህ ፡፡ ከጌታ ጋር ስትራመድ ፣ መንፈስ ለመንግስቱ እንድትሰራ የሚያዝህን ትሰራለህ ፣ እንድትሄድ ወደሚያዝህ ትሄዳለህ ፣ እንድትናገር የሚያዝህን ትናገራለህ ፡፡ ይህንን እወቅ ስለ አለመታዘዝህ በእግዚአብሔር ተጠያቂ ነህ ፡፡ እግዚአብሔርን አዳምጥ ፡፡ ልክ እግዚአብሔር የምትናገረውን ቃል ሲሰጥህ በመታዘዝ አፍህን ክፈት ፡፡ አስታውስ በመንፈስ ስትመላለስ እግዚአብሔር ለአንተ አሳብ አላማ አለው ፡፡
“ በዚያም የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች ፥ እርሱም ፦ ተነሥተህ ወደ ቈላው ሂድ በዚያም እናገርሃለሁ አለኝ ። እኔም ተነሥቼ ወደ ቈላው ሄድሁ ፤ እነሆም ፥ በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ክብር ያለ የእግዚአብሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር ፥ በግምባሬም ተደፋሁ ። “
- ሕዝቅኤል 3፡22-23
ተጨማሪ ጥቅስ
ሕዝቅኤል 3:10–11 — “ እርሱም ፦ የሰው ልጅ ሆይ ፥ የነገርሁህን ቃሌን ሁሉ በልብህ ተቀበል በጆሮህም ስማ ። ተነሥተህም ወደ ተማረኩ ወደ ወገንህ ልጆች ሂድ ፤ እነርሱም ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው አለኝ ። “
ሕዝቅኤል 3:27 — “ ነገር ግን በተናገርሁህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አንተ ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የሚሰማ ይስማ ፥ የማይሰማም አይስማ ትላቸዋለህ ። “
ገላትያ 5:25 — “ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።