Major Prophets Ezekiel

Ezekiel's Vision

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New David Ezekiel 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 626 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በታላላቅ ነቢያት በሕዝቅኤል ላይ ይህ የአዲስ ጥናት መጀመሪያችን ነው ፡፡ ትናትና ሕዝቅኤልን እንደ አንድ “ አስገራሚ ሰዉ “ ገልጨዋለሁ ፡፡ በመጀመሪያም መፅሀፉ ለሕዝቅኤል የተሰየመ ነበር ፤ ኮንስታብል የሕዝቅኤል ስም “ እግዚአብሄር አጠነከረ ወይም እግዚአብሄር ያጠነቅራል “ ማለት ነው (ሕዝ 3፡ 8-9) ፡፡ በአገልግሎቱ “ ሕዝቅኤል በግዞት ለነበረዉ ሕዝቡ የእግዚአብሄርን መልዕክት ለመናገር እና ለማሳየት ራዕይን፣ ትንቢትን፣ ምሳሌዎችን፣ ድንቆችን እና ምልክቶችን ይጠቀማል “ ፡፡

በምዕራፍ 1 ለሕዝቅኤል የመጣለትን ራዕይ ማክጊ “ የእግዚአብሄር ሰዉ ራዕይ እንዳልሆነ - በእዚያ አላየዉ ፤ ይህ የእግዚአብሄር መገኘት ራዕይ ነው፣ ቴዎፋንይ ነው ፤ የክብር አምላክ በሰረገላዉ ላይ በድል ተቀምጦአል በሚሞተዉም ሰዉ እንደማይታይ “ ይናገራል ፡፡

ቁጥር 1 የመፅሀፉን እድሜ ያስቀምጣል ፡፡ ምናልባትም “ 30 አመት “ የእግዚአብሄር ራዕይ መጀመሪያ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ የሕዝቅኤልን እድሜ ያመለክታል ፡፡ ማክአርቱር ሕዝቅኤል “ ከክርስቶስ ልደት 593 በፊት ትንቢት ለመናገር፣ ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት በመጀመር በንጉስ ዮአኪን አምስት የምርኮ አመታት ጊዜ በባቢሎን ( “ በከለዳዉያን ምድር “ ) ትንቢት ለመናገር ጥሪዉን እንደተቀበለ “ ይገልፀዋል ፤ ከአምስት አመት በፊት በ25 አመቱ በምርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ ፡፡ የሕዝቅኤል አገልግሎት ከ22 እስከ 23 አመት ቆይቷል (ሕዝ 29፡ 17) ፡፡ የኤርምያስ ዘመን ሰዉ የነበረ እና እንደ ዳንኤል ተመሳሳይ እድሜ አለው ፡፡ ከእግዚአብሄር ጥሪ በፊት ካህን ነበር (ሕዝ 1፡ 3) ፤ ኤርምያስ፣ ዘካሪያስ እና መጥምቁ ዮሐንስም ካህናት እና ነቢያት ሁለቱንም ነበሩ ፡፡

ሕዝቅኤል ያገባ ሲሆን ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት ወደ ባቢሎን ተወስደዉ ከነበሩት 10,000 አይሁዶች ዉስጥ አካል ነበር (2ነገ 24፡ 11-18) ፡፡ በሕዝ (3፡ 15) መሰረት ምናልባትም ከባቢሎን ደቡብ ምስራቅ ይገኝ በነበረው በኮበር ወንዝ ዳርቻ በቴልአቢብ ኖሩ ፤ በምርኮ ጊዜ በዚያ ሚስቱ ሞተች (ሕዝ 24፡ 18) ፡፡ በአይሁድ ታሪክ አዋቂዎች መሰረት ሕዝቅኤል “ ከክርስቶስ ልደት 560 በፊት አካባቢ በገሰፀዉ አንድ ጣዖት በሆነ እስራኤላዊ ልዑል/አለቃ እጅ ሞተ “ ፡፡

ሕዝቅኤል ትንቢቶቹን በመፅሀፉ በዉስጥ ቀኑን መዝግቧል ለምሳሌም ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት (ሕዝ 8፡ 1)፣ ከክርስቶስ ልደት 573/572 በፊት (ሕዝ 40፡ 1) እና ከክርስቶስ ልደት 571-570 በፊት (ሕዝ 29፡ 1) ፡፡ ምዕራፍ (1-29) በቅደም ተከተላቸዉ የተፃፉ ነበሩ ነገር ግን በምዕራፍ 29 ሕዝቅኤል ከሕዝ (26፡ 1) በፊት ወደ ነበረዉ አመት ተመለሰ ፤ ይሁን እንጂ በምዕራፍ 30 የቀረዉን ወደ ጠቅላላ ጊዜ ቅደም ተከተሉ ሄደ ፡፡

በታሪካዊነት ከ110 አመታት በኋል እንደ ተዋሀደ አንድ ሕዝብ ከክርስቶስ ልደት 931 በፊት እስራኤል ወደ ደቡብ እና ሰሜን መንግስት ተለያዬች ፤ የሰሜኑ የእስራኤል መንግስት ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት በአሶራዊያን ወደቀ ፤ ከ135 አመታት በኋላ የደቡቡ የይሁዳ መንግስት ከክርስቶስ ልደት (605-586) በፊት በባቢሎን ወደቀ ፡፡ የአሶራዊያን ሰራዊት በመፍረሱ ዋና ከተማዋ ነንዌ በባቢሎናዊያን እና በሜዶን ፈረሰች (ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት) ፡፡ ባቢሎን ስፍራዎችን መቆጣጠሯን በመቀጠል ሙሉ በሙሉ አሶርን እና ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት ግብፅን በከርከሚሽ ላይ አሸነፈች ፤ ከዚያም ባቢሎን በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ላይ ቀጠለች ፡፡ ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት ኢየሩሳሌም በባቢሎን በመዉደቅ የኢየሩሳሌም ሰዎች ምርኮኝነት ጀመረ ፤ ከክርስቶስ ልደት 596 በፊት ባቢሎን የኢየሩሳሌም ከተማ አጠፋቻት ፡፡

ይህ ለሕዝቅኤል መፅሀፍ መነሻ ሀሳብ ነው ፤ ምርኮኞቹ ወደ ባቢሎን የተወሰዱባቸዉ ሰዎስት ጊዜያት ነበሩ ፡፡ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ምርኮ ትንቢትን ተናግሯል ነገር ግን ይህ ራሱ አልቀመሰዉም/አላየዉም ፡፡ ኤርምያስ ሁለቱንም ስለ ምርኮዉም ተንብዮአልም ምስክርም ነበር ፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት ከኢየሩሳሌም ተወስደዉ በነበሩት የመጀመሪያዎቹ የምርኮ ቡድን አካል ነበር ፤ ሕዝቅኤል ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት በመጋቢት 16 ላይ ንጉስ ዮአኪን ከአካተተዉ ከሁለተኛዉ የምርኮ ቡድን ጋር የተወሰደ ነበር ፡፡ ሰዎስተኛዉ የምርኮኛ ቡድን ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ወደ ባቢሎን የተወሰደ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ዳንኤል እና ሕዝቅኤል ሁሉም በተመሳሳይ የጊዜ ቆይታ ዉስጥ አገልግለዋል ፤ ማክአርቱር ወደ ባቢሎን ተሰደዉ የነበሩትን “ በብዛት ከተማራኪ በላይ እንደ ወራሪ/እንደ ገዢ በመኖር በጥቂት የሚመች ሁኔታ ዉስጥ የምድሪቱን ትራክት እንዲያርሱ የተፈቀደላቸዉ እንደሆኑ (ኤርምያስ 29) “ ይገልፃል ፡፡ በሕዝ (3፡ 24) መሰረት ሕዝቅኤል የራሱ ቤት ነበረው ፡፡

ልክ እንደ ኤርምያስ ሕዝቅኤል ሕዝቡን በባቢሎን ለረጅም ጊዜ እንደማይቆዩ ከተናገሩት ሐሰተኛ ነቢያቶች ጋር አዉርቷል/ተነጋግሯል ፡፡ ሕዝቅኤል ግዞቱ በጣም ስለሚቆይ ቤታቸዉን በባቢሎን መስራት እንደሚያስፈልጋቸዉ ከክርስቶስ ልደት 593 እስከ 583 በፊት አስጠንቅቋል ፡፡ ከክርስቶስ ልደት 585 በፊት የኢየሩሳሌም መፈራረስ በመጠናቀቁ አንድ ኮብላይ ከኢየሩሳሌም ጥፋቱን ለሕዝቅኤል ሪፖርት አደረገለት (ሕዝ 33፡ 21) ፡፡ የሕዝቅኤል አስታዋሽ አሁንም እግዚአብሄር ሁሉም በስሩ መሆኑ ነበር ፤ ሕዝቅኤል (1-24) “ የኢየሩሳሌምን መፍረስ ትንቢቶች “ ሲይዝ ከምዕራፍ (25-32) “ ለሕዝብ ሁሉ የሚገባ ቅጣት ትንቢትን “ ይሸፍናሉ፣ ምዕራፍ 33 “ የእስራኤል ንስኃ መግባት መሰጠትን “ የመዘገበ ሲሆን ምዕራፍ (34-48) “ የእስራኤልን የመታደስ ትንቢትን መዝግቧል “ ፡፡

ትምህርት

ሕዝቅኤል (1፡ 1-14)፡ መዝ (137፡ 1) በኮቦርም ቦይ (ወንዝ) አጠገብ እንደተቀመጡ ይናገራል ፤ ሕዝቅኤል ከእግዚአብሄር ራዕይን በዚያ ተቀበለ (ቁጥር 1) ፡፡ ታሪካዊ ቀኑ የእግዚአብሄር እጅ በእርሱ ላይ የመጣበት ንግግር የተካተተ ነው (ቁጥር 2-3) ፡፡ ሕዝቅኤል ታላቅ ንፋስ ያዘለ ዳመና ከሚያብረቀርቅ መብረቅ እና ከሚምር ፀዳል ጋር ገልፆአል (ቁጥር 4) ፤ ጄይ.ቮሮን ማክጊ ይህን የሚበረቀረቅ ብርኃን (ቁጥር 4, 13, 14) “ ከፀኃይ በላይ የሚያበራ ልክ እንደ አቶሚክ ፍንዳታ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ በቁጥር (5-26) ሕዝቅኤል እያንዳንዳቸዉ አራት ፊት እና አራት ክንፎች ያሉዓቸዉን ኪሩቤሎች ራዕይ ይገልፃል ፤ ማክአርቱር “ ወደ መጀመሪያዉ መዞር ሳያስፈልጋቸዉ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለማድረግ ወደ ማንኛዉም አቅጣጫ መንቀሳቀስ የሚችሉ እንደ ነበሩ “ ይናገራል ፡፡ ማክጊ በቁጥር 10 እና 18 “ የብልህነትን አላማ “ ማስረጃን ያመለክታል ፤ በተጨማሪም “ አሪቱ ፊቶች ክርስቶስ በአራት መልኩ የገለጣቸዉን አራቱን ወንጌላት ያሳስቡናል፡ በንግስናው - በአንበሳ ተወክለዋል (ማቴዎስ)፣ እንደ አገልጋይ - በበሬ ተወክሏል (ማርቆስ)፣ በፍፁም ሰብዓዊነቱ - በሰዉ መልክ ተወክሏል (ሉቃስ)፣ በአምላክነቱ - በሚበርር መለዓክ ተወክሏል (ዮሐንስ) “ በማለት አመልክቷል ፡፡

ሕዝቅኤል (1፡ 15-28)፡ በቁጥር (15-16) እያንዳንዱ ፍጥረት ከአጠገባቸዉ ካለ መንኮራኩር አንድ መንኮራኩር እንዳላቸዉ ገልፆአቸዋል (ቁጥር 15-16) ፡፡ ማክጊ ይህ “ የመለኮት ኃይል የማያቋርጥ ድርጊትን እና ኃይልን እንደሚያሳይ ፤ የእግዚአብሄር ወደፊት መቀጠል እና አርቆ አሳቢነት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር ክቡን በመንኮራኩሩ ዉስጥ “ የእግዚአብሄር ትልቅ ፍርድ ማሽነሪይ በማያሳስት እርግጠኝነት አላማዉን ስለ ማምጣት በጣም ግዙፍ ኃይል እንዳለዉ ነዉጥ “ ይገልፀዋል (ቁጥር 17-21) ፡፡ ራሳቸዉ በጠፈር አምሳያ የተሸፈነ ነበር፣ ክንፎቻቸዉ እርስ በእርሳቸዉ ተቃንተዉ ነበር እንዲሁም በእያንዳንዳቸዉ ላይ ሁለቱ ክንፎች ሰዉነታቸዉን ሸፍነዋል (ቁጥር 22-23) ፡፡ ክንፎቻቸዉ ልክ እንደ እግዚአብሄር ድምፅ ከኃይለኛ ጩኸት የተሰሩ ናቸው (ቁጥር 24) ፤ የእግዚአብሄር ድምፅ ከራሳቸዉ ድምፅ በላይ ሲመጣ ከእነርሱ በላይ ባለዉ ዙፋን ላይ ሰዉ (ምናልባትም ክርስቶስ) አለ (ቁጥር 25-26) ፡፡ ይህ ሰዉ በመዝ ( 103፡ 19) እና በራዕ (4፡ 2-8) ላይ የተሳለ ነው ፤ በእግዚአብሄር መገኘት በመዉደቅ የእግዚአብሄርን ድምፅ ሲናገር ሰማ (ቁጥር 28) ፡፡ የእግዚአብሄር ክብር የታዬ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ይሁን እንጂ ተገልፆ ያልነበረ የሆነ ነገር ለመስራት ኪሩቤል የለቀቀዉ የእግዚአብሄር ክብር ሰዉ መልክ መገኘት አለን ፤ ማክአርቱር ምዕራፍ 1 “ ለሕዝቅኤል እንደ መለኮታዊ መልክ “ እና ምዕራፍ 2 “ ለሕዝቅኤል እንደ መለኮታዊ አሳይመንት “ ይገልፃቸዋል ፡፡

5 Constable, p 1.

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 1; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ezekiel.pdf.

  2. MacArthur, p. 891.

  3. J. Vernon McGee, Ezekiel: Notes & Outlines, n.p.; available at https://ttb.org/docs/default-source/notes-outlines/no18_ezekiel.pdf?sfvrsn=2.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 891.

  5. MacArthur, p. 891.

  6. MacArthur, p. 891.

  7. MacArthur, p. 891.

  8. MacArthur, p. 891-892.

  9. MacArthur, p. 892.

  10. MacArthur, p. 894.

  11. McGee, n.p.

  12. MacArthur, p. 896.

  13. McGee, n.p.

  14. McGee, n.p.

  15. MacArthur, p. 896.

  16. MacArthur, p. 896.

ጥያቄዎች

  1. ለሕዝቅኤል የነበሩት ሁለት ስራዎች ምን ነበሩ (ሕዝ 1፡ 1-3) ? ሁለቱም የነበሯቸዉ ሌሎች ነቢያቶች ማን ነበሩ ? (ነህ 12፡ 16, ኤር 1፡ 1, ዘካ 1፡ 1)
  2. በእግዚአብሄር በትንቢታዊ አገልግሎት ሕዝቅኤል የተጠራዉ የት ነበር ?
  3. በሕዝቅኤል 1 ስለ እርሱ እየተማራችሁ ካደጋችሁት ወይም ስለ እግዚአብሄር ከምታዉቁት የተለዬ አንዳንድ የእግዚአብሄር ባህሪያት ምንድን ናቸው ? (ሕዝ 1፡ 25-28)
  4. የእግዚአብሄርን ክብር ባዬ ጊዜ የሕዝቅኤል ምላሽ ምን ነበር (ሕዝ 1፡ 25-28) ? ይህ ለእናንተ ካደረገላችሁ ነገር የተነሳ እንዴት እግዚአብሄርን መቅረብ እንዳለባችሁ እንድትረዱ ይረዳችኋል ? (ሮሜ 6፡ 6-11)
  5. በሕዝቅኤል 2 እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን መልሶ በእግሩ እንዲቆም እንዴት ኃልን ሰጠው ? ሕዝቅኤልን ሰጥቶት የነበረዉ ትዕዛዝ ምን ነበር (ሕዝ 2፡ 3-7) ?ይህ ለማይሰሙት ወንጌልን እንድትናገሩ ያበረታታችኋል?
  6. በሕዝቅኤል (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezekiel 2:3–5

“He said to me: ‘Son of man, I am sending you to the Israelites, to the rebellious pagans who have rebelled against Me. The Israelites and their ancestors have transgressed against Me to this day. The children are obstinate and hardhearted. I am sending you to them, and you must say to them, “This is what the Lord GOD says.” Whether they listen or refuse to listen—for they are a rebellious house—they will know that a prophet has been among them.’”

እግዚአብሔር በራዕይ ክብሩን ለሕዝቅኤል አሳየው ፡፡ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ሕዝቅኤል የእግዚአብሔርን ድምጽ በሰማ ጊዜ በፊቱ ተደፋ ፡፡ በዚያም ቅጽበት ሕዝቅኤል መለኮታዊ ተልዕኮውን ተቀበለ ፣ ተልዕኮውም ፡- በእግዚአብሔር ላይ ለመጹት ለእስራኤላዊያን እንድናገር ፡፡ እሺ ብለው ሊያደምጡ ወይም እምቢ ሊሉ ይችላሉ ነገር ግን በእነርሱ መካከል እግዚአብሔር ነቢይ እንደላው ያውቃሉ ፡፡ እግዚአብሔርም ነቢዩ ሕዝቅኤል አፉን ሲከፍት የሚናገረውን ቃል እርሱ እንደሚሰጠው ኪዳንን ሰጠው ፡፡

የሕዝቅኤል የተለየ የነቢይነት ጥሪ በአንድ አስፈላጊ መንገድ ከአንተ የደቀ መዝሙርነት ጥሪ ጋር ይመሳሰላል ፡፡ ኢየሱስ አንተንም ለተመሳሳይ ሀላፊነት ይጠራሃል ፣ እርሱም ፡- የኢየሱስ ክርስቶስን ክብርና የምስራች ወንጌል እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አንድትናገር ፡፡ አዎን እንድትናገር ማለትም ለእነዚህ ለማይሰሙትና ለማይታዘዙትም ጭምር ፡፡ ወደ ሁሉም ህዝቦች ስትሄድ ፣ የመጀመሪያዋን ጌታ አንተን የጠራባትን አጋጣሚ አስታውስ ፡፡ በውስጥህ ያለው እሳት በድፍረት ወደፊት እንድትራመድ ያነቃቃሃል ፣ ታድያ በፍርኃት መንፈስ አይደለም ይልቁንም በኃይል ፣ በፍቅርና ራስን በመግዛት መንፈስ እንጂ ፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረህ ለዚህ ነው ፡፡ የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ናትና በድፍረት ተራመድ ፡፡ እርሱ ስሙን ለማወጅ የሚያስፈልግህን ቃል ፣ የምትመልሰውን መልስና እያንዳንዱን ነገር እንደሚሰጥህ ይናገራል ፡፡ የእርሱን ድምጽ ጠብቅ ፣ አዳምጥ እናም ድምጹን እመን ፡፡ እርሱም ይገለጣል ፣ ለአንተም ራሱን ይገልጥልሃል ፡፡ በእርሱ ኃይል ታመን ተደገፍ ፡፡

“ እርሱም እንዲህ አለኝ ፦ የሰው ልጅ ሆይ ፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁ ወደ ዓመፀኞች ሰዎች ወደ እስራኤል ልጆች እልክሃለሁ ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ ። እነርሱ ፊታቸው የተጨማተረ ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው ። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ ፤ አንተም ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው ። እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ ። “

  • ሕዝቅኤል 2፡3-5

ተጨማሪ ጥቅስ

ሕዝቅኤል 1:28 — “ በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደ ቀስተ ደመና አምሳያ ፥ እንዲሁ በዙሪያው ያለ ፀዳል አምሳያ ነበረ ። የእግዚአብሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ ። ባየሁም ጊዜ በግምባሬ ተደፋሁ ፥ የሚናገርንም ድምፅ ሰማሁ ። “

ሕዝቅኤል 2:7 — “ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ቃሌን ትነግራቸዋለህ ። “

2ኛ ጢሞቲዎስ 1:6–8 — “ ስለዚህ ምክንያት ፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው ፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ ። እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና ። እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር ፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል ፡፡ "