Prayer For Restoration
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ My Portion Lamentations 4-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ከኢሳይያስ እና ከኤርምያስ መፅኀፍት በኋላ ጥናታችን ወደ ሰቆቃዉ ኤርምያስ ዞሯል ፡፡ አብዛኞቹ ምሁራን ነቢዩ ኤርምያስ ሰቆቃዉ ኤርምያስን እንደ ፃፈዉ ያምናሉ ፡፡ በመቀጠልም ወደ ሕዝቅኤል መፅሀፍ እንጓዛለን/እንቀጥላለን ፡፡ እነዚህ ሁሉ ነቢያቶች የተስፋን መልዕክት አቅርበዋል ፤ እግዚአብሄር እስራኤል እና ይሁዳ የሚያስፈልጋቸዉ ሁሉም ነገር ነበር ነገር ግን በእድል ፋንታቸዉን አልያዙትም ፤ ሁልጊዜ ምህረቱ አዲስ የነበረ ቢሆንም ሊያዩት አልቻሉም ፡፡
ኤርምያስ ሕዝቡ የሚመጣዉን የኢየሩሳሌም መፈራረስ የሚናገረዉን መልዕክቱን መስማት ስላልፈለጉ እንደ እቃ መያዣነት ያገለግል በነበረ ጉድጓድ ዉስጥ ተወርዉሮ ነበር ፡፡ ሕይወት ለእርሱ መልካም አልነበረችም ፤ ይሁን እንጂ (ኤርምያስ እና ሌሎች ነቢያቶች) እድል ፋንታቸዉ እና ምህረታቸዉ ከራሳቸዉ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደሚመጣ ተረድተዋል ፡፡ እግዚአብሄር ምህረቱን እንደሚያፈስስባቸው በመጠበቅ ተስፋ አደረጉ ፤ እግዚአብሄርን መጠበቅ እና መታመን አስፈላጊዎች ነበሩ ፡፡ ለእስራኤል እና ለይሁዳ ሰዎች እድል ፋንታቸዉን መቼ እንደሚያድስ ማንም አያዉቅም ነገር ግን ምናልባትም እግዚአብሄር ኤርምያስን ከጉድጓድ ያወጣበት እዉቀት ሁል ጊዜ በዚያ ነበር፡፡
የመጠበቅ ሂደቱ ያለሟቋረጥ በመፀለይ እና ወደ እግዚአብሄር መጮኽን አካትቷል ፤ ሰቆቃዉ ኤርምያስ 5 ለመነቃቀት፣ ለመታደስ እና ለትኩረት የተደረገ ጩኸት ነበር ፤ ይህ እንዲገለጥ ወደ እግዚአብሔር የተደረገ ጩኸት ነበር ፡፡ ኮንስታብል በምዕራፍ 5 “ ከቁጥር 2 እስከ 18 የምስጋና ዝርዝሮችን ይይዛል ፤ በቁጥር 1 እና 21-22 ያለዉ ልመና ይህን ክፍል የያዘና የዝርዝሩ አላማ የእግዚአብሄር ፍላጎት በደንብ ስለሚስብ እንደሚያደርግ ግልፅ እንደሚያደርግ “ ይገልፃል ፡፡
ሰቆቃዉ ኤርምያስ እንደ ታላቅ ለቅሶ የተገለፀ ነው ፤ ለኤርምያስ ኃዘኑን/ጭንቀቱን ለእግዚአብሄር ለማፍሰስ ሁሉም ትክክል ነበር ፡፡ ኃዘኑ ግልፅ የተደረገ ቢሆንም ኤርምያስ እግዚአብሄር ምህረቱን ማፍሰሱን እንደሚቀጥል ያውቃል ፡፡
ትምህርት
ሰቆቃዉ ኤርምያስ (5፡ 1-22)፡ በምዕራፍ 4 ራይኬን የሕዝቡ ቅጣት ምክንያት የመሪነት ዉድቀት እንደ ነበር አመልክቷል ፤ “ ነቢያቶቹ ኃጢዓትን ሰርተዉ ስለ ነበር ሕዝቡን ልክ እንደ ምግብ የእግዚአብሄርን ቃል እንዲራቡ ተዋአቸው ፤ የቤተ መቅደሱ ካህናት የንፁኃንን ደም አፍስሰዉ ነበር ፤ ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሄርን ቁጣ ዉርደት ይሸከማሉ፡ በኃይለኛዉ ንጉሱ መልካም/እንደ እግዚአብሄር የሆነ መሪነትን ለመስጠት ወድቆ ነበር ፤ ልክ እንደ ግብፅ አይነት እግዚአብሄራዊ ካልሆኑ አሕዛቦች ጋር ጥምረትን አድርጎ ነበር እናም ተስፋ የገባለት ተስፋም በፍፁም አልመጣም “ በማለት ፅፏል ፡፡
የመጀመሪያዎቹ 18 ጥቅሶች ትኩረት ለማግኘት ጩኸቶች ናቸው ፤ ማኬይ “ መፅኀፉ ለሌሎች እንደ ማስጠንቀቂያ ለማገልገል በመጀመሪያ አልተፃፈም ነበር ከዚያም የተነሳ የማህበረሱ ዉስጥ የተሰበሰበ ሀሳብ የቀድሞን መከራ እና ጥፋት ማስታወሻን ህያዉ ሆኖ እንዲጠበቅ ነበር ፤ በግልፅ በአንድ ደረጃ እነዚህ ግጥሞች ኢየሩሳሌም በሚያስጨንቅ በትልቅ ከበባ አጥተዉት በነበረዉ እና ከሞት በኋላ እንደ ቅሬታ እንዲሰሩ እንደ አንድ እንደነበሩት ሁሉንም ደግሞ በመጥራት ለቀድሞዉ ገባሮች እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡
እነዚህ ጥቅሶችም ስለ ትኩረት ማግኘት ነበሩ ፤ ኮንስታብል “ ኤርምያስ በያህዌ ሕዝቡን ይጠል የነበረዉ መቅሰፍት እና አሁን የሚኖሩትን እንዴት እንደሚወቅሳቸዉ እንዲያሳስባቸዉ ተጠርቷል (3፡ 34-36) ፤ የአይሁዳዊነት የትህትና ሁኔታ በደካማነት በእግዚአብሄር ላይ ተንፀባርቋል ምክንያቱም አሕዛቦች/ጣዖት አምላኪዎች በኃይል እና በነፃነት ሕዝቡን መጠበቅ አይችልም በማለት ደምድመዉ ስለ ነበር ፡፡ ኤርምያስ ያህዌ ሕዝቡን ካስታወሰ ነፃ ሊያወጣቸዉ እንደሚሰራ ማለቱ እንደሆነ (ዘጸ 2፡ 24-25, 3፡ 7-8) “ ይናገራል ፡፡
ኤርምያስ ወደ እግዚአብሄር በሕዝቡ ላይ ያለዉ መዋረድ በእግዚአብሄር ላይ የሚያንፀባርቅ እንደ ነበር ለመነ ፤ የእነርሱ መዋረድ የእግዚአብሄር ዉርደት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ካስታወሰ ኤርምያስ አለቀሰ ነፃም ያወጣቸዋል ፡፡ ኤርምያስ ያነሳዉ ጥያቄ አይሁዶች ይህንን ራሳቸዉ ነዉ ያመጡት ወይስ አልነበሩም የሚል ነበር ፡፡ አሁን ለሚጠጡት ዉኃ ጨምሮ ለተቀበሉት እቃ ይከፍላሉ ፤ የተሳደዱ ነበሩ ለማረፍም እድል አልነበራቸዉም ፤ ነገር ግን የተስፋይቱ ምድር የእረፍት ምድር ለመሆን የተመረጠች ነበረች ፡፡ እረፍት ባልነበረበት በምርኮ ምድር ነበሩ ወይም ደግሞ እረፍት ባልነበረበት በራሳቸዉ ምድር ነበሩ ፤ እግዚአብሄር አቅዶት የነበረዉ ነገር ያ አልነበረም ፡፡ እግዚአብሄር እረፍትን ያቀረበላቸዉ ነበር ፡፡
አይሁዶች ራሳቸዉን ያገኙበት ዋናዉ ምክንያት የራሳቸዉ ኃጢዓት ነበር ፤ ማክአርቱር “ የአይሁዶች ኃጢዓት የተሞላው ላለተቀደሰ ጥምረት መታዘዘለጥበቃ እና ለመልካም ነገር በሰዉ ላይ እምነት ማድረግን ይገልጻል (ኤር 2፡ 18, 36) “ በማለት ይናገራል ፡፡ “ ለመኖር በቂ ምግብ ለማግኘትም እንኳን ሕዝቡ ለእርዳታ ግብፅን እና አሶርን ይለምናል ፤ ምናልባትም ይህ ከእነዚህ አሕዛቦች ጋር የአይሁድ የቀደም ጥምረት ከንቱነትን ያረጋግጣል (ሕዝ 16፡ 26-28, 23፡ 12, 21) ፤ ምናልባትም ፀኃፊዉ አሶራዊያንን ለባቢሎናዊያን እንደ ተተኪ ተጠቅሞባቸዋል (ኤር 2፡ 18) ፡፡ ሀሳቡ ይሁዳ ለራሷ ድጋፍ ማድረግ እንደማትችል ነገር ግን ከአሕዛብ ጠላቶቿ እርዳታን እንደምትለምን ነው “ ፡፡
ቁጥር 7 የወቅቱ ትዉልድ የቤተሰቦቻቸዉን ቅጣት ሸክም መሸከም እንደነበረባቸዉ ይናገራል ፤ በተጨማሪም ስለ ራሳቸዉ ኃጢዓት ቅጣት ነበረባቸው ፤ በራሳቸዉ ላይ አደጋን አምጥተዋል ፡፡ ምግብ በጣም አጥሮ ስለነበር በገለዳዉያን ጥቃት ስጋት የተሳ የወቅቱን አካባቢን ይለቃሉ ፤ ዉጤቱም ኢኮኖሚካል እና ፖለቲካል እንዲሁም ግላዊ ዉርደቶችን እና በደሎችን አካትቷል ፡፡ ከሞት በኋላ ሰዎች እንደ ዉርደት በራሳቸዉ እጅ የተንጠለጠሉ ነበሩ ፤ ሕዝቡ ልክ እንደ እንስሳት እየኖሩ ነበር ፡፡ ኮንስታብል “ ጎልማሳ ሰዎች እንደ እንስሳት ወይም አገልጋይ ሴት እህልን ይፈጫሉ (መሳ 16፡ 21) እና ህፃናት ልጆች ጠላት እንዲሸከሙ በሚያስገድዷቸዉ የእሳት እንጨት እንደ ደከሙ “ ይገልፃል ፡፡
በሰቆቃዉ ኤርምያስ 3 እግዚአብሄር ለሕዝቡ እንደ ተስፋ ታዉጆ ነበር ነገር ግን በሰቆቃዉ ኤርምያስ 5 ከኃጢዓታቸዉ የተነሳ ደስታ አልነበረም ፤ ደስታና ጭፈራ አልነበረም ምክንያቱም እነዚህን ሁኔታዎች በራሳቸዉ ላይ አምጥተዉት ስለ ነበር ፤ ዘዉዱ/ክብሩ ወድቆ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ የዳዊት ንጉሳዊነት አገዛዝ ለጊዜዉ አብቅቶ እንደ ነበርና ክርስቶስ እንደ ንጉስ እስኪ መጣ ድረስ እንደማይመለስ (ኤር 23፡ 5-8, ሕዝ 37፡ 24-28, ራዕ 19፡ 1-21) “ ፡፡ ዘዉዱ/አክሊሉ በክርስቶስ መመለስ ላይ ብቻ በእዉነት የሚመሰረት ነው ፡፡
የመታደስ ፀሎት እንዲመልሳቸዉ ለእግዚአብሄር ስለ ነበር ሕዝቡ መመለስ ይችላል ፤ ዮሐንስ ማኬይ “ ሀዘኑ ለትኩረት ከመለመን ወደ እነርሱን እንዲያድሳቸዉ ወደ እግዚአብሄር ወደ መፀለይ እንደ ሄደ “ ተናግሯል ፡፡ አሁንም ኤርምያስ ሁሉም ነገር በእግዚአብሄር ቁጥጥር ስር እንደ ነበር ሕዝቡን መመለስ እንደሚችል ያምናል ፤ ሕዝቡ እንዲያድሳቸዉ እግዚአብሄር ስላስፈለጋቸው ወደ ምድራቸዉ መመለስ ይችላሉ ፡፡
መደምደሚያ
ክርስቶስ መልስ ነው ፡፡ ክርስቶስ እስከ መጨረሻው እስኪመለስ ድረስ በዚህ ሂደት ዉስጥ እንሄዳለን ፤ እግዚአብሄር ለምን ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ጥያቄ እንጠይቃለን ፡፡ ኤርምያስ በሰቆ.ኤር (5፡ 21) ለመታደስ እና እንደ ገና ለመገንባት ፀለዬ ፤ ሕዝባችን በእግዚአብሄር መርህ ላይ የተመሰረተ ሲሆን መነቃቃትን ለማምጣት ፀሎት ለእግዚአብሄር መሆን አለበት ፡፡
9 MacKay, np.
Thomas Constable, Constables Expository (Bible Study Notes): Lamentations, p. 65; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/lamentations.pdf.
Phillip Graham Ryken, Jeremiah and Lamentations: From Sorrow to Hope (Wheaton, IL, Crossway, 2001), p. 767.
John L. MacKay, Lamentations: A Mentor Commentary, (Ross-Shire, Great Britain: Christian Focus Publications, 2008), p. 7.
Constable, p. 64.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 889.
Constable, p. 66.
Constable, p. 68.
MacArthur, p. 889.
ጥያቄዎች
-
ሰቆቃዉ ኤርምያስ 4፡ 4 እና 9 አንብቡ ፤ እነዚህ ጥቅሶች የመንፈሳዊ ነገር ድርቅ ምልክት እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ ? (ዘዳ 8፡ 3, ዮሐ 6፡ 33, 35)
-
ሰቆ. ኤር (4፡ 10) ከከበባዉ ለመዳን ሴቶች ለምግብነት ልጆቻቸዉን እንደ ቀቀሉ መዝግቧል ፤ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች እንዴት ያልተወለዱትን ያጠፋሉ ይህ እንዴት ከመንፈሳዊ ከበባ እና ከሚያመጣዉ ድርቀት ጋር ይገናኛል ?
-
በሰቆ.ኤር (5፡ 3 እና 7) ኤርምያስ በይሁዳ ጥፋት እንደ ዉጤቱ አካል አባት የሌላቸዉን ገልፆአቸዋል ፤ በአሁኑ ልምዳችን ለየቲምነት/አባት አልባ ልጆች እንዲፈጠሩ ምክንያቱ ምንድን ነው ? በይሁዳ ምርኮኝነት እና አሁን ባሉን ነገሮች ሁኔታ መካከል የመንፈሳዊ ነገር ተመሳሳይነቶች አሉ ?
-
በሰቆቃዉ ኤርምያስ 4-5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Lamentations 5:21–22
“LORD, restore us to Yourself, so we may return; renew our days as in former times, unless You have completely rejected us and are intensely angry with us.”
የእግዚአብሔር ህዝብ እርሱን በመተው ፣ የውሸት አማልክትን በማምለክ እና ፍጹም በሆነ ክህደት ውስጥ በመግባት እንድሁም ለእግዚአብሔር መንገድ ባለመታዘዝ ብዙ አመታትን አሳልፈዋል ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ፍርድና ቅጣትን በእነርሱ ላይ አመጣ ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ትተው እንደነበር አወቁ ሆኖም ግን ጥያቄው ፡- እግዚአብሔር የራሱን ህዝብ ፈጽሞ ትቶ ነበር ? ወይስ እርሱ እንደገና ምህረትንና ጸጋን ይሰጣቸዋል ፤ ወደ እርሱም ይመለሱ ዘንድ መልሶ በማቆም ያድሳቸዋል ? እነርሱም እንደገና ያነቃቃቸው ያነሳሳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ ፡- “ አቤቱ ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን ፡፡ “
የታሪኩን መጨረሻ ታውቁታላችሁ ፡፡ እናንተም እግዚአብሔር በምህረቱ ባለጸጋ ፣ ፍቅሩም የበዛ ጸጋውም ከአዕምሮ በላይ እንደሆነ ታውቃላችሁ ፡፡ ከአመታትም በኋላ ስለ ዓለም ኃጢአት የሞተውን ልጁን ላከ ፡፡ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ አይጠፋም ይልቁንም የዘላለምን ህይወት ያገኛል ፡፡ እናንተ ስለፈለጋችሁት ወይም ስለሚገባችሁ አይደለም ይልቁንም እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ እንጂ ፡፡ እርሱ ይቤዣችኋል ፡፡ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን በማስወገድ ይቅር ብሏችኋል ፡፡ መቼም ቢሆን ምንም ነገር ከታላቅ ፍቅሩ አይለያችሁም ፡፡
“ አቤቱ ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን ፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ ። ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል ፤ እጅግ ተቈጥተኸናል ። “
- ሰቆቃው ኤርምያስ 5፡21-22
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 103:12 — “ ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ ። “
ዮሐንስ 3:16 — “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ። “
ሮሜ 8:37–39 — “ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ። ሞት ቢሆን ፥ ሕይወትም ቢሆን ፥ መላእክትም ቢሆኑ ፥ ግዛትም ቢሆን ፥ ያለውም ቢሆን ፥ የሚመጣውም ቢሆን ፥ ኃይላትም ቢሆኑ ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን ፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።