Major Prophets Lamentations

Mercy For The One Who Suffers

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ My Portion Lamentations 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 624 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሰቆቃዉ ኤርምያስ ስለ አስቸጋሪያ ጊዜያት ይናገራል ነገር ግን ተስፋን ያመጣል ፡፡ ምናልባትም ይህ መፅኀፍ በባቢሎን እጅ የኢየሩሳሌምን መፈራረስ ባየ የአይን ምስክር በነቢዩ ኤርምያስ የተፃፈ ነበር ፡፡ ትናትና እንዳየነው በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣዉ ጥፋት በብሉይ ኪዳን ላይ አራት ጊዜ የተመዘገበ ነበር፡ 2ነገስት 25፣ ኤርምያስ 39፡ 1-11፣ ኤርምያስ 52 እና 2ዜና 36፡ 11-21 ፡፡

ኢየሩሳሌም ሁለት ጊዜ ጠፍታ/ፈራርሳ ነበር - ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት በባቢሎን እና ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ በሮማዉያን ፡፡ የኢየሩሳሌም አስፈላጊነት የእግዚአብሄር ቅዱስ ከተማ በሚለዉ እዉነት ዉስጥ የተገኘ ነው ፡፡ መዝሙር 132 በዳዊት ዘመን ጊዜ እንደ ከፍታ ዝማሬ የተፃፈ ሲሆን ኢየሩሳሌምንም እንደ እግዚአብሄር ቤት እዉቅና ይሰጣል (ቁጥር 13-14) ፡፡ ኤርምያስ የእግዚአብሄር ቤት ጠፍታ እንደ ነበር መዝግቧል ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን የዘላለም ቤቱ እንድትሆን መርጧታል ፤ ያ በፍፁም አይቀየርም ፡፡ ኢየሱስ የሚመለስባት ስፍራ ነች ፡፡ ለሰቆቃዉ ኤርምያስ ቃላችን እድል ፋንታዬ የሚል ነው ፡፡

የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅኀፍት አምስት ግጥሞችን ያካትታል ፤ ፈሊፕ ራይከን የእያንዳንዱን ግጥም አላማ ያሳያል፡ 1) “ የኃጢዓት መከራ “፣ 2) “ ዘመኑ አይቀጥልም “፣ 3) “ መከራ ለሚያዩት ምህረት “፣ 4) “ የመሪነት ዉድቀት “ እና 5) “ የመታደስ ፀሎት “ ፤ በሰዎስተኛዉ የኃዘን እንጉርጉሮ/ለቅሶ 66 ጥቅሶች ሲኖሩ በክፍሎቹም ላይ እንመለከታቸዋለን ፡፡

ትምህርት

ሰቆቃዉ ኤርምያስ (3፡ 1-20)፡ ማክአርቱር የመጀመሪያዉን ክፍል “ እንደ ኤርምያስ ጭንቀት “ ይገልፀዋል ፡፡ ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ላይ የመጣዉን ቁጣ በማየት እግዚአብሄር ከኢየሩሳሌም በጨለማ ወስዶት እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሄር ከእርሶ ዞር ብሎ እንደ ነበር፣ በአካላዊ ሕመም እና በሽታ ዉስጥ እያኖረዉ እንደ ነበር ተሰማው (ቁጥር 3-4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሁኔታዉ በጣም ተስፋ ቢስ ስለሚመስል ለረጅም ጊዜ ሞት እንደ ነበር እንደተሰማው “ አመለከተ ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሄር በግል ሁሉንም ነገር በእርሱ ላይ እያደረገ እንደ ነበር ተሰማው (ቁጥር 5-6) ፤ ኤርምያስ በእስር ቤት እንደ ሆነ ገለፅ - በአካል ወይም በሀሳቡ (ኤር 38፡ 6) (ቁጥር 7) ፡፡ እግዚአብሄር ፀሎቱንም እንኳን አልተቀበለዉም ነበር (ቁጥር 8) ፡፡ ማክአርቱር “ ለኤርምያስ ፀሎት የእግዚአብሄር ምላሽ አለመኖር በኤርምያስ በግሉ ኃጢዓት ምክንያት አልነበረም (መዝ 66፡ 18) ይልቁንም ያለ ንስኃ በሆነዉ በእስራኤል የማያቋርጥ ኃጢዓት ነበር (ኤር 19፡ 15) “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ኤርምያስ ከእግዚአብሄር በታየበት ነገር ማዘኑን ቀጠለ - እግዚአብሄር እንደ ተደበቀ ድብ እና አንበሳ ሲጠብቀዉ የተከበበ/የተዘጋ ነበር (ቁጥር 9-10)፣ መንገዱን እንዲለዉጥ የተገደደ እና እንደ ቁርጥራጭ የተገነጣጠለ ነበር (ቁጥር 11)፣ እግዚአብሄር በቀስቱ እንደ ኢላ በመጠቀም ኩላሊቶቹን ወጋ (ቁጥር 12-13)፣ የወገኑ ሰዎች መሳቂያ ሆኖ ነበር (ቁጥር 14) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኤርምያስ የማላገጫ እና የማሾፊያ መሳለቂያ ተደርጎ እንደ ነበር “ አመልክቷል ፡፡ እግዚአብሄርም በኃይለኛዉ አጠቃዉ - በምሬትና በፍርሀትም ሞላው (ቁጥር 15) ፤ እግዚአብሄር እንዲያዝን፣ ትቢያ እንዲበላ እና በአመድ ላይ እንዲቀመጥ ምክንያት ሆነበት (ቁጥር 16) ፡፡ ማክአርቱር “ በድንጋይ ጥርሴን ሰበረ “ የሚለዉን ሀረግ “ በምስራቅ የተለመደ እንደ ነበረው ብዙ ጊዜ ከዳቦ ዱቄትን በአመድ መቀላቀልን ክክ/የአሸዋ ብናኝን ያመለክታል “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ እግዚአብሄር ከሰላም እና ከደስታ አርቆት/ከልክሎት ነበር (ቁጥር 17) ፡፡ ኤርምያስ ለወደፊት ጊዜዉ ተስፋ አልነበረውም (ቁጥር 18) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በቁጥር 19 “ ኤርምያስ ያለፈዉን ልምምዱን መልሶ በመጥራት ሙዱን ለመቀየር ሞከረ ፤ ይሁን እንጂ ያስታወሰው የከፋ ነገር ብቻ እንዲሰማዉ እንዳደረገው “ ይናገራል (ቁጥር 19-20) ፡፡

ሰቆቃዉ ኤርምያስ (3፡ 21-38)፡ ኤርምያስ ከጭንቀት ወደ ተስፋ ዞር አለ (ቁጥር 21) ፡፡ ማክአርቱር “ በይሁዳ ፍርድ ላይ እረፍት የሌለዉ ኃዘን ኤርምያስ የእግዚአብሄርን ፀጋ፣ ምህረት እና ርህራሄ እንዳያመለከት እንደ ከለከለው “ ይፅፋል ፡፡ ቁጥር (22-26) የሰቆቃዉ ኤርምያስን ፍሬ ነገር ይሰጣል ፡፡ ኤርምያስ የእግዚአብሄርን የታመነ ፍቅር እና የማያልቀዉን ምህረቱን አስታወሰ (ቁጥር 22) ፡፡ ምህረት ስለሚለዉ ቃል ማክአርቱር “ ይህ የዕብራዊያን ቃል በብሉይ ኪዳን ላይ 250 ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው የእግዚአብሄርን የከበረ ፍቅርን እንደሚያመለክት “ ይናገራል ፡፡ ማክአርቱር በምህረት ዉስጥ የሚካተቱትን ስምት እዉነቶችን በመዘርዘር ይቀጥላል፡ “ ፍቅርን፣ ጸጋን፣ ምህረትን፣ ቸርነትን፣ ይቅርታን፣ እዉነትን፣ ርህራሄን እና ታማኝነትነን የያዘ ሰፊ ቃል ነው “ ፡፡ ኤርምያስ ምህረቱ ሁል ጊዜ አዲስ እንደ ሆነና ታማኝነቱም ብዙ ነዉ በማለት ተናግሯል (ቁጥር 23) ፡፡ ቁጥር 24 ለሰቆቃዉ ኤርምያስ ጭብጥ ጥቅስ ነው፡ “ ነፍሴ፡- እግዚአብሄር እድል ፋንታዬ ነው ፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች “ ፤ (ዘኁ 18፡ 20) “ እድል ፋንታዬ “ የሚያስፈልገን ሁሉ እግዚአብሄር ነዉ የሚለዉን እዉነት ያመለክታል ፡፡ በዮሐ (4፡ 14) ኢየሱስ በእግዚአብሄር የዘላለም ህይወትን ማግኘት እንደምንችል ተናግሯል ፡፡

ከማንኛዉም ጭንቀት የምንወጣበት ብቸኛዉ መንገድ ተስፋችንን በእግዚአብሄር ላይ በማስቀመጥ ነው ፡፡ ተስፋችንን በእግዚአብሄር ላይ እንዴት እናስቀምጣለን ?

  • መዝ (16፡ 5)፡ “ እግዚአብሄር የርስቴ እድል ፋንታና ጽዋዬ ነው ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ “ ፡፡
  • መዝ (73፡ 26)፡ “ የልቤ አምላክ ሆይ ልቤና ስጋዬ አለቀ ፤ እግዚአብሄር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው “ ፡፡
  • መዝ (119፡ 57)፡ “ እግዚአብሄር ክፍሌ ነው ፤ ሕግህን እጠብቃለሁ አልሁ “ ፡፡

ኤርምያስ ሕዝቡን የእግዚአብሄርን ቃል ሰጣቸዉ ሊሰሙት ግን አልፈለጉም ፤ ነገር ግን ከአስቸጋሪ ጊዜያት ዉስጥ መዉጫዉ ብቸኛዉ መንገድ የእግዚአብሄር ቃል ነው ፡፡ በቁጥር (25-26) ኤርምያስ እግዚአብሄር እርሱን በመጠበቅ ለሚፈልጉት መልካም እንደሆነ ገልፆአል ፤ በዝምታ እግዚአብሄርን መጠበቅ መልካም ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እግዚአብሄርን መጠበቅ የሚለዉ ሀሳብ “ የእግዚአብሄርን ፍቃድ እና ጊዜ መቀበል/ተቀባይነት ማግኘት ማለት እንደ ሆነ (መዝ 40፡ 1, ኢሳ 40፡ 31) “ ይገልፃል ፡፡ በእርሱ ላይ እምነታችንን በምናስቀምጥ ጊዜ እግዚአብሄርን እንጠብቃለን ፡፡

“ በልጅነት ቀንበርን መሸከም “ የሚለዉ ሀረግ (ቁጥር 27-28) “ ከእግዚአብሄር የሆነን ኃላፊነት ስለመቀበል ኤርምያስ በልጅነቱ የተቀበለዉን የቅጣት ስልጠናዎች ስለሚያካትት ይናገራል (ኤር 1፡ 6, 7) “ ፡፡ አሁንም ተስፋ ስለ ነበር ኤርምያስ ታናናሾችን ዝም እንዲሉ ነገራቸዉ (ቁጥር 29) ፤ ኤርምያስ ታናሾችን ከሌላ ጎጉንጭ ዞር በማለት በሰላም እንዲቀመጡ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 30) ፡፡ ኢሳይያስ ኢየሱስ እርሱን እና ጉንጩን ለሚመቱት እና በጥፊ ለሚመቱት ጀርባዉን እንደሚሰጣቸዉ ትንቢትን ተናግሯል (ኢሳ 50፡ 6) ፡፡ በእነርሱ ላይ ለመጡባቸዉ ራሳቸዉን ያስገዙ ነበር ፤ በቁጥር (33-47) ኤርምያስ ይሁዳን በፍርዱና በቅጣቱ ስር ለማስቀመጥ ምክንያት እንደ ነበረዉ አብራርቷል ፡፡

ሰቆቃዉ ኤርምያስ (3፡ 39-66)፡ ኤርምያስ ኃዘኑን/ለቅሶዉን ምክሩን እና ፀሎቱን በመስጠት አጠቃለለ ፡፡

መደምደሚያ

አሁንም እግዚአብሄር ሁሉም በቁጥጥሩ ስር እንደ ሆነ ስታምኑ እዉነተኛ ተስፋ ሊኖራችሁ ይችላል ፡፡

  1. Philip Graham Ryken, Jeremiah and Lamentations: From Sorrow to Hope (Wheaton, IL: Crossway, 2001), pp. 746, 751, 761, 764, 770.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 897.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 951.

  4. MacArthur, p. 888.

  5. Nelson’s Commentary, p. 951.

  6. Nelson’s Commentary, p. 951..

  7. MacArthur, p. 888.

  8. Nelson’s Commentary, p. 951.

  9. MacArthur, p. 888.

  10. MacArthur, p. 888.

  11. MacArthur, p. 888.

  12. Nelson’s Commentary, p. 952.

  13. MacArthur, p. 888.

  14. MacArthur, p. 888.

ጥያቄዎች

  1. በሰቆ.ኤር (3፡ 2) ኤርምያስ እግዚአብሄር በብርኃን ሳይሆን በጨለማ እንዲሄድ እንዳደረገዉ ይናገራል ፤ “ በጨለማ “ እንደ ተመታችሁ ተሰምቷችሁ ያዉቃል ? ሌሎች ምን እንዳላችሁ ታውቃላችሁ ? የት ላይ ታመለክታቸዋላችሁ ? (1ዮሐ 1፡ 6-7)
  2. በሰቆቃዉ ኤርምያስ (3፡ 18) መሰረት ከእግዚአብሄር የኤርምያስ የነፃ መዉጣት ተስፋ የነበረው ተፍቶ ነበር ፤ ለተስፋ ቢሶች ምን መልዕክት ማቅረብ ትችላላችሁ ? በቁጥር 21-24 ኤርምያስ የእግዚአብሄር ርህራሄ እና የማያቋርጥ ፍቅር ሲያስታዉስ እንዴት ምላሽ ሰጠ ? ለእናንተ እግዚአብሄር እድል ፋንታችሁ ነዉ ማለት ምን ማለት ነው ? (ሰቆ.ኤር 3፡ 24)
  3. ሰቆ.ኤር (3፡ 33) በሚያነቡ ጊዜ ሌሎችን እንዴት ተጋፈጣችኋቸዉ እንዴትስ ነዉ የምትጋፈጧቸው ? በመፅኀፍ ላይ የዚህን ማስረጃን ታያላችሁ ? (2ዜና 7፡ 13-14, ኤር 17፡ 24-26, 29፡ 11, ሮሜ 6፡ 23, 2ጴጥ 3፡ 9)
  4. ሰቆ.ኤር (3፡ 37-40) በማንበብ እግዚአብሄር እንዴት አለምን በመናገር ብቻ እንደ ፈጠረ አስቡ (ዘፍ 1፡ 3, 6, 9) ፤ በዚህ በኃሳባችሁ ራሳችሁን (ሰዉን ሁሉ) እንዴት ታዩታላችሁ ?
  5. ኤርምያስ ሰቆ.ኤር (3፡ 52-54) በሚፅፍበት ጊዜ ምን ሊያስብ እንደሚችል ምን ታስባላችሁ (ኤር 38፡ 6-13) ? ሰዎቹ በኤርምያስ ላይ የተነሱት ለምን ነበር ? ለእርዳታ ማንን ተመለከተ ?
  6. በሰቆቃዉ ኤርምያስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Lamentations 3:21–24

“Yet I call this to mind, and therefore I have hope: Because of the LORD’s faithful love we do not perish, for His mercies never end. They are new every morning; great is Your faithfulness! I say: The LORD is my portion, therefore I will put my hope in Him.”

ነቢዩ ኤርምያስ በጭንቅ ውስጥ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ተጣራ ፡፡ እርሱ በግልጽ የሚሰማውን ስሜት ሁሉ ተናገረ ፡- “ ነፍሴን ከሰላም አራቅህ ፤ በጎ ነገርን ረሳሁ ……….. ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ ……ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች ፡፡ “ ነገር ግን አሁንም በሀዘን ውስጥ ሆኖ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አስታወስ ፡- “ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው ፤ ርኅራኄው አያልቅምና ። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው ። ነፍሴ ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው ፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች ። “

በህይወትህ በጨለማ ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ፣ በድብርት ፣ በሀዘን ፣ በብቸኝነት ወይም በውድቀት ውስጥ አልፈህ ካወክ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ለአንተም ይሆናል ፡፡ አስታውስ የሚሰማህን ስሜት ለእግዚአብሔር መናገር ትክክለኛ ነገር ነው ፡፡ ለእርሱ እንደተበሳጨህ እንደተናደድክ ንገረው ፡፡ ለእርሱ እንደተጎዳህ ንገረው ፡፡ ሆኖም ግን እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ሳለህ ወደ እርሱ ፊትህን በመመለስ እርሱን ጠብቅ ፡፡ እርሱ ፍቅሩ ፈጽሞ እንደማያልቅ ፤ በየማለዳም ምህረቱ አዲስ እንደሆነ ታማኝነቱም ብዙ እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ ፤ በማለዳም ከእንቅልፍህ ስትነሳ እርሱ ስለሰጠህ ተስፋ ፣ ስለ ታማኝነቱ ፣ አዲስ ስለሆነው ምህረቱ እንዲሁም ስለማይቋረጠው ፍቅሩ አመስግነው ፡፡ የእግዚአብሔር ታማኝነት እንደሚከተልህ በማመን በየቀኑ ወደፊት ተራመድ ፡፡

“ ይህችን በልቤ አኖራለሁ ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ ። ሔት ። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው ፤ ርኅራኄው አያልቅምና ። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው ። ነፍሴ ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው ፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች ። “

  • ሰቆቃው ኤርምያስ 3፡21-24

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 16:5 — “ እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው ፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ ። “

መዝሙር 73:26 — “ የልቤ አምላክ ሆይ ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው ። “

ሰቆቃው ኤርምያስ 3:17–21 — “ነፍሴን ከሰላም አራቅህ ፤ በጎ ነገርን ረሳሁ ። እኔም ፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ ። ዛይ ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች ። ይህችን በልቤ አኖራለሁ ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ ። “