Major Prophets Lamentations

Jeremiah's Laments

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ My Portion Lamentations 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 623 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅኀፍት በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ላይ በሆነዉ ነገር እያዘነ የነበረው አንድ ነቢይ የመዘገበዉ ነው ፡፡ የአምስት ለቅሶዎች ሀዘን ነው ፤ ይህ ትንሽ መፅኀፍ በተለዬ ስሜትን የማይቀሰቅስ እና ጭንቀት እንኳን ሊያሰማ የሚችል ነው ነገር ግን በዉስጡ በምታጠኑ ጊዜ በአስቸጋሪ ጊዜያት ተስፋን እንድታገኙ ሊረዳችሁ ይችላል ፡፡ ይህን የሚያዳምጥ ሰው ወይም ቀድሞ በአስቸጋሪ ጊዜያት ዉስጥ ይህ ጥናት ተስፋን ሊያመጣላችሁ እንደሚችል ቃል እገባላችኋለሁ ፡፡ በሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅሀፍት ዉስጥ ለክርስቶስ ቃላችን እድል ፋንታዬ የሚል ነው (ሰቆ ኤር 3፡ 22-24) ፤ እድል ፋንታዬ በአስቸጋሪ ጊዜያት ዉስጥ እንዴት እወጣለሁ የሚል ነው ፡፡

ማክአርቱር “ የታላቅ ለቅሶ ትርጓሜን የያዘው ሀዘን /ሰቆቃ በላቲን ብልግና እና ድካም/በእድም መድከም ከተገኘበት ርዕስ የመጣ ነበር ፤ የዕብራዊያን ቃል አጋኖ እንዴት ( ጭንቀትን የሚገልፀውን 1፡ 1, 2፡ 1, 4፡ 1) የዕብራዊያን ርዕሱን መፅኀፉ ይሰጠዋል ፤ ይሁን እንጂ የአይሁድ አስተማሪዎች/ሸንጎዎች ቀድመዉ በኤር (7፡ 29) ላይ መፅሀፉን ሰቆቃዉ ወይም ታላቅ ኃዘን በማለት መጥራት እንደ ጀመሩ “ ይገልፃል ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ኃዘን/ለቅሶ ያለዉ ሰቆቃዉ ኤርምያስ ብቻ ሲሆን “ ይህ የሚያስጨንቅ ሙሾ የምታምረዉ የኢየሩሳሌም ከተማ የቀብር ስነ ስርዓትን አሳይቷል (2፡ 15) “ ፡፡ መፅሀፉ የነቢዩ የኤርምያስን ልብን በማሳየት “ የዛች ከተማ ዉድቀት ማስታወሻን ህያዉ አድርጎ በመጠበቅ ሁሉንም አማኞች በመከራ እንዴት እንደሚታለፍ ያስተምራል “ ፡፡

የሰቆቃዉ ኤርምያስ ፀኃፊ በመፅሀፉ ዉስጥ አልተጠቀሰም “ ነገር ግን ኤርምያስ እንደ ነበር ዉስጣዉ እና ታሪካዊ አመላካቾች አሉ “ ፤ ለምሳሌ ኤር (7፡ 29) የኤርምያስን ለቅሶ ሲያሳይ 2ዜና (35፡ 25) ኤርምያስ ለንጉስ ኢዮስያስ ለቅሶዎችን እንደፃፈ ይናገራል ፡፡ ኤርምያስ ስለ ኢየሩሳሌም ዉድቀት ትንቢትን ተናግሮ ነበር የኢየሩሳሌምን መፈራረስ ለማየትም በዚያ ነበር - የአይን ምስክር መግለጫ ነበረው ፡፡ ማክአርቱር “ ከተማዋ ስትወድቅ ሐምሌ አጋምሻ ላይ ሲሆን ቤተ መቅደሱ በተቃጠለ ጊዜ ደግሞ ነሐሴ አጋማሽ ነበር ፤ ከዚህም የተነሳ ኤርምያስ የቅጥሮቹን፣ የሕንፃዎቹን፣ የቤቶቹን፣ የነገስታት መኖሪያዎቹን እና የቤተ መቅደሱን መፈራረስ ስላዬ ክስተቱ በአይምሮዉ ዉስጥ አዲስ ሕመም እንዳስታወሰዉ ፅፏል ነገር ግን ከክርስቶስ ልደት 583 በፊት ወደ ግብፅ በግዴታ ከመፍለሱ በፊት ነበር (ኤር 43፡ 1-7) “ በማለት ይገልፃል ፡፡

በኤርምያስ መፅኀፍ እና በሰቆቃዉ ኤርምያስ በተነፃፀሩ ጊዜ መፅሀፍ የተለዩ ንግግሮችን ሲጠቀም የኤርምያስ ንግግር የተሰማ ነው (ሰቆ.ኤር 1፡ 2 ከኤር 30፡ 14)፣ ሰቆ.ኤር 1፡ 15 ከኤር 8፡ 21፣ ሰቆ.ኤር 1፡ 6, 2፡ 11 ከኤር 9፡ 1, 18፣ ሰቆ.ኤር 2፡ 22 ከኤር 6፡ 25፣ ሰቆ.ኤር 4፡ 21 ከኤር ኤር 49፡ 12) ፡፡

የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅሀፍት ለምን ነበር የተፃፈው ? እንደ ማክአርቱር አገላለፅ “ የኢየሩሳሌም መጥፋት ትንቢታዊ ዘር ቀድሞዉኑ በኢያሱ በኩል ከ800 አመት በፊት ተዘርቶ ነበር (ኢያ 23፡ 15-16) ፤ አሁን ከ40 አመታት በላይ ኤርምያስ ስለሚመጣዉ ፍርድ ሰብኮ የነበርና ስለ ሰበከዉ ርግማንም በሕዝቡ የተናቀ ነበር (ከክርስቶስ ልደት 645-605በፊት) “ ፡፡

በኢየሩሳሌም የሚመጣዉ ጥፋት በብሉይ ኪዳን አራት ጊዜ የተመዘገበ ነበር፡ 2ነገስት 25፣ ኤር (39፡ 1-11)፣ ኤርምያስ 52 እና 2ዜና (36፡ 11-21) ፡፡ የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅኀፍ በመታሰቢያ በተለዬ ቀን ላይ የሚነበቡትን አምስት የተቀደሱ መፅሀፍትን(ሩት፣ አስቴር፣ መኃልዬ መኃለይ ሰለሞን፣ መክብብ እና ሰቆቃዉ ኤርምያስ) በሚይዘዉ በአይሁዶች ሚሎዝ ዉስጥ የተካተተ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ ሰቆቃዉ ኤርምያስ በናቡከደነፆር ኢየሩሳሌም የፈራረሰችበትን ቀን ለማስታወስ በሐምሌ/በነሐሴ በዘጠነኛዉ ቀን ላይ የሚነበብ ነው ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ ይህ ተመሳሳይ ቀን በኋላም ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ በሮማዊያን የሄሮድስ ቤተ መቅደስ የፈረሰበት ቀንም ተሰየመበት “ በማለት አመልክቷል ፡፡ ኤርምያስ ትንቢታዊ ቃሉ ወደ መፈፀም እንደ መጣ ባዬ ጊዜ “ ስለ መከራዉ እና ስለ ሕዝቡ ግትርነት በኃዘን እና በታላቅ ርህራሄ አለቀሰ “ ፤ ይህም አይሁዶች ከኃጢዓታቸዉ የተነሳ የኢየሩሳሌምን መፈራረስ እንዳይረሱት ጠቃሚ ነበር ፡፡

በመፅሀፉ ዉስጥ የተካተቱት ጭብጦች፡ “ የእግዚአብሄር ፍርድ ለይሁዳ ኃጢዓት ምላሽ….በእግዚአብሄር ርህራሄ ተስፋ ተገኜ…. የእግዚአብሄር ሉዓላዊ ፍርድ…. የሚጠርገዉ ፍርድ ለእስራኤል ድነት እና ለእግዚአብሄር ተስፋ መፈፀም የሁሉም ተስፋ መጨረሻ የሚሆን ይመስላል …. በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ የኤርምያስ እንባ ከኢየሱስ ለቅሶ ጋር ይወዳደራል “ ፡፡ ኤርምያስና ኢየሱስ ሁለቱም እግዚአብሄር እቅድ ላለዉ ከተማ አለቀሱ ፡፡ እስከ አሁን ድረስ የኢየሩሳሌም ከተማ ሙሉ ታድሳ/ተመልሳ አናያትም ፡፡ ራይከን “ መፅሀፉን ከግል ኃዘን ይልቅ ማህበረሰባዊ / ብሔራዊ ያደረጉ አምስት ግጥሞችን “ ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ሰቆቃዉ ኤርምያስ (1፡ 1-11)፡ የመጀመሪያዎቹ 11 ጥቅሶች ለኤርምያስ ግላዊ ነበሩ ፡፡ በኢየሩሳሌም “ መበለት”፣ “ ሉዑል “ እና በባሪያ ላይ አዘነ ፤ አፅናኝ በሌለበት ወዳጅ ወይም ጎረቤት በሌለበት በምሽት አለቀሰች ፡፡ በወዳጆቿም እንኳን ሳይቀር (ምናልባትም ጣዖት አምላኪዎች ሕዝቦችን ያመለክታል) ተላልፋ ተሰጥታ ነበር ( ቁጥር 1-2) ፡፡ ይሁዳ በባርነት ለባቢሎን በግዞት ተወስዶ ነበር ፤ መበለት/አለቆች/ባሪያ እረፍት አልነበራቸዉም (ቁጥር 3) ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስኬዱት መንገዶችም እንኳን አዘኑ ምክንያቱም በዓላት ስላልነበሩ (ፋሲካ፣ በዓለ ኃምሳ ቀን፣ የሳምንት በዓላት እና የዳስ በዓል ) (ቁጥር 4) ፡፡ ቁጥር 5 ልብ የሚሰብር መልክን ያሳያል - ልጆች እንኳን አልነበሩም ፤ ለከተማዋ በሚመጣዉ ጊዜም ተስፋ አልነበራትም ፡፡ ኢየሩሳሌም ስለመተላለፏ ተፈርዶባት እና ተቀጥታ ነበር (ቁጥር 6-8) ፡፡ “ ባዶነቷ/እርቃንነቷ “ መተላለፏ ሙሉ ለሙሉ ለአለም የተጋለጠ እንደ ነበር እዉነቱን ያመለክታል ፤ ኮንስታብል “ ኢየሩሳሌም በራሷ አፍራ ነበር፣ ኃጢዓቷ እና ብልግናዋ ወደ ብርኃን መጥቶ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ ኢየሩሳሌም የመተላለፋቸዉን ዉጤት (መጨረሻዋን) በፍፁም አላስተዋሉትም ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ጠላት በመቅደሷ በመግባት ሁሉ ሁሉንም ነገር ወሰደው (ቁጥር 10) ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩትም ሁሉ በምግብ አለመኖር እየተራቡ ነበር (ቁጥር 11) ፡፡

ሰቆቃዉ ኤርምያስ (1፡ 12-22)፡ የኤርምያስ ኃዘን/ለቅሶ ኢየሩሳሌም ወደ ዉጪ ስትመለከት ማየት እንደምትችለው እንደ ገለፀው በተጣመረ ተፈጥሮ ላይ ተደረገ ፡፡ ማክአርቱር ቁጥር 12 “ ከእንግዶችም/ከሌሎች እንኳን ቢሆንም ስለ ጥቂት ቸርነት/ርህራሄ እንደ ኢየሩሳሌም ግድየለሽ ልመና “ ይገልፀዋል ፡፡ ኤርምያስ የመከራዋን ጭካኔ “ በእሳት፣ በመረብ፣ በቀንበር፣ በሰራዊት፣ ጎልማሳ ተዋጊዎቿን በመስበር እና እንደ ወይን እንደ ተረገጠች “ በሚሉት ስዕሎች ገለፀው (ቁጥር 13-15) ፡፡ የኢየሩሳሌም ከተማ አለቀሰች - አጽናኝ አልነበራትም ከተማዋን እንድትኖር የሚጠብቅ ማንም የለም (ቁጥር 16-17) ፤ ይሁን እንጂ ከተማዋ በእግዚአብሄር ላይ አምፃ እንደ ነበር እና ከእርሷ ጋር ቆሞ የቀረ ማንም እንዳልነበር ትናገራለች (ቁጥር 18-22) ፤ ለዚህ ነዉ የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅሀፍ ለአይሁዶች በጣም አስፈላጊ የሆነው ፡፡ በእግዚአብሄር ላይ የማመፅ ዉጤትን ማስታወስ አለባቸው ፡፡

መደምደሚያ

ይህ በጣም ትክክል የሆነ ሁኔታ ነው ፡፡ እዚህ ስፍራ/ሁኔታ ላይ የመድረሻዉ ብቸኛዉ መንገድ በእግዚአብሄር ላይ ማመፅ ብቻ ነው ፤ እንዲሁም ደግሞ ይህን ነገር የማለፊያዉ ብቸኛዉ መንገድ በእግዚአብሄር ፊት ማመፅን መናገር እና ወደ እርሱ መመለስ ነው ፤ ይህን በሰቆቃዉ ኤርምያስ 3 ላይ እናየዋለን ፡፡ እግዚአብሄር እድል ፋንታዬ ስለሆነ በዚህ ይሸከመናል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የሰቆቃዉ ኤርምያስ መፅሀፍ የሚነበቡት ወይም እን ኃዘን እንጉርጉሮ የተዘመሩት የአምስት ግጥም ስብስቦች ነው ፤ ኃዘን ምን ማለት ነው ? የኤርምያስ ኃዘኖች/የለቅሶ እንጉርጎሮች ምን ነበሩ ?
  2. የሰቆቃዉ ኤርምያስ 1 የመጀመሪያዉ ጥቅስ ከምርኮ በኋላ ፂዎንን እና ከዚያ በኋላ ምን ትመስል እንደ ነበር ያነፃፅራል ፤ ነገሮችን እና ሞገስን በማጣት በሁኔታው ማዘን/ማልቀስ ገጥሟችሁ ያውቃል ? አዎ ከሆነ እንዴት ይህን አሳለፋችሁት ?
  3. በሰቆ.ኤር (2፡ 6-7) ኤርምያስ እግዚአብሄር እርሱን ከማምለክ ጋር የሚገኛኑ ስፍራዎችን እና ነገሮችን እንዴት እንዳጠፋቸዉ ገልፆአል ፤ እነዚህ የተለዩ ነገሮች ለምን ተጠቅሰዉ እንደ ነበር እና ለምን እግዚአብሄር እንዲጠፉ ወይም ባዶ እንዲሆኑ ምክንያት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በሰቆቃዉ ኤርምያስ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Lamentations 1:20

“LORD, see how I am in distress. I am churning within; my heart is broken, for I have been very rebellious. Outside, the sword takes the children; inside, there is death.”

ኤርምያስ ይህን መጽሀፍ የጻፈው ከይሁዳ ውድመትና ቅጣት በኋላ ኢየሩሳሌም ስላለችበት ውድመትና አስቸጋሪ ሁኔታ አንጻር ነው ፡፡ ከተማዋ ምድረ በዳ ሆና ነበር ፡፡ ሁሉም ጓደኞቿ ክደዋት ነበርና በመራራ ምሽቶች ውስጥ ተቧሳቁላ ታዝን ነበር ፡፡ የስጋት የጭንቀት ስሜቶች ብቻ ነበር ያሉት ፡፡ እረፍት የሚባል ነገር አይገኝም ነበር ፡፡ ኢየሩሳሌም ትልቅ በደልን ሰርታ ነበር እናም አሁን ቅጣቷን እየተቀበለች ነው ፡፡ ተዋረደች ማመጽዋንም አመነች ፡፡ በስተመጨረሻም ልቧ ተሰበረ ፡፡

እንዳንዴ ብቸኝነት ፣ ውርደት ወይም ኃፍረት ይሰማሃል ፤ ስላለፈው ስለ ሰራኸው በደል እናም አሁን በፊትህ ስለተጋረጠው ሁሉ ትጸጸታለህ ፡፡ አንተን ለማጽናናት ማንም ግድ ሳይለው ሲቀር ጉዳት ህመም አለው ፡፡ ራቁትህን እንደሆንክ ፣ እንደተጋለጥክ ወይም በቀላሉ እንደተሰበርክ ሊሰማህም ይችላል ፡፡ ዛሬ የሚሰማህን ስሜት አምነህ ተቀበል ፡፡ ስሜት ወደ ፈውስ የሚመራ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ደግሞም እንዲሁ በህመም በሀዘን ውስጥ ሆነህ እግዚአብሔርን እንዲታይ ይመራሃል ፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሰማህን ስሜት ለመናገር እራስህን ፍቃደኛ አድርገው ማልቀስ ካለብህም አልቅስ ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚወድህ አስታውስ ፡፡ እግዚአብሔር ልባቸው ከተሰበረ ጎን ነው ፡፡ አሁን የእግዚአብሔር ፍቅርና ጸጋ በአንተ ላይ ይፈስ ዘንድ ፍቀድ ፡፡

“ ሬስ ። አቤቱ ፥ ተጨንቄአለሁና ፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት ፤ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ ፤ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ ። “

  • ሰቆቃው ኤርምያስ 1፡20

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 34:18 — “ እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው ፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል ። “

ሰቆቃው ኤርምያስ 1:2 — “ ቤት ። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች ፥ እንባዋም በጕንጭዋ ላይ አለ ፤ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም ፤ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት ። “

ሮሜ 8:18 — “ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ ። “