The Fulfillment Of God's Promises
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 51-52 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ የኤርምያስ ጥናታችንን እንደመድማለን ፡፡ ትናትና ፓስተር ጎርዲይ ምዕራፍ 50 እና ስለ ባቢሎን የኤርምያስ ሸክምን መጀመሪያንም ይሸፍናል ፤ ያ ሸክም በምዕራፍ 51 ይቀጥላል ፡፡ በምዕራፍ (50-51) ያለዉ ሸክም በአጠቃላይ ለሁሉም ሌላ ሕዝብ በጥምረት እንደ ሸክም ብዙ ስፍራን ይዟል ፡፡ እንዲሁም በእነዚህ ምዕራፎች ተከናዉነው ተመዝግበዉ የነበሩ ቃለ ምልልሶች አሉ ፤ ምዕራፍ 51 ከክርስቶስ ልደት 560 በኋላ ከኢየሩሳሌም ዉድቀት በኋላ ተከናዉኗል ፡፡ ባቢሎን በጣም በርቀት/በብዙ ኢየሩሳሌም እስካሁን የገጠማት አስፈሪ ኃይል ነበር ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (51፡ 1-8)፡ በቁጥር (1-8) እግዚአብሄር ባቢሎንን በይሁዳ ላይ እንደ መቅጫ መሳሪያ (“ በእግዚአብሄር እጅ እንደ ወርቅ ፅዋ “ ) ተጠቅሞባቸዉ እንደ ነበር አጋርቷል/ተናግሯል ፤ እግዚአብሄር በኤርምያስ (46-49) ተገልፀው በነበሩት አብዛኞቹ ሕዝቦች ላይ ባቢሎንን ተጠቅሞ ነበር ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄር መሳሪያ የሆኑበት ያጊዜ አበቃ ፡፡ ባቢሎን ላደረገው ነገር ተጠያቂ ይሆናል ፤ እግዚአብሄር ባቢሎንን በሰሜኑ መንግስት ለእርሱ አስቀምጦአት የነበረዉን ስራ ጨርሳ በነበረ ጊዜ በአሶርን አስቀምጦበት በነበረዉ በምናምንቴ ክምር ላይ ያስቀምጣታል ፡፡
ኤርምያስ (51፡ 9-19)፡ በኤርምያስ በኩል እግዚአብሄር ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክሮ ነበር ነገር ግን ልትድን አትችል (ቁጥር 9) ፤ በእስራኤል መካከል ያሉ ፃድቃኖች ዳንኤልን ጨምሮ ያለ ስኬት ባቢሎንን ወደ ትክክለኛዉ መንገድ ለመምራት ሞክረዉ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ባቢሎንን ለማጥፋት ሜዶንን እንደሚጠቀም ተናግሯል (ቁጥር 11) ፡፡ የእግዚአብሄር በቀል ለቤተ መቅደሱ መጥፋት ምላሽ ነበር (ቁጥር 11) ፡፡ እግዚአብሄር በመቅሰፍት/በመከራ በእነርሱ ላይ በድል አድራጊነት ከሚጮኹ አንበጣዎች በላይ ብዙ ቁጥር ሰዎችን በባቢሎናዊያን ላይ እንደሚልክ ይናገራል (ቁጥር 14) ፡፡
የእግዚአብሄር ፍርድ በባቢሎን ላይ እንግዳ የነበረ ሂደት እና ብዙ ጊዜ በታሪክ በኩል የተደጋገመ ነበር፡ 1) እግዚአብሄር የሚመጣዉን ፍርድ መረጠ፣ 2) በዚያ ፍርድ እግዚአብሄር የሰዉን መሳሪያነት ተጠቀመ፣ 3) የሰዉ መሳሪያነቱ በእግዚአብሄር የተነሳሳ አልነበረም ነገር ግን በራሳቸዉ የኃጢዓተኝነት ፍላጎት እንጂ፣ 4) እግዚአብሄር በተጠቀማቸዉ መሳሪያዎቹ ላይ ፍርድን አመጣ ፡፡ የእግዚአብሄር ፍርድ መፈፀም በሜዶ እና በፋሪስ በኩል መጣ ፤ ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት ነነዌን በማጥፋት ዉስጥ ሜዶን ከባቢሎን ጋር የተጣመረ ነበር ነገር ግን በኋላ ባቢሎንን ለማሸነፍ ከክርስቶስ ልደት 539 በፊት ከፋሪስ ጋር ተጣመሩ ፡፡
ኤርምያስ (51፡ 20-26)፡ የቃለ ምልልሱ ቀጣዩ ክፍል ስለ ፋሪሱ ቂሮስ (ቁጥር 20-23)፣ ለእስራኤል (ቁጥር 24) እና ለባቢሎን ነበር (ቁጥር 25-26) ፡፡ እግዚአብሄር ቂሮስን እግዚአብሄር ጥፋትን ሁሉ የሚሰባብርበት/የሚያጠፋበት የመዉጊያ መዶሻዉ እንደሚሆን ነገረው ፤ በመቀጠልም እግዚአብሄር የእርሱ ሕዝብ በአይኖቻቸዉ ፊት በእስራኤል እና በይሁዳ ላይ አድርገዉት ስለ ነበረዉ ነገር ለባቢሎን እና ለነዋሪዎቿ መልሶ እንደሚከፍላቸዉ ቃል ገባለት ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር በገዛ በራሱ እጅ ባቢሎንን እንደሚያጠፋት ተስፋን ሰጠው ፡፡
ኤርምያስ (51፡ 27-53)፡ ይህ የሚያወዛግብ/ግራ የሚያጋባ ክፍል ሲሆን ማንም በዚህ ዉስጥ ኤርምያስ ማን እያወራ እንደ ነበር ማንም እርግጠኛ አይደለም ፡፡ ምናልባትም ኤርምያስ በባቢሎን ተጠቅተዉ ለነበሩት ሁሉም ሕዝቦች ምልዕክት እየላከ ነበር ፤ ሰዎስት ቡድኖች የተለዩ ነበሩ (ቁጥር 27) ሁሉም ከባቢሎን በስተሰሜን በኩል በአሁኗ በሶሪያ አካባቢ ስፍራ የሚገኙ የነበሩና ከሜዶን ግዛት ጋር የተገናኙ ነበሩ ፡፡ ከእነዚህ ዉስጥ እያንዳንዳቸው በአሶራዊያን ፊደል አፃፃፍ የታወቅ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር ባቢሎንን ለመዋጋት በአንድ ላይ እንዲመጡ አሕዛቦቹን ተጣራ (ቁጥር 28) ፡፡ ባቢሎን በሜዶን እና በፋሪስ በወደቀች ጊዜ የአሕዛቦች ጥምረት ነበር ፤ ይህ በባቢሎን ጠቅላላ መጥፋት ላይ እዉነት ይሆናል (ራዕይ 17-18) ፡፡
ቁጥር 33 ሌላ ቃለ ምልልስን ይጀምራል ፡፡ እግዚአብሄር ( “ የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር በላኝ፣ በታተነኝ “ ) የምትለዉን እስራኤል የባቢሎንን ዉድቀት ስለምታይ የተዘጋጀች እንድትሆን ጠራት (ቁጥር 34-35) ፡፡ እግዚአብሄር በባቢሎን ላይ በሚመጥነዉ መንገድ የሚሆነዉን እንደሚያደርግባቸዉ አረጋገጠላቸው ፡፡ በቁጥር (36-44) እግዚአብሄር በባቢሎን ላይ ስለሚያመጣዉ ፍርድ ዘርዝረሯል ፤ በቁጥር 44 እግዚአብሄር የባቢሎንን ቤል/ጣዖት እንደሚቀጣ ቃል ገብቷል ፤ ቤል የባቢሎንን አማልዕክት ባዖልን የሚያመለክት ነው ፡፡ የቤልን/የባዖል ፅሁፍ/ዜማ ባቢሎናዊያን ከአሶራዊያን ፅሁፍ (በትልቅ ድንጋይ ቅርፅ ከተፃፈው) ከተተረጎመዉ እና ባዖልን እንደ ታላቅ አስተዳዳሪ፣ እንደ ሕይወት ሰጪ፣ የነገሮች ተቆጣጣሪ - በተለይም እንደ እሳት ማህበረሰቡን በአንድ ላይ እንደ ያዘ እንደ ፍትሕ አማልዕክት ባዖልን በመግለፅ ፅፈው ነበር ፡፡ እነዚህ ሸክሞች በአሁኑ ጊዜም እኛን ይጣራሉ ፤ አሁን አማልዕክቶቻችን ብዙ ስሞች አሏቸዉ ነገር ግን ለግርማዊነታቸዉ ማጋራት መደፋት በምንችል ጊዜ ለእነርሱ እና ለሚታይ ዉበታቸዉ ያለምንም እንሰግዳለን ፡፡ በቁጥር (45-48) እግዚአብሄር የእስራኤል ሰዎችን ከባቢሎን ለቀዉ እንዲወጡ ትዕዛዝን ሰጣቸው ፤ እስከ ባቢሎን ሽንፈት ኋላ ድረስ ያን ፍቃድ አልተቀበሉም ፡፡
ኤርምያስ (51፡ 59-64)፡ የይሁዳ ንጉስ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ኤርምያስ የተለዬዉን ትዕዛዝ መጋቢ ሰራያን ሰጥቶታል ፡፡ ሰራያ በንጉስ ኢዮስያስ ዘመን የጠፋዉን የህጉን መፅሀፍት አግኝቶት የነበረው የታላቁ ካህን የመሕሴያ የልጅ ልጅ ነበር ፡፡ ኤርምያስ ባቢሎን የሚደርስባትን ሁሉንም ጥፋት በብራናው ላይ በመፃፍ ፅሁፉን ለሰራያ በመስጠት ሰራያን በባቢሎን በደረሰ ጊዜ ጮኾ እንዲያነበዉ ነገረው ፡፡ ሰራያም ከብራናዉ ፅሁፍ ጋር አንድ ድንጋይን በማሰር ባቢሎን እንዴት እንደምትሰምጥ እና በፍፁም እንደ ገና እንደማትነሳ ለማሳየት በኤፍራጠስ ወንዝ መካከል ዉስጥ ይወረዉረዋል ፤ የኤርምያስ ቃል እዚህ ጋር ያበቃል ፡፡
ኤርምያስ (52)፡ ምዕራፍ 52 ከክርስቶስ ልደት (560-538) በፊት መካከል በይሁዳ ላይ ምን እንደሆነ ታሪካዊ ማጠቃለያን ይሰጣል ፡፡ ይህ ከኢየሩሳሌም ዉድቀት በኋላ እና ምናልባትም ከኤርምያስ ሞት በኋላ (ኤር 51፡ 64, ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት) እና ከክርስቶስ ልደት 538 በፊት በፋሪሳዊያን ከባቢሎን ሽንፈት በፊት የተፃ ነበር ፡፡ በተጨማሪም (ከክርስቶስ ልደት 560 በፊት) ንጉስ ዮር ማሮዴክ ዮአኪን ነፃ ካወጣዉ በኋላ የተፃፈ ነበር ፤ ምናልባትም በባሮክ የተፃፈ ሲሆን እንደ እግዚአብሄር ነቢይ የኤርምያስን ናፍቆት፣ የታመኑ ስራዎች እዉነተኝነትን እና ሀቀኝነትን ይመሰክራሉ ፡፡ ራይከን “ በቅርብ ሁሉም የምዕራፍ 52 ትንቢቶ ተፈፅመዋል ፤ በእርግጥ ምዕራፉን ማንበብ የኤርምያስን ጠቅላላ መፅሀፉን ለመዳሰስ መልካም መንገድ ነው ፡፡ እዉነቶቹ ስለራሳቸዉ ይናገራሉ፡ ኤርምያስ የእግዚአብሄርን እዉነተኛ ቃል ተናገረ “ በማለት ይናገራል ፡፡
ሴዴቅያስ በ21 አመቱ ንጉስ በመሆን 11 አመታትን ገዛ (ቁጥር 1) ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ (ቁጥር 2) ፡፡ እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን እና ይሁዳን ከመገኘቱ አስወገዳቸው ፡፡ ሴዴቅያስ ሰራዊቷ በመጨረሻም በኢየሩሳሌም ላይ የሚሰለጥነዉን እና ለሁለት አመታት በከበባ በያዟት በባቢሎን ላይ አመፀ ፡፡ ከአራት ወራት በኋላ በኢየሩሳሌም ምግብ ስላልነበር ሕዝቡ ከከተማዋ ሸሹ (ቁጥር 6-7) ፡፡ በኢያሪኮ አጠገብ በከለዳዉያን ተወስደዉ ነበር ፤ የይሁዳ ሰራዊት ተበታተነ ሴዴቅያስም ወደ ባቢሎን ንጉስ ተወሰደ (ቁጥር 8-9) ፡፡ የባቢሎን ንጉስ ሴዴቅያስ እያዬ ልጆቹን አረዳቸዉ ሴዴቅያስንም አይኑን በማጥፋት ሴዴቅያስ እስኪሞት ድረስ በግዞት ቤት አስቀመጠው (ቁጥር 10-11) ፤ ይህ ከኢየሩሳሌም መዉደቅ በፊት እግዚአብሄር በሕዝቅኤል በኩል በአጭሩ ከሴዴቅያስ አንፃር ያደረገዉን ቃል ኪዳን ሚስጥር መፈፀም የመፈፀም መልክ/ክስተት ነው፡ “ መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል ወደ ከለዳዉያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣለሁ ፤ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል “ (ሕዝ 12፡ 13) ፡፡
ባቢሎናዊያን ሙሉ ለሙሉ ቤተ መቅደሱን አጥፍተዉታል ፡፡ የይሁዳም አለቆች ተገድለዋል ፤ 10,000 የሚያክሎ ሰዎችም ከኢየሩሳሌም በመፈናቀል ወደ ባቢሎን ተልከዋል ፤ ይሁን እንጂ የባቢሎን ንጉስ ለአመታት በባቢሎን በእስራት የነበረዉን የይሁዳን ንጉስ ዮአኪን ይቅርታ አደረገለት ፡፡ የባቢሎን ንጉስ ዮአኪንን የማያቋጥ ፍቃድን ሰጠው ዮአኪንም በባቢሎን ንጉስ ፊት ያለማቋረጥ ተመገበ (ቁጥር 31-34) ፡፡ ይህ የመጨረሻ መደምደሚያ ለምን ነበር የተሰጠው ? ምናልባትም የኤርምያስን የፍርድ ትንቢት በምድሪቱ ላይ መፈፀሙን ያሳያል ፤ በተጨማሪም ኤርምያስ ለወደፊቱ ጊዜ ተስፋን ተመልክቷል - አዲሱን ኪዳን ፡፡ ዮአኪን የሚመጣዉን መታደስ እና በዳዊት በእዉነተኛ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚመጣዉን የማያቋርጥ ንጉሳዊ መስመር ቀድሞ አሳይቷል/ጥላ ሆኗል ፡፡ ኤርምያስ ክርስቶስን የእግዚአብሄር ተስፋ እዉነተኛ መፈፀም እንደ ሆነ አመልክቷል ፡፡
መደምደሚያ
ማንም ሊሰማዉ ባይፈልግም እንኳን እግዚአብሄር ኤርምያስን ለቃሉ እንዲቆም ጠራው ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ ኤርምያስ ለጥሪዉ የታመነ ነበር ፡፡ በደንብ በሚገርም ሁኔታ የኤርምያስ መልዕክት በክርስቶስ ስለ ተገኘዉ አዲሱ ኪዳን ነበር ፡፡ ኤርምያስ ለአሕዛብ ሁሉ የተስፋን መልዕክት አደረሰ ፤ የሚሰማን አለም ቢጠላንም እንኳን በትህትናና በእዉነት ተመሳሳይ ነገርን እንድናደርግ ተጠርተናል !
ኤር (52፡ 24-27) ለሰራያ ምን እንደሆነበት ይናገራል ፤ በባቢሎን የእግዚአብሄርን ቃል ከተናገረ አምስት አመት በኋላ ሰራያ ከኢየሩሳሌም መዉደቅ በኋላ ከሌሎች የከተማዋ አለቆች ጋር ወደ ግዞት ቤት በመወሰድ ከከተማዋ ዉጪ ተገደለ ፡፡
1 Philip Ryken; quoted by David Guzik; https://www.blueletterbible.org/Comm/guzik_david_StudyGuide2017-Jer/Jer-49.cfm.
ጥያቄዎች
-
በባቢሎን መፈራረስ መካከል ላይ አሁንም እግዚአብሄር ለሕዝቡ ምህረትን አሳዬ ፤ በኤር (51፡ 5) የዚህን ምህረት ምሳሌ ታያላችሁ ? በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ይህን ምህረት ይታያል ? (ዘፍ 18፡ 16-33)
-
በኤር (51፡ 20-23) እግዚአብሄር ባቢሎን ላይ ቅጣትን ለማምጣት ከሰዎች ጋር አጋርነትን እያደረገ ነበር ፤ በአንድ ሁኔታ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር አጋር የሆነበት ጊዜ አለ ? ዉጤቱስ ምን ነበር ?
-
ኤር (51፡ 46-47) ከማቴ (24፡ 6-7) ጋር አወዳድሩ ፤ በአሁኑ ጊዜ ጦርነትን እና የጦርነት ወሬዎችን እንሰማለን ? ይህ ማለት የመጨረሻዉ ዘመን ደርሷል ማለት ይቻላል ? ለምን ወይስ ለምን አይቻልም ?
-
በኤርምያስ (51-52) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 52:32–33
“He spoke kindly to him and set his throne above the thrones of the kings who were with him in Babylon. So Jehoiachin changed his prison clothes, and he dined regularly in the presence of the king of Babylon for the rest of his life.”
ልክ ኤርምያስ ቀድሞ እንደተናገረው ፍርድና ጥፋት በይሁዳ ምድር ላይ መጣ ፡፡ ሆኖም ግን በእነዚህ የጨለማ ጊዜያት እንኳ ሳይቀር ኤርምያስ ለይሁዳ ንጉሥ ዮአኪም በዳዊት ዘር ውስጥ ስላለው የክርስቶስ የዘር ሐረግ ያሳየው ነበር ፡፡ ከጥፋቱም በኋላ ንጉሥ ዮአኪም በእስር ቤት ውስጥ ኖረ ፡፡ ሆኖም ግን የይሁዳ ንጉስ ዮአኪም በንጉሥ ዮርማሮዴክ ይቅርታን አገኘ ፡፡ ንጉሥ ዮአኪም አዲስ ልብስን ተቀበለ ደግሞም ቀሪ ህይወቱንም በንጉሥ ፊት እንጀራን ይበላ ነበር ፡፡
ለአንተም እንዲሁ ነው ፡፡ ያለህበት መከራ ፣ ያለህበት ግዞት ወይም በዙሪያህ ያለው ጥፋት ምንም ይሁን የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ የሆነው እርሱ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእርሱ ጋር አብረህ እንድትቀመጥ ይጋብዝሃል ፡፡ ግብዣውንም ስትቀበል እርሱ ንጹህ የሆነ የጽድቅን ልብስ ያለብስሃል ፡፡ የእርሱም ምርጥ ሆነህ ወደ ንጉሥ ካህነት ቤተሰብ ትገባለህ ፡፡ አንተ የሰማዩ አባትህ ፣ የኃያሉ አምላክ እግዚአብሔር ፣ የነበረው ያለውና የሚመጣው የእርሱ ነህ ፡፡ ለግብዣው እሺ ትላለህን ? በኢየሱስ በእርሱ ፊት እንድትቀመጥና የጽድቅን ልብስ እንድትለብስ ያቀረበልህን ግብዣ በትህትና ትቀበላለህን ? እርሱ ስለሚያፈቅርህ ከእርሱ ጋር እንድትቀመጥ ይፈልጋል ፡፡
“ በመልካምም ተናገረው ፥ ዙፋኑንም ከእርሱ ጋር በባቢሎን ከነበሩት ነገሥታት ዙፋን በላይ አደረገለት ። በወህኒም ውስጥ ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት ፥ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቴ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር ። “
- ኤርምያስ 52፡32-33
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘካርያስ 3:4 — “ እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው ። እርሱንም ፦ እነሆ ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው ። “
ሉቃስ 12:37 — “ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው ፤ እውነት እላችኋለሁ ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል ። “
ራዕይ 22:14 — “ ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።