Major Prophets Jeremiah

Persia Overthrowing Babylon

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 50 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 621 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኤርምያስ ያለማቋረጥ የመከራ መልዕክቶችን አመጣ ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች አካላዊ ሰዎች ሲሆኑ የእግዚአብሄር ሰዎች ጠላቶች በሁሉም ስፍራ ነበሩ ፤ እነዚህ ጠላቶች ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን ፈለጉ ፡፡ በእግዚአብሄር ሰዎች በራሳቸው የመታዘዝ ችግር ምክንያቶች ነበሩ ፤ እግዚአብሄር ይቀጣባቸዉ የነበሩ ጊዜያት ነበሩ ፡፡ የኤርምያስ ቃል በሁለቱም በእነዚህ ሁኔታዎች እና አዉዶች በሁለቱም ይሁዳን እና እስራኤልን ደረሰ ፤ ከኤርምያስ መልዕክት በጣም የተለዬዉ መንገድ እግዚአብሄር ለእስራኤል ሰዎች ቃልን ተናግሯል ነገር ግን ፍቃዱን ለማምጣት እንደሚጠቀምባቸው ለጠላቶቻቸወ መናገሩ ነበር ፡፡

ይህ ምዕራፍ በአብዛኛዉ በባቢሎናዊያን ጋዛት ላይ የተነገረ ነበር ፤ አሶራዊያን በእግዚአብሄር እቅድ መጀመሪያ የተያዘ ሰራዊት ነበሩ ፤ ቀጥሎም ወደ ባቢሎናዊያን መጣ፣ ከዚያም አሁን እንደ እግዚአብሄር ድል አድራጊ በፋሪሳዊያን በቂሮስ ላይ መጣ ፡፡ ሜዶ እና ፋሪሳዊያን ለጥቂት ጊዜ ወደ ባቢሎን ላይ በመሰብሰብ መጥተዉ ነበር ፤ ባቢሎናዊያን ግብፅን በመዉሰድ ማርከዉ ነበር ፡፡ እነዚህ የተለያዩ ኢምፓየሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር እስከ ባቢሎን ምርኮ ላይ እስካበቃ ድረስ ታሪካቸዉ አብሮ በመጓዝ የተሳተፈ ነበር ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ (50፡ 1-5)፡ እግዚአብሄር በባቢሎን እና በባቢሎናዊያን ምድር ላይ ተናገረ ፡፡ ኤርምያስ ባቢሎን እንደምትወረወር እና አማልዕክቶቿም እንደሚጠፉ/እንደሚቆሙ ተናግሯል ፡፡ እስራኤል እና ይሁዳ በአንድ ላይ በመምጣት ራሳቸዉን ከእግዚአብሄር ጋር ያጣምራሉ ፡፡

ምናልባትም ከኤርምያስ የመጣዉን የእግዚአብሄርን ቃል አክብረዉ ያልነበሩ በዚያን ጊዜ ሞተዉ የነበሩ አይሁዶች ነበሩ ፤ ኤርምያስ ወደ ግብፅ ከሄዱ በዚያ እንደሚሞቱ ነግሯቸዉ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 50 እነዚህ የትንቢት ቃሎች ለአዲሱ ለአይሁድ ትዉልድ ይሆናሉ ፤ እነዚህ ሰዎች ቀርተዉ የነበሩት የአይሁድ ቅሬታዎች ይሆናሉ ፡፡

ኤርምያስ (50፡ 6-8)፡ ኤርምያስ የሕዝቡ እረኞቹ - ሐሰተኛ ነቢያቶቹ አጣመዉ/ወደ ተሳሳተ መንገድ መርተዋቸዉ ነበር ፤ ሕዝቡ እንደሚመሩ መንጋዎች እና በእረኞቻቸዉ ፊት እንደሚሄዱ በጎች የሚመስሉ ነበሩ ፡፡ የኤርምያስ መልዕክት ይጠፉበት ከነበረዉ ምድር በባቢሎን ከመኖር ይልቅ እንደ ዘላን በመኖር ባቢሎን መልቀቅ ለሕዝቡ የተሻለ እንደሚሆን ነበር ፤ ኤርምያስ ባቢሎንን ለማጥፋት አንድ ሕዝብ ከሰሜን እንደሚመጣ ተነበዬ ፡፡

ኤርምያስ (50፡ 9-10)፡ ኤርምያስ በዉጊያቸዉ በባቢሎን ላይ በእግዚአብሄር እጅ ስለሚመሩት ከሰሜን ስለሚመጣዉ ታላቅ ሕዝብ ትንቢትን ተናግሯል ፤ ከእነዚህ ተዋጊዎቹ ማንኛዎቹም በከንቱ አይዋጉም፣ ሁሉም በዉጊያዉ ስኬታማ ይሆናሉ ፡፡

ኤርምያስ (50፡ 11-13)፡ ኤርምያስ ሕዝቡ ደስተኞች ሆነዉ እንደ ነበርና የባቢሎንን ምድር እንደያዙ እንዳሰቡ አመልክቷል ፤ ደስተኞች የሆኑም መስለዉ ነበር ፡፡ እየመጣ የነበረው ሙሉ ጥፋት የሚያመጣ የእግዚአብሄር ቁጣ ነበር ፡፡ ባቢሎን የታላቅ ኃይል ግዛት ነበረች ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ባድማ በመሆን ጥፋቷም/መፈራረሷም በአጠገቧ በሚያልፉት አይታመንም ፡፡

ኤርምያስ (50፡ 14-22)፡ ኤርምያስ እግዚአብሄር ፋሪሳዊያን/በዙሪያዋ ያሉ ሕዝቦች ያለበቀል ቀስት እንዴት ባቢሎንን እንደሚገጥሙ እንደሚጠብቅ ገልፆአል ፡፡ የእግዚአብሄር በቀል ባቢሎን ሌሎች ሕዝቦችን ይዛ እና አጥቅታ እንደ ነበረዉ የተጠቃች መሆኗን ይፈልጋል ፡፡ ባቢሎን ከመጀመሪያዉ የተፈረደባት ነበረች ሙሉ ለሙሉም የምትጠፋ ነበረች ፡፡ ከእግዚአብሄር የሆነዉ ትዕዛዝ ምንም እስረኛ አለመዉሰድ ነበር ፡፡

በዚህን ጊዜ የሰሜኑ መንግስት እስራኤል እና የደቡቡ መንግስት ይሁዳ ሁለቱም በአሶራዊያን፣ በግብፃዊያን እና በባቢሎናዊያን የተቀጡ ነበሩ ፤ አሁን የእግዚአብሄር ተግሳፅ/ቅጣት ሞልቶ ነበር ፡፡ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሄር ታዘዉት ያልነበረዉን ያክል ቀጥቷቸዉ እንደ ነበር ተሰማው ፤ እግዚአብሄር ለኃጢዓታቸው ይቅርታ ማድረግን እየሰጣቸዉ ነበር ፡፡

ኤርምያስ (50፡ 23-46)፡ ኤርምያስ የአለም ሁሉ መዶሻ የነበረችዉ ባቢሎን እንዴት ተሰብራ እና ጠፍታ እንደ ነበር ጥያቄን ያነሳል ፤ አሁን እግዚአብሄር ስለ ባቢሎን እየተናገረ ነበር ፡፡ እግዚአብሄርን ተቃዉመዉት ነበር እናም አሁን እግዚአብሄር የጦር በትሩን እያመጣባቸዉ/እየከፈተባቸዉ ነበር ፤ የእግዚአብሄር ቁጣ ወደ ባቢሎናዊያን ላይ የዞረ ነበር ፡፡

የእግዚአብሄር በቀል የቤተ መቅደሱ በቀል ነበር ፤ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ እና የያዛቸዉ ሁሉ ለአምልኮ ለእግዚአብሄር የተቀደሱ ነበሩ ፡፡ የባቢሎናዊያን ንጉስ እቃዎቹን ከቤተ መቅደሱ ዉስጥ በመዉሰድ ለራሱ ተጠቅሞባቸዉ ነበር ፡፡

በዳንኤል 5 ንጉሱ ከቤተ መቅደሱ ዉስጥ ስለወሰዳቸዉ የአምልኮ እቃዎች መዝገብ አለ ፡፡ ንጉሱ ከቤተ መቅደሱ ዉስጥ ያስፈሩ የነበሩ ነገሮችን ወስዷል አሁን እግዚአብሄርም በሚገባ ይቀጣዋል ፤ ዘመኑ የተቆጠረ ይሆናል ፡፡ ዳንኤል በመንግስቱ ለዳንኤል እና ለእግዚአብሄር የመለመን ጥረትን ለማድረግ ሰዎስተኛዉ የአገዛዙ አለቃ የተደረገ ነበር ፤ ነገር ግን ያ ምሽት ንጉሱ የሞተበት እና መንግስቱ ለሜዲያ የተሰጠበት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር የባቢሎን የሆነዉ ሁሉ ለሜዲ እና ለፋሪስ የተሰጠ እንደሚሆን ለባቢሎን እደንተናገረ ይገልፃል ፡፡ ባቢሎን በመጨረሻም በጠፋች ጊዜ በዳንኤል ዘመን ምን እንደሚሆን ፅሁፉ ቀድሞ ይናገራል ፡፡

ባቢሎን የመላዉ ምድር ድል አድራጊ ነበረች ፤ በፊታቸዉ ማንም ሊያቆመዉ የማይችል መሳሪያ ነበራት እንዲሁም በሁሉም ሕዝብ ላይ ያስተዳደረች መንግስት ሆና ነበር ፡፡ ነገር ግን ኤርምያስ የባቢሎን ዘመን እንዳበቃ ትንቢት ተናገረ ፡፡ በዳንኤል መፅሀፍት ጥቅሶች ላይ የዚህን መግለጫ መደምደሚያ ማየት እንችላለን ፡፡

መደምደሚያ

በራዕይ፣ በዳንኤል እና በኤርምያስ ጥቅሶች መሰረት በአንድ ስዓት ዉስጥ የሚጠፋ ሕዝብ በእኛ ዘመን ዉስጥ ሊኖር የሚችልበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ፡፡ ዛሬም በእግዚአብሄር ጥበቃ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልገን ማስተዋል አለብን ፤ ከእግዚአብሄር ዉጪ ከቅጥር/ከሚከላከልልን ዉጪ ነን ፡፡ እግዚአብሄር በፊታችሁ የማይበገር ሕዝብ እንደማይኖር እንድንረዳ ይረዳናል ፡፡ የእግዚአብሄርን ምክንያት ለማስነሳት አንዶቹ እንሆናለን ? በአለም ላይ እና ኤርምያስ በኖረበት ጊዜ ላይ እንዴት ኖረን ? ኤርምያስ ለጥሩ ምክንያት የሚያለቅሰዉን ነቢይ ተጣራ ፡፡

የእግዚአብሄርን ቃል በራሳችን በምንሰማ ጊዜ የእግዚአብሄር መገለጥ ከእኛ ጋር ነው ፡፡ አንድ የማያቋርጥ ነገር አለን ፤ እግዚአብሄር እቅድ እንዳለዉ እናዉቃለን ፡፡ እግዚአብሄርን እንድናደርገዉ ለእኛና ለቤተ ክርስቲያን ምን እንዳለዉ መጠየቅ አለብን ፤ ቀጥለንም እግዚአብሄር እንድንረሳዉ እንደማይፈቅድ መጠየቅ አለብን ፡፡ ለአላማዉ ተቀድሰዉ የነበሩን ነገሮችን ባለመዉሰድ ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች መጠቀም አለብን ፡፡ ምናልባትም ለእርሱ ክብር ምልክት ተደርጎብናል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ኤር (50፡ 15) በማንበብ ማቴ (7፡ 2) አንብቡ ፤ ኤርምያስ 50 በማቴዎስ 7 ላለዉ ለኢየሱስ ቃል ታላቅ መሆን የሚችል ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይችልም ?
  2. በግል አስተያየታችሁ ኤር (50፡ 4-5) ኢየሱስ ስለሚመለስበት የመጨረሻዉ ዘመን ሊሆን ይችላል ? (መዝ 102፡ 13-22, ኢሳ 66፡ 20)
  3. በኤርምያስ 50 በባቢሎን ውድቀት እና በራዕይ 18 ባለዉ ውድቀት መካከል ልዩነት ካለ ልዩነቶቹ ምንድን ናቸው ? እነዚህ ዉድቀቶች ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ ? ለምን ወይስ ለምን አይሆኑም ?
  4. በኤርምያስ 50 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 50:33–34

“This is what the LORD of Hosts says: Israelites and Judeans alike have been oppressed. All their captors hold them fast; they refuse to release them. Their Redeemer is strong; Yahweh of Hosts is His name. He will fervently plead their case so that He might bring rest to the earth but turmoil to those who live in Babylon.”

ባቢሎን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ምድር አጠፋ ፡፡ እግዚአብሔርም የባቢሎን ከተሞችን እንደሚያወድም ተናገረ ፡፡ ልክ በሰዶምና በጎሞራ እንደሆነውም ሁሉ ማንም አይተርፍም አለ ፡፡ እግዚአብሔርም እስራኤላውያንን በእርሱ የተዋጁ ፣ በእርሱ የተወደዱና ለእርሱ የተመረጡ ህዝቦች ብሎ ይጠራቸዋል ፡፡ እርሱ በጥንቃቄ የራሱን ህዝብ ይጠብቃል እነርሱን የሚጎዷቸውንም ያያል ፡፡ እግዚአብሔር የእርሱን ውድ ህዝቦች በጎዱት በባቢሎን ህዝቦች ላይ ፍርድን ያደርጋል ፡፡ እርሱ የጦር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ በባቢሎን ላይ መዓቱን ያመጣል ፡፡

እግዚአብሔር ህይወታችሁን ያያል ፡፡ እርሱም እናንተን የምወዳችሁ ፣ የዋጀኋችሁና የመረጥኋችሁ በማለት ይጠራችኋል ፡፡ እጁ በእናንተ ላይ ናት ፡፡ እግዚአብሔር በክንፎቹ ጥላ ስር እንደሚሸሽጋችሁና እንደሚጠብቃችሁ ይናገራል ፡፡ እርሱ እናንተን በቀንና በሌሊት ይጠብቃችኋል ፡፡ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው ፈጽሞም አይተዋችሁም ወይም ጥሏችሁ አይሄድም ፡፡ እርሱ የሚያስጨንቋችሁን ፣ የሚጎዷችሁንና የሚበድሏችሁን ያያል ፡፡ ወደ እርሱ ሩጡ ፡፡ በኃይሉ ይጠብቃችኋል ፡፡ የሰራዊት አምላክ እጁን ዘርግቶ የቁጣ በትሩን እንደሚያነሳ ይናገራል ፡፡ እርሱ ውጊያችሁን እንድሚዋጋላችሁ ይናገራል ፡፡ ዛሬ የሰራዊት ጌታ እንድዋጋላችሁ አድርጉ ፡፡ በፍቅሩ ኑሩ ፡፡

“ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተገፍተዋል ፥ የማረኳቸውም ሁሉ በኃይል ይይዙአቸዋል ፥ ይለቅቁአቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል ። ተቤዢአቸው ብርቱ ነው ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው ፤ ምድርንም ያሳርፍ ዘንድ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ሙግታቸውን ፈጽም ይምዋገታል ። “

  • ኤርምያስ 50፡33-34

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 78:35 — “ ረዳታቸውም እግዚአብሔር ፥ መድኃኒታቸውም ልዑል አምላክ እንደ ሆነ አሰቡ ። “

ኤርምያስ 50:24–25 — “ ባቢሎን ሆይ ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለውና እግዚአብሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍጣውን ዕቃ ጦር አውጥቶአል ። “

ኤርምያስ 50:40 — “ ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው ፥ ይላል እግዚአብሔር ፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም ። “