Major Prophets Jeremiah

Restoration Through The New Covenant

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 48-49 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 620 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኤርምያስ (48-49) ብዙ ነገር አለ ፡፡ መጀመሪያ ሕዝቦቹ ማን እንደ ነበሩ እና በዚህ የታሪክ ጊዜ ማን ጥምረት ፈጥሮም እንደ ነበር መመልከት እፈልጋለሁ ፤ ደማስቆ የሰሜኑ መንግስት እስራኤልን በያዙበት በተመሳሳይ ጊዜ በአሶራዎያን ተይዛ የነበረች የሶሪያ ዋና ከተማ ነበረች ፤ ነንዌ የአሶር ዋና ከተማ ነበረች ፡፡ የነንዌ ማስታወሻዎች ቅሬቶች ከአሁኑ ሞስሎ ዉጪ ኢራቅ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት በባቢሎናዊያን ጠፍታለች ፡፡ ባቢሎን ከለዳዊያን ተብለዉ ተጠቅሰዉ የነበሩት የባቢሎናዊያን ዋና ከተማ ነበረች ፤ ሱሳ የፋሪስ ግዛት ዋና ከተማ ነበረች ብዙ ቆይቶም የንግስት አስቴር መንግስት ነበር ፡፡ በአሕዛቦች ላይ ስለሚሆን ፍርድ ጥናታችንን እንቀጥላለን ፤ ለአሕዛብ የኤርምያስ መልዕክት ለእነዚህ ሕዝቦች ብቻ አልነበረም ፡፡ ዉድ እና ማክላረን “ የኤርምያስ ሸክሞች የቀደሙ ይሆናሉ ነገር ግን የጥንት እንዳይደሉ “ ፅፈዋል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ አነጋገሮች ያሕዌ ለሁሉም ሕዝብ ቅዱስ አምላክ እንደሆነ ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፡፡ ለእነዚህ ምዕራፎች የተዘጋጀዉ ትምህርት እግዚአብሄር አምላክ ያሕዌ በመከራ እና በምርኮ መካከል ላይ ለይሁዳ እና ለአሕዛብ ሁሉ መፅናናትን እንደሚያመጣ ነዉ ምክንያቱም በእግዚአብሄር የተመቤዠት እቅድ ዉስጥ የተካተቱ ስለ ነበሩ ፡፡

በዚህ ሂደት ዉስጥ የእግዚአብሄር ነቢያቶች አስፈላጊዎች ነበሩ ፡፡ ፊ እና ሰታዉርት ነቢያቶቹን “ እንደ ኪዳን አጠንካሪ መካከለኞች “ ይገልፁአቸዋል ፡፡ ነቢያቶች በተለዬ ለይሁዳ እና ለእስራኤል የተላኩ ነበሩ ነገር ግን ሁሉንም የእግዚአብሄርን ፍጥረቶች ደረሱ ፡፡ በምዕራፍ (48-49) ለአሕዛብ የተነገሩት ሸክሞች እንደሚከተለዉ ሊቀመጡ ይችላሉ፡

  • ሞዓብ በራሱ ስለተደገፈ በባቢሎን ይጠፋል ፤ ይታደሳሉም (ኤር 48፡ 1-47) ፡፡
  • አሞናዊያን ለራሳቸዉ ጋድን ወሰዱ ነገር ግን ርካሽ ይሆናሉ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ሕዝቦች ላይ ከራሳቸዉ በላይ ስለደረሱ ፤ አንድ ቀንም ይታደሳሉ (ኤር 49፡ 1-6) ፡፡
  • የኤዶምያስ ጥበብ ተለዬ በሙሉ እንደሚለቀም ወይንም ይሆናሉ ፡፡ የተጠቀስ መታደስ አልነበረም (ኤር 49፡ 7-22) ፡፡
  • ደማስቆ (ሶሪያ) አሁንም የሚያደርገዉ ስራ ነበረዉ ነገር ግን መኖሪያቸዉም ባድማ ይሆናል (ኤር 49፡ 23-27) ፡፡
  • ቄዳርና አሶር የዘላን እና በደንብ ቅጥር ያላቸዉ ሁለት ከተሞች ነበሩ ፤ ሁሉም ግመሎቻቸው እና ንብረታቸው ይዘረፋሉ/ይወሰዳሉ (ኤር 49፡ 28-33) ፡፡
  • ኤላ አራት የጥፋት ንፋሶችን ይታገሳል ነገር ግን መታደስም ቃል ተገብቶላቸዉ ነበር (ኤር 49፡ 34-39) ፡፡

እንዴት ኤርምያስ እነዚህን ሸክሞች እንዳደረሰ ወይም ወደ እያንዳንዱ ስፍራ እንደተጓዘ አናዉቅም ፤ ለየብቻ በተለያዬ መልኩ ደርሷቸዉ እንደ ነበር የዚያ አይነት ስሜት አለ ፤ በስብስቡ ዉስጥ ግንኙነታቸው የታዬ ነው ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ (48)፡ ነቢያቶች አስፈላጊ እንደ ነበሩ የተመለከቷቸዉን እግዚአብሄር በቀጥታ ለእነርሱ ተናግሯቸዉ የነበሩትን ቃሎች የእግዚአብሄርን መልዕክት በቀጥታ አምጥተዋል ፡፡ ሞዓብ ከሎጥ ከትልቅ ሴት ልጁ ጋር ግንኙነት ከነበረዉ ወንድ የልጅ ልጁ ጋር ግንኙነት ነበረው (ዘፍ 19፡ 30-38) ፡፡ እስራኤል ወደ ከነዓን በመጣች በዚያን ጊዜ ሞዓብ በማጥቃት በእነርሱ ላይ በመንገስም አስተዳደረ (መሳ 3፡ 12-14) ፤ ሩት ከሞዓብ በመዉጣት ወደ ዳዊት ዘር ዉስጥ ገባች ፡፡ ንጉስ ዳዊት ከሞዓብ ጋር በመዋጋት ሞዓብ በመሸነፋቸዉም ለእስራኤል አገልጋይ መንግስት ሆነ (2ነገ 1፡ 1, 3፡ 4-5) ፡፡ እግዚአብሄር በነቢያቶቹ በኩል ተናግሮ የነበረዉን በሞዓባዊያን ነገር ነበረው (ኢሳይያስ 15-16, ኤርምያስ 27, ሕዝቅኤል 25፡ 8-11, አሞ 2፡ 1-3, ሶፎ 2፡ 9) ፡፡ የአሶር ንጉስ ሳርጎን ሞዓብን በያዜ ጊዜ የኢሳይያስ የተፈፀመ ሲሆን የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር ሞዓብን በያዘ ጊዜ የኤርምያስ ትንቢት ተፈፀሟል ፡፡ ይሁ ሁለተኛ ክስተት ከኢየሩሳሌም መፈራረስ አምስት አመት በኋላ እና ትንቢቱ በኤርምያስ ከተነገረ ከ23 አመት በኋላ ተከናወነ/ተከሰተ ፡፡

በሚያስደንቅ ሁኔታ ለሞዓብ የነበረዉ መልዕክት ከሀገሪቱ መጠን/ስፋት አንፃር ረጅም ነበር ፤ አብዛኞቹ ከተሞች በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ የተጠቀሱት በሙሴ ለሮቤላዊያን የተሰጡ ነበሩ (ዘኁ 32፡ 33-38, ኢያ 13፡ 15-23) ፡፡ የሞዓብ ሰዎች ይሰባበራሉ አማልዕክታቸዉም ካሞሽ ከአለቆቹና ከካህናቱ ጋር ወደ ምርኮ ይላካል (ቁጥር 4-8) ፡፡ አማልዕክቱ ካሞሽ የልጆችን መስዋዕት ይፈልጋል (2ነገ 3፡ 27) የሞዓብ ንጉስም ለዚያ አማልዕክት ወንድ ልጁን ሰዉቷል ፡፡ የእግዚአብሄር ቅጣት ንስሐ ስላልገቡበት ክፋታቸው ሙሉ ነበር፡ “ በእግዚአብሄር ላይ ኮርቶአልና አስክሩት ፤ ሞዓብም በትፋቱ ላይ ይንከባለላል ደግሞም መሳቂያ ይሆናል “ (ቁጥር 26) ፡፡ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ሆኖ በነበረዉ ነገር ስቆ ነበር ይሁን እንጂ በእስራኤል ላይ የደረሰዉ ተመሳሳይ መከራ ይደርስበታል (ቁጥር 40-46) ፤ ቁጥር 33 “ ሐሴትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻ ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል ፤ ጠጁን ከመጥመቂያዉ አጥፍቻለሁ ፤ ጠማቂዉም በእልልታ አይጠምቅም እልልታቸዉም እልልታ አይሆንም “ በማለት ይናገራል ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄር መታደስ ተስፋ አለ (ቁጥር 47) ፡፡

ኤርምያስ (49፡ 1-6)፡ ኤርምያስ በታናሽ ሴት ልጁ በሎጥ በኩል ከተወለደዉ ወንድ ልጅ (ዘፍ 19፡ 30-38) መነሻዉ ሎጥ እንደሆነ በተሳለው በአሞን ላይ ትንቢትን ተናገረ (ቁጥር 1-6) ፡፡ አሞን ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምስራቅ በኩል እና ከሞዓብ በስተሰሜን በኩል የሚገኝ ነበር ፡፡ አሞን ከመሳፍንት ዘመን ከእስራኤል ጋር በጦርነት የገጠመ ነበር ፡፡ አማልዕክታቸዉ ሚልኮም አንዳንድ ጊዜ እንደ ሞሎክ ሲጠቀስ የልጅ መስዋእትንም ይፈልጋል (ቁጥር 1) ፡፡ አሞን የእግዚአብሄር ፍርድ ይደርስበታል ነገር ግን የመታደስ ተስፋዉንም ተቀበለዋል ፡፡

ኤርምያስ (49፡ 7-22)፡ የኤዶም ሕዝቦች ከያዕቆብ መንታ ወንድም ከኤሳዉ የመጣ ትዉልድ ነበሩ ፡፡ ኤዶምያስ እስራኤልን በመዋጋት ከተማዋን ለመዝረፍ ድርሻን ለመዉሰድ እና አይሁዶችን ለማረድ ከናቡከነደጾር ጋር ተጣመረ፡፡ የተተነበየዉ ጥፋት በቁጥር (12-13) ላይ የተቀመጠ ነበር ፤ ደህንነቷ በተጠበቀ በቴማን “ በአለት ተራሮች “ ላይ ኖሮ ነገር ግን በዚያ ቢሆኑም እንኳን እግዚአብሄር አዉርዶ ያመጣቸዋል ፡፡

ኤርምያስ (49፡ 23-27)፡ ደማስቆ ከሐማትና አርፉድ ጋር በክፋታቸዉ የሚታወቁ የሶሪያ ታላላቅ የኃይል ግዛቶች ነበሩ (አሞ 1፡ 3-5) ፡፡ ደማስቆ ትሸነፋለች ነገር ግንባድማ አትሆንም ፡፡

ኤርምያስ (49፡ 28-33)፡ የቄዳር ሰዎች የበግ እረኞች (ኢሳ 60፡ 7)፣ ነጋዴዎች (ሕዝ 27፡ 21) እና የሰለጠኑ ቀስተኞች (ኢሳ 21፡ 16-17) ነበሩ ፤ ከእስማኤል ዘር የወረዱ ዘላን የአረብ ሰዎች ነገድ ነበር (ዘፍ 25፡ 13) ፡፡ ሀዞር ከተማ በምስራቅ በርኃ እና ምናልባትም ቅጥር የሌላቸዉን አካባቢዎች ያካትታል ፡፡ ኤርምያስ እነዚህ የአረብ ጎሳዎች በሁሉም በኩል ፍርኃት ይሆንባቸዋል (ቁጥር 29) ፡፡

ኤርምያስ (49፡ 34-39)፡ ኤርምያስ ኤላም ከግብፅ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፍርድን እንደሚጋራ ተናግሯል ፤ ኤላም መነሻው ወደ ኋላ ወደ ኖህ ዘመን በመመለስ የሴም ትልቅ ወንድ ልጅ ነበር ፡፡ የኤላም ሰዎች ታዋቂ ቀስተኞች የነበሩና ቀስታቸዉም የኃይላቸዉ ምልክት ነበር (ቁጥር 35) ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሄር የኤላን ሰዎች ከሰማያ ከአራቱም መዓዘን በእነርሱ ላይ በሚያመጣቸዉ አራት ነፋሳት በመላዉ አለም ይበትናቸዋል አለ (ቁጥር 36) ፡፡ ባቢሎናዊያን ሌላዉን ሁሉንም ቢይዙም በፍፁም ሙሉ ለሙሉ አልያዘም ፤ የኤላ ሽንፈት ከሌላ አቅጣጫ ይመጣ (ቁጥር 38) ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር “ በመጨረሻዉ ቀን “ ተሀድሶ እንደሚያደርግላቸዉ ቃል ገብቷል (ቁጥር 39) ፡፡ ይህ ተስፋ ከክርስቶስ ልደት 539 በፊት ኤላ ሱሳን ዋና ከተማዋ በማድረግ የፋሪስ ግዛት ማዕከል በሆነ ጊዜ ግማሹ ተፈፅሟል ፡፡

መደምደሚያ

ፈሊፕ ራይኬን “ ኃብት አሞናዊያንን አላዳናቸውም ፤ ከፍርድ የሚወጡበትን መንገድ መግዛት አይችሉም ፤ ጥበብ ኤዶምያስን አላዳነዉም የወታደራዊ ኃይላቸዉም አላዳነዉም ፤ ዝና ሶሪያን አላዳናትም ምክንያቱም እግዚአብሄር የሰዎች ዝና አክባሪ አይደለም ፡፡ ነፃነት የአረብ ዘላኖች አላዳናቸዉም ፣ እግዚአብሄር በምድረበዳ በማግኘት በተመሳሳይ ያጠፋቸዋል ፤ መሳዊያ ኢላሜጤዋያን አላዳናቸዉ “ በማለት ይፅፋል ፡፡

የኤላ ታላቅ ሙላት በበዓለ ኃምሳ ቀን ላይ ይመጣል ፡ “ ተገርመዉም ተደንቀዉም እንዲህ አሉ፡- እነሆ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን ? እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን ? የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም “ (ሐዋ 2፡ 7-9) ፡፡ በቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ መንፈስ በወረደ ጊዜ ሜዴ እና ኢላሜጤ በኢየሩሳሌም ነበሩ ! በአዲሱ ኪዳን በእግዚአብሄር መንፈስ የተዳሰሱ/የተነኩ ነበሩ ፡፡

3 Philip Ryken; quoted by David Guzik; https://www.blueletterbible.org/Comm/guzik_david_StudyGuide2017-Jer/Jer-49.cfm.

  1. Fred W. Wood and Ross McLaren, Holman Old Testament Commentary: Jeremiah, Lamentations (Nashville: Holman Reference, 2006), p. 326.

  2. Gordon Fee and Douglas Stuart, How to Read the Bible for All Its Worth (Grand Rapids, MI: Zondervan, 2014), p. 167.

ጥያቄዎች

  1. ኤርምያስ 48 በሞዓብ ላይ ይናገራል ፤ ሞዓባዊያን እነማን ነበሩ በእስራኤል ሕዝብስ ላይ ምን አደረጉ ? (ዘፍ 19፡ 30-37, ዘኁ 25፡ 1-3)
  2. በኤር (48፡ 7) ኤርምያስ ስለ ካሞሽ አወራ ፤ ካምሽ ምን ነበር (መሳ 11፡ 24, 1ነገ 11፡ 7) ? ከካሞሽ ጋር የተገናኘዉ/የተሳሰረው ምን ነበር (2ነገ 3፡ 26-27) ? ይህ አሁንም በዛሬ ጊዜ በቀጥታ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ይሆናል ብላችሁ ታምናላችሁ ? እንዴት አድርጎ ?
  3. በኤር (48፡ 29) የሞዓብ ትዕቢት ተነግሯል ፤ የትዕቢት ትርጉሙ ምንድን ነው ለምን/በምን መጥፎ ነገር ሊሆን ይችላልስ ? በህይወታችሁ ባለ ሰዉ ወይም በዙሪያችሁ ባሉ ጓደኞች መኩራት መጥፎ ነገር እንደሆነ ታምናላችሁ ? ኤርምያስ ከሞዓብ አንፃር ከተናገረዉ ኩራት/ትዕቢት ጋር ስታወዳድሩት ልዩነት አለው ? (ምሳ 16፡ 18)
  4. አሞናዊያን በምን አማልዕክት በማምለክ የታወቁ ነበሩ (ዘሌ 18፡ 21, 20፡ 3, 1ነገ 11፡ 7) ? ይህ አማልዕክት እንዴት ከካሞሽ ጣዖት ጋር ይመሳሰላል ? አማልክቱን ለማስደሰት ልጆችን መስዋዕት ማድረግ ተቀባይነት የነበረዉ ነገር እንደሆነ እንዲያምኑ ምን እንዳደረጋቸዉ ምን ታስባላችሁ ? በዙሪያችሁ እነዚህ ሰዎች ምን ያክል ክፉዎች እንደ ነበሩ በመሞከር ሀሳባችሁን ለማፅዳት በዚህ ላይ አሰላስሉ ፤ በራሳችሁ ህይወት ላይ እንደዚህ አይነት ክፉ ነገር ታያላችሁ ?
  5. እግዚአብሄር ሁሉንም ሕዝብ ያጠፋበት ጥቂት ምክንያቶች ምን ነበሩ (ዘፍ 19፡ 1-13, ኤር 49፡ 16, 18) ? በመፅሀፍ ላይ ወይም በአሁኑ ጊዜም ማህበረሰብም እንኳን እግዚአብሄር ሁሉንም ሕዝብ ለማጥፋት ፍቃደኝ የሚሆንበት ሌላ ምሳሌ ማሰብ ትችላላችሁ ? ልክ እንደ ISIS እንዲሁም ወዚብ አዘዋዋሪዎችን አይነቶቹን ሕዝቦች እስካሁን ለምን እንደታገሳቸዉ ምን ታስባላችሁ ?
  6. በኤርምያስ (48-49) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 48:47

“Yet, I will restore the fortunes of Moab in the last days. This is the LORD’s declaration. The judgment on Moab ends here.”

ኤርምያስ በብዙ ህዝቦች ላይ ትንቢትን ተናገረ ፡- ስለ ሞአብ ፣ ስለ አሞን ፣ ስለ ኤዶም ፣ ስለ ደማስቆ ፣ ስለ ቄዳር ፣ ስለ አሶርና ኤላም ፡፡ እነርሱ የራሳቸውን መንገድ ተከትለዋል ፣ የራሳቸውን አማልክቶች ሰርተዋል ደግሞም በእግዚአብሔር ሳይሆን በራሳቸው ተመክተዋል ፡፡ እግዚአብሔርም ሁሉንም ነገር አይቷል ስለዚህም በእነርሱ ላይ ተገቢውን ፍርድና ቅጣት አዘጋጅቷል ፡፡ ይሁን እንጂ ለአንዳንዶቹ ህዝቦች እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን ህይወታቸውን ይታደግላቸዋል ፡፡

እግዚአብሔር ያያል ደግሞም እንዲሁ መልሶ ያቆማል ፡፡ እርሱ የሚወደድና የተመሰገነ አምላክ ነው ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር ትምክትህን ፣ ራስ ወዳድነትህን ፣ ትዕቢትህን ፣ በዕብሪት የተሞላ ልብህን እናም ገንዘብህ አድርገህ የያዝከውን ነገር ያያል ፡፡ እርሱ ያያል ፡፡ ከእግዚአብሔር መደበቅ አትችልም ፡፡ እርሱ በዘላለማዊ ፍቅሩ ወደ ራሱ ሊስብህ ይጥራል ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ ፡፡ በልብህም ውስጥ እርሱን የሚቃረን አሳብ መንገድ ካለ ፣ ልብህን ይመረምር ዘንድ ወደ እርሱ ጸልይ ፡፡ እርሱም በልብህ ውስጥ ንስሀ መግባት ፣ ራስን ማዋረድ ወይም ደግሞ ይቅርታ የሚያስፈልገውን ነገር ሲገልጥልህ ፣ የሚሰጥህን ምሪት ተቀበል ፣ ታዘዝ ፡፡ እግዚአብሔር መልሶ ያቆምሃል ፡፡ እግዚአብሔር ልብህን ያድሳል ፡፡ ዛሬን ከእርሱ መራቅ የምታቆምባት ቀን አድርጋት ፡፡ ያንን ማድረግ ማቆም ያለብህን ነገር ፣ አቁም ፡፡ ይቅርታ ልጠይቀው እንደሚገባ የምታውቀውን ሰው ፣ በል ጥራውና ይቅርታ ጠይቀው ፡፡ ልትተወው የሚገባውን ነገር ግን ገንዘብህ ያደረከው ነገር ፣ ተወው ፡፡ እግዚአብሔር ከምታስበው በላይ መልሶ ሊያቆምህ ይፈልጋል ፡፡

“ ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፦ የሞዓብ ፍርድ እስከዚህ ድረስ ነው ። “

  • ኤርምያስ 48፡47

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 26:2–3 — “ አቤቱ ፥ ፍተነኝ መርምረኝም ፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፍተን። ምሕረትህ በዓይኔ ፊት ነውና ፥ በእውነትህም ተመላለስሁ ። “

መዝሙር 139:23–24 — “ አቤቱ ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ ። “

ኤርምያስ 48:29–30 — “ እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኵራቱም ስለ መጓደዱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል ። ቍጣው ምንም እንደ ሆነ አውቃለሁ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፤ ፉከራው ምንም አልሠራም ። “