Prophecies Against Egypt
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 46-47 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ታላላቅ ነቢያቶች በመጨረሻዉ ጊዜ ላይ ምልከታዎች ያቀርባሉ ፡፡ ማቴ (5፡ 17) ክርስቶስ በመፅሀፍት የተካተቱትን ትንቢቶች ሊፈፅም እንደ መጣ ይናገራል ፡፡ የመፅሀፍት ጥናት በእያንዳንዱ የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ዉስጥ ኢየሱስን የት እንደምናየዉ በመጠየቅ የመሲሁን ሙሉ ስዕል ያቀርባል ፡፡ እንዲህ አይነቱ የአመለካከት ማዕበል ፍርድ እና ነፃ መዉጣት ሁሉም በአንድ ላይ ይመጣሉ ፤ የእግዚአብሄር ቃል ሕያዉ እና የሚሰራ ሲሆን ታላላቂ ነቢያቶችም አስፈላጊዎች ነበሩ ፤ የክርስቶስን የመጀመሪያ ጊዜ መምጣት፣ የክርስቶስን መመለስ እና የሺዉ አመትን አካትተዋል ፡፡
ኤርምያስ ለሕዝቡ ለ40 አመታት ያክል ሰብኳቸው ነበር ፤ የኤርምያስ መልዕክት በአብዛኛዉ የደቡብን መንግስት ይሁዳ ላይ ያነጣጠረ/ያተኮረ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 46 ኤርምያስ ለአሕዛቦች መስበክ ጀመረ ፤ እግዚአብሄር የኤርምያስን መልዕክት አስፍቶት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ፅዋዉን እያፈሰሰ ነበር ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (46፡ 1-7)፡ የብሉይ ኪዳን አምላክ አስፈልጎ በነበረ ጊዜ ቁጣዉን ያፈስሳል ፤ በምዕራፍ 46 የተጠቀሰዉ ፅዋ የእግዚአብሄር የመዓት/የቁጣ ፅዋ ነበር ፡፡ ምዕራፍ (46-51) ስለ እግዚአብሄር ፍርድ ናቸው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚገልፀው፡-
“ ኤርምያስ እግዚአብሄር በዘጠኝ ሕዝቦች ላይ ለማምጣት የማለባቸዉን የተወሰኑ ፍርዶችን ያሳዉቃል (ምዕራፍ 46-51) ፤ እነዚህን የሚመጡትን ቃላቶች በማጥናት ዉስጥ ሁለቱን እዉነቶች ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡
- የእግዚአብሄር ቁጣ ያለ ምክንያት አልነበረም ፤ ለእግዚአብሄር ቁጣ ግልፅ የሆነ ምክንያት ነበር፡ ተዘርዝረዉ የነበሩት እያንዳንዳቸዉ ሁሉም ሕዝቦች የፈጠራቸዉን አምላክ ከማምለክ ወደ የኃሰት አማልዕክቶችን ወደ ማምለክና ወደ ማገልገል ዞረዋል ፤ እያንዳንዳቸዉም ጥፋተኞች ስለ ነበሩ የእግዚአብሄር ቅዱስ ተፈጥሮ በኃጢዓታቸው ላይ ፍርድን ይፈልጋሉ ፡፡
የእግዚአብሄር ቁጣ ያለማስተካከያ/ያለመፍትሄ አልነበረም ፤ ምንም እንኳን እግዚአብሄር በኤርምያስ የአገልግሎት አመታት ዉስጥ ይሁዳን ከኃጢዓቱ እንዲመለስ ሲጣራ አሕዛቦችንም ወደ እርሱ በመመለስ እንዲድኑ ጠርቷቸው ነበር ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ የእግዚአብሄርን የቸርነት አቅርቦት/እድል አልተቀበሉም ነበር ፡፡ አሁን ቁጣዉ ደረሰባቸው “ ፡፡
ኤርምያስ በሕይወቱ ላይ የእግዚአብሄርን ጥሪ እንደ ገና ተናገረ ፡፡ የእግዚአብሄር ጥሪ አይቸኩልም፣ መጠበቅን ይፈልጋል/ መታገስን ይፈልጋል ፡፡ ቁጥር (2-28) በግብፅ ላይ ያለዉን ፍርድ እና ናቡከደነፆርን በፈርዖን ኒካዑ የሚደርሱበትን በመድረስ ይጀምራሉ ፡፡ ዋይርስቤ “ ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት በመጊዶ ፈርዖን ኒካዑ ይሁዳን በማሸነፍ ንጉስ ኢዮስያስን ገደለው (2ዜና 35፡ 20-27) ነገር ግን ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት በኢዮአቄም አራት አመታት ዉስጥ በታላቁ በከርከሚሽ ናቡከደነፆር ኒካዑን አሸነፈው ፤ ያ ሽንፈትም የግብፅን ኃያልነት በመስበር በምስራቅ አጠገብ ባቢሎንን ኃያል እንዳደረጋት “ ይናገራል ፡፡ ከርከሚሽ የግብፃዊያንን መዉደቅ አምጥቷል ፤ ባቢሎናዊያን በመላዉ አካባቢ ኃያላን ነበሩ ፤ ዋይርስቤ ይህንን “ የግብፃዊያን የሚያሳፍር ሽንፈት “ በማለት ገልፆታል ፡፡ ዉጊያዉ በወንዝ አጠገብ ተካሄደ ፡፡
ግብፃዊያን በትንሽ ጋሻ እና በትልቅ ጋሻ ለዉጊያ የተዘጋጁ ነበሩ ፤ ለዉጊያ በፈረሶች እና በተዘጋጁ በምሽጎች የተዘጋጁ ነበሩ ነገር ግን በሽብርም ሸሹ ፡፡ ባቢሎናዊያን በግብፃዊያን ላይ የበላይነትን ያዙ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የግብፃዊያን ጠንካራ ሰራዊት ወዲያዉኑ በኃያላኖቹ በባቢሎናዊያን የተበለጠ ነበር ፤ በሁሉም ዙሪያ…ፈሩ፡ ይህ ገለፃ በኤር (20፡ 3, 4 እና በኤር (20፡ 10) ለኤርምያስ አሳዳጆች ለጳስኮር የተሰጠዉ ስም እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡
ኤርምያስ (46፡ 8-2)፡ ለመዋጋት ግብፅ ተዘጋጅታ ቢሆንም እንኳን (ቁጥር 8) ዋይርስቤ “ ያ ቀን የሁሉን ቻዩ አምላክ የእግዚአብሄር ይሆናል (ቁጥር 10) ፤ እግዚአብሄር ግብፅን እንደ መስዋዕት ያቀረበበት ቅዱስ ጦርነት ነበር (ቁጥር 10) ፤ የግብፃዊያን ቁስል የማይድን እና እፍረቷም የማይቀር እንደ ነበር (ቁጥር 11-12) “ ይገልፃል ፡፡
ለምን ቁጣዉ እና ፍርዱን ለማትኮር/ለመመልከት ጥያቄዎች ናቸው ፤ ምናልባትም አንዱ የግብፅ የመሸነፍ ምክንያት የኢዮስያስ ሞት ይሆናል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እዚህ ላይ የጌታ ቀን ለኢዮስያስ ሞት ግብፅ የተቀጣችበት እንደ በቀል ቀን የተገለፀ ነው ፤ በሰይፍ የመበላት ስዕል በ2፡ 30 ላይ የሚገኝ ነው ፤ የግብፃዊያን መሸነፍ እንደ መስዋዕት ድግስ የተሳለ ነው ፤ ኃጢዓት ለሰራዉ ይሁዳ ምንም የፈዉስ ማስታገሻ ስላልነበር አሁን ግብፅ ከልብ በመቁሰል ወደ ሞቷ እንደወደቀች “ ይናገራል ፡፡
ኤርምያስ (46፡ 13)፡ ኤርምያስ እየተናገረ በነበረበት ጊዜ ይህ እስካሁን የሆነ አልነበረም ፡፡ በቁጥር 13 ኤርምያስ ስለሚሆነው ወረራ ያወራል ፤ እስከዚህ ጥቅስ/ቁጥር ድረስ በትክክል ግብፅን ለማሸነፍ ማን እንደሚመጣ አልተናገረም ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ በቁጥር 13 ባቢሎናዊያንን ግብፅን እንደሚይዙ ያስቀምጣቸዋል ፤ ኤርምያስ ስለዚህ ክስተት በዝርዝር ከኤርምያስ ጋር እግዚአብሄር ብቻ ሊነጋገር እንደሚችል ግልፅ አድርጎ ነበር ፡፡
ኤርምያስ (46፡ 14)፡ በቁጥር 14 እና በሚከተሉት ኤርምያስ ባቢሎናዊያን እንዴት ግብፃዊያንን እንደሚያጠፏቸው ይገልፃል ፡፡ ዋይርስቤ “ የባቢሎናዊያን ወታደሮች ፈርዖን ኒካዑን ጉረኛ ብለዉ እንደ ጠሩት “ ይገልፃል ፡፡
ኤርምያስ (46፡ 15-27)፡ የግብፃዊያን ከተማ ሜምፎስ በኤርምያስ ትንቢት ተነግሮ እንደ ነበረው ሙሉ በሙሉ ትጠፋለች ፡፡ ግብፅ እንደሚጠፋ የደለበ ጥጃ ጋር የተወዳደረች ነበረች ፡፡ ዋይርስቤ “ ኤርምያስ የተጠቀመዉ ስዕላዊ መልክ ላይ ስለመመልከት ፤ ግብፅ ልክ እንደ አንድ ጊደር እንደነበረች (ቁጥር 20) ፤ በፈርዖን ሰራዊት ዉስጥ የተቀጠሩት ሰራተኞች እንደ ደለበ ወይፈኖች የታተሙ ነበሩ (ቁጥር 21 )፣ የግብፃዊያን ሰራዊትም እንደ እባቦች ጩኸት በመሸሽ (ቁጥር 22) ዛፎች በእንጨት ቆራጭ ፊት እንደሚሆኑት በባቢሎናዊያን ፊት ይወድቃል (ቁጥር 23) “ በማለት ይፅፋል ፡፡
በተጨማሪም ዋይርስቤ ባቢሎናዊያንን “ ወራሪዉ ሰራዊት ማስወገድ እንደ ማይቻል እንደ አንበጣ መንጋ እንደ ነበር (ቁጥር 23) “ በመናገር ገልፆአቸዋል ፡፡ ቁጥር 26 ግብፃዊያን ለባቢሎናዊያን ተላልፈዉ እንደሚሰጡ ነገር ግን እግዚአብሄር ግብፃዊያንን እንደማያጠፋቸዉ ይናገራል ፡፡ አሁንም እግዚአብሄር ግብፅን እንደ ቀድሞው መልሶ እንደሚያቋቁማት ጥቂት ተስፋ ነበር ፤ በቁጥር 25-26 እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ ሁሉም በተናገሩ እና በፈፀሙት ጊዜ አሁንም ወደ እግዚአብሄር ለመመለስ ተስፋ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
በኢሳይያስ ብዙ ሀገራት እግዚአብሄር የወደፊታቸዉን እንደሚሰጣቸው የተለዩ ናቸው ፤ ከእነዚህ አገራት ዉስጥ አንዷ ግብፅ ነበረች ፡፡ ፍርድ በግብፅ ላይ እየመጣ ነበር ፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሄር እቅድ ትልቅ መልክ ዉስጥ እግዚአብሄርን ወደ ማምለክ ይመለሳሉ ፡፡ አሁንም እግዚአብሄር መፍትሄን ሰጥቷቸዋል ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 938.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 136.
Wiersbe, p. 136.
Nelson’s Commentary, p. 939.
Wiersbe, p. 136.
Nelson’s Commentary, p. 93.
Wiersbe, p. 136.
Wiersbe, p. 136.
Wiersbe, p. 136.
ጥያቄዎች
-
በኤርምያስ 46 ስለተወሰኑ እንግዳ ስለሆኑ ሕዝቦች ትንቢት መስጠትን ጀመረ ፤ እነዚህን ማስጠንቀቂያዎች ስለ ሕዝቡ ማንበብ ስትጀምሩ በአሁኑ ዘመን ባሉት ሕዝቦች ላይ ተመሳሳይ ነገርን ታያላችሁ ? እግዚአብሄር በሕዝቦች ላይ በሚያመጣው ፍርዱ ምንም እንኳን ያንን ሕዝብ ከሚያስተዳድሩት ክፉ ፖለቲካ መሪዎች የተነሳ ፍርድ የሚደርስባቸዉ ብዙ ንፁህ ሕዝቦች ቢኖሩም ትክክለኛ እና ፍትሐዊ እንደሆነ ታምናላችሁ ?
-
በመጊዶ ጦርነት ላይ ማንኛው “ መልካም “ ንጉስ ተገደለ (2ነገ 23፡ 29) ? ቆይቶስ በንጉስ ናቡከደነፆር ላይ ምን ሆነ/ተፈጠረ (ዳን 4፡ 33) ? ከዚህ የተነሳ ናቡከደነፆር ምን አደረገ (ዳን 4፡ 34) ? ይህ ምን ያስተምራችኋል ?
-
በኤርምያስ 46 ከእነዚህ አስከፊ ፍርዶች ማን እንዲሚያድን እግዚአብሄር ተስፋን ሰጠ ?
-
በኤርምያስ 47 ኤርምያስ እንደ ገና በፍልስጤም ላይ ተናገረ ፤ ሌሎች ነቢያት ስለዚህ ሕዝብ ምን ተናገሩ ? (ኢሳ 14፡ 28-32, ሕዝ 25፡ 15-17, አሞ 1፡ 6-8, ሶፎ 2፡ 4-7)
-
በእነዚያም ቀናት ሕዝቡ እግዚአብሄር ለኤርምያስ የተናገረዉን ማስጠንቀቂያዎችን ሰምተዉቷል ? አሁንም እግዚአብሄር ሕዝቡን ስለሚመጣ ፍርድ እንደሚያስጠነቅቅ ታምናላችሁ ? አዎ ከሆነ እንዴት እና በማን በኩል ?
-
በኤርምያስ (46-47) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 46:25–26
“The LORD of Hosts, the God of Israel, says: ‘I am about to punish Amon, god of Thebes, along with Pharaoh, Egypt, her gods, and her kings—Pharaoh and those trusting in him. I will hand them over to those who want to take their lives—to Nebuchadnezzar king of Babylon and his officers. But after this, it will be inhabited again as in ancient times.’ This is the LORD’s declaration.”
ግብጻዊያን ኃጢአትን ሰሩ ፊታቸውንም ከእግዚአብሔር መለሱ ስለዚህም እግዚአብሔር በባቢሎን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው ፡፡ ነገር ግን ከዚህ የጦርነትና የቅጣት ጊዜ በኋላ እንኳ እግዚአብሔር በኤርምያስ በኩል ህዝቡ እንደገና ምድራቸውን እንደሚወርሱ ተናገረ ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር በእስራኤል ህዝብ ላይ ቅጣትንና ተግሳጽን ያመጣል ፤ ወደ እርሱ ከተመለሱ ግን ያድናቸዋል ፡፡
እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ቀን ይምራል ፣ ጸጋና ምህረትንም ይሰጣል ፡፡ እግዚአብሔር ያለምንም ምክንያት ይወዳችኋል ፣ ይህም ማለት ፍቅሩ እናንተ በምታደርጉት ነገር ወይም በእናንተ ማንነት ላይ የተመሰረተ አይደለም ማለት ነው ፡፡ በቃ እግዚአብሔር በኃይል አጥብቆ ይወዳችኋል ፡፡ ኃጢአትን ብትሰሩ ፣ ከእርሱ ብትርቁ ወይም ብትቆሽሹ እንኳ ፣ እርሱ ፈጽሞ አይተዋችሁም ፡፡ እግዚአብሔር ንስሀ እስክትገቡና ከክፉ መንገዳችሁ እስክትመለሱ ይጠብቃችኋል ፡፡ ስለዚህም ራሳችሁን በማዋረድ ወደ እርሱ ተመለሱ ፡፡ ዛሬ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ለሚያስፈልገው ለአንድ ሰው ጸልዩ ፡፡ እርሱ የተስፋ አምላክ ፣ የፈውስ አምላክ ደግሞም የታምራት አምላክ ነው ፡፡ ዛሬ ታምራት እንድሆን ጸልዩ ፡፡ እርሱ ሰዎች ራሳቸውን ካዋረዱና ወደ እርሱ ከተመለሱ ብቻ የሚያድን አምላክ ነው ፡፡
“ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ እነሆ ፥ የኖእ አሞንን ፥ ፈርዖንንም ፥ ግብጽንም ፥ አማልክቶችዋንና ነገሥታቶችዋንም ፥ ፈርዖንና በእርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ ፤ ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ ፥ በባቢሎንም ንጉሥ በናቡክደነፆር እጅ ፥ በባሪያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ ፤ ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች ፥ ይላል እግዚአብሔር ፦ “
- ኤርምያስ 46፡25-26
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ዜና 7:14–15 — “ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ። አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ ። “
ኤርምያስ 46:28 — “ አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፤ አንተንም ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም ፤ በመጠን እቀጣሃለሁ ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም ። “
ሉቃስ 17:3-4 — “ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ፦ ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው ፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው ። በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ ፦ ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ፥ ይቅር በለው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።