Major Prophets Jeremiah

Returning To Egypt

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 43-45 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 618 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኤርምያስ መፅኀፍት ታሪክ እግዚአብሄር ቀድሞ ምን እንደሰራ እና አሁንም እንዴት መስራት እንደሚችል ሀሳቡን ያሳየናል ፡፡ በኤርምያስ 42 ዮሐናን ኤርምያስን ሕዝቡ ተመልሰዉ ወደ ግብፅ ስለመሄዳቸዉ ቃል እንደሚያስፈልጋቸዉ ነገረው ፤ ኤርምያስን እግዚአብሄር የነገራቸዉ ማንኛዉም ነገር የሚያደርጉት ነገር እንደ ሆነ ነገረው ፡፡ ለእነርሱ የኤርምያስ ቃል እንዳይሄዱ እና ይልቁንም በነበሩበት እንዲቀመጡ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ዮሐናን እንደሚጠብቃቸዉ እና እንደሚከላከልላቸው እና አሁን እንዳሉት እንደሚያደርጋቸዉ ቃል ገብቶለታል ፤ ኤርምያስ የቀርቱን ምዕራፎች አይሁዶች ወደ ግብፅ ከተመለሱ ምን እንደሚሆንባቸዉ በመግለፅ አሳለፈ ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ 43፡ መሪዎቹ ኤርምያስን በዉሸት ከሰሱት ፡፡ ሕዝቡ ወደ ግብፅ ተመልሶ ስለሚሄድ እያወሩ ነበር ፤ ከኤርምያስ ይልቅ ዮሐናን በመከተል ሕዝቡ እግዚአብሄርን ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ሄዱ ፡፡ ሕዝቡ እግዚአብሄር በግብፅ ላይም ይመጣ እንደ ነበርና በፈርዖን ቤተ መንግስት መግቢያ አጠገብ ኤርምያስ በመቀመጥ የመቃብር ድንጋዮችን በማስቀመጥ (ቁጥር 10) የናቡከደነፆር መንግስት መሰረት ይሆን እንደ ነበር አላስተዋሉም ነበር ፡፡ ድንጋዮቹም በሁሉም ሕዝቦች ፊት የተቀመጡ ስለነበሩ እነዚህ የአይሁድ ሕዝቦች ታዛዥነት ቅሬታዎች ይሆናሉ ፡፡

ኤርምያስ (44፡ 1-10)፡ ይህ ምዕራፍ ለምዕራፍ 42 እና 43 አንድ መልስ ነበር ፡፡ የኤርምያስ ቃል በቀጥታ በተለይም ለይሁዳ ነበር ፤ ሌሎች አማልዕክቶችን ከማምለካቸዉ እና ከማገልገላቸው በሕዝቡ ክፉነት የተነሳ የተቀጡ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄርን በማበሳጨት የእግዚአብሄርን ቁጣ አነሳሱ ፡፡

የሰራዊት አምላክ የይሁዳን ሰዎች በቀጣ ጊዜ እቅዱን እየተከላከለ ነበር ፤ ቅጣቱ ስለ እስራኤል ነበር ፡፡ በራሳቸዉ ምድር ላይ እግዚአብሄርን አልታዘዙም በባዕድ ምድርም በምርኮ በተያዙ ጊዜም አለመታዘዛቸዉን ቀጠሉበት ፤ ሕዝቡ ታዛዥች አልነበሩም፣ ፍርኃትን አላሳዩም እንዲሁም እግዚአብሄር ሰጥቷቸዉ የነበረዉን ትዕዛዝ እና ስርዓት አለመከተልን መረጡ ፡፡

ዘጸዓት 20 እግዚአብሄር ሕዝቡን ከግብፅ እንዳወጣቸዉ ሕዝቡም ደግሞ እርሱን ብቻ ያመልኩ እንደ ነበር ይናገራል፡፡ በአምልኮ ለሌሎች አማልዕክቶች እጣንን በማቃጠል ለአማልዕክቶቾ ታማኝነታቸዉን ሰጥተዋል ፤ የመጀመሪያዉ ትዕዛዝ እግዚአብሄር ለሙሴ እና ለእስራኤላዊያን የሰጠው በእርሱ ፊት ሌሎች አማልዕክቶች እንዳይኖሩ ነበር ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ ይህን ትዕዛዝ መጣሱን ቀጠለ ፡፡

ኤርምያስ (44፡ 11-17)፡ እግዚአብሄር በግብፅ እያሉም ሌሎች አማልክቶችን ማምለካቸዉን የሚቀጥሉ ከሆነ ሕዝቡን መቅጣቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሄር ማንም ሳይቀጣ እንደማይቀር ቃል ገባ ፤ በሰይፍ፣ በርኃብ እና በመቅሰፍቶች ይቀጣሉ ፡፡ እግዚአብሄር ቀድሞ እንዳደረገው ሕዝቡን ይቀጣል ፤ ከኮበለሉት ከጥቂቶች በስተቀር ከቅሬታዎቹ ዉስጥ ማንም አይተርፍም ፡፡

ኤርምያስ (44፡ 18-20)፡ ሕዝቡን የመቅጣት አላማው በመጨረሻ በንፅህና እግዚአብሄርን ማምለክ ነበር ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ተመልሰዉ ኤርምያስን ለመናገር በአንድ ላይ ተሰበሰቡ ፤ ከእርሱ የሆነዉን ቃልም እንደማይሰሙ ነገሩት፡፡ ለሰማይያ ንግስት ዕጣን ማቃጠላችንን እንቀጥላለን አሉት ምክንያቱም ቀድሞ እርሷ እያመለኩ እንደ ነበር ነገሮች በመልካም ስለሄዱ እና ለሚበሉት ምግብ ስለ ነበራቸው ፡፡ የእግዚአብሄርን ሕግ እና ቃል አለመቀበልን መረጡ ፡፡ ሌሎች አማልዕክቶችን ለማምለክ ምክንያታቸው በትክክል ከእግዚአብሄር እጅ የነበረዉን በረከት ቀድሞ በኑሮአቸዉ ከገጠማቸዉ በረከት የተነሳ ነበር ፡፡

በነቢያት በኩል እግዚአብሄር በተደጋጋሚ ሕዝቡን እግዚአብሄርን የማያስደስት ነገር እንዳያደርጉ ነግሯቸዋል ፡፡ በትዉልዱ ለእግዚአብሄር ቃል ያለዉ ትኩረት ማጣት ወደ ዚህ ነገር መርቷቸዉ ነበር ፡፡ እዉነታቸው ለሰማዩያ ንግስት ዕጣን ማቃጠላቸዉን ካቆሙ ጊዜያቱ አስቸጋሪዎች እንደሚሆኑ ነበር ፡፡

ሴቶቹ በመጀመሪያነት የሰማይያን ንግስት ወደ ማምለክ መርተዉ የነበሩ ይመስላሉ ነገር ግን በባሎቻቸዉ እዉቀት አደረጉ ፡፡ የይሁዳ ሰዎች በምርኮ በነበሩበት ጊዜ ከተለያዩ ባህሎች የሆኑ ሰዎችን አግብተዉ ነበር ፤ እነዚህ ግለሰቦችም ወደ ጋብቻዉ ዉስጥ የራሳቸዉን አማልዕክቶች በማምጣት ማምለካቸዉን በመቀጠል ለእነዚህ የኃሸት አማልዕክቶች ዕጣናቸዉን ያቃጥላሉ ፡፡

ኤርምያስ (44፡ 21-30)፡ ኤርምያስ ሕዝቡን ባለፉት ጊዜያት እግዚአብሄር አባቶቻቸዉን እና አያቶቻቸዉን ባርኳቸዉ እንደ ነበር እንዲያስታዉሱ ነገራቸው ፡፡ እግዚአብሄር በራሳቸዉ ምድር ሕዝቡን ባርኳቸዉ ነበር ነገር ግን ሌሎች አማልዕክቶችን ማምለክን መረጡ ፤ ሕዝቡ በእርሱ ሕግ፣ በስርዓቱ እንዲሁም ደግሞ በምስክርነቱ አልተመላለሱም ነበር ፡፡ ሕዝቡ ኃሰተኛ አማልዕክቶችን ማምለክ ምርጫዉ አድርጎ ስለ ነበር አይሁዶች በግብፅ ምድር ይጠፋሉ ፤ ጥቂት ቅሬቶች ብቻ በማምለጥ ወደ ራሳቸዉ ምድር ይመለሳሉ ፡፡

እግዚአብሄር በግብፅ ምድር እንደሚቀጣቸዉ ቃል ገባ ፡፡ በምዕራፍ 43 ተጠቅሱት ድንጋዮች ይህ የመጨረሻዉ እንደ ነበር ለእነርሱ እንደ ቅሬታዎች የሚያገለግሉ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር አይሁዶች እንደሚጠነቅቅላቸዉ የሚያስቡትን ፈርዖን ሖፍራን ሴዴቅያስ ለናቡከነደፆር ተላልፎ እንደ ተሰጠው ለጠላቶቹ አሳልፎ እንደሚሰጠው ነገራቸው ፡፡

መደምደሚያ

በአሁኑም ጊዜ ኤርምያስ ከተናገረው ቃል ለእኛ እንዴት እንደሚናገረን መጠየቅ አለብን ፡፡ በእነዚህ ትንቢቶች ላይ ማጥናት እና ከኑሮአችን ጋር እንዴት እንደሚገናኙ አለመመልከት ቀላል ሊሆን ይችላል ፡፡ ምናልባትም ለእኛ ሕጉን፣ ስርዓቱን እና ምስክርነቱን እየተከተልን እንደሆነ እርግጠኛ የሚያደርገንን መልዕክት በሚይዝ ጊዜ አኗኗራችንን እንደ እግዚአብሄር በረከት መቀበል እንዴት ቀላል ነው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በኤርምያስ 43 ስለ እግዚአብሄር ኤርምያስ በተናገረዉ ነገር ያልተስማማዉ እና የተከራከረው ማነው ? ኤር (43፡ 2) ከዘፍጥረት ምን ያስታዉሳችኋል ? (ዘፍ 3፡ 1)
  2. ሕዝቡ በኤር (42፡ 5) የገቡትን ቃል ጠብቀዋል ? እንዴት እግዚአብሄርን አላከበሩትም ? የድርጊታቸዉ ዉጤት ምን ምን ነበሩ ?
  3. ሕዝቡ በእነርሱ ላይ ስለመጣዉ የእግዚአብሄር ቃል እና ፍርድ በኤርምያስ 44 እንዴት ምላሽ ሰጡ ? ሕዝቡ ብልፅግናቸዉ ከየት እየመጣ እንደ ነበር ያስቡ ነበር ?
  4. ሕዝቡ ለእነርሱ ነገሮች እየከፉ እንደ ሆነ ማስተዋል መቼ ጀመሩ ? ይህ ትክክለኛ ግምት/ሀሳብ ነበር (ምሳ 3፡ 5-7, ያዕ 1፡ 17) ? ነገሮች ሁል ጊዜ በእናንተ መንገድ በማይሄዱ ጊዜ ደስታን እንዴት ማግኘት ትችላላችሁ ? (ዮሐ 15፡ 11)
  5. በኤርምያስ 45 ኤርምያስ ወደ ባሮክ ያመጣዉ ግሰፃ ምን ነበር ? ማበረታቻዉስ ምን ነበር ? (ማቴ 6፡ 33)
  6. በኤርምያስ (43-45) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 44:4–5

“So I sent you all My servants the prophets time and time again, saying: Don’t do this detestable thing that I hate. But they did not listen or pay attention; they did not turn from their evil or stop burning incense to other gods.”

እግዚአብሔር የአይሁድን ህዝብ ከጣዖት አምላኪነት ለመመለስ ደጋግሞ ሞከረ ነገር ግን እነርሱ እምቢ አሉ ፡፡ በትዕቢት ተሞልተው ስለነበር ለእግዚአብሔር ትኩረት አልሰጡም ፡፡ እነርሱ ለሌሎች አማልክት የዕጣንና የመጠጥ መስዋትን ማቅረባቸውን ቀጠሉ ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር እጁን ከይሁዳ ላይ አነሳ ፣ ለጥፋት ለክፋትም ተጋባቸው ፡፡

ኢየሱስን የህይወታችሁ ጌታ እና አዳኝ አድርጋችሁ ከተቀበላችሁ ፣ እርሱን ለማዳመጥና ለእርሱ ለመታዘዝ ጊዜ ስጡ ፡፡ በትህትና ተመላለሱ የምትፈልጉትንም ለእርሱ አሳውቁ ፡፡ እግዚአብሔር ለእናንተ በቃሉ ፣ በሌሎች ሰዎች ፣ በህልምና በመንፈስ ቅዱስ ወደ ሚያሳያችሁ መንገዶች ተመልከቱ ፡፡ ያኔም እርሱ ከእናንተ ጋር እንደሆነ ማየት ትጀምራላችሁ ፡፡ በህይወታችሁም ውስጥ ያሉ እርምጃዎችን መውሰድ እንድትቀጥሉ ያበረታችኋል ወይም ደግሞ ከጣዖታት ፣ ከሀሰተኛ አማልክት ፣ ከትዕቢት ወይም ለእግዚአብሔር ባላችሁ ፍቅር ውስጥ ጣልቃ ከገቡ ነገሮች ትመለሱ ዘንድ ያስጠነቅቃችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ልባችሁን እንድመረምር ጠይቁ ፡፡ እንድሁም ቀስ ብላችሁ እግዚአብሔርን ፈልጉ ፡፡ በፍጹም ልባችሁም እርሱን ስትፈልጉ ያኔ እርሱ ይገኝላችኋል ፡፡ እስኪ አስቡ ምን ያህል ጊዜ የዚህ ዓለም ነገሮችን ትፈልጋላችሁ ደግሞም እንደገና እግዚአብሔርንስ ምን ያህል ትፈልጉታላችሁ ? እስኪ ዛሬ ለሰላሳ ደቂቃ ስልካችሁን መነካካት ተውና ይህን ሰዓት በእግዚአብሔር ቃል ወይም በጸሎት አሳልፉት ፡፡ የህይወታችሁ ጌታና አምላክ የሆነውን እርሱን ችላ አትበሉ ፣ አትተው ፡፡

“ በማለዳም ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ሰደድሁባችሁና ፦ እንደዚህ እንደ ጠላሁት ያለ ርኩስ ነገር አታድርጉ አልኋችሁ ። ነገር ግን አልሰሙም ከክፋታቸውም ተመልሰው ለሌሎች አማልክት እንዳያጥኑ ጆሮአቸውን አላዘነበሉም ። “

  • ኤርምያስ 44፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 119:10 — “ በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ ። “

ኤርምያስ 44:10 — “ እስከ ዛሬ ድረስ አልተዋረዱም አልፈሩምም ፥ በእናንተና በአባቶቻችሁም ፊት ባኖርሁት ሕጌና ሥርዓቴ አልሄዱም ። “

ኤርምያስ 44:26b–28 — “ “ ሕያው እግዚአብሔርን ! ” ፡፡ እነሆ ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ ፤ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ ። ከሰይፍም የሚያመልጡ ጥቂት ሰዎች ሆነው ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ ፤ ሊቀመጡም ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ ። “