Hypocritically Seeking God's Will
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 40-42 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዛሬዉ የመፅሀፍ ፅሁፍ የሚያምር አዝናኝ እና አስተማሪ ነው ፡፡ ለኤርምያስ መፅሀፍት ሐረጉ/ቃሉ አዲስ ኪዳን ነው ፡፡ ኤርምያስ በጣም የሚያነሳሳ መፅኀፍት አይደለም ነገር ግን ስለ ሚመጣዉ ጻድቅ ቁጥቋጦ በማመልከት ተስፋን ይሰጣል ፤ ኤር (31፡ 31) ይህን ተስፋ ያጠቃልለዋል፡ “ እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል እግዚአብሄር “ ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (40፡ 1-16)፡ በመጨረሻም ኤርምያስ በራማ በጠባቂዎቹ አለቃ ተለቀቀ ፡፡ ኤርምያስ ከኢየሩሳሌም እና ከይሁዳ ለባቢሎን ተላልፈዉ ከተሰጡት ሁሉም ምርኮኞች ጋር በሰንሰለት የታሰረ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ አዛዡም እግዚአብሄር በኤርምያስ በኩል ተናግሯቸዉ እንደ ነበርና ሕዝቡም እንዳልሰማ ያውቃል (ቁጥር 2-3) ፤ አዛዡም ኤርምያስን ነፃነትን በመስጠት በእርሱ ጥበቃ ስር ወደ ባቢሎን እንዲመጣ ወይም ወደ ቤቱ እንዲመለስ እድሎችን አቀረበለት (ቁጥር 4) ፡፡ በመቀጠልም አዛዡ ኤርምያስን በባቢሎን ንጉስ በይሁዳ ላይ እንደ ጠባቂ በመሾም ኤርምያስን ምግብ እና ስጦታ ሰጥቶት ወደ ነበረው ወደ ጎዶልያስ እንዲመለስ ነገረው (ቁጥር 5) ፡፡ ኤርምያስም አዛዡ እንዲያደርግ የነገረዉን አደረገ (ቁጥር 6) ፡፡
የባቢሎናዊያን ሰራዊት አዛዦች የጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እና ከሕዝቡ መካከል ድሆች በመሆናቸዉ ወደ እዛዉ ምድሪቱ ዉስጥ ቀርተዉ በነበሩት ላይ እንደተሸመ በሰሙ ጊዜ ጎዶልያስን ለማየት ከእነርሱ ጋር ሰራዊታቸዉን ይዘዉ መጡ (ቁጥር 7-8) ፡፡ የመጡት ዝርዝር በቁጥር (8-13) ላይ ናቸው ፡፡ ዮሐናን ጎዶልያስን (ቁጥር 13) የአሞናዊዉ ንጉስ እንዲገድለዉ እስማኤልን እንደላከበት አስጠነቀቀው ፤ ጎዶልያስም አላመነውም (ቁጥር 14) ፡፡ በመቀጠልም ዮሐናን በመሄድ በድብቅ እስማኤልን እንዲገድል ያ ከሆነ በጎዶልያስ ላይ ስለሆነ ማስፈራራትም ማንም እንደማያዉቅ አቀረበ (ቁጥር 15) ፤ ነገር ግን ጎዶልያስ ዮሐናን በእስማኤል ላይ በዉሸት ከሰሰው (ቁጥር 16) ፡፡
ኤርምያስ (41፡ 1-10)፡ ምዕራፍ 41 ቀጥሎ ምን እንደሚሆን የሚያምር ስዕል ይገኝበታል ፤ ዮሐናን ጎዶልያስን አስጠንቅቆት ስለ ነበረው እስማኤል ከአስር ሰዎች ጋር ምጽጳ በመምጣት ከጎዶልያስ ጋር ምግብ በልተዉ ነበር ፤ ከግብዣዉም በኋላ እስማኤል ለባቢሎን እንዲሁም ለሌሎች አይሁዶች እና በዚያ ለነበሩት ከለዳዊያን ወታደሮች እንደ ንጉስ የተሸመዉን ጎዶልያስን ገደለው (ቁጥር 1-3) ፡፡ በቀጣዩም ቀን በኃዘን ራሳቸዉን አዘጋጅተዉ የነበሩት 80 ሰዎች ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ከቁርባናቸዉ ጋር ደረሱ (ቁጥር 4-5) ፤ እስማኤልም በበሩ ላይ አገኛቸው በማልቀስም ወደ ጎዶልያስም እንደሚወስዳቸዉም ነገራቸው (ቁጥር 6) ፤ ነገር ግን ወደ ከተማዋ በገቡ ጊዜ እስማኤል እና የእርሱ ሰዎች ከ80ዎቹ 70 ዎቹን በማረድ ወደ አንድ ጉድጓድ ዉስጥ ወረወሯቸው (ቁጥር 7) ፡፡
ከሰዎቹ ዉስጥ አስሮቹ በእርሻቸዉ ዉስጥ የተደበቀ ንብረት (ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና ማር) እንደ ነበራቸዉ በመናገር እስማኤልን ከመግደል አስቆሙት (ቁጥር 8) ፡፡ ጉድጓዱ በጣም ትልቅ ስለ ነበር እስማኤል በሞተ አካል ሞላው (ቁጥር 9) ፤ በመቀጠልም እስማኤል “ የንጉሱን ሴት ልጅ በመጨመር ሁሉንም የምጽጳ ሰዎች ቅሬታዎችን ሁሉ “ ወደ ምርኮ በመዉሰድ ከእነርሱ ጋር ወደ አሞናዊያን ሄደ (ቁጥር 10) ፡፡
ኤርምያስ (41፡ 11-18)፡ ዮሐናን እና የሰራዊቱ አዛዦች የእስማኤል ድርጊት በመስማት ሊዋጉት ሄዱ ፤ በገባዖንም ዉኃ አጠገብ አገኙት (ቁጥር 11-12) ፤ ከእስማኤል ጋር የነበሩት ምርኮኞች የሚጠጉትን ሰዎች ባዩ ጊዜ በመደሰት ዮሐናን ተቀላቀሉት (ቁጥር 13-14) ፡፡ እስማኤል ከስምንንቱ ሰዎች ጋር አመለጠ (ቁጥር 15) ፤ ዮሐናን ቅሬታዎቹን - ወንዶቹን፣ ወታደሮቹን፣ ሴቶቹን፣ ልጆቹን እና የጭፍራ አለቆቹን ወሰደ (ቁጥር 16) ፡፡
ኤርምያስ (42፡ 1-6)፡ ዮሐናን፣ የሰራዊቱ አዛዦች እና በገባዖን ነፃ ወጥተዉ የነበሩት ሰዎች ሁሉም ወደ ኤርምያስ በመምጣት ቀጥለዉ ምን እንዲያደርጉ እግዚአብሄር የሚፈልገዉን ለማድረግ በመፈለግ ጠየቁት (ቁጥር 1-3) ፡፡ ይህ ተገቢ የሆነ የፀሎት ጥያቄ ይመስላል ነገር ግን ቁጥር 19 በሌላ መልኩ ያሳያል ፡፡ ቁጥር (4-6) ለመፀለይ የኤርምያስን መስማማት እና የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለማክበር የሕዝቡን መሰጠት ይገልፃል ፤ ይሁን እንጂ ዮሐንና ቀድሞ ምን ያደርጉ እንደ ነበርና ወዴት እንደሚሄዱ ወስኖ ነበር ፡፡
ኤርምያስ (42፡ 7-22)፡ ከአስር የፀሎት ቀን በኋላ ኤርምያስ በእግዚአብሄር መልስ ተመልሶ መጣ - በዚህ ምድር እንዲቆዩና መልሶ እንደሚገነባቸዉ እና እንደሚጠብቃቸዉ በሚል መልስ (ቁጥር 7-12) ፤ እርሱን መታዘዝ በማቆም ወደ ግብፅ የሚሄዱ ከሆነ ይህ ቅሬት “ በሰይፍ፣ በርኃብ እና በመቅሰፍት ይሞታሉ ፤ በእነርሱ ላይ ከማመጣዉ ጥፋት ማንም አያመልጥም ወይም አይተርፍም “ (ቁጥር 13-18) ፡፡ ዋይርስቤ የእግዚአብሄርን መልስ ሰዎስት ክፍሎች ይሸፍናል፡
- የእግዚአብሄር ተስፋ ለዮሐናን እና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሁሉም ሕዝብ በምድሪቱ ከተቀመጡ ከባቢሎን በመጠበቅ እንደሚሰጣቸው፣ ምድሪቱን መልሶ እንደሚገነባ፣ እህሉን መልሶ እንደሚተክል እና ጥፋት እንደማይመጣባቸው ተስፋን ይገባል (ቁጥር 7-12) ፤ ማክአርቱር “ ተፀፅቻለሁ “ (ቁጥር 10) የሚለዉን ቃል ይገልፃል፡ “ በዚህ እግዚአብሄር አዲስ ጥፋትን ካልጨመራችሁ ባሰቃየኋችሁ ረክቻለሁ/በቅቶኛል ማለቱ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡
ለእነርሱ ሁሉም የእግዚአብሄር ማስጠንቀቂያ ወደ ግብፅ በመሄድ አሰቃቂ ሞት እንዳይሞቱ ነበር (ቁጥር 13-18) ፡፡
የሚያታልል ልባቸዉን የእግዚአብሄር መፈለግ (ቁጥር 19-22) ፤ ዋይርስቤ ኤርምያስ “ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ እንደሚታዘዙ ቃል በገቡ ጊዜ እርሱን ለማታለል ሞክረዉ እንደ ነበር በአደባባይ ተናገረ ፤ በትክክል የእርሱን ፀሎት ወይም የእግዚአብሄርን እቅድ አልፈለጉም ቀድመዉ ለማድረግ ወስነዉ የነበሩትን እንዲያጸድቅላቸዉ ፈለጉ እንጂ “ በማለት ይገልፃል ፤ ይህን ማክአርቱር በኃይለኛው፡ “ ቀድመዉ በግብፅ ለመሆን የወሰኑት ግብዞች “ እንደ ነበሩ አስቀምጧል ፡፡
ኤርምያስ ያደረሰዉን የእግዚአብሄር መልዕክት ሕዝቡ እንደማይቀበሉት ለማወቅ መንፈሳዊ የመለየት ፀጋ ነበረው ፤ ዋይርስቤ “ ይህ በእነርሱ ድርሻ ላይ እቅዳቸዉን የሚያደርጉ ከሆነ በግብፅ እንደሚሞቱ አጣዳፊ ዉሳኔ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ ይህን ፅሁፍ “ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ስንፈልግ ከአንገት በላይ/በዉሸት እንዳይሆን እንደሚያስጠነቅቀን “ ያመለክታል ፡፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄርን “ ዮሐናን ቀድሞ እንዳደረገው “ ስናደርግ ብቻ እንዲባርከን በመጥራት ይጠይቃል ፤ ይዞ የሚመጣዉ ነገር ምንድን ነው ሃሳቤን፣ አስተሳሰቤን እና ፍቃዴን እግዚአብሄር እንዲባርከኝ እፈልጋለሁ የማይሆን ከሆነ እንደ ምንም አደርገዋለሁ ፡፡ እግዚአብሄር በሚገባ ያንን ጨዋታ መጫወት ከፈለጋችሁ እንደምትሞቱ ልባችሁን ታምናላችሁ ይላል ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 133.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 874.
Wiersbe, p. 133.
Wiersbe, p. 133.
MacArthur, p. 874.
Wiersbe, p. 133.
Wiersbe, p. 133.
Wiersbe, p. 133.
ጥያቄዎች
-
ስለ እግዚአብሄር ከአይሁድ መሪዎች በበለጠ የዘበኞች አለቃ በምን የተረዳ ይመስላል (ኤር 40፡ 2-3) ?
-
በኤርምያስ 40 ኤርምያስ በባቢሎን ንጉስ እንክብካቤ የተደረገለት ከመሆን ይልቅ ከጎዶልያስ እና በእየሩሳሌም ከነበሩት ጋር መቀመጥን ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ ? ይህ ለሰው መልካም እረኛ ለመሆን ቅጥረኛ ላለመሆን በምን ይወሰዳል ? (ዮሐ 10፡ 12-13)
-
በኤርምያስ 40 የባቢሎን ንጉስ በይሁዳ ምድር ላይ በኃላፊነት ማንን ሾመው ? ለሕዝቡ የማለዉ መኃላዉ ምን ነበር ?
-
በኤርምያስ 40 አዛዦቹ ጎዶልያስን ስለምን አስጠነቀቁት ? ነግረዉት ስለ ነበረዉ ነገር የጎዶልያስ ምላሽ ምን ነበር ? ማስጠንቀቂያዉን ያለማመኑ ዉጤት ምን ነበር (ምሳ 11፡ 14) ? ለእናንተ የሆነዉን የሰዉ ምክር ያለከበራችሁበት ጊዜ አላችሁ ? ምክሩ መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ እንዴት አወቃችሁ ?
-
በኤርምያስ 42 አዛዦቹ ሁሉም ሕዝብ ከትንሽ እስከ ትልቅ ያደረጉት የማስተዋል ነገር ምን ነበር ? ምንም ቢሆን ሕዝቡ ምን ለማድረግ ተስማሙ ? ኤርምያስ አምኗቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ኤር 42፡ 20)
-
በኤርምያስ (40-42) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 42:21–22
“For I have told you today, but you have not obeyed the voice of the LORD your God in everything He has sent me to tell you. Now therefore, know for certain that by the sword, famine, and plague you will die in the place where you desired to go to live for a while.”
በይሁዳ የቀሩት ቅሬታዎች የእግዚአብሔርን ድምጽ ይሰሙ ዘንድ ወደ ኤርምያስ ቀረቡ ፡፡ ህዝቡም በእርግጠኝነት የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚታዘዙ ቃል ገቡ ፡፡ ከአስር ቀንም በኋላ ኤርምያስ ህዝቡ በዚያው እንድቆዩ ወደ ግብጽ ከመሸሽም እንድቆጠቡ የሚያዝ መልዕክትን ከእግዚያብሔር አመጣ ፡፡ ሆኖም ግን አሁንም እንደገና እነርሱ የእግዚአብሔርን ምሪት በመተው በራሳቸው መንገድ ተጓዙ ፡፡
ምንም እንኳ የእግዚአብሔርን ምክር አሳብ ብትጠይቁም ነገር ግን አሳባችሁን ዕቅዳችሁን አትቀይሩም ፡፡ በዕቅዳችን ውስጥ እግዚአብሔርን አካተናል ትላላችሁ ነገር ግን ልክ እርሱ ሊያስቆማችሁ ወይም አቅጣጫ ሊያስቀይራችሁ ሲሞክር ፣ አትታዘዙም ፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን እንድታከብሩ ያዛችኋል ደግሞም እርሱ ለእናንተ እቅድ አሳብ እንዳለው ይነግራችኋል አሳቡም እናንተን የሚጎዳ ሳይሆን የሚጠቅም የሚያለመልም ነው ፡፡ እግዚአብሔርን የምትሰሙ ከሆነ ፣ በመታዘዝ የሚላችሁን አድርጉ ፡፡ በአፋችሁ እግዚአብሔርን እንደምታምኑ የምትናገሩ ከሆነ ነገር ግን እርሱን በጆሯችሁ የማታዳምጡት ከሆነ ስለዚህ እናንተ በታማኝነት የምታምኑትን ነገር እየኖራችሁት አይደለም ፡፡ የእግዚአብሔርን ድምጽ ተከተሉ ፡፡ አለበለዚያ ግን በጊዜ ሂደት ውስጥ ጆሯችሁ ይደነቁራል ህይወታችሁም ወደ ጥፋት ያመራል ፡፡
“ እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ ፥ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም ። አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ ። “
- ኤርምያስ 42፡21-22
ተጨማሪ ጥቅስ
Isaiah 42:20 — “ ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትጠባበቁትም ፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል ፥ ነገር ግን አትሰሙም ። “
ኤርምያስ 42:5–6 — “ ኤርምያስንም ፦ አምላክህ እግዚአብሔር በአንተ እጅ ወደ እኛ የላከውን ነገር ሁሉ ባናደርግ ፥ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን ። የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን ፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ፥ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን አሉት ። “
2ኛ ጢሞቲዎስ 4:3–4 — “ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና ፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ ። እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።