The Fall Of Jerusalem
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 37-39 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዛረዉ የትኩረት ምዕራፋችን ኤርምያስ 39 ከመሸፈናችን በፊት በፍጥነት በኤርምያስ (37-38) ዉስጥ በፍጥነት መስራት ያስፈልገናል ፡፡ በኤርምያስ 37 “ በወቅቱ ጊዜ ላይ “ ወይም ኤርምያስ ፅፎ በነበረበት ጊዜ እየሆነ ወደ ነበረበት እንመለሳለን ፡፡ ንጉሱ ሴዴቅያስ፣ አለቆቹ እና ሕዝቡ የእግዚአብሄርን ቃል እየታዘዙ ባይሆንም (ቁጥር 1-2) ሴዴቅያስ ከለዳዉያን ኢየሩሳሌም ከመክበብ እንዲያቆም ምክንያት የሆነው “ የፈርዖን ሰራዊት ግብፅን ለቅቆ ስለ ነበር “ እንዲፀልይላቸዉ ለመጠየቅ ካህናትን ወደ ኤርምያስ ላከ (ቁጥር 5) ፡፡ ኤርምያስ በፀለዬ ጊዜ እግዚአብሄር ካህናቱን ግብፃዊያኑ እንደሚመለሱና ከለዳዉያን ኢየሩሳሌም ለማጥፋት እንደሚመለሱ እንዲነግራቸዉ ነገረው (ቁጥር 6-10) ፤ ኤርምያስ ምድሩ በቢንያም እንደ ሆነ በመናገር ኢየሩሳሌምን በተወ ጊዜ በከለዳዉያን ባዶ ማስቀረት የተከሰሰ ነበር ፡፡ አለቆቹም ኤርምያስን በመምታት ወደ እስር ቤት ወረወሩት (ቁጥር 11-16) ፤ ይህ ኤርምያስ ከደረሰበት አምስት እስራቶች አንዱ ነበር ፡፡ ቆይቶም ንጉስ ሴዴቅያስ ኤርምያስን በቤቱ በማምጣት ኤርምያስን ከእግዚአብሄር የሆነ ቃል እንደ ነበረዉ ጠየቀው ፤ ኤርምያስም ሴዴቅያስን ለባቢሎን ንጉስ ተላልፎ እንደሚሰጥ ነገረው (ቁጥር 17) ፡፡ ኤርምያስን በፀሀፊዉ በዮናትን ቤት (ቁጥር 20) ወደ እስራቱ ከመመለስ ይልቅ ኤርምያስን በግዞት ቤት አደባባይ አኖረው (ቁጥር 21) ፡፡ ስለዚህም ይህ ምዕራፍ ሁለት ሳይሆን አንድ የኤርምያስን እስራት ያካትታል ፡፡
በኤርምያስ 38 ኤርምያስ በከተማዋ የሚቆዩ እንደሚሞቱ ነገር ግን ለከለዳዉያን የሚማረኩት በሕይወት ይኖራሉ አለ (ቁጥር 1-3) ፡፡ አለቆቹም ኤርምያስ ሕዝቡን ተስፋ ስላስቆረጠ መሞት አለበት አሉ ሴዴቅያስም የፈለጉትን እንዲያደርጉ ፈቀደላቸው ፤ ኤርምያስንም ሰምጦበት ወደ ነበረዉ ጭቃ ወደ ጉድጓድ አወረዱት (ቁጥር 4-6) ፡፡ ኩሻዊዉ አቤሜሌክ ወደ ሴዴቅያስ በመሄድ ኤርምያስ በርኃብ ከመሞቱ በፊት ከጉድጓዱ ዉስጥ እንዲያወጣዉ ጠየቀው ፤ በታላቅ እንክብካቤ አቤሜሌክ እና 30 ሰዎቹ ኤርምያስን ከጉድጓዱ ዉስጥ አወጡት ኤርምያስ ግን በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ (ቁጥር 7-13) ፡፡ እንደ ገና ሴዴቅያስ ኤርምያስን እዉነቱን በመናገሩ እንዲገደል እንደማያደርግ/እንደማይፈቅድ ቃል በመግባት ከእግዚአብሄር የሆነዉን ቃል ጠየቀው ፤ እንደ ገና ኤርምያስ ለከለዳዉያን የማይማረኩ ከሆነ ይገደላሉ ከተማዋም ትፈርሳለች አለ (ቁጥር 14-18) ፡፡ ሴዴቅያስም ኤርምያስን ስለዚህ ቃለ ምልልስ ለአለቆቹ እንዳይነግራቸዉ አስጠነቀቀው (ቁጥር 24-25) ፤ ኤርምያስም የሴዴቅያስን ትዕዛዝን በመከተል ኢየሩሳሌም በምርኮ እስክትያዝ ድረስ ተቀመጠ (ቁጥር 26-28) ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር በኤርምያስ መከራ ላይ የሚያስደንቅ ምልከታን አድርጓል ፤ “ በሞት የማስፈራራት መከራ ነበር (ኤርምያስ 11)፣ ለይቶ በማስቀመጥ (ኤርምያስ 15)፣ በእግር ግንድ ዉስጥ በመቀመጥ (ኤርምያስ 19)፣ በመታሰር (ኤርምያስ 26)፣ በመከራ (ኤርምያስ 28)፣ በጥፋት (ኤርምያስ 36)፣ በብጥብጥ እና በእስራት (ኤርምያስ 37)፣ በርኃብ (ኤርምያስ 38)፣ በእስራት (ኤርምያስ 40) እና በመገፋት ነበር (ኤርምያስ 42) “ ፡፡ ኤርምያስ አሉታዊ ነገር እንጂ ምንም ሌላ ምንም አልደረሰበትም ፤ ማንም ወደ እርሱ ባያዳምጥም እንኳን ኤርምያስ በሁሉም ሕይወቱ ለእግዚአብሄር እቅድ የታመነ ነበር ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (39፡ 1-3)፡ ይህ ምዕራፍ ከክርስቶስ ልደት 588 እስከ 586 በፊት ድረስ የኢየሩሳሌምን ዉድቀት ይሸፍናል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የእስራኤልን ዉድቀት “ በሕዝቡ ታሪክ በጣም ከሚያሳዝኑ ክስተቶች ዉስጥ አንዱ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ለ30 ወራት ያክል ባቢሎን በእስራኤል ላይ ከበባን ጣለ/አደረገ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ የዚህ ጊዜ መዋቅሩ/ቆይታው በሁሉም መንገድ ከክርስቶስ ልደት 588 በፊት እስከ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ ባቢሎን “ ሁሉንም መግቢያዎች፣ መዊጪያዎች፣ ምግብ ማቅረቢያዎች እና ዉኃም የሚገኝበትን ሁሉ ስለቆረጠ ርኃብ፣ ዉኃ ጥም እና በሽታ የተከበበዉን ከተማ ያደክመዋል “ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ የምግብ አቅርቦት ደክሞ በነበረበት ጊዜ የኢየሩሳሌም ቅጥሮች ተጥሰዉ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ የባቢሎን አለቆች የባቢሎናዊያን ሰራዊት ከተማዋን ሙሉ በሙሉ እንደያዘ እንደ ምልክት በመካከለኛው በር ላይ ተቀመጡ ባቢሎን ኢየሩሳሌምን በተቆጣጠረች ጊዜ “ የአሕዛብ ዘመን “ ጀምሮ ነበር (ሉቃ 21፡ 24) ፡፡ በኢየሩሳሌም ሁለት ታላላቅ ዉድቀቶች ነበሩ፡ ይህንኛው ከክርስቶስ ልደት በ586 በፊት ሲሆን እንደገና ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ ደግሞ ሌለኛው ነበር ፤ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት የነበረዉ ዉድቀት ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ እና የሚመጣው ዉድቀት አርቆ ያሳያል (ዳን 9፡ 27) ፡፡
ኤርምያስ (39፡ 4-10)፡ ሴዴቅያስ እና ወታደሮቹ ከከተማዋ ሸሹ ነገር ግን ከለዳዉያን በኢያሪኮ ከእነርሱ ጋር ተገናኙ ፤ ለፍርድም በሪብላ በንጉስ ናቡከደነፆር ፊት በመታሰር ተወሰዱ ፡፡ ማክአርቱር ናቡከደነፆር “ ንጉሱን በተለመደ ወንጀል እንደተመለከተው “ ያስቀምጣል ፤ ናቡከደነፆር ሴዴቅያስን አይኑን ከማጥፋቱ እና በነሐስ ሰንሰለት በማሰር ወደ ባቢሎን ከመዉሰዱ በፊት የሴዴቅያስን ወንድ ልጆች እና የይሁዳን ታዋቂ ሰዎችን ገደለ ፡፡ የሴዴቅያስን መኖሪያ ቤት/ቤተ መንግስትን በማቃጠል የኢየሩሳሌም ቅጥሮች አፈራረሰ ፤ ሕዝቡም ወደ ባቢሎን ተወሰዱ በይሁዳ ድሆቹን ብቻ በመተው (ቁጥር 4-10) ፡፡
ሁሉም ነገር ኤርምያስ የተነበያቸዉ ሁሉ በትክክል ሆነ (ኤር 32፡ 4 እና ሕዝ 12፡ 13) ፡፡ ኤር (52፡ 13) ናቡከደነፆር ቤተ መቅደሱንም እንደሚያቃጥለዉ ይናገራል ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ አይሁዶች ወደ ባቢሎን ተወስደዉ የነበሩባቸዉን ሰዎስት ጊዜያት አስቀምጧ፡ ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት፣ 586 በፊት እና እንደ ገና 582 በፊት ፡፡ ይሁን እንጂ ባቢሎናዊያን ጥቂት ድሀ አይሁዶችን በይሁዳ ትተዋል ፡፡
ኤርምያስ (39፡ 11-18)፡ ንጉስ ናቡከደነፆር ኤርምያስ እንዲለቀቅ በማዘዝ አዛዡንም ኤርምያስ የሚለዉን ሁሉንም ነገር እንዲያደርግለት አዘዘው (ቁጥር 11-12) ፤ ኤርምያስም ተለቆ ስለ ነበር በራሱ ሕዝብ መካከልም ተቀመጠ (ቁጥር 14) ፡፡ እስረኛ እንደ ነበር ኤርምያስ በ17 ሸቅል መሬት ገዝቶ ነበር ፤ አሁን ከለዳዉያን ነፃ ስላደረጉት በራሱ መሬት ላይ ተቀመጠ ፡፡ ናቡከደነፆር በምድሪቱ በቀሩት ቅሬታዎች ላይ የጎዶልያስን በመሾም አስተዳደር አደረገ (ኤር 40፡ 5, 7) ፡፡ እግዚአብሄርም ኤርምያስን ከጉድጓድ ዉስጥ አዉጥቶት የነበረዉን የኩሹን አቤሜሌክ ህይወት አዳነው (ኤር 38፡ 7-9) ፡፡ የመፅኀፍ ቅዱስ ማብራሪያዉ ቃል በኤርምያስ ላይ በኤርምያስ 39 መታመንን እና አለመታመንን ያወዳድራል፡
“ ኤርምያስ 39 በመታመን እና ባለመታመን መካከል ያለዉን ኃይለኛ ልዩነት ያቀርባል ፤ ኤርምያስ እና አቤሜሌክ ለእግዚአብሄር ታማኝ የሆኑትን እና በምላሹ እግዚአብሄር የታመነላቸዉን ይወክላሉ ፡፡ ሴዴቅያስ አለመታመንን ይወክላል ፡፡ በአንዳንድ ረገድ የሴዴቅያስ አለመታመን በሚያምኑት ሰዎች መካከል እንደ አደገኛ ችግር ነው ፤ አለመታመኑ እግዚአብሄርን መተዉ አይደለም ግፊት በመጣ ጊዜ በብርታት/በድፍረት መስራት አለመቻል እንጂ ፤ በራዕ (3፡ 15) እንዳለችዉ እንደ ሎዶቂያ ቤተ ክርስቲያን (የማያይ እንደነበረችዉ) ሴዴቅያስ ሞቃትም ቀዝቃዛም ስለ ነበር ስላለመወሰኑም አስደንጋጭ ዋጋን ከፈለ” ፡፡
መደምደሚያ
በእምነት በምትሰሩ ጊዜ ነፃ ናችሁ ፡፡ ከእምነት ዉጪ በምትሰሩ ጊዜ በባርነት ዉስጥ ናችሁ ፤ አቤሜሌክ እና ኤርምያስ በእምነት ስለሰሩ ነፃ ነበሩ ፡፡
10 Gerald L. Keown, Pamela J. Scalise, and Thomas G. Smothers, Jeremiah 26-52, Word Biblical Commentary Series (Dallas: Word Books, 1995), p. 231; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Notes: Jeremiah, p. 338, available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 873.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 934.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 1252.
MacArthur, p. 873.
Nelson’s Commentary, p. 934.
MacArthur, p. 873.
Wiersbe, p. 1252.
MacArthur, p. 873.
Wiersbe, pp. 1252-53.
ጥያቄዎች
-
በኤርምያስ 37 ንጉስ ሴዴቅያስ ዮካልን እና ሶፎንያስን ወደ ኤርምያስ ለምን ላካቸው ? ሁኔታዉ ምንም ቢሆን ከመፅናት ይልቅ በአስቸጋሪ ጊዜ ለምን ወደ እግዚአብሄር እንደምንሳብ ምን ታስባላችሁ ?
-
በኤርምያስ በኩል ለይሁዳ ንጉስ የእግዚአብሄር ምላሽ ምን ነበር ?
-
በኤርምያስ 37 ኤርምያስ ለምን ነበር የታሰረው ? ለዚያ እስራት ምላሹ ምን ነበር ?
-
በኤርምያስ 37 ሴዴቅያስ የባህሪዉን ድክመት እንዴት አሳዬ ? በሌሎች ፊት የእግዚአብሄር ስለ ሆነ ነገር ስትናገሩ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ጊዜያት አሉአችሁ ? ንጉሱ ለኤርምያስ ብዙ ርህራሄዎችን እንዴት አሳዬ ?
-
በኤርምያስ 39 ንጉስ ናቡከደነፆር ኤርምያስን በተመለከተ ምን አዘዘ ? በኤር (39፡ 16-18) ምን ተስፋ ነዉ የተገኘው ? ይህ እንዴት ያበረታታችኋል ?
-
በኤርምያስ (37-39) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 38:17–18
“Jeremiah therefore said to Zedekiah, ‘This is what the LORD, the God of Hosts, the God of Israel, says: “If indeed you surrender to the officials of the king of Babylon, then you will live, this city will not be burned down, and you and your household will survive. But if you do not surrender to the officials of the king of Babylon, then this city will be handed over to the Chaldeans. They will burn it down, and you yourself will not escape from them.’”
ኤርምያስ ለንጉሱ ሴደቅያስ ሶስት ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገረ ፡፡ በእያንዳንዱ ጊዜም ተመሳሳይ የሆነ መልዕክትን ነበር ያስተላለፈው መልዕክቱም ፡- ለእግዚአብሔር ራስህን ምርኮኛ አድርግ ከክፉም ትድናለህ የሚል ነበር ፡፡ ንጉሱም ምርጫ ነበረው ፡- በእምነት ራሱን ምርኮኛ ማድረግ ወይም በፍርኃት መሸሽ ፡፡ ንጉሱም ፈራ ሞተም ፡፡ ኤርምያስም በእምነት በመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አወጀ ነጻነትንም አገኘ ፡፡
አንተም ተመሳሳይ ምርጫ ነው ያለህ ፡- በፍርኃት መኖር ወይም በእምነት መኖር ፡፡ በፍርኃት መኖር ማለት ምናልባት ፡- ራስን መቆጣጠር መቆጠብ ፣ መጨነቅ ፣ ቀላል መስሎ የታየህን ማድረግ ፣ እችለዋለሁ ብልህ የምታስበውን ብቻ ማድረግ ወይም ቀድመህ ያደረከውን ማድረግ ፡፡ ምናልባት በእምነት መመራት ፡- ምክንያት አልባ የሆነ ፣ ከቁጥጥርህ ውጭ የሆነ ፣ ዝግጁ እንዳልሆንክለት የሚሰማህ ነገር ሊመስል ይችላል ሆኖም ግን ሰላም ይሰማሃል ደግሞም በውሳኔህ በጀብዱ ሙሉ በሙሉ ትደሰታለህ ፡፡ ስለዚህ ታደርገዋለህ ፡፡ ስለዚህ በእምነት ራስህን ለእግዚአብሔር በመማረክ የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰድ ፡፡ እርሱ በማየት ሳይሆን በእምነት እንድትራመድ ያዝሃል ፡፡ በየጊዜው አንድ የእምነት እርምጃ ተራመድ ፡፡ ዛሬ የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰድ !
“ ኤርምያስም ሴዴቅያስን ፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ ፥ ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም ፤ አንተም ቤትህም በሕይወት ትኖራላችሁ ። ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም አለው ። “
- ኤርምያስ 38፡17-18
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢያሱ 1:9 — “ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና ፥ አይዞህ አትፍራ ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን ? “
ኤርምያስ 38:19–20 — “ ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን ፦ ወደ ከለዳውያን በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል እነርሱም ያፌዙብኛል ብዬ እፈራለሁ አለው ። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ አሳልፈው አይሰጡህም ። እኔ የምነግርህን የእግዚአብሔርን ቃል እባክህ ፥ ስማ ፤ ይቀናሃል ነፍስህም በሕይወት ትኖራለች ። “
2ኛ ቆሮንቶስ 5:7 — “ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።