Examples Of Faithfulness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 34-36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁሉንም የኤርምያስ መልዕክቶች ትንቢታዊ ጊዜአቸዉን መወሰን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡ ትናትና በኤርምያስ 33 ስለ እስራኤል መታደስ አዉርተናል ፡፡ ኤርምያስ ለእስራኤል ወደ ምድሯ እንደ ምትመለስ እንደ ምልክት መሬትን ገዛ ነገር ግን ከፅሁፉ ሁሉም ማሳያዎች ይህ በእኛ የህይወት ዘመን እንኳን እንዳልሆነ ነበር ፡፡ እስራኤል ወደ ሕዝቧ ምድር በአካል ስፍራ ላይ ብትመለስም እስካሁን ሙሉ የእግዚአብሄር ሕዝቦች ሙሉ በሙሉ መሰብሰብን አላዬንም ምክንያቱም ከእነርሱ ዉስጥ አብዛኞቹ እንደተበታተኑ ስለሆኑ ፡፡ ትንቢት በተለይም አብዛኞቹ የኤርምያስ ትንቢቶች “ ሆነዋል ነገር ግን ሁሉም ነብረት አይደለም “ ፡፡ የጥቂት ትንቢቶች ዝርዝር ወደ እዉነት ቢመጣም ሙሉ ፍፃሜአቸዉ ግን አሁንም ይሆናል/ይከሰታል ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (34፡ 1-3)፡ ኤርምያስ በሴዴቅያስ ታስሮ ስለ ነበር (ኤር 33፡ 1) ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ላይ በመጣም ጊዜ እንደተያዘ ነበር ፤ ወደ ባቢሎን አንድ ዙር ማፍለሱ ሆኖ ነበር በተጨማሪም ናቡከደነፆር ብዙ ሰዎችን ለመዉሰድ ተመለሰ ፡፡ የወራሪዉ ሰራዊት ማተራመስ እየተካሄደ እንደ ነበር ኤርምያስ እንደ እስረኛ ከአደባባዩ ለንጉስ ሴዴቅያስ አንድን ቃል ተናገረ ፡፡
ኤርምያስ በእስርቤት ነበር ምክንያቱም ያለፉትን 23 አመታት የሚመጣዉን የእግዚአብሄርን ፍርድ እና ንስኃ መግባት እንደሚያስፈልጋቸው በመናገር አሳልፎ ስለ ነበር ፡፡ አሁን ደግሞ በበሮቹ ላይ በናቡከደነፆር እንደ አንድ እስረኛ ኤርምያስ አሁንም ሌላ ፍርድን ተናገረ፡ ኤርምያስ ወደ ባቢሎን እንደሚወሰድ፣ ናቡከደነፆር ከተማዋን እንደሚያቃጥላት እና ሴዴቅያስ ለናቡከደነፆር ተላልፎ እንደሚሰጥ (ቁጥር 2-3) ፡፡
ኤርምያስ (35፡ 1-11)፡ ምዕራፍ 35 የንጉስ ወደ ኢዮስያስ ልጅ ወደ ኢዮአቄም ዘመን ተመልሶ ይሄዳል ፡፡ በዚያን ጊዜ ኤርምያስ ሬካባያዊያንን ወደ ቤተ መቅደሱ በመሰብሰብ በፊታቸዉ ወይንን በማስቀመጥ እንዲጠጡት ነገራቸዉ ፤ ይሁን እንጂ ከአባቶቻቸዉ አንዱ በፍፁም ወይን እንዳይጠጡ ስላዘዛቸዉ ሬካባዉያን እምቢ አሉ /አልጠጡም ፤ በፍፁም ወይን አይጠጡም ነበር፣ የራሳቸዉ የሆነ ምንም መሬት ሳይሆኖራቸው ከከተማዋ ዉጪ የኖሩ ነበሩ እንዲሁም ባቢሎናዊያን የመጀመሪያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን እስከያዙ ድረስ ለአባቶቻቸዉ በመታዘዝ ነበሩ ፡፡
የዘር ግንድ መስመር ዉስጥ ሳይሆኑ የሬካባዊያን መዝገብ ለምን እዚህ ጋር ይካተታል ? ምናልባትም ሬካባዊያን በእግዚአብሄር ካላቸዉ እምነት የተነሳ ለአባቶቻቸዉ ሙሉ የመታዘዝ የእግዚአብሄር ሰዎች ምሳሌ ቅሬታዎች ነበሩ ፡፡
ኤርምያስ (35፡ 12-17)፡ እግዚአብሄር እስራኤልን ሬካባያዊያን ለአባቶቻቸዉ እንደ ነበራቸዉ አይነት ተመሳሳይ መታመን ለእርሱ እንዲታሳየው ፈለገ ፤ ነገር ግን የነቢያትን መልዕክት ገፍተዉ ስለ ነበር እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ ፍርድን እንደሚያመጣ ቃል ገባ ፡፡
ኤርምያስ (36፡ 1-8)፡ አሁንም ኤርምያስ ወደ ወቅቱ ጊዜ ተመለሰ ፤ በምዕራፍ 36 በኢዮአቄም ዘመን የተከሰተን ሌላ ክስተትን መዘገበ ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስ እግዚአብሄር በ23 አመታቱ ጊዜ እንዲያዉጀዉ ሰጥቶት የነበረዉን መልዕክት ለእርሱ ተናግሮት የነበረዉን ሁሉ እንዲፅፈዉ ነገረው ፡፡ የእግዚአብሄር ልብ ሕዝቡ የሚነበበዉን የኤርምያስን መልዕክት በመስማት ከኃጢዓታቸዉ እንዲመለሱ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡
ኤርምያስ ሁሉንም ትንቢቶችን ለሚመዘግባቸዉ ለባሮክ አሳየው ፤ በመቀጠልም ኤርምያስ ባሮክን ኤርምያስ “ ታግዶ ስለነበር “ (ቁጥር 5) ወደ ቤተ መቅደስ በመሄድ ትንቢቶቹን እንዲያነብ ኃላፊነት ሰጠው ፡፡ ማክአርቱር የዕብራዊያን ቃል መታገድ የሚለዉ ቃል እስራትን ለመግለፅ በኤር (33፡ 1) እና (39፡ 15) ጥቅም ላይ ከዋለዉ ቃል ጋር ተመሳሳይ እንደ ሆነ አስቀምጧል ፤ ይህ መታደግ በኤርምያስ 33 ከተጠቀሰዉ የተለዬ የነበረ እስራት እንደሚሆን ነው ፡፡
ሁሉንም የኤርምያስን ትንቢቶች እንዲመዘገቡ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ለመፈፀመ ጥቂት ጊዜን ይወስዳል ምክንያቱም ባሮክ ሁሉንም በእጁ ይፅፍ ስለ ነበር ፤ ይህ ምዕራፍ 36 ባሮክ ትንቢቶቹን በቤተ መቅደስ እንዲያነብ ኃላፊነት በተሰጠበት ጊዜ ቀድሞ ስለጀመረ በኤርምያስ 34 እንደ ተገለፀው ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ላይ ከበባን ሲጥል ታሪኩ እስከዚያ ጊዜ የተያዘ ስለነበር ቀላል ነው ፡፡ “ በፀሙ ቀን “ (ቁጥር 6) ባሮክ በቤተ መቅደሱ ላይ የኤርምያስን ትንቢቶች ያነብበት የየነበረው በበሩ ላይ ለናቡከደነፆር ምላሽ እንደሆነ ተጠርቷል ፡፡ በተጨማሪም ይህ ከይሁዳ አገርም ሕዝቡ ወደ ከተማዋ ለምን ይመጣ እንደ ነበር ይገልፃል (ቁጥር 6) ፤ ይህ በ 2ዜና (20፡ 1-4) ላይ እንደተደረገው ስሜት ጋር ተመሳሳይ ነው፡
“ እንዲህም ሆነ ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሣፍጥን ሊወጉ መጡ ፡፡ ወሬኞችም መጥተው ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሰራዊት መጥቶብሃል ፤ እነሆም ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው ብለዉ ለኢዮሳፍጥ ነገሩት ፡፡ ኢዮሳፍጥም ፈራ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና ፤ ከይሁዳ ከተሞችም ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ “ ፡፡
ኤርምያስ (36፡ 9-20)፡ ኮንስታብል የመጀመሪያዎቹ ስምንት ቁጥሮች ስለ ኤርምያስ ፅሁፍ ጥቅል እንደሚገልፁ ያስቀምጣል ፤ በመቀጠልም ቁጥር (9-26) የጥቅሉ መነበብን ይገልፃሉ ፡፡ በሁሉም ሕዝብ መስማት ባሮክ ጥቅሉን ካነበበዉ በኋላ ይህን “ በአለቆች ፊት “ እንዲያነበው ታዘዘ (ቁጥር 14) ፤ ለአለቆቹ ባሮክ ያነበበዉ መልዕክት በፍርኃት ስለሞላቸው ንጉሱም ይህን መልዕክት መስማት እንደሚያስፈልገዉ ወሰኑ (ቁጥር 15) ፡፡ አለቆቹም ባሮክን እነዚህን ቃላቶች እንዴት ፅፏቸዉ እንደ ነበር በመጠየቅ ባሮክ የመልዕክቱ ምንጭ እርሱ እንደ ነበር ወይም በኤርምያስ ማሳያ/ገለፃ ፅፎት እንደ ነበር ጠየቁት (ቁጥር 17) ፡፡ አለቆቹም ኤርምያስን እና ባሮክን ሁለቱንም ራሳቸዉን እንዲደብቁ አዘዟቸው (ቁጥር 19) ፤ ኢዮአቄም የኦርዮን ቃል ስላልወደደው ቀድሞ ኦርዮን ገሎት ስለ ነበር (ኤር 26፡ 20-23) ፡፡ አለቆቹም ጥቅሉን አርቀዉ በማስቀመጥ ስለ ጥቅሉ ንጉሱን ነገሩት ፡፡
ኤርምያስ (36፡ 21-26)፡ ንጉሱም ጥቅሉን እንዲያገኙት ሰዉን በመላክ ክረምት ስለ ነበር በእሳት አጠገብ በመቀመጫዉ ላይ በመቀመጥ ሲነበብ አዳመጠ (ቁጥር 21-22) ፡፡ ጥቅሉም እንደ ተነበበ ኢዮአቄም ጥቅሉን በመቁረጥ በመቆራረጥ በእሳት ላይ ወረወረው (ቁጥር 23) ፤ ንጉሱና አለቆቹ በኤርምያስ ስለ ታወጀዉ የእግዚአብሄር ፍርድ የሚያስቡ አልነበሩም (ቁጥር 24) ፡፡ ባሮክ እና ኤርምያስ ለመሸሽ የሚክያስን ክስ ሰምተዉ ነበር ፡፡ ንጉሱም ባዘዛቸዉ ጊዜ ሊያገኟቸዉ አልቻሉም ምክንያቱም “ እግዚአብሄር ደብቋቸዉ ስለ ነበር “ (ቁጥር 26) ፡፡
ኤርምያስ (36፡ 27-32)፡ ንጉሱ የመጀመሪያዉን ጥቅል/ክርታስ ካቃጠለዉ በኋላ እግዚአብሄር ኤርምያስን ክርታሱን መልሶ እንዲፅፈው ነገረው (ቁጥር 28) ፡፡ እግዚአብሄርም ኢዮአቄም “ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም…. ስለ ኃጢዓታቸውም እርሱንና ዘሩን ባሪያዎቹንም እቀጣለሁ “ ይላል (ቁጥር 30-31) ፡፡
መደምደሚያ
ኢሳ (40፡ 8) “ ሳሩ ይደርቃል አበባዉም ይረግፋል የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች “ በማለት ይናገራል ፡፡ ንጉስ ኢዮአቄም የእግዚአብሄርን ቃል ባቃጠለዉ ጊዜ እግዚአብሄር ኤርምያስን ቃሉን እንደ ገና እንዲፅፈው አዘዘው ፡፡ እግዚአብሄር ማንም ሰዉ ሊያመልጥ እንደማይችል ለመናገር ፈለገ ፡፡ እግዚአብሄር ልክ እንደ ሬካባዉያን እና እንደ ኤርምያስ ለእርሱ የታመኑ የሚሆኑትን እየተመለከተ ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary, (Thomas Nelson: Nashville, 2005), p. 871.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, pp. 312–314; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf.
ጥያቄዎች
-
በኤር (34፡ 12-16) የእስራኤል ሕዝቦች ባሪያዎቻቸዉን ነፃ አዉጥተዉ ካስቀመጡ በኋላ አስተሳሰባቸዉን እና ስምምነታቸዉን እንደ ገና ለምን እንደቀየሩ ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር እንዳላችሁ ጀምራችሁ ሀሳባችሁን ቀይራችሁ ታዉቃላችሁ ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
-
ወደ ትዉልድ የተላለፈ እና አሁንም የምታደርጉት ድርጊት ቤተ ሰቦቻችሁ አላቸው ? ሬካባዉያን በትዉልድ በኩል ለተላለፈው አዋጅ በመታመን ተቀመጡ (ኤርምያስ 35) ፤ ቤተሰቦቻችሁ እንደ እግዚአብሄር የሆነ ልምድ ያላቸዉን ጀምራችሁበት እና እየቀጠላችሁበትስ ነው ? አዎ ከሆነ ምንድን ነው ? አይደለም ከሆነ እንዴት ልትጀምሩ ትችላላችሁ ?
-
በኤር (36፡ 3) እግዚአብሄር ስለ ንስኃና ስለ ይቅርታ ተናገረ ፤ በመፅሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ይህ ተጠቅሶ እናየዋለን (2ዜና 7፡ 14) ? ይህ የማይሆን ጥያቄን ይመስላል ? ለምን ወይም ለምን አይመስልም ?
-
በኤርምያስ (34-36) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 36:32
“Then Jeremiah took another scroll and gave it to Baruch son of Neriah, the scribe, and he wrote on it at Jeremiah’s dictation all the words of the scroll that Jehoiakim, Judah’s king, had burned in the fire. And many other words like them were added.”
ነቢዩ ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ቃል ለጸሀፊው ለባሮክ በብራና ላይ አጻፈው ፡፡ ከዚያም ኤርምያስ ባሮክን ቃሉን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ላሉት እንድያነብላቸው አዘዘው ፡፡ ህዝቡም ባሮክ ቃሉን ለአለቆቹ እንድያነብላቸውና እነርሱም ለንጉሥ ኢዮአቄም እንድነግሩት ጠየቁት ፡፡ ንጉሥ ኢዮአቄምም የብራና መጽሀፉ እንድቃጠልና ኤርምያስና ባሮክም እንድታሰሩ አዘዘ ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሰወራቸው ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ደስ የማያሰኝ መልዕክትን ተናገረ እግዚአብሔርም ጠበቀው ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ኤርምያስን እንደገና ሌላ ብራና እንድወስድ አዘዘው ባሮክም መልሶ መልዕክቱን ጻፈው ፡፡ እርሱም እንዲሁ አደረገ ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል አይደመሰስም ፡፡ አይደበዝዝም ፡፡ አይጠፋም ፡፡ ፈጽሞ ከንቱ አይደለም ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ያሸንፋል ፡፡ እግዚአብሔር በእምነት እንድትራመዱ ደግሞም ስለእምነታችሁ እና ስለቃሉ ደፋር እንድትሆኑ ሲያዛችሁ ፣ እግዚአብሔር እንደሚጠብቃችሁ እንደሚታደጋችሁ እመኑት ፡፡ ለመሄድና እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ በእምነት ለመፈጸም ጊዜው አሁን ነው ! ቃሉን ስበኩ ፡፡ እውነቱን አውጁ ፡፡ በፍቅር ድፈሩ ፡፡ በእግዚአብሔርና በቃሉ ላይ በድፍረት ቁሙ ፡፡
“ ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ ለኔርያም ልጅ ለተጸሐፊውለባሮክ ሰጠው ፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት ፡፡ “
- ኤርምያስ 36፡32
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 19:21 — “በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል ። “
ኢሳይያስ 40:8 — “ ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል ፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች ። “
ኤርምያስ 36:26 — “ ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ ፥ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።