Major Prophets Jeremiah

Taking Action In Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 32-33 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 614 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና በምዕራፍ 31 እና በአዲሱ ኪዳን ላይ ተመልክተናል ፡፡ በኤርምያስ በኩል እግዚአብሄር ሕዝቡን ከምርኮ በማዉጣት ህጉን በልባቸዉ እንደሚያስቀምጥ ነገራቸው ፤ እግዚአብሄር ተስፋን በመስጠት የእስራኤልን እና የይሁዳን ሕዝቦች በአንድ ላይ አመጣቸው ፡፡ ምዕራፍ 31 የሚመጣዉ ክርስቶስ የተለዬ መልክ ነው ፡፡ ከምዕራፍ 31 ወደ 32 ያለዉ ሽግግር ሕዝቡን ለ70 አመታት በምርኮ ይሆኑ እንደ ነበር ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ (32፡ 1-15)፡ ቁጥር (1-3) ደረጃን ያስቀምጣል፡ ሴዴቅያስ የይሁዳ ንጉስ ነበር የባቢሎን ሰራዊትም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከበባን አደረገ ኤርምያስም በንጉሱ ቤተ መንግስት በእስር ቤት ነበር ፡፡ ሴዴቅያስ ኤርምያስን በእስራት አስቀምጦት ነበር ምክንያቱም ባቢሎን ይሁዳን እንደምታሸንፍ እና ሴዴቅያስ እንደ እስረኛ ወደ ባቢሎን ይወሰዳል የሚለዉን የኤርምያስን ትንቢት ስላልወደደው (ቁጥር 3-5) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አይን ለአይን “ የሚለዉ ሐረግ “ በናቡከደነፆር የሴዴቅያስ አይን መወገድ ዉጤት የሚሆነዉ አንዱ በአንዱ ላይ የመጋጠም ትንቢት (39፡ 5-7) “ እንደሆነ ይገልፃል ፡፡

ኤርምያስ የአጎቱ ልጅ አናምኤል በዓናቶት ያለዉን የእርሻ ማሳዉን እንዲገዛዉ እንደሚመጣ ምላሽ ሰጠ ፤ እግዚአብሄርም ኤርምያስን ይህን ከአጎቱ ልጅ እንዲገዛዉ ነግሮት ነበር (ቁጥር 6-7) ፡፡ ኤርምያስም በመታዘዝ መሬቱን/ እርሻዉን በ17 ሰቅል ብር በመግዛት መዝግቦ ግዢዉን እንዲያዩ ምስክሮችን ጠራ (ቁጥር 8-10) ፤ ኤርምያስም ንብረቱን በአጉቶ ሉጅ በአናምኤል ፊት እና ምስክሮቹ ባሉበት ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠው (ቁጥር 11-12) ፡፡ ኤርምያስ ባሮክን እግዚአብሄር መዝገቡን/የዉል ወረቀቱን በመዉሰድ ለብዙ ጊዜ ስለሚቆይ በምድር ማጠራቀሚያ እንስራ ዉስጥ እንዲያስቀምጠ እንደፈለገ አዘዘው ምክንያቱም “ ቤቶች፣ እርሻዎች እና የወይን ስፍራዎች እንደ ገና በዚህ ምድር ላይ ስለሚመጡ “ (ቁጥር 13-15) ፡፡ ኤርምያስ ምድሩን መልሱ የራሱ የሚሆንበት ጊዜ ያ ጊዜ እንደሚመጣ ተረድቷል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እርሱን/መረቱን የመግዛት የኤርምያስ ድርጊት የይሁዳ ሕዝቦች ወደ ምድራቸዉ አንድ ቀን እንደሚመለሱ በእግዚአብሄር ላይ ያለን እምነት የሚያስደንቅ ማሳያ እንደ ነበር “ ያመለክታል ፡፡

ኤርምያስ (32፡ 16-25)፡ ኤርምያስም ወደ እግዚአብሄር በመመለስ አመሰገነዉ ለእርሱም የሚያስቸግር ምንም ነገር እንደሌለ ተናገረ (ቁጥር 16-17) ፤ ስለ ኃይሉና ስለ ቸርነቱ እግዚአብሄርን አመሰገነ (ቁጥር 18-21) ፡፡ በመቀጠልም ኤርምያስ አገሪቱ የነበረችበትን ሁኔታ ገለፀ (ቁጥር 22-24) ፤ ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ነገር እያለ የወደፊትን ጨለማ በመመልከት እግዚአብሄር ኤርምያስን መልካም የቢዝነስ ስምምነት የማይመስለዉን መሬት እንዲገዛ ነገረው (ቁጥር 25) ፡፡

ኤርምያስ (32፡ 26-44)፡ እግዚአብሄር ለኤርምያስ ለእርሱ ለማድረግ የሚያስቸግረዉ ምንም ነገር እንዳልነበረ በማስታወስ ምላሽን ሰጠው (ቁጥር 26-27) ፡፡ ቬርኖን ማክጌ ቁጥር (36-40) “ እግዚአብሄር ከተማዋን ለከላዳዊያን እንደሰጣቸዉ እና በራሱም ጊዜ ከተማዋን ከከላዳዊያን ነፃ እንደሚያወጣ “ የሚገልፁ እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡

ኤርምያስ (33፡ 1-9)፡ የኔልሰን ማብራሪያ ምዕራፍ 33 በሰዎስት ክፍል ያስቀምጠዋል፡ “ 1) የኢየሩሳሌም መታደስ እና መንፃት (ቁጥር 1-9)፣ 2) በመታደስ ያለ ደስታ (ቁጥር 10, 11) እና 3) የይሁዳ መታደስ (ቁጥር 12, 13) “ በማለት ያስቀምጠዋል ፡፡ አንዱ የምርኮ ማዕበል ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ወደ ባቢሎን ቀድሞዉ ተወስደዉ ነበረ በተጨማሪም ሌለኛዉ የምርኮኝነት ማዕበል ከክርስቶስ ልደት 588 በፊት የተላኩ የሚሆኑበት ነበር በባቢሎናዊያን የኢየሩሳሌም መከበብ ጊዜ ኤርምያስ በግዞት ቤት አደባባይ ነበር ፡፡ እግዚአብሄርም በዚያ ኤርምያስን ተናገረው ፤ በቁጥር 3 “ ወደ እኔ ጩኽ እኔም እመልስልሃለሁ ፤ አንተም የማታዉቀዉን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይኃለሁ “ ይላል፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሄር የኤርምያስን ፀሎት ከተስፋዉ አንፃር ለመፈፀም ለዋስትና እርሱን ለመለመን ጋበዘው “ በማለት ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር ቤቶቹና የነገስታት መኖሪያዎቹ ፈራርሰዉ እንደ ነበርና ከላደዉያንን ለመከላከል ታላቅ መከላከያን ለመገንባት ፍርስራሽን እንደፈጠረ ነገር ግን ከለዳዊያንን የተዋጉትን በራሱ በእግዚአብሄር ቁጣ እና መዓት እንደሚገድላቸዉ ተናገረ (ቁጥር 4-5) ፡፡ እግዚአብሄር ሰዎስት ነገሮችን ቃል ገብቷል፡ 1) ንስኃ መግባት በሚሆን ጊዜ ጤንነት እና ፈዉስን ስለሚያመጣ የሰላም እና የእዉነት መትረፍረፍን እንደሚቀምሱ፣ 2) የይሁዳን እና የእስራኤልን እድሎች በማደስ ወደ ቀድሞዉ ክብራቸው መልሶ እንደሚገነባቸው (ቁጥር 7) እና 3) በእርሱ ላይ ከሰሯቸዉ ስህተቶች በማንፃት ሁሉንም ስህተታቸዉን እና አመፃቸዉን ይቅር እንደሚል (ቁጥር 8) ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር ከተማዋ በምድር አሕዛቦች ሁሉ ፊት ደስታ፣ ምስጋና እና ክብር እንደሚኖራት ቃል ገባ (ቁጥር 9) ፡፡

ኤርምያስ (33፡ 10-13)፡ ቁጥር (10-11) በባዶነት የምትተወዉን ከተማ በመቀጠልም እንደ ገና የታደሰች በመሆን በደስታ፣ በመደሰት እና በበዓላት ስለምትሞላዉ ከተማ ሁለተኛዉን ክፍል ይይዛሉ ፡፡ በቁጥር 11 “ እግዚአብሄር ቸር ነዉና ምሕረቱም ለዘላለም ነዉና እግዚአብሄርን አመስግኑ “ የሚለዉ ቃል ከመዝ (136፡ 1) ተጠቅሶ የነበርና “ አይሁዶችም ከባቢሎን ሲመለሱ ተጠቅመዉበት ነበር “ ፡፡ ቁጥር (12-13) በይሁዳ ስላለዉ መፈራረስ እና መታደስ ሰዎስተኛዉን ክፍል ይይዛል ፡፡

ኤርምያስ (33፡ 14-20)፡ እግዚአብሄር ለእስራኤል እና ለይሁዳ ቤት ያደረጋቸዉን ተስፋዎች ይፈፅማል “ ለዳዊት የጽድቅን ቁጥቋጦ አበቅልለታለሁ ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል “ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ በዳዊት የዘር መስመር ንጉሱ መሲሁ ነው ፤ በኃይል በተገለጠ ጊዜ ዘመኑ ወዲያዉኑ ሁለተኛ መምጣቱን የሚከተል ንጉስ ነው “ በማለት ይገልፃል ፤ ይህ ሺዉ አመትን እና ከሺዉ አመት በፊት የመከራዉ ጊዜ እንደሚመጣ ያመለክታል ፡፡ የጽድቅ ቁጥቋጦ አንድ ሺዉ የሺህ አመት ከመምጣቱ በፊት ይመጣል ፤ “ በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች ፤ የምትጠራበትም ስም ፡- እግዚአብሄር ጽድቃችን ተብሎ ነው “ (ቁጥር 16) ፡፡ ቁጥር (17-18) የዳዊት ግንድ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ንጉስ በፍፁም እንደማያጣ እና የሌዋዊያን ካህናት ሁል ጊዜ በእግዚአብሄር ፊት መስዋዕትን ለማቅረብ በፍፁም አንድም ሰዉ እንደማይጠፋ ይነግረናል (2ሳሙ 7፡ 16) ፤ ኮንስታብል “ በሺዉ ዘመን የሌዋዊያን ካህናት መታደስ ስለሚሆን የመጨረሻዉን መስዋዕት ከመመልከት ይልቅ አምላኪዎች ወደ ዚያ ወደ ኋላ እንደሚመለከቱ “ ይፅፋል ፡፡

እግዚአብሄር ወደ ኤርምያስ መናገሩን በመቀጠል የፍጥረቱን ኪዳን ካላፈረሰ የዳዊትንም ኪዳን እንደማያፈርስ ለማመልገት የፍጥረትን መገለጫዎች ተጠቀመ (ቁጥር 20-21) ፡፡ ማክአርቱር “ ተስፋዉ የሌሊት እና የቀን በእርግጠንነት ከመገለጥ/ከመሆን እና የከዋክብት እና የአሸዋ ቁጥር ከመሰራትም በላይ እርግጥ እንደ ነበር “ ይናገራል (ቁጥር 22) ፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች መርጧቸዉ የነበሩትን ቤተሰቦች አንዳንዶች የእስራኤልን እና የይሁዳን ቤት በማለት ሲተረጉሙ ሌሎች ደግሞ የዳዊት እና የሌዊ ቤተሰቦች እንደሚሆኑ በመተርጎም ሁለቱን ቤተሰቦች ትቷቸዉ ነበር ይላሉ በማለት ተናገረ (ቁጥር 23-24) ፡፡ ማክአርቱር “ ብዙ ሰዎች በኡኑ ጊዜም እንኳን እስራኤል እንደ አንድ ሕዝብ ወደፊት እንደሌላት ያምናሉ ፤ በቁጥር 25, 26 እነዚያን ሕዝቦች እግዚአብሄር በአፅዕኖት/በጥብቅ ይክዳቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ያድሳል “ በማለት ፅፏል ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር እንደ ገና ሕዝቡን በፍፁም እንደ ማይተዉ ተስፋ እየገባ ነበር ፤ ዋይርስቤ “ የእስራኤል ሕዝብ ብሩህ እና የተባረከ መጪ ጊዜ አላቸው ኤርምያስም በዚያ በመጪዉ ጊዜ ላይ ኢንቨስት እንዳደረገ “ ይናገራል ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 925.

  2. Nelson’s Commentary, p. 925.

  3. J. Vernon McGee, Thru the Bible: The Prophets (Jeremiah/Lamentations), vol. 24 (Nashville: Nelson Word Publishing Group, 1991), n.p.

  4. Nelson’s, p. 926

  5. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 869.

  6. MacArthur, p. 869.

  7. MacArthur, p. 869.

  8. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 297; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf.

  9. MacArthur, p. 869.

  10. MacArthur, p. 869.

  11. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 125.

ጥያቄዎች

  1. በኤር (32፡ 6-15) እግዚአብሄር ኤርምያስ የአናምኤልን መሬት ለምን እንዲገዛዉ አደረገ ? ባቢሎን ከያዘችዉ በኋላ መሬቱ የእርሱ መሆኑ አሁንም ሕጋዊ ለመሆኑ ይቻላል ?
  2. በኤር (32፡ 34) እግዚአብሄር ኤርምያስን ሕዝቡ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ጣዖትን እንዳስቀመጡ ነገረው ፤ የአሁኗ ቤተ ክርስቲያን ያስቀመጠችዉ ጣዖት አላት ? ጥቂት ምሳሌን ስጡ
  3. በኤር (32፡ 35) ለሞሎክ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች በሚሰዉበት ላይ ተናገረ ፤ ይህን “ የማይመስል ክፋት “ በማለት ጠራው ፤ በግል አስተያየታችሁ ማስወረድ የዚህ ቁጥር ምሳሌ ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አልሆነም ?
  4. የእግዚአብሄር ቃል እዉነት እንደ ሆነና በእርሱ (በእግዚአብሄር) ዉሸት እንደሌለ እናዉቃለን ፤ ስለዚህ ኤር (33፡ 17-18) እንዴት ትገልፁታላችሁ ? አሁንም ቁርባን የሚሰጡ ሌዋዊያን ካህናቶች አሉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? በዙፋኑ ላይስ ስለ ዳዊት ዘር/ልጆች ?
  5. በኤርምያስ (32-33) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 33:3

“Call to Me and I will answer you and tell you great and incomprehensible things you do not know

በእምነትና በመታዘዝ ኤርምያስ ከአጎቱ ልጅ መሬት ገዛ ፡፡ ኤርምያስ ለእግዚአብሔር ምንም ነገር ከባድ እንዳልሆነ አመነ ፡፡ እርሱ የእግዚአብሔርን ታማኝነት አስታወሰ ስለ ዘላለም ፍቅሩም ጌታን አመሰገነ ፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ሲጮኽ እግዚአብሔር እንደሚመልስለትና እርሱም የማያውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገር እንደሚነግረው አመነ ፡፡ እግዚአብሔር ለህዝቡ ፈውስን ፣ መልሶ መገንባትንና ከኃጢአት መንጻትን እንደሚያደርግ ኤርምያስ እግዚአብሔርን አመነው ፡፡

ዛሬ ለእግዚአብሔር ምንም የማይቻል ነገር እንደሌለ እመኑ ፡፡ አሁን በፊታችሁ ያለ “ ከባድ ተራራ “ ምንድን ነው ? ለእግዚአብሔር ግን ከባድ አይደለም ፡፡ በፊታችሁ ካለው ተራራ ላይ አፍጥጣችሁ ጊዜን ከማሳለፍ ይልቅ ፣ በህወታችሁ ያያችሁትን የእግዚአብሔርን ታማኝነት አስታውሱ ፡፡ እናም ልክ ልጅ ወደ ቤተሰቦቹ እርዳታን ለማግኘት እንደሚጣራ ሁሉ ፣ ወደ ጌታ ተጣሩ ፡፡ እርሱ እንደሚመልስላችሁ ይናገራል ፡፡ እርሱም የልቡን አሳብ ፣ ቃሉን ፣ እውነቱንም ያካፍላችኋል ደግሞም እናንተ የማታውቁትን ታላቅና ኃይለኛ ነገር ይነግራችኋል ፡፡ እግዚአብሔር በህይወታችሁ መስራት ይችላል ፡፡ ከእርሱ ጋር ተራመዱ ፣ ከእርሱ ጋር አውሩ ፣ እርሱን አድምጡ ደግሞም በእምነት ለቃሉ ታዘዙ ፡፡ ዛሬ ጌታን ታጣሩ እናም እንደሚመልስላችሁ እመኑ ፡፡ ለእርሱ የማይቻል ነገር የለም ፡፡

“ ወደ እኔ ጩኽ ፥ እኔም እመልስልሃለሁ ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ ። “

  • ኤርምያስ 33፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 136:1 — “ እግዚአብሔርን አመስግኑ ፤ ቸር ነውና ፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና ። “

ኤርምያስ 32:17 — “ አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ፥ እነሆ ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል ፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም ። “

ኤርምያስ 33:11 — “ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ድምፅ ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡት ድምፅ እንደ ገና ይሰማል ። የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና ፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “