The New Covenant
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 30-31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኤርምያስ 29 ኤርምያስ የይሁዳ እና የኢየሩሳሌም ሰዎች ከናቡከደነፆር የተነሳ ሳይሆን በእግዚአብሄር ፍቃድ ለ70 አመታት በምርኮ ይሆናሉ አለ ፡፡ በኤር (30፡ 3) እግዚአብሄር አንድ ቀን የሕዝቡን ቀዳሚዎች እንደሚመልሳቸዉ ቃል ገባ - የእስራኤልን እና የይሁዳን ሕዝቦች ሁለቱንም ፡፡ እስካሁን የዚህ ትንቢት ሙሉ መፈፀምን አላዬንም ፤ ኤር (30፡ 7) “ ወዬ ያ ቀን ታላቅ ነዉና ! “ ይላል ፤ ታላቅ መከራ እንደሚኖር እናዉቃለን ፡፡ ቤተ መቅደሱ ለሰዎስት አመት ከግማሽ በዚያ እንደሚሆን እናዉቃለን ፤ ሐሰተኛዉ ክርስቶስም እንደሚገኝበት እናዉቃለን ፡፡ “ የያዕቆብ የመከራ ጊዜ “ ለመከራዉ ቋንቋ እንደ ሆነ እናዉቃለን ፤ “ ታላቁ ቀን “ ማለት የክርስቶስ መመለስ እንደ ሆነ እናዉቃለን ፡፡ ጄ.ቬርኖን ማጌ “ ወደ ምድር የሚመለሰዉ የወደፊቱ ታላቅ ክብር በታላቅ መከራ የሚቀደም ነው “ አለ ፡፡ ይህ ሁሉ እግዚአብሄር እስራኤልን እና ይሁዳን ከሚሰበስብበት ጊዜ ከሺዉ አመት በፊት ይከናወናል ፤ በዚያ ቀን እግዚአብሄር ዳዊትን እንደ ንጉሳቸዉ እንደሚያስነሳዉ ተስፋን ይሰጣል (ኤር 30፡ 9) ፤ በዚህ በሺዉ ዘመን ጊዜ የፂዎን ቁስል ይፈወሳል (ኤር 30፡ 12-17) ምድራቸዉም ትታደሳለች (ኤር 30፡ 18-22) ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (31፡ 1, 27-30)፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ ገለፃ ይህ ምዕራፍ “ እግዚአብሄር ለእነርሱ አዲስ ነገር እንደሚያደርግ “ ያብራራል ፤ እዚህ ስፍራ ላይ በብሉይ ኪዳን ጉዞ የእስራኤል መንግስት የተከፈለ ነበር ፤ የእስራኤል የሰሜኑ መንግስት የጠፋዉ መንግስት ሲሆን የደቡቡ የይሁዳ መንግስት የተማረከዉ መንግስት ነበር ፡፡ በመክፈቻዉ ጥቅስ ላይ እግዚአብሄር “ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ “ ይላል ማለትም ለይሁዳ ብቻ ሳይሆን ለእስራአልም ጭምር ማለት ነው ፡፡ ኤርምያስ በቁጥር (27-30) በዚህ ንግግር ላይ በመስፋት/በማስፋት እንደ ገና ስለተዋሀደዉ ሕዝብ አወራ ፤ በመሰረቱ የሁለቱም መንግስታት ሕዝቦች የቀድሞ አባቶቻቸዉ አድርገዉት በነበረዉ ነገር መሰረት የገጠማቸዉ አይቆይም ነገር ግን ለማድረግ በመረጡት እንጂ (ቁጥር 29-30) ፡፡
ኤርምያስ (31፡ 2-20)፡ እግዚአብሄር ወደ ሰሜን መንግስት በእስራኤል ላይ ተናገረ ፡፡ የሰማሪያ (ቁጥር 5) እና የኤፍሬም (ቁጥር 6) መጠቀስ ለሰሜኑ መንግስት ማጣቀሻ ናቸው ፡፡ አንድ ቀን የሰሜኑ መንግስት ሕዝቦች ወደ ፂዎን (ኢየሩሳሌም) ለመመለስ ይወስናሉ (ቁጥር 6) ፤ እግዚአብሄር እስራኤልን መልሶ ያመጣታል (ቁጥር 7-9) ምክንያቱም ዋጅቷቸዉ ስለ ነበር (ቁጥር 10-11) ፡፡ ቁጥር 15 የሚያስደንቅ ትንቢታዊ ጥቅስ ነው ፡፡ በዮሐንስ ማክአርቱር አገላለፅ መሰረት “ በባቢሎናዊያን ወረራ ስለ ተገደሉት ልጆቿ የተጨነቅች አንድ የእስራኤላዊ እናት “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ ማቴዎስ በወንጌሉ ላይ “ በቤተ ልሄም ንጉስ ሄርዶስ በትንሽነቱ ለማጥፋት ብዙ ሕፃናትን ገድሎ በነበረ ጊዜ የአይሁድ እናቶች ተመሳሳይ ኃዘን እንዳዘኑ ያሳያል “ (ማቴ 2፡ 17-18) ፡፡ ዋይርስቤ ተጨማሪ መረጃን አቅርቧል፡ “ ራሔል የዮሴፍ እና የቢንያም እናት ነበረች፣ በሰሜኑ መንግስት የሁለቱ መሪዎች ነገድ ዮሴፍ የኤፍሬም እና የምናሴ አባት ነበር (ዘፍ 30፡ 22-24) ፡፡ ኤርምያስ የአይሁድ እስረኞች ወደ ባቢሎን ለሚያደርጉት ረጅም ጉዞአቸዉ ተሰብስበዉ በነበረበት በራማ ራሔል ስታለቅስ ሰማ (ኤር 40፡ 1) ፡፡ በዮሴፍ በኩል ያሉት ልጆቿ በአሶራዊያን ተይዘዉ ነበር አሁን ደግሞ በቢንያም (በደቡቡ መንግስት) በኩል ያሉት ልጆቿ ወደ ባቢሎን እየሄዱ ነበር ፤ እንደ አንድ እናት ምጧ በከንቱ ነበር ! “ ሁሉም ተስፋ የሌላቸዉ በመሰሉ ጊዜ ኤርምያስ እግዚአብሄር የተሸለ መልክ እንደ ነበረው ገለፀ (ቁጥር 16-20) ፡፡ እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር እንደ ነበርና ከእስራኤል ጋር ነገር እንዳልጨረሰ ተስፋን ገባላቸው ፡፡
ኤርምያስ (31፡ 21-26)፡ እግዚአብሄር ወደ ይሁዳ ተናገረ ፡፡ ቁጥር 22 ወደኋላ የመንሸራተትን (ይከዳተኝነትን) መልክ ይይዛል ፡፡ የማትታመን ሴት ልጅ ከአንድ አፍቃሪ ጋር ከዚያም ከሌላ ጋር የምትዳራ የአንድ ሴት ስዕል ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቦቹ ከኃላዉ ከመምጣት በፊት ምን ያክል ዞር እንደሚሉ ማወቅ ፈለገ ፤ አንዳንዶች ሐረጉን ለድንግል መዉለድ ትንቢት እንዲሆን “ ሴት ወንድን ትከብባለች “ (ቁጥር 22) ከሚል ጋር ይስተካከላል ፡፡
ኤርምያስ (31፡ 31-32)፡ በአንድ ላይ መልሶ እንደሚያመጣቸው እስራኤልን እና ይሁዳን ደግሞ ሲያረጋግጥ እግዚአብሄር በሁሉም ብሉይ ኪዳን ላይ በጥልቀት ከሚገኙት ክፍል አንዱን አወሀደዉ/አጣመረው ፡፡ በኤርምያስ መፅኀፍ ለክርስቶስ አንዲ ቃላችን አዲስ ኪዳን የሚል ነው ምክንያቱም በክርስቶስ በኩል ብቻ መምጣት የሚችል አዲስ የሆነ ነገር ስለሚኖር ፡፡ እግዚአብሄር ከእስራኤል እና ከይሁዳ - ከ12ቱም ነገድ ጋር አዲስን ኪዳን ለማድረግ ቃል ገባ ፡፡ አይሁዶች ሕጉን -ሙሴያዊዉን ኪዳን መጠበቅ አልቻሉም ነበር ፤ ስለዚህም እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳን ስር ሌላ እድልን እንደሚሰጣቸዉ ቃል ገባ (ቁጥር 31-32) ፡፡ በብዛት ኢያሱ፣ ሳሙኤል፣ ሕዝቅያስ፣ ኢዮስያስ እና ሌሎች ከእግዚአብሄር ጋር ያለዉን የኪዳን ትስስር በማረጋገጥ የእስራኤልን ሕዝብ ቢመሩም አሮጌዉን ኪዳን ሰብረዉት ነበር ፡፡
ኤርምያስ (31፡ 33-40)፡ በልባቸዉ ላይ ትምህረቱን የመፃፍ (ቁጥር33) የእግዚአብሄር ተስፋ ህይወት ቀያሪ ነበር ፤ እግዚአብሄር በአዲሱ ኪዳን በኩል ኃጢዓታቸዉን እንደሚጠርግ ቃል ገባ (ቁጥር 34) ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን የኢየሩሳሌም ከተማ መልሶ እንደሚገነባን እና እንደ ገና በፍፁም እንደማይፈርስ ነገራቸው (ቁጥር 38-40) ፡፡
ኢየሱስ መጀመሪያ የእነዚህን ተስፋዎች መፈፀም ለግለሰቦች ይሰጣል በመቀጠልም በአዲሱ ኪዳን በኩል ለእስራኤል ሕዝብ ፡፡ ማክአርቱር ይህን አዲስ ኪዳን “ እርሱን የሚያዉቁት በድነት በረከት በመሳተፍ የሚቀያየር መለኮታዊ የሆነ መንፈሳዊነትን እንደሚያመጣ “ ይገልፀዋል ፡፡ እግዚአብሄር ነገሮችን እያስቀመጠ ስለ ነበር ሕዝቦቹ በሚያደርጉት መሰረት ሳይሆን ከእርሱ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት መሰረት መዳን ይችላሉ ፡፡ በማቴ (5፡ 17) ኢየሱስ ህግንና ነቢያትን ላጠፋ አልመጣሁም ልፈፅማቸዉ እንጂ አለ ፤ ኢየሱስ የኤር (31፡ 33) መፈፀም ነው ፡፡
ኢየሱስ በመስቀል እንደ ሞተ ለሰዎስት ቀን እንደተቀበረና ወደ ህይወት ተመልሶ እነደመጣ የሚለዉን እዉነት በምትይዙ ጊዜ እግዚአብሄር ይህን በልባችሁ እንዳስቀመጠ ታስተዉላላችሁ ፡፡ የኢሳይያስ 53 የመከራ አገልጋዩን አስታዉሱ ? በኤርምያስ ተስፋን ሊሰጠን የሚመጣዉን የዳዊት ፃድቅ ቁጥቋጦን አስታዉሱ ? ይህ አሁን በልባችን ላይ የተቀመጠዉ አዲሱ ኪዳን ነው ፡፡ በመስቀል ላይ የክርስቶስ ስራ በሚገባ የአዲሱ ኪዳን መሰረት ነው ፤ በማቴ (26፡ 26-28) ኤርምያስ ያወራዉን ኢየሱስ አዲሱን ኪዳን መሰረተው ፤ ማር (14፡ 22-24) ኢየሱስ ይህን አዲስ ኪዳን እንደመሰረተ ያሳያል ፤ ያንን ክስተትም ሉቃስ ሉቃ (22፡ 19-20) መዝግቧል ፡፡
ነቢያቶቹ ስለ መጨረሻው ጊዜ፣ ስለ መሲሁ የመጀመሪያ ጊዜ መምጣት፣ ስለ ክርስቶስ መመለስ እና ሰላም የሚመጣበት ጊዜ ስለ ሺሁ አመት ተናግረዋል ፡፡ ያ ሺህ አመት አይሁዶች መሲሁን እንደ ወጉት ባስተዋሉ ጊዜ - በመስቀል ላይ እንደሞተና ስለ እነርሱ ደሙን እንዳፈሰሰ ባስተዋሉ ጊዜ ይመጣል (ዘካሪያስ 12) ፡፡ ኢየሱስ ስለ እነርሱ የአዲስ ኪዳን መስራች እንደ ሆነ ባስተዋሉ ጊዜ ወደ ዚህ ወደ ሰላም ዘመን መግባት እንጀምራለን ፡፡
መደምደሚያ
ክርስቶስ አዲስ ኪዳን ነው ፡፡ አይሁድ ወይም አሕዛብ ብትሆኑም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁሉም ሞተዋል ፤ ከዚህ በኋላ ሕጉን በመጠበቅ መልካም መሆን እንደማይቻል መረዳት ትችላላችሁ ነገር ግን ሕጉን በልባችሁ እና ክርስቶስን እንደ ጌታችሁ እና አዳኛችሁ ስትይዙ በአዲሱ ኪዳን ህይወት እንዳላችሁ መረዳት ትጀምራላችሁ ፡፡
J. Vernon McGee, Thru the Bible: The Prophets (Jeremiah/Lamentations), vol. 24 (Nashville: Nelson Word Publishing Group, 1991), n.p.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 1245.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 867.
MacArthur, p. 867.
Wiersbe, p. 1246.
MacArthur, p. 867–868.
Wiersbe, p. 1246.
MacArthur, p. 868.
MacArthur, p. 868.
ጥያቄዎች
-
ኤር (30፡ 12-13) የይሁዳ ቁስል የማይሽር እንደ ነበርና ስለ ጉዳያቸዉም የሚለምን ማንም እንዳልነበር ይናገራል ፤ ይሁን እንጂ ኤር (30፡ 17) “ እኔ ጤናህን እመልስልሀለሁ ቁስልህንም እፈዉሳለሁ ይላል እግዚአብሄር “ ይላል ፤ ይህ ተቃራኒ መምሰሉን ግለፁ
-
ኤር (30፡ 21) አንብቡ ፤ ምን አይነት መሪ/አስተዳዳሪ ከራሳቸዉ ህዝብ ይመጣሉ እግዚአብሄርንስ መጠጋት ይችላሉን ? ለምሳሌ እንደ ንጉስ እና ካህን ሁለቱንም ያገለግላል ? (ዘካ 6፡ 12-13, ዕብ 5፡ 10, ራዕ 19፡ 16)
-
ኤር (31፡ 12) “ ነፍሳቸዉም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም “ በሚለዉ መግለጫ የመጪዉ ጊዜን ደስታ ቀድሞ ተናገረ ፤ ይህ ከኃጢዓት ርግማን የመታደስ ጊዜን ወደፊት በማመልከት ከዉድቀት በፊት ዘፍ (2፡ 8-10) ሊያሳስብ /ሊያስታዉስ ይችላል ?
-
ኤር (31፡ 15) በማቴ (2፡ 18) ላይ የተጠቀሰ ነው ፤ በማቴዎስ መፅኀፍ መሰረት ይህ ትንቢት እንዴት ነበር የተፈፀመዉ ከመሲሁስ ጋር ግንኙነቱ ምን ነበር (ማቴ 2፡ 13-18) ?
-
ኤር (31፡ 31-34) በዕብራዊያን መፅሀፍ የተጠቀሰ ነው ፤ የዕብራዊ ፀሀፊ ምን አይነት ሀሳብን እያደረገ ነበር (ዕብ 8፡ 6-13) ?
-
“ አዲሱ ኪዳን “ ከመሲሁ ጋር እንዴት በቀጥታ ይገናኛል ? (ማቴ 26፡ 27-29, ማር 14፡ 22-24, ሉቃ 22፡ 15-20, 1ቆሮ 11፡ 25, ዕብ 10፡ 15-17, 12፡ 24, 13፡ 20)
-
በኤርምያስ (30-31) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 31:33–34
“‘Instead, this is the covenant I will make with the house of Israel after those days’—the LORD’s declaration. ‘I will put My teaching within them and write it on their hearts. I will be their God, and they will be My people. No longer will one teach his neighbor or his brother, saying, “Know the Lord,” for they will all know Me, from the least to the greatest of them’—this is the LORD’s declaration. ‘For I will forgive their wrongdoing and never again remember their sin.’”
እግዚአብሔር በኤርምያስ በኩል አዲስ ኪዳን አየመጣ እንደነበር አወጀ ፡፡ ይህም አዲስ ኪዳን የሚያመላክተው መሲሁን ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ ኤርምያስ ከትንሹ እስከ ትልቁ ፣ ለእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተስፋንና ይቅርታን አወጀ ፡፡ መሲሁ ለቅሶን ወደ ሳቅ ይለውጣል ደግሞም ጠፍቶ የነበረውን ይመልሳል ፡፡ እግዚአብሔር በአዲሱ ኪዳን በኩል ለህዝቡ ያዘጋጀው ተስፋ ነበረው ፡፡
እግዚአብሔር አዲሱን ኪዳን ፣ መሲሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተም አቅርቦላችኋል ፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሁኖ ነው ፡፡ እርሱ ሞተ ፣ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነሳ ፡፡ እርሱ ይህን ሁሉ ያደረገው ለእናንተ ነው ፡፡ በርግጥም ኢየሱስ እናንተን ለማዳን በማያቋርጥ ፍቅር ወደ ምድር መጣ ፡፡ እርሱም በመምጣቱ ፣ ተስፋን አገኛችሁ ፡፡ ምንም እንኳ ከጌታ እርቃችሁ የነበራችሁ ቢሆንም ፣ ኢየሱስ መልሶ ተቀብሏችኋል ፡፡ ወደ ህይወታችሁ እርሱን ተቀበሉ ፡፡ ኤርምያስ ከብዙ ጊዜ በፊት የተነበየውን እናንተ አሁን በድል በአሸናፊነት ትኖሩት ዘንድ አግኝታችሁታል ፡፡ አዲሱ ኪዳን ጥሩ ስለመስራት ወይም ጥሩ ሁኖ ስለመገኘት አይደለም ፡፡ ኢየሱስ የይቅርታና የጸጋ ፣ ነጻ ስጦታ ሁኖ መጥቷል ፡፡ በክርስቶስ ነጻነትና ጽድቅን ታገኛላችሁ ፡፡ ዛሬ ለህይወታችሁ ይህን አዲስ ኪዳን ተቀበሉ ከዘላለምም ባርነት ነጻ ውጡ ፡፡
“ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ፥ ይላል እግዚአብሔር ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል ። እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን ፥ እያንዳንዱም ወንድሙን ፦ እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም ፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና ፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ በደላቸውን እምራቸዋለሁና ፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና ። “
- ኤርምያስ 31፡33-34
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤርምያስ 31:3 — “ እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ ። “
ኤርምያስ 31:17 — “ ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፥ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ ። “
ማርቆስ 14:22–24 — “ ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውና ፦ እንካችሁ ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው ፥ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ ። እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።