Major Prophets Jeremiah

Jeremiah's Letter To The Exiles

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 27-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 612 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኤርምያስ መልዕክት የሚያስጨንቅ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር ለሰጠዉ መልዕክት በመታመን ተቀመጠ ፡፡ በተደጋጋሚም ይህን ለእስራኤል ስለ 70 አመት ምርኮ ነገራቸው ፤ ያንን መልዕክት በማካተት ከእግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ክፋትን አድርገዉ በነበሩት አሕዛቦች ላይ አንድ ትንቢት ነበረው - ይቀጣሉ ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ 27፡ በምዕራፍ 27 መጀመሪያ ላይ ስለ ባቢሎን ቀንበር ማጣቀሻ ነበር ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ቀንበር እና መታዘዝ ይገጥማቸዋል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኤርምያስ መልዕክት ለሰዴቅያስ ለእንግዳ/ለዉጪ አምባሳደር ተመሳሳይ ነበር (ቁጥር 4-11)፡ ለአቡከደነፆር እና ለባቢሎናዊያን በመታዘዝ እንደሚኖር በናቡከደነፆር ላይ ካመፀ ደግሞ በእግዚአብሄርም ላይ ስለሚሆን ይሞታል “ ፡፡

ኤርምያስ 28፡ ምዕራፍ 28 የአይሁዶች የምርኮ ጊዜ ቆይታን ሁለት አመት ብቻ ይሆናል ብሎ የተናገረዉ የኃሰተኛዉን ነቢይ የሐናንያን መግለጫ አካትቷል ፤ ኤርምያስ የለበሰዉን ቀንበርን ሰበረው ፡፡ በቁጥር 12 መጀመሪያ ላይ ሐናንያ ተነቀፈ ፡፡ የእንጨቱ ቀንበር ተሰበረ ነገር ግን እግዚአብሄር በኤርምያስ በኩል በመናገር ሐናንያን የእንጨት ቀንበሩም ወደ ብረት ቀንበር እንደሚቀየር ነገረው ፡፡ በተጨማሪም ኤርምያስ በአንድ አመት ዉስጥ የሚሆነዉን የሐናንያን ሞት ተነበዬ ፡፡

ኤርምያስ (29፡ 1-14)፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የተፃፈዉ ዶክመንት/ማስረጃ ከኢየሩሳሌም እስከ አይሁድ በባቢሎን ድረስ የተከናወነ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ሰዎስት ፍልሰቶች/ስደቶች ነበሩ፡ አንዱ ከክርስቶስ ልደት 590ዎቹ በፊት ሲሆን፣ አንዱ ደግሞ ከክርስቶስ ልደት 580ዎቹ በፊት አካባቢ ሲሆን ሰዎስተኛዉ ደግሞ ከክርስቶስ ልደት 580 በፊት ቀደም ብሎ ነበር ፡፡ እነዚህን ማስረጃዎች ኤርምያስ በሚፅፍበት ጊዜ አንዳንድ አይሁዶች በምርኮኝነት ነበሩ ፤ ማክአርቱር “ በአጭሩ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ597 በኋላ ከብዙ የአገሩ ሰዎች ከተወሰዱ በኋላ በግዞት መፅናናት እንደሚገጥማቸዉ ኤርምያስ እንደ ፃፈ “ ይናገራል ፡፡ ከኤርምያስ መልዕክት አፃፃፍ ከሽማግሌዎቹ አንዳንዶቹ ባለመሄድ የተሳሳቱት ወይም አንዳንዶች በሂደቱ ሞተዉ ነበር ፡፡

ኤርምያስ የመፅናናት እና የማበረታታት መልዕክትን እየፃፈ ነበር ፡፡ የመጀመሪያዉ መልዕክት ቁጥር (1-14) በባቢሎናዊያን ላይ ምስክሮች እንዲሆኑ ስደተኞቹን ለማበረታታት የተፃፈ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ንፁህ እና ንፁህ ያልሆነ ነገር በተመለከተ በተለዬ ህግ የሚተዳደረው የአይሁድ ሕዝብ ጣዖት አምላኪ ማህበረሰብን ለማስተካከል አስቸጋሪ ጊዜ ይሆናል ፤ ኤርምያስ ለባቢሎናዊያን አመንዝራነት/ጣዖት አምላኪነት ትክክለኛ ምስክሮች እንዲሆኑ ፈለገ በተጨማሪም ከአገልግሎታቸዉ እና ከቤተ መቅደሳቸዉ የተለዩ ቢሆንም መልካም አይሁድ እንዲሆኑ ፈለገ …. ለሚያስፈልጋቸዉ ለሰዎስት አይነት ሰዎች ራሱን አደረሰ ፤ ተስፋ ለሌላቸው (ቁጥር 4-6)፣ የኃሰት ተስፋ ያላቸዉን (ቁጥር 6-9) እና እዉነተኛ ተስፋ ያላቸዉን (ቁጥር 10-14) “ በማለት ይፅፋል ፡፡

ምርከኞቹ በግዞት ስለ ነበሩ ኤርምያስ እየተነበዬ አልነበረም ፤ በዚያን ጊዜ ምርከኞቹን አዘዛቸው ፡፡ እግዚአብሄር አይሁዶችን ቤቶችን እንዲሰሩ፣ ዛፎችን እንዲተክሉ፣ ሚስቶችን እንዲወስዱ እና ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች እንዲኖሯቸው ፈለገ ያ ከሆነ አይቀንሱም ፡፡ ምንም እንኳን በምርኮ ዉስጥ ቢሆኑም እግዚአብሄር ይህ ሁኔታ የእርሱ እንደ ነበር እንዲቀበሉ ፈለገ ፤ የሁኔታዉን ምርጡን እንዲያደርጉ እና እግዚአብሄር እየሰራበት የነበረዉን ሁኔታ እንዲይዙ ፈለገ ፡፡ እግዚአብሄር አይሁዶች አስቀምጦአቸዉ በነበረዉ ስፍራ የከተማዋን ደህንነት እንዲፈልጉ በመፈለግ ለከተማዋ እንዲፀልዩ ይጠብቃል ፡፡ ኤርምያስ 29 እግዚአብሄር የት አስቀምጧቸው እንደ ነበር ለመያዝ ለሁሉም ትምህርት ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ስደተኞቹ/ግዘቶኞቹ ችግር ፈጣሪ ሳይሆን የሰላም ሰዉ መሆን ነበረባቸዉ በተጨማሪም ለጠላቶቻቸዉ በትህትና መፀለይ እንደ ነበረባቸው ይገልፃል (ማቴ 5፡ 43-48, 1ጢሞ 2፡ 1-3, ቲቶ 3፡ 1-2) “ ፡፡ በመጨረሻም አይሁዶች ተመልሰዉ ወደ ምድራቸዉ ይመጣሉ/ይታደሳሉ ፤ እግዚአብሄር ቃል ኪዳኑን የሚፈፅም እና የሚጠብቅ አንድ አምላክ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር አይሁዶች ድንቁን እና ሙላቱን እንዲያገኙት/እንዲያዩት ፈለገ ፡፡

ቁጥር 11 በምርኮ ለነበሩት ለእግዚአብሄር ሰዎች የተስፋ መልዕክት ነበር ፤ በቁጥር 12 ኤርምያስ አይሁዶችን በሚፀልዩ ጊዜ እግዚአብሄር እንደሚሰማቸው አሳሰባቸው ፤ አይሁዶች እግዚአብሄርን መፈለግ ብቻ አስፈለጋቸው ፡፡ ምርኮኝነታቸው እንደ ቅጣት/ተግሳፅ የሚያገለግል ነበር ፡፡

ዋይርስቤ “ በኤር (29፡ 14) በባቢሎን ምርኮኝነቱ ከአይሁዶች በላይ የሆኑት ተስፋዎች በመላዉ አለም ዉስጥ ያሉትን እስራኤላዊያንን ያካትታል ፤ ኤርምያስ ወደፊት በዘመኑ መጨረሻ ላይ እስራኤል መሲኋን ለመገናኘት እንደ ገና በመሰባሰብ ወደ መንግስታቸዉ በሚገቡ ጊዜ እየተመለከ ነበር (ኢሳ 10፡ 20 – 12፡ 6) “ ይፅፋል ፡፡

ኤርምያስ (29፡ 15-23)፡ ዋይርስቤ በቁጥር (15-23) “ በባቢሎን ኃሰተኛ ነቢያቶች ስለ ኢየሩሳሌም እና ስለ ይሁዳ ለሕዝቡ የኃሰት ተስፋን እየሰጡ እንደ ነበርና ይህ ቃልም ተመልሶ ኤርምያስ ላይ እንዳለ “ ያመለክታል ፡፡ ኤርምያስ ከነቢያቶቹ ሁለቱን በስማቸዉ በመጥራት ለናቡከደነፆር እንዲገደሉ ተላልፈዉ የሚሰጡ እንደ ነበሩ ተንገረ ፡፡

ኤርምያስ (29፡ 24-29)፡ እነዚህ ቁጥሮች ኤርምያስን እንደ እብድ እና ሕዝቡ ለምን እንደማይዘጉት ጠይቆ ለነበረዉ ለቤተ መቅደሱ ካህን ለሸማያ መልዕክትን አካትተዋል ፡፡

ኤርምያስ (29፡ 30-32)፡ በኤርምያስ በዚህ ምዕራፍ የመጨረሻዉ መልዕክት በቁጥር (30-32) የተካተተ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ሸማያ በባቢሎን ተከታዮች እንደ ነበሩት፣ ኤርምያስ ምርኮኞቹን ሰዉዬዉ በእግዚአብሄር ላይ ያመፀ እንደ ነበርና ጌታም ልኮት ወይም መልዕክት ሰጥቶት እንዳልነበር አስጠነቀቃቸው ፡፡ ሸማያ ስለ ኃጢዓቱ በባቢሎን ልጅ ሳይኖረዉ በመሞት እና እንደ ገና ምድሩን በፍፁም እንደማያያት ይፈረድበታል “ በማለት ይናገራል ፡፡

መደምደሚያ

የኤርምያስ መልዕክት ለእስራኤል የሚያስደስት አልነበረም ፡፡ ኤርምያስ ፍርድን ቢያዉጅም/ቢናገርም እግዚአብሄር ደግሞ ወደ ምድሪቱ ሕዝቡን እንደሚመልሳቸዉ ተስፋን ሰጠ ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 918.

  2. Nelsons Commentary, p. 919.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 866.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 119, 120.

  5. Wiersbe, p. 120

  6. Wiersbe, p. 120.

  7. Wiersbe, p. 120.

  8. Wiersbe, p. 120.

ጥያቄዎች

  1. በኤር (27፡ 2) እግዚአብሄር ኤርምያስን ምን እንዲያደርግ ነገረው ? ይህን ለምን አደረገ (ኤር 27፡ 11)
  2. ከኤርምያስ አንገት ላይ ቀንበሩን ማን ሰበረው ? በድርጊቱ እግዚአብሄር ተደስቶ ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልተደሰተም ?
  3. በኤር (29፡ 11-14) ፊቱን በመፈለግ ፀልየዉ እርሱን ተደግፈዉ ጠርተዉት ቢሆን እግዚአብሄር ለሕዝቡ ምን ተስፋን ገብቶ ነበር ? ይህ ተስፋ ለእናንተም እንዲሁ እዉነት እንደሆነ ታምናላችሁ ? ይህ በሕይወታችሁ ሲሆን አይታችኋል ? ኤርምያስ ወደ እግዚአብሄር ሰዎች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ዉስጥ እንዴት እንደ መጣ ምን ታስባላችሁ ? (ኢሳ 63፡ 7, ኤር 9፡ 24, 16፡ 15)
  4. በኤርምያስ መልዕክት ዉስጥ ለምርኮኞቹ መጥፎ እና መልካም ነገሮቹ ሁለቱንም እግዚአብሄር ያላቸዉን ጥቂት ሌላ ነገሮችን ጥቀሱ ?
  5. ኤር (29፡ 23) “ ተግባሩን አዉቀዋለሁ እመሰክራለሁም “ በማለት ይናገራል ፤ ምን እያመለከተ ነበር በአሁኑ ጊዜ “ በድብቅ “ ስለምታደርጉት ነገር ይህ ምን ይላችኋል ? (ዘኁ 32፡ 23)
  6. በኤርምያስ (27-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 29:11–14a

“‘For I know the plans I have for you’—this is the LORD’s declaration—‘plans for your welfare, not for disaster, to give you a future and a hope. You will call to Me and come and pray to Me, and I will listen to you. You will seek Me and find Me when you search for Me with all your heart. I will be found by you’—this is the LORD’s declaration.”

እግዚአብሔር ህዝቡን ለግዞት አሳልፎ ሰጠ ፡፡ እነርሱም ጨለማ የሆኑና የሚያስጠሉ ቀናት ይኖሩ ነበር ፡፡ ነገር ግን አሁንም ነቢዩ ኤርምያስ ለህይወታቸው የሚያስፈልገውን መናገሩን ቀጠለ ፡፡ እግዚአብሔር በላካቸው ቦታ ላይ ይቀመጡ ዘንድ መከራቸው ፡፡ በዚህም የጨለማና አስቸጋሪ ጊዜ እንዳይሰንፉ ነገራቸው ፡፡ ይልቁንም ቤት መስራት ፣ አትክልት መትከል ፣ ትዳር መያዝና ልጆች መውለድ እንዳለባቸው ነገራቸው ፡፡ ኤርምያስ ህዝቡ በዚህ የምርኮና የግዞት ጊዜ ውስጥ ሆነው አሁንም በህይወት ያሉት ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ አሳብ እቅድ ስላለው እንደሆነ አስረገጠ ፡፡ ህዝቡም እንድጸልዩና የከተማዋን ሰላም እንድሹ መከራቸው ፡፡

ምናልባት ልትጠይቁ ትችላላችሁ ፡፡ እዚህ ምን እያደረኩኝ ነው ? ይህ ከባድ ነው ፣ ይህ የማይወደድ ደግሞም ይህ ምርኮኝነት ነው ፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ጨለማ በሆነ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ መኖር ቀጥሉ ፡፡ አይኖቻችሁን ከራሳችሁ ላይ አንሱ ፡፡ እግዚአብሔርንና መንግስቱን ፈልጉ ፡፡ አትጨነቁ ፡፡ ዘርን ዝሩ ፤ ውኃም አጠጡ እንድሁም በቃ ቀኑን አታባክኑ ተጠቀሙ ፡፡ ዛሬ የመጀመሪያውን እርምጃ ተራመዱ እግዚአብሔርንም ፈልጉ ፡፡ ለምን ? እርሱ ቃሉን ስለሚጠብቅና ለእናንተም ስትፈልጉት እንደሚገኝላችሁ ቃል ስለገባ ፡፡

“ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ ፡፡ ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “

  • ኤርምያስ 29፡11-14

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 8:17 — “ እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል ። “

ኤርምያስ 29:5–7 — “ ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤ ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ ። በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ ። “

ማቴዎስ 6:33–34 — “ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ። ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል ። “