Exile, Wrath, And Judgement
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 24-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በአራቱ ታላላቅ ነቢያት መፅኀፍት (በኢሳይያስ፣ በኤርምያስ፣ በሕዝቅኤል እና በዳንኤል) ዉስጥ ሁል ጊዜ ስለ ነፃ መዉጣት መልዕክቶች ነበሩ ፡፡ ሁሉም ስሕተቶቿ እና ክፉ አድራጎቷ እያሉ እስራኤል አሁንም የዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጦ ነበረች ፡፡ እግዚአብሄር ጣልቃ ስለገባ የእስራኤል ሕዝብ የራሳቸዉ ነፃነት ሊኖራቸዉ ቻለ ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (24፡ 1-14)፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ኤርምያስ ሕዝቡ ወደ ባቢሎን ይሄዱ እንደነበር ትንቢትን ተናገረ ፡፡ ዋይርስቤ “ ከክርስቶስ ልደት 597 በፊት ባቢሎናዊያን በምድሪቱ እንዲሰሩ ድሀዎቹን ብቻ በመተው ንጉስ ዮአኪንን ከብዙ ታዋቂ እና ቁልፍ ሰዎች ጋር አፈለሱት (2ነገ 24፡ 14-16) ፤ ይህ ለይሁዳ የመጨረሻዉ መጀመሪያ ነበር ኤርምያስም በኃይለኛው ጭንቀት ዉስጥ እንደ ነበር ጥርጥር እንደሌለ “ ይገልፃል ፡፡
እግዚአብሄር ኤርምያስን የበለስ ቅርጫቶችን በማሳየት ኤርምያስ ምን እንዳዬ ጠየቀው ፤ ኤርምያስ የበለስ ቅርጫቶችን እንዳዬ ምላሽ ሰጠ - የመልካሙን በለስ እና የመጥፎዉን በለስ ሁለቱንም እንዳዬ ፡፡ መጥፎዎቹ በለሶች የማይበሉ እና በጣም መጥፎዎች ነበሩ ፤ መልካሞቹ በለሶች እግዚአብሄርን የሚታዘዙትን የእስራኤልን ቅሬታዎችን ይወክላሉ ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስን ቅሬታዎቹን ከምድሪቱ ቢልካቸዉም እነርሱን መጠበቁን በመቀጠል በመጨረሻም ወደ ምድሪቱ እንደሚመልሳቸዉ ነገረው ፡፡ እግዚአብሄር እንደሚመልሳቸዉ እና እንደሚገነባቸዉ ከስራቸዉም እንደማያጠፋቸዉ ቃል ገባ ፤ የእግዚአብሄርም ሕዝብ ይሆናሉ እግዚአብሄርም አምላካቸዉ ይሆናል ፡፡ እግዚአብሄር እርሱን የሚያዉቅ ልብ ይሰጣቸዋል ፤ ይህ የአዲስ ኪዳን አስተሳሰብ ነበር ፡፡
የይሁዳ ንጉስ ሴዴቅያስ አብረዉት ከሚሰሩት ባለስልጣኖቹ/ሰራተኞቹ እና እግዚአብሄርን ያልተከተሉት የይሁዳ ቅሬታዎች የመጥፎዉ/የተበላሸዉ በለስ ቅርጫት እንደሚወክሉ የታዩ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር የተበላሹትን በለሶች ይተዋቸዋል/አይቀበላቸውም ፤ ለአሕዛብ ሁሉ የመጥፋትን መልክ ይወክላሉ ፡፡ የበለሶቹ ስዕል 12 የእስራኤል ነገዶች ይወክላሉ ፡፡ ሰይፍ፣ ርኃብ እና መቅሰፍት እግዚአብሄርን በማይታዘዙትን ወይም በማይከተሉት ሕዝቦች ላይ ጥቅም ላይ ይዉላሉ ፡፡
ዋይርስቤ “ ኤርምያስ በምዕራፍ 25 እና 26 የተመዘገበዉን መልዕክት በሚያደርስ ጊዜ ለ23 አመታት ያገለገለ ነበር ፤ ከክርስቶስ ልደት ከ626 በፊት ወደ ትንቢት አገልግሎት የተጠራ ሲሆን ከክርስቶስ ልደት ከ587 ከኢየሩሳሌም ዉድቀት በኋላ አገልግሎቱን በመቀጠል ከ40 አመታት በላይ እንዳገለገለ “ ይናገራል ፡፡ ኤርምያስ የይሁዳን እና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ከእነዚያ 23 አመታት በኋላ ያዳመጡ ወይም የሚታዘዙ እንዳልነበሩ ነገራቸው ፡፡ ሁል ጊዜ በየቀኑ ፍርድን እና ንስኃን እየሰበከ ነበር ፤ እግዚአብሄር ብዙ ነቢያቶችን ልኮላቸዉ እንደ ነበርና ማንኛዎቹም ሰምተዋቸዉ እንዳልነበሩ አሳሰባቸው ፡፡
በቁጥር 5 ኤርምያስ መልዕክቱን በመደጋገም ጣዖትን በማምለክ እግዚአብሄርን በቁጣ እንዳያነሳሱት ማበረታታቱን ቀጠለ ፤ እዚህ ስፍራ ላይ የኤርምያስ መልዕክት በሁለት አቅጣጫ ሄዷል ፤ አንዱ የፍርድ መልዕክት ለይሁዳ ነበር፣ ሌለኛዉ መልዕክት ደግሞ ለአሕዛቦች ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ባቢሎናዊያን እንደ ወኪል ይጠቀምባቸዋል ፡፡
ዋይርስቤ በቁጥር 9 ስለ ናቡከነደፆር ማሳያን ይገልፃል፡ “ ናቡከነደፆር በእዉነተኛዉ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሄር የሚያምን አልነበረም ነገር ግን በእርሱ ድል ማድረግ የእግዚአብሄርን ፍቃድ እየፈፀመ ነበር (51፡ 20-23) “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ናቡከደነፆር….. አገልጋዬ፡ ይህ ገለፃ የባቢሎናዊያን ገዢዎች የእስራኤልን አምላክ ያመልካሉ ማለት አይደለም በቀላሉ የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም በእግዚአብር ጥቅም ላይ የዋለ ማለት ነበር( በኢሳ (45፡ 1 ) በእግዚአብሄር የተቀባ ተብሎ እንደተጠራው ልክ እንደ ቂሮስ) “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር አላማዉን ለማስፈፀም ክፉ ነገስታትን ተጠቅሟል ፡፡
በቁጥር 11 “ ስለዚች ጠቅላላ ምድር “ ንግግሩ ሁሉንም ይሁዳ እና እስራኤል የሚያመለክት ነበር ፡፡ የባቢሎናዊያን ምርኮ ለ70 አመታት ይቆያል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ይህ በመጀመሪያዉ ቤተ መቅደስ መፈራረስ (ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት) እና የሁለተኛዉን ቤተ መቅደስ መገንባት (ከክርስቶስ ልደት 520-515 በፊት ) መካከል ከ66 እስከ 72 አመታትን ያክል ይወክላል ፡፡ 70 አመት የሚለዉ ሀረግ ለባቢሎናዊያን ምርኮ የቀረበ የጊዜ ቆይታን ምርጥ ማሳያ ነው፣ ይህ እምቅ ባህሪይ ያለዉ ቁጥር ነው ፤ አስር ሰባቶች ፡፡ በተጨማሪም በምርኮ የዳንኤልን ትኩረት የያዘ ቁጥር ነው (ዳን 9፡ 2) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ለ 70 አመታት እስራኤልን ለምርኮ የመስጠት ምክንያት ለምድሪቱ እረፍት ለመስጠት ነበር ፤ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ለምርኮ በመስጠት ምድሪቱን ያድሳል ፡፡
በቁጥር 12 ኤርምያስ 70 አመት መጨረሻ ላይ እግዚአብሄርየባቢሎንን ሕዝብ ከለዳዉያንን በመጠቀም እንደሚያጠፋ እና ምድራቸዉን ለዘላለም ባድማ እንደሚያደርግ ትንቢትን እየተናገረ ነበር ፡፡ ሕዝቡን ያለ አግባብ እና ስርዓት በሌለ መልኩ በመያዛቸዉ ምክንያት ይፈረድባቸዋል ፡፡
ከቁጥር (1-14) በኋላ አይሁዶችን እና የ70 አመት ምርኮኝነትን በመድረስ ኤርምያስ ወደ አሕዛቦች ዞረ (ቁጥር 15-38) ፡፡ አሕዛቦች የእግዚአብሄርን ፍርድ እንዴት እንደሚቀምሱ/እንደሚቀበሉ ለመግለፅ ስምንት ስዕሎችን ጥቅም ላይ ዉለዉ ነበር፡ የመዓት ፅዋ፣ የሚጮኽ/የሚያጓራ አንበሳ፣ ሙግት፣ ማዕበል፣ ተቃዉሞ፣ የተሰባባረ ሸክላ እና የታረደ መንጋ ፤ ከእነዚህ ስዕሎች እያንዳንዳቸዉ የፍርድ ምሳሌዎች ነበሩ ፡፡ ስዕሎቹ በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት ያደረጉት የሁሉንም ሕዝቦች ጥፋት ደግመዉ ደግመው ይናገራሉ ፡፡
መደምደሚያ
በምዕራፍ 26 ኤርምያስ እንደ ገና በቤተ መቅደሱ ላይ ለንስኃ አይሁዶችን ተጣራ ፤ ይህ እንደ ነቢይ ተጠርቶ እንደ ነበር ኤርምያስ እርግጠኛ ከሆነ ከ23 አመታት በኋላ ይከሰታል ፡፡ በትንቢቱ ኤርምያስ አይሁዶችን ለ70 አመታት በምርኮ እንደሚሆኑና እግዚአብሄርም በምድራቸዉ መልሶ እንደሚያቋቁማቸው ስለዚህም ተስፋ እንዳለ ነገራቸው፡፡ በአሕዛብ ላይ ያለ ፍርድ የመጨረሻ ነበር ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 114.
Wiersbe, p. 115.
Wiersbe, p. 115.
Nelson’s Commentary, p. 914.
Nelson’s Commentary, p. 914.
ጥያቄዎች
-
በኤር (24፡ 2-10) መልካሙ በለስ ማንን ወክሏል (ኤር 29፡ 4-10, ሕዝ 11፡ 14-17) ? መጥፎዉ / የተበላሸው በለስስ ? (1ነገ 9፡ 7, መዝ 44፡ 12-14)
-
በኤር (25፡ 3) ኤርምያስ ለ23 አመታት የእግዚአብሄርን ቃል ለሕዝቡ ተናግሮ ነበር ነገር ግን አሁንም አይሰሙትም ፤ ይህ እንዴት እንዲሰማችሁ አድርጓችኋል ? ኤርምያስ እንዳደረገው ትቀጥላላችሁ ? እምነታችሁን ስታጋሩ/ስትናገሩ ሰዎች በማይቀበሏችሁ ጊዜ እንዴት ምላሽ ትሰጣላችሁ ?
-
በተዘዋዋሪ ነቢዩ ሚክያስ የኤርምያስን ህይወት እንዴት አዳነው (ኤር 26፡ 16-19)
-
የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ያልሆነ በኤርምያስ 26 ላይ የተጠቀሰዉ ሌላ ነቢይ ማነው ? ለዚህ ነቢይ ምን ተፈጠረ/ሆነ ?
-
በኤርምያስ (24-26) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 25:3–4
“From the thirteenth year of Josiah son of Amon, king of Judah, until this very day—23 years—the word of the LORD has come to me, and I have spoken to you time and time again, but you have not obeyed. The LORD sent all His servants the prophets to you time and time again, but you have not obeyed or even paid attention.”
ኤርምያስ ለሀያ ሶስት ዓመታት ያክል ተመሳሳይ ጭብጥን የሚጋሩ ትንቢቶችን ተናገረ ይህም ፡- ፍርድ ፣ ጥፋትና ግዞት እግዚአብሔርን በማይታዘዝ ትውልድ ላይ እየመጡ እንደነበር ነው ፡፡ ነገር ግን በቃ ህዝቡ አልሰሙም እምቢ አሉ ፡፡ ባለመታዘዛቸውም ምክንያት እግዚአብሔር እንደ እሚያገሳ እንበሳ ፣ ወድ የሸክላ እቃ እንደሚሰበር ፣ የቁጣው ጽዋ ሞልቶ ፣ እንደሚታረድ መንጋ ይመጣባችኋል ፡፡ ሳቅንና የእልልታንም ድምጽ ያስቀራል ፡፡ ከዚህም የሚተርፉት ወደ እርሱ ከተመለሱና ከታዘዙ ብቻ ነው ፡፡
ዛሬም ለእናንተ ይህ እውነት ፡- ጌታን ተቀበሉ ለቃሉም ታዘዙ ፡፡ ይህ ነው በቃ ጌታ እርሱን ሰትከተሉ እንድታደርጉ የሚጠይቃችሁ ፡፡ ምናልባት ልታመቻምቹ ትችላላችሁ ፣ እንዲህ በማለት ፡- “ ኦው ፣ ልጆች ሲኖሩኝ ፣ ልጆቼ አድገው መራመድ ሲጀምሩ ፣ ቢዝነሴ ሲስተካከል ወይም ስለራሴ ጥሩ ስሜት ሲሰማኝ ፣ ኢየሱስን እከተላለሁ ፡፡ ህይወት ትቀጥላለች ፡፡ አቁሙ ፡፡ በቃ አቁሙ ፡፡ አሁን ኢየሱስን ታዘዙ ፡፡ ምናልባት የለመዳችሁትን አኗኗር መቀየር ከባድ ሊሆን ይችላል ፣ ሆኖም ግን ወደ ኢየሱስ ፊታችሁን ስትመለሱ ፣ እርሱ ይመራችኋል ፡፡ ኃይሉ ያግዛችኋል ፡፡ ፍቅሩም ያጽናናችኋል ፡፡ ስለዚህ ተመለሱ ፡፡ ዛሬ ተመለሱና የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዙ ፡፡ ኢየሱስ ታላቁ ትዕዛዝ በፍጹም ልባችሁ እርሱን መውደድ እንደሆነ ተናግሯል ፡፡
“ ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከአሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት ፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ነገር ግን አልሰማችሁም ። እግዚአብሔርም ማልዶ ተነሥቶ ባሪያዎቹን ነቢያትን ወደ እናንተ ላከ፤ እናንተም አላደመጣችሁም ጆሮአችሁንም አላዘነበላችሁም ። “
- ኤርምያስ 25፡3-4
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 28:1–2 — “ እንዲህም ይሆናል ፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል ። የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል ። “
ኤርምያስ 25:8, 10–11 — “ ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ቃሌን አልሰማችሁምና……. ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ ። ይህችም ምድር ሁሉ ባድማና መደነቂያ ትሆናለች ፤ እነዚህም አሕዛብ ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ ። “
ማርቆስ 12:30 — “ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት ። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።