The Righteous Branch of David
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 22-23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለኤርምያስ መፅሀፍት ቃላችን አዲስ ኪዳን የሚል ነው ፡፡ ኤርምያስ ከኢሳይያስ ጋር ተመሳሳይ ነገርን ይናገራል ፤ ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንንት ኤርምያስ የራሱን ትንቢታዊ ቃሎች ይቀምሳቸዋል/ያገኛቸዋል ፡፡
ኤርምያስ ከኢሳይያስ ከአመታት በኋላ ትንቢትን በመናገር ስለሚመጣዉ የባቢሎን ምርኮ እየቀረበ ነበር ፡፡ ኤርምያስ ክፉ ለነበሩ ለአራት የአይሁድ ነገስታቶች የመናገር እድሎች ነበሩት ፤ ኢዮአክስ ከሰዎስት እስከ አምስት ወር ድረስ ንጉስ ነበር፣ ኢዮአቄም ለ 11 አንድ አመታት ንጉስ ነበር፣ ዮአኪን ለሰዎስት ወራት ንጉስ ነበር እና ሴዴቅያስ ለ 11 አመታት ንጉስ ነበር ፡፡
በኤርምያስ 22 ኤርምያስ ሴዴቅያስን ወደ እግዚአብሄር እንዲመለስ ያ ካልሆነ ደግሞ ፈጣን የሆነ ፍርድ እንደሚደርስበት ነገረው ፡፡ በኢሳይያስ ንጉስ ሕዝቅያስ የአሶርን መልዕክተኞችን ወደ መንግስቱ በመጋበዝ ሁሉንም ኃብቱን እና መንግስቱን እንዳሳያቸዉ ያስታዉሰናል ፤ ሴዴቅያስ የሕዝቅያስ አለማስተዋልን ፈፀመው ፡፡ ኤር (22፡ 25-30) “ እስካሁን በእግዚአብሄር ቃል ከተነገሩት ፍርዶች ከባድ/ኃይለኛ ነው ፤ በእግዚአብሄር በቃየል ላይ እና በኢየሱስ በይሁዳ ላይ ከተነገረዉ ፍርድ የሚበልጥ ነው ፤ የሚያስፈራ እና በተመሳሳይም በእግዚአብሄር ቃል በጣም የሚያስደንቀዉ ትንቢት ነው “ ፡፡
ሕዝቡ አሁንም የመሲሁን መምጣት እየተጠባበቁ ነበር የእግዚአብሄርም ፍርድ ይህ በእነዚህ ነገስታቶች የዘር መስመር በኩል እንደማይመጣ አዉጇል/ተናግሯል ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ የፍርድ ቃላት በኋላ በኤርምያስ 23 ኤርምያስ የተስፋ መልዕክትን ያመጣል ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (23፡ 1-8)፡ በእነዚህ በመጀመሪያዎቹ ጥቅሶች ዉስጥ ኤርምያስ ቅሬቶቹን የመሰብሰብ ትንቢትን ሰጠ ፡፡ ኃሰተኛ አስተማሪዎቹ (እረኞቹ) የእግዚአብሄርን ፍርድ በመቀበል ከምድሪቱ ላይ ይጠፋሉ (ቁጥር 1-2) ፡፡ እነዚህ ኃሰተኛ አስተማሪዎችን ማክአርቱር “ እግዚአብሄር ቆይቶ ለኅዝቡ ከሚሰጣቸዉ እረኞች ጋር በንፅፅር እንደሚቆሙ “ ይገልፃል ፤ እግዚአብሄርም ቅሬታዎቹን በመሰብሰብ ፍሬአማና ብዙ ወደ ሚሆኑባት ምድሩ ይመልሳቸዋል (ቁጥር 3) ፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝቦች በክፉ ነገስታቶች፣ በመጥፎ መሪዎች እና በኃሰተኛ ተመርተዉ ስለ ነበር እግዚአብሄር ታምነዉ ያልነበሩትን በመቅጣት የታመኑትን ቅሬታዎች ወደ መለምለም መልሶ ያመጣቸዋል ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር….. ሕዝቦቹን እንደ ገና በመሰብሰብ ቅሬታዎቹን ወደ ሕዝብ እንደሚቀይራቸው ፤ ቅሬታዉ ከምርኮ በኋላ ወደ ይሁዳ በመመለስ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ እንደሚሰሩ እና ሀገራዊ ሕይወትን /መኖርን እንደሚያድሱ “ ይገልፃል ፡፡ በቁጥር 4 ኤርምያስ እግዚአብሄር በተመለሱት ቅሬታዎች ላይ የሚያስተዳድር እረኛን እንደሚያስነሳ ተናገረ ፡፡
በእስራኤል እንዳየነው የኤርምያስ ትንቢት ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ስለ ባቢሎናዊያን ምርኮ ነበር ነገር ግን እንደ መሲህ ስለ ኢየሱስ መምጣት እና በመጨረሻዉ ዘመን ስለ ክርስቶስ መመለስም ነበር ፡፡ በ1948 እስራኤል ሀገር በሆነችበት ጊዜ የዚህ ትንቢት በከፊል መፈፀሙ ሆኗል ፡፡ አንዳንዶች ቁጥር (3-8) በሺሁ ዘመን የእስራኤልን መታደስ ያመለክታል ይላሉ ፡፡
በቁጥር (5-6) ኤርምያስ ሁለተኛዉን ትንቢቱን ሰጠ - እግዚአብሄር “ የዳዊትን ፃድቅ ቁጥቋጦ “ ያስነሳል ፤ ማክአርቱር ይህ ማለት “ ወደ ፊት በእግዚአብሄር ሕዝቦች ላይ የሚነግሰዉ መሲሁ ከዳዊት ቤተሰብ ገንድ ይመጣል “ ማለት እንደ ሆነ ይገልፃል (ኤር 33፡ 15) ፡፡ ቁጥር (7-8) በቁጥር (1-4) የተሰጠዉን የመጀመሪያዉን ትንቢት ድጋፍ የሚሰጡ ይመስላሉ ፡፡
ኤርምያስ (23፡ 9-40)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ የኃሰተኛ ነቢያቶች ኃጢዓት ተቀምጦአል ፤ ኤር (14፡ 14) የእነዚህን ቁጥሮች ማጠቃለያን ይሰጣል ፡፡
“ እግዚአብሄርም እንዲህ አለኝ፡- ነቢያቱ ዉሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ ፤ አላክኋቸዉም፣ አላዘዝኋቸዉም፣ አልተናገርኋቸውም ፤ የዉሸቱን ራዕይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸዉንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል “ ፡፡
በቁጥር 11 ኮንስታብል “ እግዚአብሄር ነቢዩና ካህኑ ሁለቱም ባለመታመን እንደረከሱ ተናገረ ፤ ለእግዚአብሄር ሁሉም የታመነ በሚሆንበት ስፍራ በቤተ መቅደሱም እንኳን ክፋትን አደረጉ “ በማለት ይገልፃል ፡፡
በቁጥር (13-20) ኤርምያስ ሰዎስተኛዉን ትንቢት ሰጠ ፡፡ የሰሜኑ መንግስት ነቢያቶች በባዖል አማልዕክት ትንቢትን ተናግረዉ ስለ ነበር ሕዝቦን በስሕተት መሩት (ቁጥር 13) ፤ በኢየሩሳሌም ግን እግዚአብሄር “ የሚያሰደነግጥ ነገርን አዬ “ - ነቢያቶቹ አመንዝረዋል፣ ኃሰት ተናግረዋል እንዲሁም ማንኛቸዉም በክፉ ላይ ጀርባቸዉን አላዞሩም (ቁጥር 14) ፤ እግዚአብሄር በጎሞራ ከነበሩት ክፉ ሰዎች ይልቅ የከፉ እንደሆኑ ገለፃቸዉ ፡፡ ከዚህም የተነሳ ኤርምያስ እግዚአብሄር ለደቡብ ነቢያቶች የሚመር እንጨት እና እንዲጠጡ የሚመር ዉኃን እንደሚሰጣቸዉ ትንቢትን ተናገረ (ቁጥር 15) ፡፡
ኤርምያስ እነዚህ ነቢያቶች ከእግዚአብሄር ያልመጣን ሀሰተኛ ትንቢትን እና ራዕይን እየሰጡ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 16) ፤ እግዚአብሄር ሁሉንም ሰላም እንደሚሰጣቸው ቃል ገብተዋል - ለሕዝቡ ለወደፊት ኃሰት የሆነ ትንቢትን ለመስጠት ዋሽጸዋል (ቁጥር 17) ፡፡ ማክአርቱር ኃሰተኛ እረኞችን “ ኃጢዓታቸዉ መፅናናትን ሳይሆን ቁጣን እንዲያመጣ እግዚአብሄርን ያነሳሳውን ሰዎች ሰላምን ተስፋ በመስጠት ከፍሬ ይልቅ ገለባዎች እንደሆኑ “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ዋይርስቤ ኃሰተኛ ነቢያቶች “ በኃሰተኛ መነሳሳት ስር “ (ቁጥር 25 -32) “ በኃሰተኛ ስልጣን “ (ቁጥር 21-24) “ ኃሰተኛ/የዉሸት ተስፋን “ ይሰጣሉ (ቁጥር 16-20) በማለት ያመለክታል ፡፡ የዚህን መፅኀፍት (ቁጥር 9-40) ይህን ክፍል ዋይርስቤ “ እንደ ሚያሳፍር ባህሪያቸው “ (ቁጥር 9-15)፣ “ እንደ ያለመታመን/የክህደት መልዕክት” (ቁጥር 16-32) እና “ እንደ ብልግን አመለካከታቸው “ (ቁጥር 33-40) በማለት ያጠቃልላል ፡፡
መደምደሚያ
ኤርምያስ ለሕዝቡ ፍርድ እየመጣ እንደ ነበር ትንቢት መናገሩን ቀጠለ ፡፡ የኤርምያስ መፅኀፍን ጥናታችንን ከመጨረሳችን በፊት በሚገባ የሚሆነዉን ፍርድ እናያለን ፡፡
J. Vernon McGee, Thru the Bible: The Prophets (Jeremiah/Lamentations), vol. 24 (Nashville: Nelson Word Publishing Group, 1991), np.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 862.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Jeremiah (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2002), p. 112.
MacArthur, p. 862.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 215; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf.
MacArthur, p. 863.
Wiersbe, p. 113.
Wiersbe, p. 113.
ጥያቄዎች
-
በኤር (23፡ 1-2) ላይ እግዚአብሄር የተናገራቸዉ እረኞች እነማን ነበሩ በምንስ ከሰሳቸው ?
-
ኤር (23፡ 5-6) ወደ መሲሁ ያመለክታል ፤ እርሱን ለመጥቀስ/ለማመልከት ምን ስምች ጥቅም ላይ የዋሉ ናቸው ? እነዚህ ስሞች ወይም ማጣቀሻዎችን በቃሉ ሌላ የት ስፍራ ላይ ይገኛል ? (ኢሳ 4፡ 2, ኤር 33፡ 15, ዘካ 3፡ 8, 6፡ 12, ሮሜ 3፡ 22, 2ቆሮ 5፡ 21)
-
በኤር (23፡ 21-32) ከነቢያቶቹ አንፃር እግዚአብሄር ምን የታወቀ እንዲሆን ፈለገ ?
-
መዝ (139፡ 7-10) እና ኤር (23፡ 24) ሁለቱም ስለ እግዚአብሄር ምን ይነግሩናል ? ከእግዚአብሄር መደበቅ እንደሚችሉ ወይም ኃጢዓታቸዉን ደብቀዉ መጠበቅ እንደሚችሉ የሚያስቡትን እንዴት ልትረዱአቸዉ ትችላላችሁ ?
-
በኤርምያስ (22-23) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 23:6
“In His days Judah will be saved, and Israel will dwell securely. This is what He will be named: Yahweh Our Righteousness.”
የይሁዳን ህዝብ ስለሚመጣው ጥፋትና ፍርድ በማስጠንቀቅ ላይ ሳለ ፣ ኤርምያስ ጻድቅ ስለሆነው የዳዊት ቁጥቋጥ እንዲህ በማለት ተነበየ ፡- ይህ ቁጥቋጥ በጥበብ እንደ ንጉሥ ይነግሳል ፣ በምድርም ፍትህንና ጸድቅን ያደርጋል ፡፡ ይሁዳ ሁሉ ይድናል ፤ እስራዔልም በሰላም ይቀመጣል ፡፡ ይህም ቁጥቋጥ ፡- እግዚአብሔር ጽድቃችን የሚል ስም ይኖረዋል ፡፡ በኤርምያስ እግዚአብሔር ስለሚመጣው መሲህ ኢየሱስ ፣ ስለ ጻድቁ አዳኛችን ቀድሞ ተናገረ ፡፡
ምናልባት ጽድቅ ፈጥናችሁ የምታነቡት ቃል ሊሆን ይችላል ፣ ከዚያም ወድያው ወደ ቀጣዩ አረፍተ ነገር ትሻገራላችሁ ፣ ፈጽማችሁ ብዙ ትኩረት ሳትሰጡት ማለት ነው ፡፡ ጽድቅ ልንኖርበት ኑሯችንን ልንመራበት የሚገባ ደረጃ ነው ፡፡ ጽድቅ የተገለጠው የእግዚአብሔር ቅድስና ነው ፡፡ አንዳንዶች የእግዚብሔርን ጽድቅ እንደ እግዚአብሔር ፍርድ እንደ እግዚአብሔር ፍትህ አድርገው ይገልጹታል ፡፡ እሺ ግን ይህ “ እግዚአብሔር ጽድቃችን “ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህም ማለት የእግዚአብሔር ባህሪ ሁልጊዜ እርሱ ትክክል የሆነውን ነገር እንድያደርግ ይመራዋል ማለት ነው ፡፡ ለእናንተስ ይህ ማለት ምን ማለት ነው ? በክርስቶስ እግዚአብሔር ጻድቅ ፣ የጸደቀ እና ሙሉ አድርጎ ያያችኋል ፡፡ ፍጹም ለመሆን ወደ ሌላ ቦታ ማማተር የለባችሁም ደግሞም ጽድቅንም ለማግኘት ብዙ መስራት አይጠበቅባችሁም ፡፡ በክርስቶስ ሙሉ ነህ ፡፡ በእርሱ እረፉ ደግሞም በእምነት “ እግዚአብሔር ጽድቃችን “ በማለት ሰላምን የሚሰጠውን ወረት የሌለበት ፍቅሩን ተቀበሉ ፡፡
“ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው ። “
- ኤርምያስ 23፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 116:5 — “ እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው ፥ አምላካችንም ይቅር ባይ ነው ። “
ሮሜ 1:16–17 — “ በወንጌል አላፍርምና ፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና ። ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና ። “
ራዕይ 16:5 — “ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።