Major Prophets Jeremiah

Surrender Your Life

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 20-21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 609 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሕይወቴ ምርጥ የሚባሉት አንዳንድ ዉሳኔዎች በፊት በነበሩ ትዉልዶች ተደርገዋል ፡፡ በራሳችሁ ህይወት ላይ ስትመለከቱ ምናልባትም አንዳንድ ተመሳሳይ ነገሮችን ታያላችሁ ፡፡ ሰዎች ስራዉን አብዝቶ ስለሚወደዉ አባቴ በይበልጥ ለልጆቹ በሚያስፈልግ ጊዜ ስራ ልምዱን ለመገንባት ጠንክሮ ይሰራ በነበረው የሚያሳፍር ቤተሰብ እንደ ነበር አስተያየትን ሰጥተዋል ፤ በመቀጠልም በጊዜዉ ስራዉ ተወስዶ ስለ ነበር ልጆች ከቤታቸዉ የወጡ በመሆን ብዙ ከቤተሰቦቻቸዉ ብዙ ነገር አያስፈልጋቸዉም ፤ ይህም አባቴን ስላሳመነዉ ስራዉን በመተው ከእኛ ጋር ቤት ተቀመጠ፡፡ ለቅጽበት ይህ አስቀያሚ ቅዠት ነበር ነገር ግን አባቴ ከእኛ ጋር ጊዜን አሳለፈ ፡፡ በዉጪ አለቶችን በመሰብሰብ ቆይቶም በአባቴ ህይወቴ በፍጥነት የተቀየረበትን ጊዜ አስተዋልኩ ፤ በዚያን ጊዜ አባቴ በእግዚአብሄር ቃል ፍቅር በጥልቅ እና በከፍተኛ መነሳሳት ወደቀ ፤ ያ እኔን ለእግዚአብሄር ቃል ፍቅሬን በይበልጥ ብልጭ አደረገው ፡፡

ኤርምያስ መልካም የነበረ እና ኢየሱስ በምድር ላይ ከመሆኑ በፊት ክርስቶስን የመሰለ ሰዉ ነበር ፡፡ ህይወቱ በእግዚአብሄር ቃል ተቀየረ ፡፡ ኤርምያስ ጎልማሳ ሰዉ በነበር ጊዜ ንጉስ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን በማደስ የጠፉትን የእግዚአብሄር ቃል ኮፒዎች አገኘ ፡፡ ኢዮስያስ የእግዚአብሄርን ቃል እንዲያጠኑ ሕዝቡን ለመምራት የኤርምያስን ህይወት የቀየረዉን የተሀድሶ እንቅስቃሴ መራ ፡፡ በዛሬዉ ጥናታችን ከኢዮስያስ ተሀድሶ አንድ ትዉልድን ብቻ እነዳስወገድን ማየት እንችላለን ይሁን እንጂ ሕዝቡ የጣዖት አማልዕክት በማስበለጥ እግዚአብሄርን ትተዉት ነበር ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ (20፡ 1-6)፡ ለእግዚአብሄር ቃል የታመናችሁ ከሆናችሁ መልካም ነገር ብቻ እንደሚሆንላችሁ ታምናላችሁ ? በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛዎቹ ቤተ ክርስቲያኖቻችን ይህን እምነት እንሰማለን ኤር (29፡ 11) በመጥቀስ ጭምር “ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አዉቃለሁ ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም “ ፤ ይሁን እንጂ የኤርምያስ ህይወት የተለያዩ ዉጤቶችን ያሳያል ፡፡ በቤተ መቅደሱ ላይ ታላቅ ካህን የነበረው ጳስኮር የኤርምያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ ኤርምያስን በመደብደብ በመጋዘን ዉስጥ አስቀመጠው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ኤርምያስ ኢየሱስ በሚገረፍበት ስፍራ በአንድ ማይል ርቀት ዉስጥ ተገረፈ፣ በምድር ላይ ኢየሱስ በሚዘለፍበት በተመሳሳይ ስፍራ ተዘለፈ/ተንጓጠጠ፣ ኢየሱስ እንደሚደርስበት መከራ ለእግዚአብሄር የታመነ በመሆን መከራ ደረሰበት ፡፡ በቀጣዩም ቀን ማለዳ ከመጋዘን ተለቀቀ ከእግዚአብሄርም ትንቢታዊ ቃልን ጳስኮርን ሰጠው (ቁጥር 3) ፤ የጳስኮር ስም “ በሁሉም በኩል የሚያስፈራ “ ማጎርሚሳቢብ ተብሎ የሚቀየር ሲሆን ሁሉም ወዳጆቹም በባቢሎን ወራሪ ሰራዊት ስር ሲወድቁም ያያል (ቁጥር 3-4) ፤ በተጨማሪም ባቢሎናዊያን የኢየሩሳሌም ኃብት ሁሉ እና የይሁዳ ንጉስ መዝገብን ይቀበላሉ፣ ጳስኮር እና የተረፉትም በምርኮ ይወሰዳሉ ፡፡ ጳስኮርም በእግዚአብሄር ላይ በኃሰት ትንቢት ተናግሮ ስለ ነበር በዚያ ይሞታል (ቁጥር 5-6) ፡፡

ኤርምያስ (20፡ 7-18)፡ ኤርምያስ ከጳስኮር ጋር ማዉራቱን በማቆም ለእግዚአብሄር መናገር በመጀመር በመጠራቱ ላይ በማታለሉ ከሰሰው ፡፡ ኤርምያስ እርሱን ከሚሰሙት በየቀኑ በሚደርስበት ዘለፋ እና ፌዝ ቢደርስበትም የእግዚአብሄርን ቃል እያደረሰ ስለ ነበር ጮኸ/አለቀሰ (ቁጥር 7-8) ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላ የእግዚአብሄርን ቃል ላለመናገር ሞከረ ነገር ግን “ በአጥንቶቼ ዉስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት በልቤ ዉስጥ ሆነብኝ (ቁጥር 9) ፡፡ ኤርምያስ በዉስጡ ሳይናገር የእግዚአብሄርን ቃል መያዝ አልቻለም ፡፡ ኤርምያስ በዘለፋዎቹ እና በበደሎቹ ደከመ (ቁጥር 10) ነገር ግን እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር “ እንደ ጨካኝ ኃያል “ (ቁጥር 11) ከእርሱ ጋር ነበር ፡፡ ኤርምያስ በእርሱ ላይ እየሆነ ስለ ነበረዉ ከማሰብ እግዚአብሄር ታላቅ እንደ ሆነ ወደማሰብ ዞር ፡፡ እግዚአብሄርን ያፌዙበትም የእግዚአብሄር ቁጣን ዉጤት ይሸከማሉ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሄርን አመሰገነ (ቁጥር 13) በመቀጠልም የተወለደባትን ቀን ረገመ (ቁጥር 14) ፤ ለአባቱም የመወለዱን ዜና ያመጣዉን ሰዉ የተረገመ እንዲሆን ጠየቀ (ቁጥር 15) ፤ ኤርምያስ ከኢዮብ 3 እየጠቀሰ ነበር ፡፡

በመሰረቱ እነዚህን ጥቅሶች ለራሳችን ነገሮች ልንጠቀምባቸዉ እንችላለን ፤ መጥፎ ሁኔታ በሚገጥም ጊዜ ተወልዳችሁ ባይኖር ኖሮ ምን እንደሚያመልጣችሁ አስቡ - በተለይም የእግዚአብሄር ደስታ ያመልጣችኋል ፡፡ በፍጥነት ወደ ጥሪያችሁ ተመለሱ !

ኤርምያስ (21፡ 1-10)፡ ከምዕራፍ 20 ወደ 21 ትልቅ የሆነ ለዉጥ አለ ፤ እስከዚህ ስፍራ ድረስ ኤርምያስ ሰብኮ ነበር ነገር ግን ማንም አልሰማዉም ነበር ፤ ይሁን እንጂ ንጉስ ሴዴቅያስ ጳስኮርን(ከምዕራፍ 20 የተለየ ሰዉዬን ) ባቢሎን ይሁዳን ታሸንፍ እንደሆነ ኤርምያስን እንዲጠይቅ ላከው (ቁጥር 1-2) ፡፡ በአንዳንድ ምክንያቶች ምናልባትም ኤርምያስ የእግዚአብሄርን መልዕክት በመታዘዝ መናገሩን ቀጥሎ ስለ ነበር ንጉሱ ኤርምያስ ምን ይል እንደ ነበር መስማት መፈለገ ፡፡ ኤርምያስ በእግዚአብሄር መልዕክት መለሰ - እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ በመዞር በይሁዳ ላይ በባቢሎናዊያን ይዋጋል (ቁጥር 3-6) ፡፡

ከባቢሎን ድል በኋላ እግዚአብሄር በከተማዋ ያሉትን ሰዎች እንዲገደሉ ለባቢሎናዊያን ይሰጣቸዋል (ቁጥር 7) ፡፡ ኤርምያስም ለሕዝቡ የእግዚአብሄርን መልዕክት በመስጠት (ቁጥር 8-10) በኢየሩሳሌም ከተማ የሚቀመጡ ከሆነ በሰይፍ፣ በርሀብ እና በወረርሽይ እንደሚሞቱ አስጠነቀቃቸው ፡፡ ከዚህ ፍርድ እንዲወጡ እግዚአብሄር መዉጫዉን ሰጣቸው ፤ ከተማዋን በመልቀቅ ወደ ከለዳዉያን የሚገባ በሕይወት መኖር ይችላል ፡፡ የተማረኩት ብቻ በህይወት ይኖራሉ ፤ ያ በአሁኑ ጊዜም እዉነት ነው ፡፡ ህይወት በኢየሱስ እግር ስር በመማረክ ይመጣል ፡፡ እግዚአብሄር ባቢሎናዊያን ከተማዋ እንደምትሰጣቸዉ እና እንደሚያቃጥሏት አወጀ ፡፡

ኤርምያስ (20፡ 11-14)፡ እግዚአብሄር የይሁዳ ንጉስ ቤት (የዳዊት ስርዉ መንግስት) እርሱን የማክበር እና መንግስቱን የማደስ ወይም አለመታዘዛቸዉን በመቀጠል በዳዊት ዙፋን መብታቸዉን እንደሚያጡት ምርጫ እንደ ነበራቸው ተናገረ (ቁጥር 11-12) ፡፡

ለማድረስ/ለመናገር ይህ ለኤርምያስ ጠንካራ መልዕክት ነበር ፤ ይሁን እንጂ ኤርምያስ ለጥሪዉ ታዛዥ እና የታመነ ነበር ፡፡ በኋላም ኤርምያስ ማበረታቻን ይሰጣል የእርሱ ቃልም ከእግዚአብሄር የሚመጣ እንደሆነ ስለሚያዉቁ ሕዝቡ ሊቀበሉት ይችላሉ ፡፡ ኤርምያስ እየሰበከ የነበረዉ ቁልፍ መማረክ ነው ፡፡

መደምደሚያ

በ1904 የአስራ ስምንት አመቱ ልጅ ዊልያም ቦርደን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በመመረቅ በሚሊዬነር ቤተሰቦቹ በአለም ዙሪያ ለጉብኝት የተላከ ነበር ፤ በአለም ዙሪያ እንደ ተጓዘ የቦርደን ልብ ባያቸዉ ኢየሱስን በማያዉቁት ሰዎች መሰበር ጀመረ ፡፡ በእርሱ መፅሀፍ የኃላ ገፅ ላይ “ ያልከማቸዉን “ መዘገበ ፡፡

በ 18 አመት እንደ አንድ ሚሊዮነር ከእግዚአብሄር ምንም ነገር በኋላዉ ለመደበቅ መሄዱን አልቀጠለም ፡፡ በያላ ዩንቨርስቲይ በብዛት የማይታረሙ ከሚመስሉ ተማሪዎች ጋር በካምፓስ ስለ ክርስቶስ ለመነጋገር በካምፓስ ላይ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት ቡድንን ጀመረ ፤ ቦርደን በተመረቀበት ጊዜ ከ1,300 ዉስጥ 1,000 ክርስቲያኖች ነበሩ ፡፡ ከያላ ከምርቃኑ በኋላ ቦርደን በቅዱስ መፅሀፉ የኃላ ገፅ ላይ ሁለት ቃሎችን ጨምሯል፡ “ አላፈገፍግም “

በኃብቱ ላይ ለመደገፍ የሚጓዝ አልነበረም ወይም ሚሽነሪይ ለመሆን ሁሉንም ነገር ወደ ኋላ ተወ ፡፡ ቦርደን በመቀጠልም በፕሪስቶን ት/ቤት የምርቃን ጥናቱን በመከታተል በምርቃን ላይም ለማገልገል ወደ ቻይና ተጓዘ ፡፡ አረበኛን ለመማርም በግብፅ ላይ ስለቆመ ከሙስሊሞች ጋር መስራት ቻለ ነገር ግን በዋነኛ/በኃይለኛ ማጅራት ገትር ተያዘ ፤ በአንድ ወርም ዉስጥ ሞተ ፡፡ ይህ ከሞቱ በኋላ በመፅሀፉ የመጨረሻ ገፅ ላይ ሁለት ቃላትን ጨምሮ ይገኛል ይላል፡ “ አልፀፀትም “ ፡፡

እግዚአብሄር ታማኞች እንድንሆን እንጂ ታላቅ እንድንሆን አልጠራንም ፤ ኑሮአችንን ከስሩ እንድንጥለው ጠርቶናል ፡፡ እንድንማረክ ጠርቶናል ፡፡ ድርሻዉን በማኝነት ልክ እንደ ኤርምያስ በሚወጣ አንድ ሰዉ የምትደሰቱ አይደላችሁም ? ሌሎች ኑሮአቸዉን እንዲያስማርኩ በእነርሱ ላይ የተጠራ ቢሆንም እንኳን ራሱን አስማረከ ፡፡

2 “No Reserves. No Retreats. No Regrets. William Borden’s Life.” Available at http://home.snu.edu/~hculbert/regret.htm.

3 “No Reserves . . .”

4 “No Reserves . . .”

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 107.

ጥያቄዎች

  1. በኤር (20፡ 9) ኤርምያስ ተሰምቶት እንደ ነበረዉ የተሰማችሁ ጊዜ ነበር ? ሁኔታዎቹ ምን ነበሩ ?
  2. ኤር (20፡ 12) በፍርኃት ይሞላችኋል ወይስ ስለራሳችሁ ልብ እንድታስቡ ያደርጋችኋልስ ? ጥቂት ደቂቃን በመዉሰድ ልባችሁን እንዲመረምር እና ካለም ጉዳዩን እንዲገልጥላችሁ እግዚአብሄርን ጠይቁት
  3. ኤርምያስ በኤር (20፡ 13) እግዚአብሄርን ከማመስገን በሚቀጥሉት ጥቅሶች ዉስጥ የራሱን መወለድ ወደ መራገም ለምን እንደሄደ ምን ታስባላችሁ ? ተወልዳችሁ የነበረበትን ቀን ተራግማችሁ ታውቃላችሁ ? ለምን ?
  4. በኤርምያስ (20-21) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 20:10–11

“For I have heard the gossip of many people, ‘Terror is on every side! Report him; let’s report him!’ Everyone I trusted watches for my fall. ‘Perhaps he will be deceived so that we might prevail against him and take our vengeance on him.’ But the LORD is with me like a violent warrior. Therefore, my persecutors will stumble and not prevail. Since they have not succeeded, they will be utterly shamed, an everlasting humiliation that will never be forgotten.”

ካህኑ ጳስኮር ኤርምያስን መታው ከዚያም በእግር ግንድ ውስጥ አኖረው ፡፡ ኤርምያስም ስቃይና ውርደት ከደረሰበት በኋላ ተለቀቀ ፡፡ ኤርምያስም በቅርቡ ከእግዚአብሔር ስለሚቀበለው ቅጣት ጳስኮርን አስጠነቀቀው ፡፡ ነገር ግን ከዚያ ኤርምያስ ለህዝቡ መናገር የሚያቆምበትና ፊቱን ወደ እግዚአብሔር የሚመልስበት ጊዜ መጣ ፡፡ ኤርምያስም ሁሉንም ነገር ማለትም ፡- የሚያሳስበውን ነገር ሁሉ ፣ እያንዳንዱን ጭንቀቱንና የሚያስፈራውን ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ ፡፡ በእግዚአብሔርም ፊት ካደረገው የታማኝነት ለቅሶ ጩኸት በኋላም ኤርምያስ እግዚአብሔር በመከራው ውስጥ አብሮት እንደነበር እና እግዚአብሔር እንደሚዋጋለት ያምን ነበር ፡፡

የገጠመህ መከራ ስቃይ ምንም ይሁን ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ ፡፡ ሙሉ ልብህን ለእርሱ ስጠው ፡፡ በማስታወሻ ጻፈው ወይም ተንበርክከህ እጆችህን ወደ ላይ አንሳ ፡፡ ወደ እርሱም ስትጮኽ ስታለቅስ እያንዳንዱን ጭንቀት ፣ ሸክም ፣ ቅሬታ ፣ ወድቀት ፣ አሳብ በጌታ ፊት አቅርብ ፡፡ ጌታን እንድፈውስህ ጠይቀው ፤ እውነቱን እንድገልጥልህ ጠይቀው ፤ በመከራ ውስጥ በስቃይ ውስጥ ሳለህ እርሱ ወዴት እንደነበር ጠይቀው ፡፡ ከዚያም እርሱን አዳምጠው ፡፡ አዳምጠው ለአንተ ያለውን ፍቅር በጆሮኽ ሲያንሾካሹክ ፡፡ አንተ ተዋጊ ነህ ፡፡ እግዚአብሔርም ስለአንተ እየተዋጋ ነው ፡፡ እግዚአብሔር በመካከልህ ባለህበት አለ ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት አልቅስ ፤ በዚህም አስከፊ ወቅት እንድሸከምህ ፍቀድለት ፡፡ ትቀጥላለህ ፡፡

“ የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል ። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ ፦ ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን ይላሉ ። እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው ፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም ፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ ። “

  • ኤርምያስ 20፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 34:17-18 — “ ጻድቃን ጮኹ ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው ። እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል ። “

ኤርምያስ 20:7, 12 — “ አቤቱ ፥ አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም ፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል ………. አቤቱ ፥ ጻድቅን የምትመረምር ኵላሊትንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ ፥ ክርክሬን ገልጬልሃለሁና በቀልህን በላያቸው ለይ ። “

ሶፎንያስ 3:17 — “ አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው ፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል ፥ በፍቅሩም ያርፋል ፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል ። “