The Potter's House Sermons
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 18-19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምዕራፍ (18-19) እና የምዕራፍ 20 ክፍል በኤርምያስ ካጠናናቸዉ ሌሎች ምዕራፎች የተለዩ ናቸው ፡፡ በእነዚህ ምዕራፎች ዉስጥ ኤርምያስ ወደ ሸክላ ሰሪዉ ቤት “ የመስክ ጉዞን “ አደረገ ፤ የሁለቱም ምዕራፍ ጭብጥ ሸክላ ሰሪ የሚል ነው ፡፡ ምሁራንስ እነዚህን ምዕራፎች የሸክላ ሰሪዉ ቤት ስብከት በማለት ይጠቅሱታል ፤ እነዚህ ምዕራፎች ወደ ሰዎስት ክፍል ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡ የሸክላ ሰሪዉ የፍርድ ምሳሌ (18፡ 1-23)፣ ለተሰበረ ገንቦ የምልክት ድርጊት (19፡ 1-15) እና ስሙ ማጎርሚሳቢብ የተባለዉ ጳስኮር ነቢዩንም አሰረው (20፡ 1-6) ፡፡ ምዕራፍ 18 ወደ ሰዎስት ክፍል የተከፈለ ነው፡ የሸክላ ሰሪዉ ምሳሌ (ቁጥር 1-11)፣ ሕዝቡ በእግዚአብሄር ተገፉ/ተቀባይነት አላገኙም (ቁጥር 12-17) እና የኤርምያስ ስደት/ስቃይ/መከራ (ቁጥር 18-23) ፡፡
የሸክላ ስራ ከ30 በላይ የዕብራዊያን ቃላት የሚገናኙበት እንዲዚህ አይነት ሁኔታን የያዘ በመፅኀፍ ቅዱስ ዘመን የኢኮኖሚይ ኢንዱስትሪይ ነበር ፤ ምናልባትም ኤርምያስ ቀድሞ ከሸክላ ሰሪዉ በፊት ቀድሞ እየተመላለሰበት ነበር፡፡ ይህ ጊዜ እግዚአብሄር እንዲያጋራው ኤርምያስን የተለዬ መልዕክት ሰጥቶታል ፤ በኋላም ኤርምያስ መልዕክቱን በመናገሩ ይታሰራል ፡፡ “ ሸክላ በራሱ የሚስብ/የሚያምር አይደለም ነገር ግን የሸክላ ሰሪዉ እጅ በሚነካዉ ጊዜ፣ የሸክላ ሰሪዉ ኃሳብ እንዲሸከመዉ በሸክላዉ ላይ በመጣበት ጊዜ፣ የሸክላ ሰሪዉ እቅድ በላዉላይ እና በዉስጡ በሚሆን ጊዜ እዉነተኛ የሆነ ለዉጥ እንዳለ “ አስታዉሉ ፤ በእስራኤል ሕዝቦች እግዚአብሄር መስራት የሚፈልገዉ ያን ነው - መሆን እንደሚችሉ ወደሚያዉቀዉ ቅርፅ እና መልክ ይቀርፃቸዋል/ያስቀምጣቸዋል ፡፡ ለእኛም ተመሳሳይ ነገርን ይፈልጋል ፡፡ ምናልባትም እነዚህ ክስተቶች በኢዮስያስ ልጅ የኤርምያስን የትንቢት መፅኀፍ ባቃጠለው በኢዮአቄም የንግስና ዘመን ተከስተዋል (ኤር 36፡ 21-23) ፡፡ ኢዮአቄም ለእግዚአብሄርም ለነቢያቱም ፍቅር አልነበረውም ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (18፡ 1-12)፡ ቻርለስ ኢ ጀፈርሰን ኤርምያስ “ እየፀለዬ በነበረ ጊዜ የሰዉነቱን እይታ አላገኘም የዕለት ተግባሩን ሲያከናዉን አንድ ሸክላ ሰሪን በተመለከተ ጊዜ አገኘ እንጂ ፤ እግዚአብሄር በእንግዳ ስፍራ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ገለፀለት “ ፡፡ ሸክላ ሰሪ በሻፍት ተያይዘዉ በነበሩ ሁለት ትይዩ ድንጋዮች ላይ እየሰራ ነበር ፤ በላይኛዉ ጎማ ላይ በሚሰራ ጊዜ የታችኛዉን ጎማ በእግሩ ያዞረዉ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ኤርምያስ “ ሸክላው የሸክላ ሰሪዉን እጅ እንዴት እንደተቋቋመው ያም እቃ ጠፍቶ እንደ ነበር ነገር ግን ሸክላ ሰሪዉ በትዕግስት ሸክላዉን በማቡካት ሌላ እቃ ሰርቶበት እንደ ነበር “ መመልከቱን ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ስዕል ለእስራኤል ሕዝብ መልዕክትን ለማቅረብ ተጠቀመበት (ቁጥር 6-10) “ ነገር ግን አተገባበሩ ግላዊ ነበር (ቁጥር 11-17) ከይሁዳ እና ከኢየሩሳሌም ሕዝቦች ምላሽን እየተጣራ ነበር “ ፡፡
እግዚአብሄር ኤርምያስን አንድን ሕዝብ ፈርዶበት ንስኃ ከገባ ፍርዱን መልሶ እንደሚወስደዉ በመግለፅ በአለም ላይ ልዓላዊ ኃይሉን አሳሰበው (ዮናስ 3) ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ከአንድ ሕዝብ ጋር የመባረክ ኪዳን ቢኖረዉም ያ ሕዝብ እርሱን ካልተቀበለው ከመባረክ ይልቅ ፍርድን ያመጣባቸዋል ፡፡ ኤርምያስ ከልባቸዉ ግትርነት የተነሳ መልዕክቱን ባይቀበሉም እንኳን እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ ችግር እንደሚያመጣ ከይሁዳ እና ከኢየሩሳሌም እንዲነጋገር ተሰጥቶታል (ቁጥር 11-12) ፡፡ ኤር (17፡ 9) ይህን ግትርነታቸዉን/እልኃቸዉን ያሳያል “ የሰዉ ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ እጅግም ክፉ ነው ፤ ማንስ ያዉቃል ? “
ኤርምያስ (18፡ 13-17)፡ በኔልሰን ማብራሪያ መሰረት “ የሊባኖስ በረዶ…… ከዮርዳኖስ ወንዝ አብዝኃኛዉን ዉኃ የሚሰጠዉን በኃይል የሚፈነዱበትን ሚንጮች የአርሞኒየም የዉሃ ስፍራን ይገልፃል ፤ አብዛኛዉን ጊዜ የእግዚአብሄር በረከት ከደረቅ ክልል ዉሃን በመስጠት ታይቷል (ዘጸ 17፡ 6) ፡፡ ለእንግዳ ምንም ሰዉ የቀዘቀዘ የምንጭ ዉኃ ወይም ለሌላ ዜጋ የሚሆን ዉኃ የሚነግድ አይኖርም “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ከራሱ ፍጥረታቶች (ቁጥር 15) ለእነርሱ ንፁህ ዉኃን በሰጣቸዉ በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ይልቅ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ወደ ኃሰት አማልዕክት መመለሳቸዉን እያሳዬ እንደ ነበር በመግለፅ ይቀጥላል ፡፡ እግዚአብሄርን በመተዋቸዉ ምክንያት ምድሪቱ አስፈሪ ሆነች እንዲሁም የሚያልፉት ሁሉ በሚያዩት ነገር ራሳቸዉን ይነቀንቃሉ (ቁጥር 16, ኤር 48፡ 27, መዝ 109፡ 25) ፡፡
ኤርምያስ (18፡ 18-23)፡ የእግዚአብሄርን መልዕክት በመስማት ከመመለስ ይልቅ ሕዝቡ በኤርምያስ የተበሳጩ በመሆን የኤርምያስን መልዕክት እርሱን በመግደል ሊያስቆሙት እንደሚችሉ አሰቡ (ኤር 11፡ 19, 12፡ 6, 15፡ 15) ፤ ይህ ከክርስቶስ ህይወት ጋር የሚመሳሰል ሌላ ነው (ሉቃ 23፡ 1-5) ፡፡ ኤርምያስ ተሰምቶት በነበረዉ ተቃዉሞ መልካም ነገር ሊሰማዉ አልቻለም ነገር ግን ይህን እንደሚመጣ ይጠብቃል (ዮሐ 15፡ 18, 16፡ 33, 2ጢሞ 3፡ 12) ፡፡ ኤርምያስ ወደ እግዚአብሄር እንዲያደርግ ጠይቆት የነበረዉን እንዳደረገ እና ሕዝቡም ከእርሱና ከእግዚአብሄር መልዕክት ዞር እንዳሉ ሊነገረዉ ተመለሰ (ቁጥር 19) ፤ ሕዝቡ የኤርምያስን አካል ለመቅበር እንኳን ሳይቀር ጉድጓድን ቆፈሩ (ቁጥር 20) ፡፡ ዋይርስቤ ይህ ኤርምያስ እንዴት የታዬ ሆኖ እንደ ነበር ለማዘን በእግዚአብሄር ፊት ለአምስተኛዉ ጊዜ እንደሆነ ያመለክታል ፡፡
ኤርምያስ (19፡ 1-9)፡ በቁጥር (1-3) እግዚአብሄር ኤርምያስን መልሶ አንድ የሸክላ ማሰሮ እንዲገዛ ወደ ሸክላ ሰሪዉ ቤት ላከው ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስን ከእርሱ ጋር የካህናት እና የሽማግሌዎች መሪን በመዉሰድ ሁሉም ሸክላ ሰሪዎች በሚሰሩበትና የሸክላዉን ስብርባሪ በሚጥሉበት በካርሲት በር አጠገብ መልዕክቱን እንዲያዉጅ ነገረው፡፡ ዋይርስቤ “ በእርሱ ላይ ክፉ ሴራቸዉን እያወቀ ከእነርሱ ጋር ለመጓዝ ፈልጎ እንደ ነበር ይህ የእምነቱ ማስረጃ ሲሆን ከኃጢዓታቸዉም የተነሳ ጥፋት ወደ ምድሪቱ እየመጣ ስለ ነበረ በታላቅ ድፍረት በፊታቸዉ እንደሚናገር “ ያመለክታል ፡፡ ዋይርስቤ “ ነገር ግን የይሁዳ ነገስታት አድርገዉት በነበረዉ ነገር፡ እግዚአብሄርን በመተዋቸው፣ ጣዖትን በማምለካቸው፣ ቤተ መቅደሱን በማርከሳቸው፣ ንፁኃንን በመግደላቸዉ እን ለባዖል በሚቃጠል እሳት መሰዊያ ላይ ልጆቻቸዉን በማቅረባቸው ምክንያት ኤርምያስ በሩን ወደ መድረኩ ላይ በመመለስ አስጊ የሆነዉን ጥፋት እንዳወጀ “ (ቁጥር 3-5) ያብራራል ፡፡ በቁጥር 4 መሰረት ሕዝቡ ቤተሰቦቻቸዉም የይሁዳ ነገስታቶችም ሁለቱም የማያዉቋቸዉን ጣዖታትን ማምለክን መረጡ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ከግዑዝ አካላዊ ቁስ ጋር መቀራረብ እንደማይቻል ስለ ግል እዉቀት ስለ መቀራረብ የሚናገረ ቃል “ ማወቅ “ የሚለዉ እንደሆነ “ ይገልፃል፡፡ (ማቴ 7፡ 22-23, ሉቃ 13፡ 25-27) ፤ ቁጥር 6 የሄኖም ሸለቆ ከባቢሎን ወረራ በኋላ የማረጃ ሸለቆ ሆኖ ይቆያል ፡፡
ኤርምያስ (19፡ 10-15)፡ እግዚአብሄር ኤርምያስን በቁጥር 1 ገዝቶት የነበረዉን እንስራ/ማሰሮ በመዉሰድ አብረዉት በሚሄዱት ሰዎች ፊት እንዲሰብረዉ ነገረው (ቁጥር 10) ፡፡ ኤርምያስም እግዚአብሄር በተመሳሳይ መንገድ አመፃቸዉን እና የማትታዘዘዉን ከተማ እንደሚሰብር ይነግራቸዉ ነበር (ቁጥር 11-13) ፤ በመቀጠለም ኤርምያስ ወደ ቤተ መቅደስ በመሄድ እንደ ገና ተመሳሳይ መልዕክትን አጋራ (ቁጥር 14-15) ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ ሕዝቦች ወይም ግለሰቦች እግዚአብሄር ማደስ የማይችለዉን ያክል ታላቅ ኃጢዓት ማድረግ ይችላሉ ? አዎ ይችላሉ ፤ ሸክላዉ በሸክላ ሰሪዉ እጅ መሰራት እስከሚችል ድረስ እንደ ገና ወደ ሚፈልገዉ መስራት ይችላል (18፡ 4) ነገር ግን ሸክላዉ ጠንካራ በሆነ ጊዜ ለማስተካከል በጣም ይዘገያል ፡፡ ፍርድ ለፍቃደኛ ከሀዲዎች ብቸኛዉ መልስ ነው “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡ የእስራኤል ሰዎች በእግዚአብሄር ላይ በማመፅ ንስኃ ለመግባት እምቢ ባሉ ጊዜ እግዚአብሄር አሶራዊያን በምርኮ እንዲወስዷቸዉ ፈቀደ ፤ የይሁዳ ሰዎች እግዚአብሄርን በተዉት ጊዜ በባቢሎናዊያን በኃይል ምርኮ ገጠማቸው ፡፡ አይሁዶች ክርስቶስን ባለመቀበል ሰቅለዉት ከነበር በኋላ ከ40 አመታት በኋላ ባቢሎናዊያን ከመቶ አመታት በፊት አድርገዉት እንደ ነበረው ነገር ሮማዉያን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ ፡፡ በልባችሁ ላይ የደንዳናነት ሽፋኖች እንዳሉ ከተሰማችሁ እግዚአብሄርን ይቅር እንዲላችሁ፣ እንዲሰራችሁ እና እናንተን ማየት በሚፈልግበት ቅርፅ እንዲያስቀምጣችሁ ጠይቁት (2ቆሮ 4፡ 7) ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 104.
J. Wilbur Chapman, Revival Sermons (New York: Fleming H. Revell, 1911), p. 102; quoted in Wiersbe, p. 103.
Charles E. Jefferson, Cardinal Ideas of Jeremiah (New York, Macmillan Co., 1928), p. 102; quoted in Wiersbe, p. 104.
Wiersbe, p. 104.
Wiersbe, p. 104.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 906.
Nelson’s Commentary, p. 906.
Wiersbe, p. 105..
Wiersbe, p. 105.
Wiersbe, p. 106.
Wiersbe, p. 106.
Nelson’s Commentary, p. 907.
Wiersbe, p. 106.
Wiersbe, p. 106.
ጥያቄዎች
-
መፅሀፍ ቅዱስን ለማያዉቅ ሰው ኤር (18፡ 3-6) እንዴት ትገልፁታላችሁ ? ቁጥር 6 ማጥናት ምን እንዲሰማችሁ ያደርጋል ? ለምን እንደሆነ ግለፁ
-
በኤር (18፡ 11) ኤርምያስ ሕዝቡ ካልተቀየረ ከእግዚአብሄር ስለሚመጣዉ ጥፋት ተነግሮታል ፤ የአሁኑ ዘመን ኤርምያስ በመቆም ተመሳሳይ መልዕክት ከሰጣችሁ ዉጤቱ የተለዬ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በኤርምያስ 19 የተሰባበረዉ እንስራ በይበልጥ ለኤርምያስ (ኤር 18፡ 3-6) ወይስ ለካህናቱ እንደ ነበር ታምናላችሁ ? ለምን ?
-
በኤርምያስ (18-19) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 19:15
“This is what the LORD of Hosts, the God of Israel, says: ‘I am about to bring on this city—and on all its dependent villages—all the disaster that I spoke against it, for they have become obstinate, not obeying My words.’”
እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርምያስ ወደ ሸክላ ሰሪው ቤት እንድሄድና የሸክላ ገንቦ እንድገዛ ነገረው ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር የሸክላውን ገንቦ እንድወስድና እርሱ የሰጠውን ቃል እንድያውጅበት አዘዘው ፡፡ በአጠቃላይ መልዕክቱ እግዚአብሔር እንደ ሸክላ እቃ ስባሪ ህዝቡን ይሰባብራል ነው ፡፡ ኤርምያስ በመታዘዝ እግዚአብሔር ባዘዘው ቦታ ላይ በመቀመጥ በህዝቡ ፊት ገንቦውን ሰባበረ ከዚያም ከእግዚአብሔር የተነገረውን ይህን ቃል ተናገረ ፡- ስለ አለመታዘዛችሁ በእናንተ ላይ በህዝባችሁና በምድራችሁ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ ፡፡
ቀላል አይደለም ሌሎችን አትታዘዙም ብሎ መናገር ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቢያዝህስ በሆነ ሰው ህይወት ውስጥ ስላለው ኃጢአት እንድሁም በህይወታቸው ላይ ስላመጡት ጥፋት እንድትነጋር ቢመራህ ? በጣም ደፋር ሆነህ ታውቃለህ ? በጣም ደፋር ለመሆንስ ትፈልጋለህን ? እንዳንድ ጊዜ የአንተ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ለሆነ ሰው ጥቅም ነው ፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር ጓደኛህን ስለሰራው ወይም ስለሰራችው ኃጢአት ወይም ደግሞ ስለተሳሳተ ውሳኔው እንድታወራው ሊያዝህ ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትን ያያል መታዘዝንም አጥብቆ ይመለከታል ፡፡ ዛሬ ራስህን ጠይቅ ፡- እግዚአብሔር እንዳደርገው ላዘዘኝ ነገር በመታዘዝ እየተራመድኩ ነውን ? ላደርገው እንደሚገባ የማውቀው ነገር ግን በፍርኃት ምክንያት ያላደረኩት ነገር አለን ? ፍርኃትህን አሸንፍ እና በመታዘዝ ደፋር ሁን ፡፡ በየጊዜው ወደፊት አንድ እርምጃ ስትራመድ ጌታ ብርታትና ጸጋ ይሰጥሃል ፡፡ ታዛዥ ለመሆን ወስን ፡፡
“ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ ። “
- ኤርምያስ 19፡15
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 29:29 — “ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው ። “
ኤርምያስ 19:10–11 — “ ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ደግሞም ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል ፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ ። “
1ኛ ዮሐንስ 2:5–6 — “ ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል ። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን ፤ በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።