Life As An Object Lesson
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 15-17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የኤርምያስ ምዕራፍ በዚህ ምዕራፍም ዉስጥ ብዙ አይቀየርም ፤ የእግዚአብሄርን መልዕክት በመታዘዝ የኤርምያስን መዋጀት ለማየት እናያለን ፡፡ እንደ አንድ ነቢይ ኤርምያስ ያወጃቸዉን ቃላቶች ገጥሞታል ፤ ለምሳሌ ኤር (14፡ 7) “ አቤቱ ኃጢዓታችን ብዙ ነዉና በአንተም ላይ ኃጢዓት ሰርተናልና ኃጢዓታችን ይመሰክርብናል ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ “ አለ ፤ እግዚአብሄርም ለኤርምያስ በ(14፡ 11)፡ “ እግዚአብሄርም ፡- ለዚህ ሕዝብ ስለ መልካም አትጸልይላቸዉ “ በማለት መለሰለት ፤ እስራኤል ለኤርምያስ መልዕክት በምላሹ ንስኃ ገብቶ አልነበረም ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ 15፡ በምዕራፍ 14 እግዚአብሄር ለኤርምያስ ለሕዝቡ መፀለይን እንዲያቆም ከነገረዉ በኋላ እግዚአብሄር ሙሴ እና ሳሙኤልም እንኳን ለሕዝቡ ቢፀልዩም እንኳን እንደማይሰማቸዉ ነገረው (ቁጥር 1) ፡፡ በቁጥር 10 ኤርምያስ ለእግዚአብሄር ቅሬታን ተናገረ ፡፡ ከመልዕክቱ የተነሳ በሕዝቡ ጥያቄ ደክሞ ነበር ፤ ምንም እንኳን ኤርምያስ ጥቂት ቅሬታዎች ቢኖሩትም በእግዚአብሄር ቃል ደስታን አገኘ (ቁጥር 16) ፡፡
ኤርምያስ በእግዚአብሄር ቃል ምግቡን አገኘ ፡፡ ኤርምያስ ዕብ (4፡ 12) ስለሚናገረዉ እዉነት ያውቃል “ የእግዚአብሄር ቃል ሕያዉ ነዉና የሚሰራም ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል “ ፤ ኤርምያስ በእግዚአብሄር ቃል መፅናናትን አገኘ ፡፡ ያ ተመሳሳይ መፅናናት ምንም ሁኔታ ቢያገኘን የምናገኘዉ ነው ፡፡
ኤርምያስ (16፡ 1-4)፡ ይህ ምዕራፍ ኤርምያስ እንደ እግዚአብሄር ነቢይ በመታዘዝ ያደርጋቸዉ የነበሩትን ዝርዝር ነገሮች ያቀርባል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኤርምያስ ህይወት የሕዝቡ ትግልን ትግል የሚወክል ድርጊት እንደሆነ “ ይፅፋል ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስ እንዲያደርገዉ ያዘዘዉ ማንኛዉም ነገር እስራኤል እየደረሰባትን ነገር የሚያመለክት ወይም ቆይታ የምታልፈበት እንደሆነ ይወክላል ፤ ይህ ለእግዚአብሄር ለሕዝቡ መልዕክት ለመላክ ያልተለመደ መንገድ አልነበረም ፡፡ ቶምሰን “ የሆሴዔ የማያስደስት ጋብቻ (ሆሴዕ 1-3)፣ የኢሳይያስ ቤተሰብ (ኢሳይያስ 7-8)፣ የሕዝቅኤል ሚስት መሞት (ሕዝ 24፡ 15-27) እና ሳያገባ እንዲሆን የኤርምያስ መጠራት ሁሉም በቤተሰብ ክስተት ዉስጥ የእግዚአብሄር ቃል መታወጅ ምሳሌዎች እንደሆኑ አመልክቷል “ ፡፡
እግዚአብሄር ኤርምያስን ልጅ እንዳይኖረዉ እና እንዳያገባ አዘዘው ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ ትልቅ/ሰፊ ቤተሰብ የእግዚአብሄር በረከት ማሳያ በሆነበት ባህል ትክክል እንዳልሆነ ተመልክቶታል ፡፡ የማያገባ አንድ ነቢይ ፍላጎቱን የሚናገር የእግዚአብሄር በረከትን ከማይቀበል ነቢይ ጋር እኩል ነበር ፡፡ ባቢሎናዊያን በይሁዳ ላይ በመጡ ጊዜ የእግዚአብሄርን ሰዎች ከሚጠብቃቸዉ ቁጣ የተነሳ እግዚአብሄር ኤርምያስን ትዳር እና ልጆች እንዳይኖረዉ ከለከለዉ (ቁጥር 4) ፡፡
መዝ (137፡ 8-9)በዚህ ገለፃ፡ “ አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው ፡፡ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው “ ፤ በዚህ መንገድ እግዚአብሄር ኤርምያስን ከማግባት በመከልከል ይህ በልጆቹ ላይ ሲሆን ከማየት ኤርምያስን አዳነው ፡፡ ይህ የመጨረሻዉ ዘመን ጥላ/ማሳያ ነው፡ “ እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለዉን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችዉ ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢዉ ያስታዉል በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለዉን ሊወስድ አይዉረድ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ ፡፡ በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው ፡፡ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ “ (ማቴ 24፡ 15-20) ፡፡ ነገሮች ልጆቻችሁን ማዳን የምትፈልጉበት አስቸጋሪ ይሆናሉ ፡፡
ኤርምያስ (16፡ 5-9)፡ ኤርምያስ ከኃዘንም የተከለከለ ነበር ፤ ብዙ ሕዝቦች የማህበራዊ አቋቋማቸዉ ምንም ቢሆንም በእግዚአብሄር ፍርድ ይሞታሉ ፤ በእርግጥም አብዛኛው አሁንም የሚኖሩት “ ለእነርሱ ራሳቸዉን መላጨት ወይም ሰዉነታቸዉን መንጨት “ አይችሉም (ቁጥር 6) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ራስን መንጨት እንደ የጣዖት የማዘን ስርዓት በማለት ገልፆታል ፡፡ ኤርምያስ ከሚመጣዎ ከእግዚአብሄር ፍርድ የተነሳ በኃዘን የሚሳተፍ አልነበረም ፡፡ ኤርምያስ ከሕዝቡ ጋር እንዲፆም አልተፈቀደለትም ነበር (ቁጥር 8) ፤ እግዚአብሄር “ ከዚህ ስፍራ በዓይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ አጠፋለሁ “ በማለት ቃል ገባ (ቁጥር 9) ፡፡
ኤርምያስ (16፡ 10-13)፡ ለኤርምያስ መልዕክት በምላሹ እስራኤላዊያን ሰዎስት ጥያቄዎችን ይጠይቃል፡ “ ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሄር ተናገረብን ? በደላችንስ ምንድር ነው ? በአምላካችንስ በእግዚአብሄር ላይ የሰራነው ኃጢአታችን ምድር ነው ? “ (ቁጥር 10) እስራኤላዊያን ሙሉ ለሙሉ ኃሳቡን ስተዉት ነበር ፡፡ ሕዝቡ እንዴት ትተዉት እንደ ነበረዉ እግዚአብሄር እንዳሳየው የኔልሰን ማብራሪያ እስራኤል እንዴት ሙሉ ለሙሉ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረዉን ኪዳን እንደተው ይፅፋል ፡፡ የሕዝቦቹ አባቶች መጀመሪያ እግዚአብሄርን የተዉ ቢሆንም (ቁጥር 11) የወቅቱ ትዉልድ ግን “ ከአባቶቻቸዉ የበለጠ ክፋትን አደረጉ “ (ቁጥር 12) ፡፡ ጥፋተኝነታቸዉ በቀላሉ በቤተሰቦቻቸዉ ማለፍ አልቻሉም ፤ ለራሳቸዉ ኃጢዓት ተጠያቂዎች ነበሩ ፡፡ እስራኤላዊያን ለ70 አመታት “ ቀንና ሌሊት ጣዖትን ወደሚያመልኩበት “ (ቁጥር 13) ወደ ባቢሎን የተላኩ ይሆናሉ ፡፡
ኤርምያስ (16፡ 14-15)፡ ከዚህ ሁሉ መጥፎ ዜና በኋላ እግዚአብሄር በኤርምያስ በኩል ጥቂት መልካም ዜናዎችን ሰጣቸው ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ሕዝቡን መልሶ ወደ እስራኤል ያመጣቸዋል ፡፡
ኤርምያስ (16፡ 16-21)፡ ነገሮች የተሸሉ ከመሆናቸዉ በፊት ነገሮች መጀመሪያ አስቸጋሪ ይሆናሉ ፡፡ የባቢሎናዊያን ሰራዊት የእግዚአብሄርን ሰዎች ለማደን/ለመያዝ በመላዊ አገሪቱ ዉስጥ ይሄዳሉ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በቁጥር 16 የማደን እና አሳ የማጥመድ ቋንቋዎች ከኃግር የማስወጣት ዘይቤ ነው ፡፡ ሕዝቅኤል በሕዝ (12፡ 13) ተመሳሳይ ዘይቤ / አነጋገር ተጠቅሟል፡ “ መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል ወደ ከለዳዉያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ ፤ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል “ ፤ አሞ (4፡ 2) “ ጌታ እግዚአብሄር እናንተን በሰልፍ ዕቃ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን እነሆ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነትቱ ምሎአል “ ፡፡
ኤርምያስ 17፡ በሰዉ መታመን ከንቱ ነው (ቁጥር 5) በእግዚአብሄር የታመነ ሰዉ ግን የተባረከ ነው (ቁጥር 7) የሰዎች ልብ “ ክፉ “ ሲሆን (ቁጥር 9) እግዚአብሄር ብቻ በሚገባ የሰዉን ልብ ማወቅ ይችላል (ቁጥር 10) ፡፡
መደምደሚያ
የኤርምያስ መልዕክት ለእስራኤል የሚያስደስት አልነበረም ፡፡ ኤርምያስ ፍርድን ቢናገርም እግዚአብሄር ሕዝቡን ወደ ምድራቸዉ እንደሚመልሳቸዉ ተስፋን ገባ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 903.
John Arthur Thompson, The Book of Jeremiah (Grand Rapids: Eerdman’s, 1980), p. 403; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 164; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf.
Nelson’s, p. 903.
Nelson’s, p. 903.
Nelson’s, p. 904.
Nelson’s, p. 904.
ጥያቄዎች
-
የሙሴ እና የሳሙኤል ፀሎት/ምልጃ በእስራኤል ላይ የእግዚአብሄርን ፍርድ የተለዬ ለምን አያደርገውም ? (ኤር 15፡ 1, 26፡ 3)
-
በኤር (15፡ 19) እግዚአብሄር ኤርምያስን ምን እንዲያደርግ አዘዘው ? ለእስራኤል የኤርምያስ ሚና ምን ነበር (ኤር 6፡ 27) ? ንስኃ ከገበ ለኤርምያስ የእግዚአብሄር ተስፋ ምን ነበር ?
-
በኤር (16፡ 1-4) ኤርምያስ እንዳያገባ እና ልጅ እንዳይኖረዉ ለመፈለጉ ከኃላ የእግዚአብሄር ምክንያት ምን ነበር (1ቆሮ 7፡ 26-34) ? ኤርምያስ ወደ እግዚአብሄር ሕዝብ በሚመጡት በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜዎች እንዴት እንደሚያልፍ ምን ታስባላችሁ ? (ኢሳ 63፡ 7, ኤር 9፡ 24, 16፡ 15)
-
እግዚአብሄር በሕዝቡ ላይ እንደዚህ አይነት ኃይለኛ ፍርድ የሚያመጣዉ ለምን ነበር (ኤር 16፡ 10-13) ? በወቅቱ ጊዜ ለእስራኤል ተስፋዋ ምን ነበር ?
-
በኤርምያስ 17እምነታቸዉን በሰዉ ላይ በሚያደርጉት ላይ ምን ሆነ (ኢሳ 2፡ 22, ማቴ 7፡ 24-27) ? እምነታቸዉን በእግዚአብሄር ላይ ባደረጉት ላይስ ምን ሆነ (መዝ 139፡ 10, ምሳ 3፡ 5-6) ? በህይወታችሁ ከእግዚአብሄር ይልቅ በሰዉ ላይ እምነታችሁን እንድታደርጉ የሚገፋ ምኞት አለ ?
-
በኤርምያስ (15-17) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 15:16–17
“Your words were found, and I ate them. Your words became a delight to me and the joy of my heart, for I am called by Your name, Yahweh God of Hosts. I never sat with the band of revelers, and I did not celebrate with them. Because Your hand was on me, I sat alone, for You filled me with indignation.”
ኤርምያስ እግዚአብሔር ጠላቶቹን እንድበቀልለት በጠየቀ ጊዜ ፣ የእግዚአብሔርን ቃል አግኝቶ “ በላው ፡፡ “ ኤርምያስም የእግዚአብሔርን ቃል እንዲህ በማለት ገለጸው ፡- “ ሀሴትና የልብ ደስታ ፡፡ “ በመከራ ውስጥ እንኳን ሳለ ፣ ኤርምያስ የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ እንደነበረች ያውቅ ነበር ፡፡ እግዚአብሔርን ከማይከተሉ ሰዎች ጋር ከመቀመጥ ይልቅ እርሱ ብቻውን ተቀመጠ ፡፡
እግዚአብሔርን መፈለግና ከእርሱ ጋር ባለህ የህይወት እርምጃ ማደግ ዝም ብሎ የሚሆን ነገር አይደለም ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መወሰን አለብህ ፡፡ ስልክህን አስቀምጠህ የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ መወሰን አለብህ ፡፡ በመገኘቱ ውስጥ ለመኖር መምረጥ አለብህ ፡፡ ለዓለም ፈተና እምቢ ማለትን መምረጥ አለብህ ፣ ብቻህን መሆን እንኳ ቢያስፈልግህ እምቢ ማለትን ምረጥ ፡፡ ከጌታ ጋር ፣ በቃሉ ደግሞም በመገኘቱ ውስጥ ጊዜን ለማሳለፍ የምታደርገው ውሳኔ ዋጋ አለው ፡- ቃሉ ምሪትን ይሰጣል ደግሞም ነገሮችን ይገልጣል ፤ መገኘቱም ደስ ያሰኛል በእርሱ ውስጥ ሰላም አለህ ፡፡ እርሱን ስትከተል እጁ በአንተ ላይ ናት ፡፡ በእርሱ ደስ በመሰኘት ጊዜን ለማሳለፍ ስትወስን ፣ ድልንና ነጻነትን ታገኛለህ ፡፡ ምርጫህን ዛሬ ምረጥ !
“ ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ ። በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ ። “
- ኤርምያስ 15፡16-17
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 16:11 — “ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ ። “
መዝሙር 119:105 — “ ሕግህ ለእግሬ መብራት ፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው ። “
ዕብራውያን 4:12 — “ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና ፥ የሚሠራም ፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው ፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል ፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።