Major Prophets Jeremiah

The Persecuted Prohpet

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 12-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 606 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የእግዚአብሄርን ቃል ስናጠና መፅሀፍት በዝርዝር ያስረዳናል ፤ ለእኛ ጠቃሚ እና በህይወታችን/በኑሮአችን መስራት ስለሚችል የእግዚአብሄርን ቃል እናጠናለን ፡፡ ቃሉን ስናጠና መንፈስ ቅዱስ በእኛ ዉስጥ እንደሚገኝ ተስፋ ማድረግ እንችላለን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ሊናገረን እንደሚችል መጠበቅ እንችላለን ፡፡ በ 2ጢሞ (3፡ 16-17) መሰረት “ የእግዚአብሄርም ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሄር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለዉ ምክር ደግሞ ይጠቅማል “ ፡፡ ብዙ ነገሮች በህይወታችን ዉስጥ ጠቃሚዎች ናቸው ፤ በእግዚአብሄር ቃል ዉስጥ ከሆንን አስፈላጊ እንደሆነ ያረጋግጥልናል ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ (12፡ 1-4)፡ ኤርምያስ የእግዚአብሄርን መልዕክት እያደረሰ ስለ ነበር ዛቻ/ማስፈራራት ደርሶበት ነበር ፡፡ በኤር (11፡ 21) ሕዝቡ ኤርምያስን በማስፈራራት ምንም አይነት ትንቢት እንዳይናገር ነግረዉት ነበር ፤ በኤርምያስ 12 ኤርምያስ የእግዚአብሄርን ቃል ሰብኮ እናየዋለን ነገር ግን ስለ ተናገረው ትንቢቱ የተጨነቀ ይመስላል ፡፡ ወደ እግዚአብሄርም “ አቤቱ ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር ፡፡ የኃጢዓተኞች መንገድ ስለ ምን ይቃናል ? በደልንስ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደኅንነት ይሆናል ? “ በማለት ፀለዬ ፡፡ ኤርምያስ አንስቶት የነበረዉ ጥያቄ ለምን ክፉዎች ይበለፅጋሉ የሚል ነበር ፡፡ ሕይወት ፍትሀዊ የምትሆን አይመስልም ፤ ኤርምያስ እንዳሳየው ሁል ጊዜ ስለ ፍቃዱ ከጥያቄአችን እና ከሀሳባችን ጋር በቀጥታ ወደ እግዚአብሄር መሄድ ብቸኛዉ እና የተሸለዉ ምርጫ ነው ፡፡

የይሁዳ ሰዎች በቅጣታቸዉ አካል በሆነው በርኃብ ዉስጥ እያለፉ ነበር ፤ ነገር ግን ኤርምያስ ህዝቡ መከራን በሚቀበልባት ተመሳሳይ ምድር ላይ የሚኖር ነበር ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሄርን ስለ ሁኔታዊ ምን ፍትኃዊ/ተገቢ እንደ ነበር ጠየቀው ፡፡

በቁጥር 3 ኤርምያስ እግዚአብሄርን ሁልጊዜ ለእርሱ የታመነ እንደ ነበር አስታወሰዉ ነገር ግን ነገሮች ትክክል የሚሆኑ አይመስልም ፡፡ ሁሉም ትዉልድ ተመሳሳይ ጥያቄን ጠይቀዉ ነበር ፤ ነገር ግን ቤዛነት በፍፁም ፍትሀዊ አልነበረም ፤ ሁሉም ህይወት ፍትሀዊ ኖሮ ቢኖን መስቀልን እናጠፋለን ፡፡ ስቅላቱ ፍትሀዊ አልነበረም ፤ ቸርነት ፍትሃዊ አልነበረም ፍቅር ነበር እንጂ፣ ይህ ወንጌል ነበር ፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሄር ፍትኃዊ እንደማይሆን ነገር ግን እግዚአብሄር መልካም እንደሚሆን ተረድቷል ፡፡

በነቢያቶች የታዩ የተለዩ ሂደቶች ነበሩ፡ መጀመሪያ ኃጢዓት ነበር ከዚያም ቀጥሎ ቅጣት በመጨረሻም መታደስ ነበር፡፡ በእነዚህ በእያንዳንዱ ስፍራ ላይ እግዚአብሄር በተለያዩ መንገዶች በሰዉ ላይ ያወሳል ፡፡ ሕዝቡ ተባርከዉ በነበረ ጊዜ ሁኔታው ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር ሳይሆን ከእግዚአብሄር ዞር ይሉ ነበር ፤ ሰዎች እግዚአብሄርን ሲረሱት እግዚአብሄር ከዙሪያቸዉ ዞር ይላል ፡፡ ከዙሪያ ያ መለስ ማለት የእኩሌታ የቤዛነት ክፍል/ቁራጭ ነበር ፡፡ በዚህ ሁኔታ/ስርዓት መጀመሪያ ላይ በሕዝቡ ድርሻ ላይ ትዕቢት ነበር ፡፡

ያዕ (4፡ 6) “ እግዚአብሄር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል “ ይላል ፡፡ ሕዝቡ በትዕቢት በነበረ ጊዜ እግዚአብሄር ከዙሪያቸዉ ዞር ለማለት እየሞከረ ነበር ፤ ይህም እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ እንደዞረ ገልጦአል ፡፡

ኤርምያስ (12፡ 5-17)፡ በመቀጠልም እግዚአብሄር ለኤርምያስ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስ ነገሮች አሁን አስቸጋሪ እንደ ነበሩ ካመነ የሚመጣ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደ ነበር አለ ፡፡

ኤርምያስ 13፡ በቁጥር 1 እግዚአብሄር ለኤርያስ የተናገረዉ ንግግር አለ ፡፡ እግዚአብሄር በተለዬ መልኩ ለኤርምያስ እየተናገረ ነበር ፤ የእግዚአብሄርን ድምፅ መስማት ለኤርምያስ ቁልፍ ነበር ፤ ከዚያም የሚከተለዉን አቅጣጫ ይከተላል ፡፡ ፈተናው በትክክል እግዚአብሄርን መስማት ነበር ፤ እግዚአብሄር ኤርምያስን የተልባ እግር የተሰራ መታጠቂያ በመግዛት ወገቡን እንዲታጠቅ አዘዘው ፡፡ በመቀጠልም እግዚአብሄር የተልባ እግር መታጠቂያዉን እየታጠቀ ወደ ወደ ኤፍራጠስ በመሄድ መታጠቂያዉን በተሰነጠቀ አለት ዉስጥ እንዲደብቀዉ አዘዘው ፡፡

የኤፍራጠስ መገኛ ያከራከረ ነዉ ነገር ግን በአጠቃላይ ከአቶንት ጥቂት ማይል እንደሚርቅ ይታመናል ፡፡ መታጠቂያዋ ከተደበቀች ብዙ ቀናት በኋላ ኤርምያስ መታጠቂያዋን ለማግኘት ተመልሶ በመሄድ እንዲፈልግ ተነግሮት ነበር ፤ ድርጊቱ ለኤርምያስ እግዚአብሄር የኢየሩሳሌምን ትዕቢት እንደሚያከስር ያረጋገጠለት ነበር ፡፡

ይህ ፅሁፍ እንደ እይታ የተፃፈ ነበር - በኤርምያስ ተተግብሮ የነበረ የመታዘዝ ምሳሌ/ንግግር ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ከሕዝቡ ጋር ለመነጋገር ማመሳሰልን ተጠቅሟል ፤ ሕዝቡ በትዕቢት በነበሩ ጊዜ ቆሻሻ ወይም የተበላሹ ነበሩ ፤ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር በተመለሱ ጊዜ የከበሩና የቀረቡ ይሆናሉ ፡፡ እግዚአብሄር የይሁዳን ትዕቢት ያጠፋል ፡፡

በኤርምያስ መፅኀፍት ዉስጥ ሕዝቡ አብዛኞቹ ነቢያቶች እንደተከተሉት በቅጣት ሁኔታ ዉስጥ ነበሩ ፤ ሕዝቡ ኃጢዓት ሰርቶ ነበር እንዲሁም ኤርምያስ ቅጣቱ እንደሚመጣ እየተናገረ ነበር ፡፡ በመጨረሻም ኤርምያስ ወደ መታደስ ደረጃ ይደርሳል ፡፡ የመታደስ/የመመለስ ቃላቶች በምዕራፍ (30-34) ይመጣሉ ፡፡

ሌላ ማመሳሰል/መግለጫ/ማሳያ ወይንን እና የወይን አቁማዳን በመጠቀም ያስተዋወቀ ነበር ፡፡ ሁሉም ሕዝብ ነገስታቶችን ጨምሮ በጨለማ ይሞላሉ ፤ እግዚአብሄር ርህራሄ አይኖረዉም ሕዝቡም ይጠፋሉ ፡፡ የፈራዉ ኤርምያስ ደግሞ ደግሞ ተመሳሳይ ሀሳብን ማድረጉን ቀጠለ ፤ የእግዚአብሄር ተስፋ ሕዝቡ በመጠኑም ቢሆንም ከዙሪያቸዉ ካለዉ ነገር በመመለስ ወደ እርሱ እንደሚመለሱ ነበር ፡፡

ኤርምያስ 14፡ ምዕራፍ 14 ርሀቡን ያመለክታል ፤ ዝናብ አልነበረም ፡፡ በቁጥር 7 ሕዝቡ በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓትን ሰርተዉ እንደ ነበር ስሜቱ ነበራቸው ነገር ግን ስለ እነርሱ እና ስለ እግዚአብሄር ስ ሲባል በቸርነት ተጠሩ ፡፡ ሕዝቡም በከፍተኛ ፍላጎት ዝናብ አስፈለጋቸው ነገር ግን እግዚአብሄር ፀሎታቸዉን አይሰማም ቁርባናቸዉንም አይቀበልም ፡፡

ኤርምያስ አስቸጋሪ ህይወት ነበረው ፤ በሕዝቡ የነበረዉ ሁኔታ እና በዚያን ጊዜ የይሁዳ ትዕቢት ለመፍታት አስቸጋሪ ነበር፣ በእግዚአብሄር እርዳታም እንኳን ለመድረስ ለኤርምያስም አስቸጋሪ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር በሚያድሰን እና ፀሎታችንን በሚመልስ ጊዜ በእግዚአብሄር በረከት ደስታ “ በዝናብ እንጨፍራለን/እንደሰታለን “ ፡፡ ፀሎታችንን ለእግዚአብሄር በማቅረብ በግል ህይወታችን ላይ የትዕቢት ስፍራ ካለ በምንጠይቅ ጊዜ የእግዚአብሄርን ተሀድሶ እንዲገጥመን እድልን ይፈቅድልናል ፤ እግዚአብሄር በሚያድሰን እና ፀሎታንን በሚመልስልን ጊዜ ብዙ በረከት ባለበት ስፍራ መኖር እንችላለን ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በኤርምያስ 12 በመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ዉስጥ ኤርምያስ እግዚአብሄርን ክፉዎች እንዲበለፅጉ ለምን እንደፈቀደ ይጠይቀዋል ፤ ይህ አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ? ለኤርምያስ የእግዚአብሄር መልስ ምን ነበር ? ከእግዚአብሄር የሆነ ማንኛዉንም ነገር ጠብቃችሁ ነበር ? የሚያስፈራ ነበር ? ከዚህ ምን ተማራችሁ?
  2. እግዚአብሄር በኤር (13፡ 1-5) ኤርምያስን ምን እንዲያደርግ አዘዘው ? ይህ መግለጫ/ማሳያ ምንን ያሳያል (ኤር 13፡ 7) ? ይህ ማሳያ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ምን እንዳቀደ ያሳያል ? (ኤር 13፡ 8-11)
  3. እግዚአብሄር ኤርምያስ (እንዲሁም ሌሎች ነቢያቶች)እንዲያደርጋቸው ያዘዛቸዉ ነገሮች ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ከተናገራቸዉ ጋር ተመሳሳይነት ነበራቸዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር በስዕል፣ በምሳሌ፣ በራዕይ ወይምበሕልም ለምን እንደሚናገር ምን ታስባላችሁ ?
  4. ኤር (13፡ 23) “ በዉኑ ኢትዮጲያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለዉጥ ዘንድ ይችላልን ? ይላል ፤ ኤርምያስ በዚህ ምን ማለቱ ነው (ምሳ 27፡ 22, ኤር 4፡ 22, ማቴ 19፡ 24) ? ከዚህ ጋር ልታገናኙት ትችላላችሁ ? አንዳንድ ጊዜ መንገዳችንን ለመቀየር ለምን በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን ምን ታስባላችሁ ? የድርጊታችሁ ዉጤት እንዴት ሌሎችን እና ከእግዚአብሄር ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንዴት እንደሚጎዳ አስባችሁ ታውቃላችሁ ?
  5. በኤር (14፡ 11) እንደ ገና እግዚአብሄር ኤርምያስን “ ለዚህ ሕዝብ አትፀልይ “ በማለት አዘዘው ፤ ይህ ከእግዚአብሄር የመጣ እንግዳ ነገር እንደሆነ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  6. በዚያን ጊዜ ስለ ነበሩ ሐሰተኛ ነቢያቶች እግዚአብሄር ምን አለ (ኤር 14፡ 14-16) ? አሁንም ሐሰተኛ ነቢያቶች እንዳሉ ታምናላችሁ ? ለድርጊታቸዉ መግለጫን/ዋጋን ይሰጣሉን ? በሐሰተኛ ነቢያቶች ወጥመድ ዉስጥ ላለመዉደቅ ቅድመ ጥንቃቄዉ ምንድን ነው ?
  7. በኤርምያስ (12-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 13:1–2

“This is what the LORD said to me: ‘Go and buy yourself a linen undergarment and put it on, but do not put it in water.’ So I bought underwear as the LORD instructed me and put it on.”

እግዚአብሔር ነቢያቶቹ ሁሉ ራሳቸውን ትሁት እንድያደርጉ እንዲሁም ለህዝቡ መልዕክቱን ለማድረስ ፈጥነው እንድታዘዙ ያዛል ፡፡ እግዚአብሔር ኤርምያስን ከተልባ የተሰራ መታጠቂያን እንድገዛ ፤ ሳያጥብም እንድለብሰውና ከዚያም በኋላ በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ እንድደብቀው አዘዘው ፡፡ ኤርምያስም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተከተለ ፤ እግዚአብሔርም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ታላቅ ትዕቢት ይንድ ዘንድ ኤርምያስ ለህዝቡ መልዕክቱን ለማድረስ ያሳየውን መታዘዝ ተጠቀመ ፡፡ ምክንያቱም በትዕቢት ልክ እንደ ኤርምያስ መታጠቂያ ይሁዳም ሊፈርስና ሊጠፋ ነበርና ፡፡

እግዚአብሔር ትዕቢትን ይጸየፋል ፡፡ እርሱ ትሁታንን ከፍ ከፍ ያደርጋል ፡፡ ዛሬ በየትኛው የህይወታችሁ ክፍል ውስጥ ስላለው ትዕቢት ንስሀ መግባት እንዳለባችሁ ጌታን ጠይቁ ፡፡ ልታውቁትም ላታውቁትም ትችላላችሁ ነገር ግን ትዕቢት በማንኛውም ሰው ህይወት ውስጥ ዘልቆ ሊገባ ይችላል ፡- በስራ ቦታ ፣ በቤተሰብ ፣ በትዳር ውስጥ እንድሁም ጠዋት ልብሳችሁን ስትለብሱ ጭምር በህይወታችሁ ውስጥ ትዕቢት ሊስተዋል ይችላል ፡፡ ልባችሁን መርምሩ ፡፡ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ከመከተል ይልቅ ሌሎች ስለሚያስቡት ነገር ትጨነቃላችሁን ? ፍጹም መታዘዝ በትህትና መመላለስን ይጠይቃል ፡፡ ሌሎች ስለሚያስቡት ነገር አትጨነቁ ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ከመራችሁና እንድታደርጉት ካሳሰባችሁ ፣ ዝምብላችሁ አድርጉት ፡፡ እግዚአብሔር መታዘዛችሁን ለክብሩ ይጠቀመዋል ፡፡

“ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል ፦ ሂድ ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ ፥ ወገብህንም ታጠቅባት ፤ በውኃውም ውስጥ አትንከራት ። እንደ እግዚአብሔርም ቃል መታጠቂያን ገዛሁ ወገቤንም ታጠቅሁባት ። “

  • ኤርምያስ 13፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 20:3–4 — “ እግዚአብሔርም አለ ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ ፥ እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን ፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል ። “

ያዕቆብ 4:10 — “ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል ። “

2ኛ ዮሐንስ 1:6 — “ እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው ፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት ። “