Curses Or Blessings: Disobedience Or Obedience
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 9-11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና በማምጣት ቤትን በማንፃ ስለ እስራኤል ጠላቶች የእግዚአብሄርን ጥንቃቄ ሰምተናል (ምዕራፍ 6) ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ አልሰሙት (ምዕራፍ 7-8) ፡፡ ኤር (8፡ 20-22) “ መከሩ አልፎአል በጋዉ ሄዶአል እኛም አልዳንነም……በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን ? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን ? የወገኔ ሴት ልጅ ፈዉስ ስለምን አልሆነም ? ይላል ፡፡
ዛሬ በኤርምያስ (9-11) ላይ እንመለከታለን ፡፡ መሸጋገሪያው በጥቅስ (9፡ 3) ላይ ይገኛል፡ “ ይህ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ /አዋጅ ነው “ (ቁጥር 6, 9, 13, 15, 22) ፤ ማብራሪያው በእግዚአብሄር ቃል ላይ ነው ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ 9፡ “ ተወግተዉ ስለሞቱት ዉድ ሕዝቦቼ ቀን እና ሌሊት አለቅሳለሁ “ የሚለዉ ንግግር የአልቃሻ ነቢይ መልኩን ያቀርባል (ቁጥር 1) ፡፡ የወንጌል እና የንስኃ ልብ በሚኖራችሁ ጊዜ ሰዎች የእግዚአብሄርን መልዕክት በመስማት አልቀበልም በሚሉ ጊዜ አለማልቀስ አስቸጋሪ ነው ፡፡ ይህ በኢየሩሳሌም ላይ የማልቀስ የክርስቶስ የሚያስደንቅ መልክ ነው ፡፡ ኤርምያስ እነዚህ አታላዮች እና አመንዝሮች ካሉበት ስፍራ ወደ ምድረበዳ ስፍራ መዉጣትን ናፈቀ (ቁጥር 2) ፤ ይሁን እንጂ ኤርምያስ ከሕዝቡ አልወጣም፣ በሰይፍ በአሕዛቦች መካከል ለሚበተኑት ሕዝቦች የእግዚአብሄርን መልዕክት ማድረሱን ቀጠለ (ቁጥር 16) ፡፡
ኤርምያስ ባላቸዉ ነገሮች እንዳይታበዩ ነገር ግን በሚታመን በእግዚአብሄር ፍቅር፣ ፍትሕ እና ፅድቅ በምድር ላይ እንዲመኩ ነገራቸው (ቁጥር 23-24) ፡፡
ኤርምያስ 10፡ ምዕራፍ 10 ወደ እግዚአብሄር ቤት አላማ ቀጠለ፡ “ አቤቱ እንደ አንተ ያለ የለም ፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው “ (ቁጥር 6) ፡፡ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ከማንም ጋር ማወዳደር አይቻልም ፤ እግዚአብሄር በኃይሉ አለምን ፈጥሯል ፡፡ በፍፁም ወደፊታችንን መተንበይ አንችልም ፡፡
ኤርምያስ 11፡ ኮንስታብል ቁጥር (1-7) “ እንደ ተሰበከ/እንደ ተጣሰ ኪዳን “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ኤርምያስ ሕዝቡን “ የዚህ ኪዳንን ቃል እንዲሰሙ “ እንዲነግራቸዉ የተጠራ ነበር ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኪዳን በግለሰቦች፣ በቡድኖች ወይም በሕዝቦች መካከል የሚደረግ ህጋዊ ስምምነት ነው - በእስራኤል ጉዳይ በሕዝቦች እና በአማልካቸዉ መካከል የተደረገ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ይህ ኪዳን በተለዬ ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ነበር (ቁጥር 2) ፡፡
በተጨማሪም የኔልሰን ማብራሪያ “ የመመለስ ቃላቶች የዘዳግም መፅኀፍት የዕብራዊያን ስም ሲሆን የኪዳንን ቃል ለመግለፅ ይጠቅማል “ በማለት ይናገራል ፤ በቁጥር 3 “ ርግማን/ተረገመ “ የሚለዉ ቃል በዘዳ (27፡ 26)(ዘዳግም 27-28) እንደ ተጠቃለለው ስለ ኪዳኑ አሉታዊ ነገሮችን እንደሚሰጥ ያመለክታል “ ፤ ለኪዳኑ መታዘዝ በረከትን አምጥቷል ፡፡
ይህ የእርግማን/የበረከት ግንኙነት እግዚአብሄር ዕብራዊያንን ከግብፅ በማዉጣት በዚያ ከገጠማቸዉ አስቸጋሪ ነገሮች ባራቃቸዉ ጊዜ የተመሰረቱ ነበሩ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ይህ በግብፅ የነበረዉ መከራ አስታዋሽ በባቢሎናዊያን የሚመጣዉ ባርነት ጥላ ነው ፡፡ እግዚአብሄር አባቶቻቸዉን እግዚአብሄርን የታዘዙትን ከግብፅ ባወጣቸዉ ጊዜ እንደ ነበረዉ ማስጠንቀቂያዉ ተመሳሳይ እንደ ሆነ በመላዉ ይሁዳና ኢየሩሳሌም እንዲናገር ነገረው (ቁጥር 6-7) ፤ እግዚአብሄር ኤርምያስን ሁሉንም ሕዝብ የእግዚአብሄርን ጥሪ እንዲታዘዙ እንደጠራቸው በመናገር በሁሉም የይሁዳ ከተሞች ዉስጥ እንዲመላለስ አዘዘው ፤ በተመሳሳይ እግዚአብሄር በመንገዶች በመመላለስ ለነኔዌ ሰዎች ማስጠንቀቂያዉን እንዲናገር ዮናስን ተጠቅሞበታል (ዮና 3፡ 1-6) ፡፡
ምንም እንኳን ሕዝቡ ባይቀበለዉም የኤርምያስ መልዕክት ተስፋ ነበር ፤ (ማቴ 10፡ 5-15, 28፡ 18-20, ሉቃ 8፡ 1, ሮሜ 10፡ 15) ፤ ኢየሱስም ለሕዝቡ የመታዘዝ የእግዚአብሄርን ጥሪ እንዲናገሩ ደቀ መዛሙርቱን ላከ ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች ያለሟቋረጥ ከእግዚአብሄር መንፈስ እንደምንሰማ አምናለሁ ነገር ግን የራሳችንን ድምፅ እንደሰማን በማድረግ ራሳችንን ለማሳመን እናዘነብላለን ፡፡
ኤርምያስ (11፡ 8-10)፡ ሕዝቡም የራሳቸዉን “ ክፉ ልብ “ “ በትዕቢት/በግትርነት ተከተሉ “ (ቁጥር 8) ፤ እግዚአብሄር ኤርምያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሕዝቦች መካከል ያለዉን ክፋት ነገረው፣ ለማምለክ ወደ ሌሎች አማልዕክቶች ዞረዉ እንደ ነበርና ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸዉን ኪዳናቸዉን ሰብረዉ እንደ ነበር ነገረው (ቁጥር 9-10) ፡፡
ኤርምያስ (11፡ 11-14)፡ እግዚአብሄር በእነዚህ በአመፀኞች እና በማይታዘዙ ሕዝቦች ላይ ወደ እግዚአብሄር በሚጮኹት ነገር ግን በማይሰማቸዉ ላይ ጥፋትን እንደሚያመጣ ይናገራል (ቁጥር 11) ፤ በመቀጠልም ያመልኩት ወደ ነበረው የኃሸት አማልዕክቶች ይመለሳሉ ነገር ግን ምንም እርዳታን አይቀበሉም (ቁጥር 12) ፡፡ የሚያመልኩአቸዉ አማልዕክቶች እንደ ይሁዳ ከተሞች እና እንደ ኢየሩሳሌም መንገዶች ቁጥራቸዉ ብዙ ነበሩ (ቁጥር 13) ፡፡ ማክአርቱር “ ይሁዳ በሁሉም ከተሞች የኃሰት አማልዕክቶች በነበሩ እና በመንገዶቿ ላይ በተበከሉ መሰዊያዎች በአመንዝራዎች የተሞላች እንደ ነበረች “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስን እነዚህ ነገሮች ሁሉም በሚሆኑ ጊዜ ለእነርሱ በመፀለይ ወይም የእነርሱን መዝገብ ወደ እግዚአብሄር በመግለጥ ጊዜዉን እንዳያባክን ነገረዉ ምክንያቱም ስለማይሰማቸው (ቁጥር 14) ፡፡
ኤርምያስ (11፡ 15-17)፡ እግዚአብሄር ሕዝቦቹ፣ የሚወዳቸው ከእርሱ እዴት አድርገዉ ዞርዉ እንደ ነበር እና እንዴት ፍርዱንም እንደሚደርስባቸዉም ይገልፃል (ቁጥር 16-17, ኤር 2፡ 21) ፡፡
ኤርምያስ (11፡ 18-23)፡ ኤርምያስ የእግዚአብሄርን መልዕክት ስለማድረሱ የተጠላ ነበር እግዚአብሄርም በእርሱ ላይ ስላለዉ ሴራ አስጠነቀቀው (ቁጥር 18-20) ፡፡ የዓናቶት ሰዎች ኤርምያስን በከተሞቻቸዉ በአምላክ ስም ትንቢት እንዳይናገር ያ ከሆነ ደግሞ እንደሚገድሉት አስጠነቀቁት (ቁጥር 21) ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር እንደሚቀጣቸዉ እና በህይወት የሚተርፍ እንደማይቀር ይናገራል (ቁጥር 22-23) ፡፡
መደምደሚያ
እዉነታው በእምነት በመመላለስ የእግዚአብሄርን መልዕክት እያወጅን ካልሆነ ክርስቶስ ተንቆ እና ተገፍቶ እንደ ነበረው እንናቃለን ተቀባይነትም እናጣለን ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 364; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 897.
Nelson’s Commentary, p. 897.
Nelson’s Commentary, p. 897..
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 854.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Jeremiah (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2002), p. 93.
MacArthur, p. 854.
ጥያቄዎች
-
በግል አስተያየታችሁ ኤር (9፡ 1) ስለ ሕዝቡ ኤርምያስ ምን እየተሰማዉ እንደ ነበር ይነግራችኋል ? በኃዘን እና በርህራሄ ስለ ሰዎች ድካም ተሰምቷችሁ ያውቃል ?
-
ኤር (9፡ 2-6) ስታነቡ ሕዝቡ በምን አይነት ኃጢዓት ተይዘዉ ነበር ? በእነዚህ ኃጢዓቶች ምክንያት እግዚአብሄር ምን አደርጋለሁ አለ (ኤር 9፡ 7-11, 15-16) ? በተለዬ ለምን ቀጣቸው ? (ኤር 9፡ 13-14)
-
በኤር (9፡ 23) ሕዝቡ ለማድነቅ ማዘንበል ያለባቸዉን ሰዎስት ምን ነገሮችን አላቸው ? ለሕዝቡ የእግዚአብሄር ፍላጎት ምን ነበር (ኤር 9፡ 24) ? ሰዎች ስለ እናንተ ምን እንዲያደንቁ ትፈልጋላችሁ ?
-
ኤርምያስ 10 ሕዝቡ ከእግዚአብሄር ይልቅ እምነታቸዉን በሌሎች ነገሮች ላይ እንዳደረጉ ያወራል ፤ ከእነዚህ ነገሮች ዉስጥ ጥቂቶቹ ምን ነበሩ (ኤር 10፡ 2-5, 8-9) ? አንዳንድ ጊዜ ራሳችሁን ከእግዚአብሄር ይልቅ በምን ነገር ላይ እምነታችሁን አስቀምጣችሁ ታገኙታላችሁ ? በህይወታችሁ ዉስጥ ማንኛዉንም “ ጣዖት “ ማጥፋት ያስፈልጋችኋል ?
-
በኤር (10፡ 12-13) ላይ አሰላስሉ ፤ በመፅኀፍ ላይ በዚህ መንገድ ሌላ የት ስፍራ የእግዚአብሄርን ታላቅ ኃይል በፍጥረት ላይ ያወራል ? (ኢዮ 9፡ 8, 38፡ 4-7, መዝ 29፡ 3-9, ኤር 51፡ 15)
-
ኤር (11፡ 19) አንብቡ ፤ የኤርምያስ ህይወት ለሕዝቡ ከሚያደርሰዉ መልዕክት የተነሳ ዛቻ የበዛበት ነበር ፤ ይህ ጥቅስ እንዴት ወደ መሲሁ ያመለክታል (ኢሳ 53፡ 7) ? ሕይወታችሁን አደጋ ዉስጥ እንደሚያስቀምጥ የምታዉቁትን ኃይለኛ ቃል ከእግዚአብሄር ለመቀበል ፍቃደኞች ትሆናላችሁ ?
-
በኤርምያስ (9-11) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 9:23–24
“This is what the LORD says: The wise man must not boast in his wisdom; the strong man must not boast in his strength; the wealthy man must not boast in his wealth. But the one who boasts should boast in this, that he understands and knows Me—that I am Yahweh, showing faithful love, justice, and righteousness on the earth, for I delight in these things. This is the LORD’s declaration.”
እግዚአብሔር ህዝቡን ወደ ፍቅሩ ለመሳብና በእርሱ መንገድ በመታዘዝ እንድሄዱ ለማድረግ ፣ የኤርምያስን ድምጽ እንደ መሳሪያ ተጠቀመ ፡፡ ኤርምያስም በእግዚአብሔር ብቻ እንድመኩ ነገራቸው ፡፡ እርሱም ጥበበኞች በጥበባቸው ፤ ኃይለኞችም በኃይላቸው እንዲሁም ባለጠጎችም በብልጥግናቸው እንዳይመኩ ይልቁንም በእግዚአብሔር ይመኩ ዘንድ ነገራቸው ፡፡ በእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር ፣ በእርሱ ማስተዋል ፣ ፍትሕና ጽድቅ ተመኩ ፡፡ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጥሯል ፡፡ እንደ ያህዌ ያለ ማንም የለም ፡፡
በጥበብ ፣ በኃይልና በባለጠግነት እያደጋችሁ ስትሄዱ ፣ በማን ነው የምትመኩት ? እግዚአብሔር በህይወታችሁ ስለሰራው ስራ ምስጋናና ክብር ትሰጡታላችሁን ? እርሱ ዓለታችሁና ኃይላችሁ እንደሆነ አስታውሱ ፡፡ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ፣ ምንም ማድረግ አትችሉም ፡፡ እርሱ ፈጣሪያችሁ ነው ፡፡ እርሱ ለእናንተ ዕቅድ አሳብ አለው ፡፡ እርሱ በነገሮች ሁሉ ውስጥ ደግሞም በነገሮች ሁሉ ላይ አለ ፡፡ እርሱ የእምነታችሁ ባለቤት ነው ፡፡ እርሱ ብቻ ምስጋናችሁ ይገባዋል ፡፡ በራሳችሁ አትመኩ ይልቁንም በእግዚአብሔር ተመኩ ፡፡ ልክ እናንተ በእግዚአብሔር ስትመኩ ፣ ሌሎች የእርሱን ታላቅ ፍቅር ይመሰክራሉ ፡፡ ዛሬ በህይወታችሁ ስለሆነው በምስጋና አስቡ እንዲሁም እርሱ በህይወታችሁ ስላደረጋቸው ታላላቅ ነገሮች ምስጋናና ክብርን ስጡት ፡፡
“ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ ፤ ነገር ግን የሚመካው ፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና ፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “
- ኤርምያስ 9፡23-24
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 20:7 — “ እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን ። “
ኤርምያስ 10:6–7 — “ አቤቱ ፥ እንደ አንተ ያለ የለም ፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው ። የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ ፥ በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው ? “
1ኛ ቆሮንቶስ 1:30–31 — “ ነገር ግን ፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።