Major Prophets Jeremiah

Jeremiah Continued To Call Out God's Judgment

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 6-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 604 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ምዕራፍ (6-8) ይሁዳ በአሶር ምርኮ እየተወሰደ በነበረበት ጊዜ ተከናወነ ፡፡ ኤርምያስ በእነዚህ ምዕራፎች ዉስጥ በንጉስ ኢዮስያስ እና ኢየአቄም ዘመን የይሁዳን መንግስት እየደረሰ ነበር ፡፡ የኤርምያስ ትንቢት ማንም ሕዝብ የእግዚአብሄርን ሕግ በመጣስ እና በመናቅ እንደማይችሉና መከራን እንደማይችሉ ያስተምራል ፡፡

ኮንስታብል “ በብሉይ ኪዳን በግል በይበልጥ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚመስል ከኤርምያስ የሚበልጥ ሌላ ነቢይ የለም ፤ አይሁዳች ስልጣኑን በመግፋት ፀጋዉን ችላ ባሉት/ባልተቀበሉት ጊዜ በታማኝነት የእስራኤልን እዉነተኛ ንጉስ ያህዌን ወክሏል ፡፡ ሰዎች በሰማይ ሉዓላዊ እንዳልነበር እየሰሩ በነበሩ ጊዜ በምድር ላይ የእግዚአብሄር ተወካይ ነበር ፤ እግዚአብሄር ከመወለዱ በፊት ስለሚያዉቀዉ እና ስለመረጠው ቃሉን በመስጠትም እንዳዘጋጀው “ ይናገራል ፡፡ ክርስቶስ እና ኤርምያስ ሁለቱም ለእስራኤል እና ለአለም መልዕክት ነበራቸው፣ ትምህርታቸዉን ለማሳየት ሁለቱም ተፈጥሮን ተጠቀሙ፣ ሁለቱም ከከፍተኛ ልምድ/ወግ መጡ፣ ሁለቱም ከእግዚአብሄር ለሆነዉ ጥሪ ጠንቃቆች ነበሩ፣ ሁለቱም በቤተ መቅደስ የነበረን ንግድ ከስሰዋል/ኮንነዋል፣ ሁለቱም በፖለቲካ ከሀዲነት ተከስሰዋል፣ ሁለቱም መከራዎችን እና እስራቶች ደርሰዉባቸዋል፣ ሁለቱም የቤተ መቅደሱን መፈራረስ ቀድመዉ ተናግረዋል፣ ሁለቱም ለኢየሩሳሌም አልቅሰዋል፣ ሁለቱም የወቅቱን ካህናቶች ነቀፉ፣ ሁለቱም በቤተሰባቸዉ አባላት ተገፍተዋል፣ ሁለቱም እንደ መከራ አገልጋዮች የተገለፁ ነበሩ፣ ሁለቱም እስራኤልን ይወዳሉ፣ ሁለቱም ብቸኛ ነበሩ እንዲሁም ሁለቱም ከእግዚአብሄር ጋር በጣም በቀረበ ህብረት ተደሰቱ ፡፡

እንደ ኮንስታብል ገለፃ “ የኤርምያስ የትዉልድ ከተማ በቢንያም ግዛት ዉስጥ ከኢየሩሳሌም ሰሜን ምስራቅ ሰዎስት ማይል የምትርቀዉ ዓናቶት ነበረች ፤ የኤርምያስ አባት የኤሊ ዘር የነበረዉ የአቢያተር ዘር ኬልቅያስ ነበር (1ሳሙ 14፡ 3) ፤ ስለሆነም ኤርምያስ በእስራኤል በመሳፍንት ዘመን ታሪክ ጊዜ የታቦቱ ማደሪያ ተቀምጦበት ከነበረዉ ስፍራ ከሴሎ የዘር ግንድ ትስስር ነበረው ፡፡ ኤርምያስ በቤተ መቅደስ ስብከቱ ላይ ሴሎን ጠቅሷል (ኤር 7፡ 12, 14, 26፡ 6) ፤ አብያታር ከኢየሩሳሌም ሰሜን ምስራቅ ጥቂት ማይል ብቻ በምትርቀዉ በኖብ ከንጉስ ሳዖል የካህናት ግድያ የተረፈ ብቸኛ ነበር (1ሳሙ 22፡ 20) “ ፡፡ የኤርምያስ ህይወት እና ቤተሰብ ታሪክ በዚህ በትንቢቱ ዉስጥ ስናጠና አስፈላጊ ይሆናል ፡፡

ትምህርት

ምዕራፍ 6 ከኤርምያስ ብዙ ስብከቶች ዉስጥ የአንዱን መደምደሚያ ይሰጣል ፡፡ ይህ ትምህርት/ስብከት በሚመጣው የባቢሎን ሰራዊት ወረራ ላይ እና ሰራዊቱ በይሁዳ ላይ ስለሚያመጣዉ ጥፋት ላይ አተኩሯል ፡፡ አይሁዶች የወታደራዊ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ሰዎስት የመጀመሪያ መንገዶችን ይጠቀማሉ፡ በቅጥሩ ላይ ባሉ ዘበኞች፣ በመለከት እና በእሳት ምልክት ፡፡ ኤርምያስ ስለ ጥቂት ወታደራዊ ድርጊት እንደ ምልክት እነዚህን ሰዎስቱንም ዘዴዎች ጠቅሷቸዋል ፡፡

ኤርምያስ (6፡ 1-5)፡ ኤርምያስ ለይሁዳ ማስጠንቀቂያዉን በቢንያም ለትዉልድ ከተማው የሆነ ነገር በመናገር ጀመረ ፡፡ ወዳጆቹንም ከኢየሩሳሌም እንዲወጡ አስጠነቀቃቸው ፡፡ ኤርምያስ ኢየሩሳሌምን መበለት ከምትሆን አንድ ቆንጆ ሴት ጋር አወዳደራት ፤ እግዚአብሄር ባቢሎናዊያንን እስትራቴጁን ነገራቸው ፡፡ ቁጥር (6-15) በኢየሩሳሌም ላይ ያለዉን ጥቃት እንዴት እግዚአብሄር እንዳመጣው መግለጫን ይሰጣሉ ፤ እግዚአብሄር ባቢሎናዊያን ምን እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆነ የነገራቸው ምን እያደረገ እንደ ነበረም ነገራቸው ፡፡ ባቢሎናዊያንን በኢየሩሳሌም ላይ እንዴት በምሉዑነት እንደሚመራቸዉ የእግዚአብሄር እቅድ ትክክልኝነትን ፈለገ ፡፡ እስራኤልና መሪዎቿ በኃጢዓታቸዉ ጥልቅ እና በኃይለኛው ከእግዚአብሄር የተመለሱ ስለ ነበሩ እፍረት እና ፀፀት አልነበራቸዉም ፡፡

ኤርምያስ (6፡ 16-23)፡ እግዚአብሄር ፍርዱን አደረሰ ፤ ሕዝቡ ጥፋተኛ ስለነበር ቅጣት የተገባዉ ነበር ፡፡ በጥፋታቸዉ ዉስጥ እያሉም እንኳን ሕዝቡ በግብዝነት ኑሮ እየኖሩ እግዚአብሄርን ማምለካቸዉን ቀጠሉ ፡፡ በአሞፅ 5 እግዚአብሄር መስዋዕታቸዉን እንደማይቀበላቸዉ ይናገራል፡ የእህል ቁርባናቸዉን፣ የሚቃጠል መስዋዕታቸዉን እና የደህንነት መስዋዕታቸዉን እንደማይቀበል ፡፡ የአምልኮ ልብ በክርስቶስ በኩል በሙሉነት መምጣት እንደ ነበረበት ያመለክታል ፡፡

ኤርምያስ (6፡ 24-26)፡ እነዚህ ጥቅሶች ዉጤቱን ይገልፃሉ ፡፡ ዋይርስቤ “ ነቢዩ ዜናዉን እንደሰሙ የህዝቡን ምላሽ ገልፆአል - ምንም ሳይሆን በጠንካራ ምጥ ላይ እንዳለች አንድ ሴት ጭንቀት፣ ፍርኃት እና ድካም ነው (ኤር 6፡ 24-26) ፡፡ አንዳንድ ጊዜ መከራ በሰዎች ላይ ጥራትን ያመጣል ነገር ግን ያ በኢየሩሳሌም ከበባ ዉስጥ አይሆንም ፡፡ እግዚአብሄር በእቶን ላይ በተመለሰ ጊዜ ሕዝቡን እንደ ብር እንደተጣለ ይገልጣል ነገር ግን ቆሻሻ የተወረወረ ይሆናል፡፡ እያፀዳቸዉ ነበር፣ እየቀጣቸዉ ነበር ፤ ፅዱ የሆኑ አልነበረም፣ የተገፉ ሆነዉ ነበር ፡፡ ለመጠበቅ በጣም የረከሱ እንደ ነበሩ “ ይገልፃል ፡፡

ኤርምያስ (7፡ 1- 8፡ 3)፡ ምዕራፍ 7 አምልኮን እና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱን ይደርሳል ፤ ኤርምያስ ሰዎች ሲያልፉ በሚሰብክበት ስፍራ ወደ አደባባዩ ስፍራ ቆመ ፡፡ ዋይርስቤ “ በኤርምያስ ዘመን ጊዜ በኢየሩሳሌም የሚታተም ጋዜጣ ከነበር ከክርስቶስ ልደት 609 በፊት ተከታታይ እትም፡ ንጉስ ኢዮስያስ በዉጊያ ቆሰለ! ብርቱ ንጉስ ለኢየሩሳሌም መታደስን አመጣ፣ ንጉሱ ሞተ ! በዙፋኑም ላይ ኢዮአክስ አባቱን ተካ፣ ግብፅ ኢዮአክስንወሰደችው፣ ንጉሰ ነገስቱ ሰዎስት ወር ብቻ ገዛ፣ በግብፅ ንጉስ ኢዮአቄም ተብሎ የተጠራው ኤልያቄም አዲሱባለስልጣን ነው “ እንደነዚህ አይነቶች ርዕሶችን እንደያዙ ያመለክታል ፡፡ እነዚህ አርዕስቶች የይሁዳን መፈራረስ የመሩ ምክንያቶችን ይገልፃሉ ፤ ይህ ኃይለኛ ለዉጥ አስፈላጊ የነበረበት ምክንያት ኢዮአስ ሕዝቡን መልሶ ወደ እግዚአብሄር ለመምራት እየሞከረ ስለነበር ነበር ፡፡ ልጆቹ እና እርሱን የሚከተሉት ያን የሚመስል ሀሳብ አልነበራቸዉም ፤ ስለ አይሁዶች ትዕቢት ነበር ፤ የተመረጡ እና በእግዚአብሄር ጥበቃ እንደሚደረግላቸዉ ወደ እነርሱ የሚጎዳ መምጣት እንደማይችል ይሰማቸዉ ነበር ፡፡

ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር ስለነገሮች ፍፁም የተለያዬ እይታዎች ነበሩት ፤ ይሁን እንጂ ኤርምያስን ወደ ቤተ መቅደሱ በመዉጣት ለተሰበሰቡት ግብዝ ሰዎች መልዕክቱን እንዲናገር አዘዘው ፤ በዚህ የድፍረት ስብከት ነቢዩ የሕዝቦችን የሐሰት አምልኮ (ኤር 7፡ 1 -8፡ 3)፣ የሐሰት ነቢያቶቻቸዉን (8፡ 4-22)፣ እያከበሩት ባልነበረዉ ኪዳን የኃሰት መተማመናቸዉን (9፡ 1-26) እና እያመለኳቸዉ የነበሩትን የሐሰት አማልዕክቶች (10፡ 1-25) አጋለጠ ፡፡ በሌላ ቋንቋ ኤርምያስ ኃጢዓት በተሞላበት የቤተ መቅደስ፣ የሕጉን፣ የኪዳኑን እና ራሱን የእግዚአብሄር እይታቸዉን ይናገራል ማለት ነው “ በማለት ያመለክታል ፡፡ ይህ ኤርምያስ ሁሉም ወንዶች ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ ይጠበቅባቸዉ በነበሩት በአመት ሰዎስት ክስተቶች ሰዎስት ክስተቶች በአንዱ መልዕክቱን እያስተላለፈ እንደ ነበር የሚታመን ነው ፡፡

ኤርምያስ እንደ ሰበከው ለተገኙት “ ቢያንስ ከአስዕርቱ ትዕዛዛት አምስቱን በመጣስ ጥፋተኞች እንደ ነበሩ ነገር ግን ሐሰተኛ ነቢያቶች የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም መሆኑ የተባረኩ ሕዝቦች እንደሆኑ ዋስትና እንደሆነ እንዳረጋገጡላቸዉ “ ነገራቸው ፤ ሐሰተኛ ነቢያቶች ሕዝቡ እያደረገ በነበረዉ ነገር እንዲቀጥሉ ሲያዙዓቸዉ እግዚአብሄር ሕዝቡን ወደ ንስኃ ጠራ ፡፡

በቁጥር 16 እግዚአብሄር ኤርምያስን ለሕዝቡ እንዳይፀልይም አዘዘው ፤ በቁጥር 21 እግዚአብሄር ሕዝቡን መስዋዕታቸዉ መልካም/ተቀባይነት እንደሌለዉ ነገራቸው ፡፡

በቁጥር (7፡ 27) እና በሚከተሉት “ እግዚአብሄር ኤርምያስን ንስኃ ስለማይገቡ ስለሞቱት ሕዝቦች እንዲያዝን ነገረው “ ፤ የሕዝቡን አመለካከት እና ድርጊት ለማስተካከል የእግዚአብሄር ሙከራ መልካም አላደረገም/ፍሬ አላፈራም ፡፡ በኤርምያስ በስምንንተኛዉ ምዕራፍ እግዚአብሄር ለሕዝቡ እያዘነ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

የእግዚአብሄርን ቅዱስነት የሚቀንስ ማንኛዉም ስነ መለኮት ሐሰት ነው ፡፡ የክርስቶስ ሙሉነት ወደ ፅድቅ እና ቅዱስነት ይመራናል ፤ በአስቸጋሪ ጊዜም እንኳን ቢሆን ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር ልብ ከህዝቡ ጋር ነው ፡፡

  1. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Jeremiah, p. 34; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf

  2. Constable, p. 2.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 86.

  4. Wiersbe, p. 86.

  5. Wiersbe, p. 87.

  6. Wiersbe, p. 87.

  7. Wiersbe, p. 88.

ጥያቄዎች

  1. በኤር (7፡ 3) እና በቁጥር (5-7) እግዚአብሄር ይሁዳን መንገዷን እንድስታስተካክል ጠራት እንዲትቀይርም ጥቂት ነገሮችን ለእነርሱ ዘረዘረላቸው ፤ በትክክል መንገዳቸዉን አስተካክለዉ ቢሆን ዉጤቱ ምን ይሆናል አለ እግዚአብሄር ? ይህ መርህ ለእኛም ይሰራል ?
  2. በሉቃ (19፡ 46) ኢየሱስ ከኤር (7፡ 11) እና ከኢሳ (56፡ 7) ጠቀሰ ፤ በሉቃስ መግለጫ ላይ ምን እየተከናወነ ነበር ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ወይም በሚንስትሪይ ተመሳሳይ ነገር ይሆናል አዎ ከሆነ መልሳችሁ አንድ ምሳሌ ምንድን ነው ?
  3. በኤር (7፡ 16) እግዚአብሄር ኤርምያስን ለይሁዳ እንዳይፀልይ አዘዘው ፤ ምንን ምክንያት ሰጠው (ኤር 7፡ 17-19) ? እግዚአብሄር በእዉነት ማንን እየጎዱ ነበር አለ ? እንዴት ሆኖ ?
  4. ኤርምያስ በኤር (8፡ 18-22) በግልፅ እግዚአብሄር ይህን ለምን እንዳመጣዉ ቢያዉቅም እንኳን በይሁዳ እና ኢየሩሳሌም ባዶ መሆን ሀዘኑን አፈሰሰ ፤ በእግዚአብሄር ላይ በማመፅ ማስጠንቀቂያን ባለመስማት መከራ በደረሰበት ሰው ጥልቅ ኃዘን ተሰምቷችሁ ያውቃል ?
  5. በኤርምያስ (6-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 6:10

“Who can I speak to and give such a warning that they will listen? Look, their ear is uncircumcised, so they cannot pay attention. See, the word of the LORD has become contemptible to them—they find no pleasure in it.”

ኤርምያስ ወደ ይሁዳ ሰዎች ሄዶ ንስሀ እንድገቡና ወደ እግዚአብሔር እንድመለሱ ተማጸነ ፡፡ ሆኖም ግን የህዝቡ ጆሮ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ትቶ ነበር ፡፡ ትኩረትን መስጠትም አቁመው ነበር ፡፡ የእግዚአብሔርም ድምጽ ደስ አያሰኛቸውም ፡፡ በጣም እርቀውም ሄደው ስለነበር ኃጢአትን ሲሰሩ ሲበድሉ እንኳ አይጸጸቱም ነበር ፡፡

ያለንስሀ ወይም ከእግዚአብሔርና ከቃሉ ጋር ጊዜን ሳታሳልፍ አብዝተህ በኃጢአት ውስጥ ስትኖር የኃጢአተኝነት የጥፋተኝነት ስሜት የማይሰማህ እና “ ከዚህ መንገድ ተመለስ እኔንም ተከተል “ የሚለውን የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማትም የተሳነህ ትሆናለህ ፡፡ ለእግዚአብሔርም ቃል ያለህ ርሀብ ይቀንሳል ፡፡ ስለዚህም ምንም የበደለኛነት የኃጢአተኛነት ስሜት ሳይሰማህ በኃጢአት ላይ ኃጢአትን ትጨምራለህ ፡፡ ዛሬ እንዲህ በማለት ራስህን ጠይቅ ፡- ለብዙ ጊዜ የሰራሁት በደል ሆኖም ግን ኃጢአትን እንደሰራሁ እንደበደልኩ የማይሰማኝ ነገር በህይወቴ ውስጥ አለን ? ምናልባትም ለአንተ ከዚህ በኋላ የኃጢአትህ ብዛት ላይሰማህ ይችላል ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የልጁ መጥፋት ይሰማዋል ፡፡ ለአንተ ያለው ፍቅር ፈጽሞ አያልቅም ፡፡ ራስህን በማዋረድ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትህን ተናዘዝ ፡፡ ከዚያም ፍቅሩንና ይቅርታውን ተቀበል ፡፡ እርሱም በደልህንና ስቃይህን ያስወግድልሃል ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ፈጽሞ አልረፈደም ፡፡ ዛሬ ፣ አሁንም ወደ እግዚአብሔር እንድትመለስ ጥሪን ወደ ምታቀርብልህ ወደ ትንሷ ድምጽ አድምጥ ፡፡

“ ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ ? እነሆ ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት ለመስማትም አይችሉም ፤ እነሆ ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል ፥ ደስም አያሰኛቸውም ። “

  • ኤርምያስ 6፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤርምያስ 6:15 — “ ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን ? ምንም አላፈሩም ፥ እፍረትንም አላወቁም ፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “

ማቴዎስ 13:13–15 — “ ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ ። መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም ፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም ። በዓይናቸው እንዳያዩ ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል ። “

ሐዋርያት ሥራ 28:27 — “ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል በላቸው ሲል መልካም ተናገረ ። “