Unfaithful Israel, Treacherous Judah
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 3-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የብሉይ ኪዳን ነቢያቶች በጊዜአቸዉ ታዋቂዎች አልነበሩም ፤ ያም ለኢሳይያስ እና ለኤርምያስ ለሁለቱም እዉነት ነበር፡፡ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎናዊያን ምርኮ እና ስለ ኤርምያስ ወጥቶ ስለመኖር ትንቢትን ተናግሯል ፡፡ ኤርምያስ ነፃ ለመዉጣት ይፈልግባቸዉ የነበሩ ብዙ መጥፎ መልዕክቶች ነበሩት ፤ ከኤርምያስ ትንቢት ተስፋ የመጣው በምዕራፍ 31 ለሰሜኑ መንግስት ለእስራኤል እና ለደቡቡ መንግስት ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ለሁለቱም ስለ አዲሱ ኪዳን ባወራ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡
ከምዕራፍ 2 መጀመሪያ ምዕራፉ የሚከተለው የማስጠንቀቂያ እና የተስፋ መቁረጥ መልዕክቶች አስቸጋሪ ስለሆኑ በምዕራፍ 31 ላይ በመመልከት በዚያ ተስፋ ላይ መፅናት አስፈላጊ ነበር ፡፡ ኤርምያስ ተከታታይ የሆኑ መልዕክቶች ነበሩት ፤ የመጀመሪያዉ በምዕራፍ (2፡ 1- 3፡ 5) ያለዉን አካትቷል/ይዟል ፡፡
ትምህርት
ኤርምያስ (3፡ 1-5)፡ የመጀመሪያዉ መልዕክት መደምደሚያ በኤር (3፡ 5) ላይ ነበር ፤ ሁለተኛዉ መልዕክት በኤር (3፡ 6) በመጀመር እስከ ኤር (6፡ 30) ይቀጥላል ፡፡
ጄ. ቬሮን ማጊ በኤር (2፡ 7) “ እግዚአብሄር ፍፁም የሚያስደንቅ ነገር እያደረገ እንደሆነ ፤ ከግብፅ እንዲወጡ በጠራቸዉ ጊዜ በምሽት እንዴት በሳት አምድ በቀን ደግሞ እንዴት በደመና አምድ በተመሩ ጊዜ ከእርሱ ጋር በነበራቸዉ ግንኙነት የፀደይ ጊዜአቸዉን እንዲያስታዉሱ እስራኤልን እየጠየቀ ነው ፤ በዚያ ችግር እና ፍራት ዉስጥ እግዚአብሄርን እንደተመለከቱ ፤ አሁን እግዚአብሄር ያን ሁሉ እንዲያስታዉሱ አስታወሳቸው ፤ እግዚአብሄር ከባረካቸዉ እና መልካም ምድርን ከሰጣቸዉ በኋላ ከእርሱ ዞር እንዳሉ “ ያመለክታል ፡፡
ኤር (2፡ 8) ከእግዚአብሄር ዞር ካሉ በኋላ የእስራኤል ካህናቶች “ እግዚአብሄር የት ነው ? “ እያሉ መጠየቃቸዉን በመተው እግዚአብሄር አድርጎት ስለ ነበረዉ ነገር እንኳን ሳይጨነቁ ባዖልን ማምለክ ጀመሩ ፤ በኤር (2፡ 13) የራሳቸዉን አማልዕክት በማስቀመጥ የራሳቸዉን ነገር/መስሪያ ተከተሉ ፡፡ ሕዝቡ እግዚአብሄርን ትቶ ነበር ነገር ግን ለእርሱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማድረግ መሄድ አልቻሉም ፤ ከዚህም የተነሳ በእግዚአብሄር ስፍራ ላይ የሆነ ነገርን ለመተካት ሞከሩ ፡፡
ኤርምያስ ሕዝቡ ለራሱ ሰርቶአቸዉ የነበሩትን የዉኃ ማጠራቀሚያ/የእንስራን መልክ በማስተዋወቅ እንደ ተሰነጠቁ እና በቁ እንዳልሆኑ ገለፃቸው ፡፡ በአንፃሩ ኤርምያስ የመሲሁን መልክ/ስዕል በፍፁም እንደማይደርቅ እንደሚወርድ የህይወት ዉሃ ስሎታል ፡፡
በኤርምያስ ዋናዉ ጭብጡ ምን እያደረጉ እንደ ነበር ሕዝቡን አንድ ጥያቄ መጠየቅ ነበር ፤ የኤርምያስ የማያቋርጥ ልመናው ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነበር ፡፡
በኤር (3፡ 1) ኤርምያስ በእግዚአብሄር እና በጌታ መካከል ያለዉን የግንኙነት ችግር ለመግለፅ የፍቺ ምሳሌን ተጠቅሟል ፤ ማክአርቱር “ አንደ ወንድ ከፈታ እንደዚያ አይነቱ ወንድ ያችን ሴት እንደ ገና እንደሚስቱ አይወስዳትም ከዚህ የተነሳ ስለምትረክስ (ዘዳ 24፡ 4) እና የተናቀ ይሆናል ፤ ኤርምያስ በመንፈሳዊ አለም እስራኤልን በብዙ በአሕዛቦች (2፡ 18, 25) እና ጣዖቶች (2፡ 23-25, 3፡ 2, 6-9) እንደ ጋለሞታ ለመሳል ይህን ማመሳሰል እንደተጠቀመና ፤ ይሁን እንጂ እስራኤል ንስኃ ከገባች እግዚአብሄር በታላቅ ቸርነቱ እስራኤልን /ይሁዳን መልሶ እንደሚስቱ እንደሚቀበላት (3፡ 12-14) “ ይገልፃል ፡፡ በይሁዳ እና በእስራኤል በትንቢት እና በሁኔታዉ ግንኙነት መካከል ወደ ባቢሎን ምርኮ ለምን ይሄዱ እንደ ነበር መግለጫ ነበር ፡፡
ኤርምያስ በመቀጠልም የእስራኤልን የኃጢዓት መጠን እንደማሳያነት “ ባዶ /ወና ኮረብታ “የሚለዉን ሀረግ ተጠቅሟል (ኤር 3፡ 2) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ቃሉ የኤር (2፡ 30) ከፍተኛ ኮረብቶች ከሚለዉ ጋር ትይዩ እንደሆነ ፤ በእነዚህ ባዶ ኮረብታዎች ላይ እስራኤል አካላዊ እና መንፈሳዊ ማመንዘርን ፈፀመች ፤ መጋደም የሚለዉ ቃል ኃይለኛ የወሲብ አስተሳሰብ አለው ፡፡ በጉዞ ደፈጣ የታወቁ እንደ ነበሩት ልክ እንደ አረቦች እስራኤል በአመንዝራነት ሌሎች አማልዕክቶችን እንደተመለከቱ “ ይገልፃል ፡፡ እስራኤል በዚያው በአመንዝራነቷ ዉስጥ እየጠበቀች ነበር ፡፡ የእስራኤል ሕዝቦች በራሳቸዉ እቃዎች/ነገሮች እርካታን/ደስታን ፈለጉ ፤ በእግዚአብሄር የሚገኘዉን የህይወት ዉኃ ለማግኘት አልሞከሩም ነበር ፡፡ ህያዉ ዉኃ የሚለዉ ቃል የሚመጣዉ መሲህ እንደሚጠቅስ ያመለክታል ፡፡
ኤርምያስ እግዚአብሄር እንዴት ሕዝቡን እንደሚቀጣ እንደ ምሳሌ “ ያልመጣን ሻወር ምስል “ ተጠቅሟል ፤ የይሁዳን እና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ እግዚአብሄር ሲመለሱ የሚመጣዉ ርኃብ ፍራት አያገኝም ፡፡ ወደ እግዚአብሄር በንስኃ መመለስ አስፈላጊ ነበርም አለ ፡፡ ሕዝቡ ደህና እንደ ነበሩና አስበዉ ስለ ነበር እግዚአብሄር አላስፈለጋቸዉም ፤ ትዕቢተኞች ነበሩ ፡፡ መልዕክቱ ለእስራኤል እና ለይሁዳ ሕዝቦች ቀላል ነበር፡ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ ምህረትን ጠይቁ እግዚአብሄርም በሰማይ ሆኖ ይሰማችኋል የሚል ነበር ፡፡
የሕዝቡ ሞድ የእግዚአብሄር ይቅርታ ተሰጥቶ እንደ ነበር ማስተዋል ነበር ፡፡ ምንም ቢሆን ይቅርታ እንዳለ በማሰብ ኃጢዓትን ይጨምራሉ ፡፡
ለእስራኤል እና ለይሁዳ ሁለተኛዉ መልዕክት በኤር (3፡ 6- 6፡ 30) የተካተተ ነበር ፤ የመልዕክቱም ማዕከላዉ ጭብጥ እግዚአብሄር ከአንድም ሁለቴ ሕዝቡን ወደ እርሱ እንዲመለሱ ጠይቋቸዉ እና አበረታቷቸው ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ሁሉምእንዳሉትእናእንደፈፀሙትተስፋአለ ፡፡ እንዴት እነዚህ ጥቅሶች በአሁኑ ጊዜ እንተገብራቸዋለን እርሱን በእዉነት እንዳናመልከዉ የሚከለክሉን በኑሮአችን የነበሩ ጣዖቶችን እግዚአብሄር እንዲያሳዬን በምላሻችን እና በፀሎታችን ይታያሉ ፡፡ የክርስቶስ ህይወት እና ዋጋ መክፈል በትህትና በእግዚአብሄር ፊት በመምጣት ምህረትን ከእርሱ እንድነጠይቅ ነፃነትን ይፈቅድልናል እግዚአብሄርም ከእርሱ ጋር ግንኙነታችን ያድሳል ፡፡
McGhee, J. Vernon, Thru the Bible: Proverbs to Malachi, vol. 3 (Nashville Thomas Nelson Publishers 1982), p. 359.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 849.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 882.
ጥያቄዎች
-
በኤርምያስ 3 እግዚአብሄር ከእስራኤል እና ከይሁዳ ጋር ያለዉን ግንኙነት ለመግለፅ ምን ግንኙነት እግዚአብሄር ገለፀ (ኤር 3፡ 1, 8, 14, 22) ? በኤር (3፡ 11) የትኛዉ መንግስት ይበልጥ ፃድቅ እንደ ነበር እግዚአብሄር ተናገረ እስራኤል ወይስ ይሁዳ ? ያንን ልዩነት ለምን አደረገ ?
-
በኤር (3፡ 12) እግዚአብሄር በእስራኤል ለዘላለም በፍፁም አልቆጣም አለ ፤ በኤር (3፡ 13) ከእነርሱ ምን ለመቀበል እየተመለከተ ነበር ?
-
ኤር (4፡ 4) የይሁዳን እና የኢየሩሳሌም ሰዎች በልባቸዉ የተገረዙ እንዲሆኑ ይጠራቸዋል ፤ ዘዳ (30፡ 6, ሮሜ 2፡ 28-29 እና ቆላ (2፡ 11) በመመልከት የልብ መገረዝ ምን ማለት እንደሆነ ግለፁ ፡፡
-
ኤር (4፡ 23) ከዘፍ (1፡ 2) ጋር አወዳድሩ ፤ ተመሳሳይ ነገር መናገራቸዉ ሆን ተብሎ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
-
ኤር (5፡ 10) ኤር (2፡ 21) እንዳደረገው የወይንን ስዕል ይጠቀማል ፤ በዮሐ (15፡ 1-6) የኢየሱስ ቃል ከኤርምያስ ፅሁፍ ጋር እንዴት ይተሳሰራል ?
-
ኢየሱስ በማር (8፡ 18) ላይ ኤር (5፡ 21) ጠቅሶታል ፤ ኢየሱስ እየተናገረ ምን ሁኔታን እየተናገረ ነበር ? ተመዝግቦ የነበረዉ ቀጣዩ ታሪክ ኢየሱስ የአይነስዉሩን አይን መክፈቱ አስፈላጊ እንደ ሆነ ታስባላችሁ ? (ማር 8፡ 22-25)
-
በኤርምያስ (3-5) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Jeremiah 3:12–13
“Go, proclaim these words to the north, and say: Return, unfaithful Israel. This is the LORD’s declaration. I will not look on you with anger, for I am unfailing in My love. This is the LORD’s declaration. I will not be angry forever. Only acknowledge your guilt—you have rebelled against the LORD your God. You have scattered your favors to strangers under every green tree and have not obeyed My voice. This is the LORD’s declaration.”
ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ቃል ለይሁዳ እንድህ በማለት ተናገረ ፡- “ ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ ፥ ተመለሽ ፡፡ “ እግዚአብሔርም እንዲህ በማለት አሳሰባቸው ፡- “ መሐሪ ነኝና ፥ ለዘላለምም አልቈጣምና በእናንተ ላይ ፊቴን አላደርግም ፡፡ “ እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑት ህዝቦች ወደ እርሱ እንድመለሱ ይሻል ፡፡ ምንም እንኳ ህዝቡ ሀሰተኛ አማልክትን ቢያመልኩም ደግሞም እንድሁ ተስፋ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ጣዖታት ቢመልሱም ፣ እግዚአብሔር ግን አይቆጣም ፡፡ እግዚአብሔር በማያቋርጥ ፍቅር ይወዳል ፡፡
ጓደኞቼ እግዚአብሔር መንገዱን እንድትፈልጉ ይሻል ፡፡ ፊታችሁን ወደ ሌሎች አማልክት ካዞራችሁ ፣ ጣዖታት ከሏችሁ ፣ ወይም ደግሞ ገና በልጅነታችሁ ካወቃችሁት እምነት ፈቀቅ ብላችሁ ከሆነ ፣ ወደ እርሱ ለመመለስ ጊዜው አሁን ፡፡ እርሱም መልሶ ይቀበላችኋል ፡፡ ይቅር ይላችኋል ፡፡ በሚታደግ ፣ በማያልቅ እና ፈጽሞ በማያቋርጥ ፍቅር ይወዳችኋል ፡፡ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ ፣ ንስሀ ግቡ ፣ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ ከዚያም የእርሱ ህያው ውሃ በእናንተ ላይ ይፈሳል ፣ ያጥባችኋልም ፡፡ ፍቅሩ ፈጽሞ አያልቅም ፡፡ ዛሬ ህይወትን ከሚያበላሹ ሱሶች ራቁ ፣ ከሀሰት ከማጭበርበር ራቁ ፣ ከአላስፈላጊ ወጭ ራቁ ፣ ከሀሜት ራቁ …… ወደ ኢየሱስ ተመለሱ ፡፡ እርሱ ይወዳችኋል !
“ ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተናገር ፥ እንዲህም በል ። ከዳተናይቱ እስራኤል ሆይ ፥ ተመለሽ ፥ ይላል እግዚአብሔር መሐሪ ነኝና ፥ ለዘላለምም አልቈጣምና በእናንተ ላይ ፊቴን አላደርግም ፥ ይላል እግዚአብሔር ፦በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ብቻ እወቂ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “
- ኤርምያስ 3፡12-13
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 109:26–27 — “ አቤቱ አምላኬ ፥ እርዳኝ ፥ እንደ ምሕረትህም አድነኝ ። አቤቱ ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች ፥ አንተም ይህችን እንዳደረግህ ይወቁ ። “
ኤርምያስ 4:1–2 — “ እስራኤል ሆይ ፥ ብትመለስ ፥ ወደ እኔ ተመለስ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፤ ርኵሰትህንም ከፊቴ ብታስወግድ ፥ ባትናወጥም ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል ፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ በእርሱም ይመካሉ ። “
ሐዋርያት 3:19–20 — “ እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።